• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የመጣላቸውን የመተንፈሻ አጋዥ የሕክምና ቁስ ይቅርብኝ ብለው አሳልፈው ለሌላ ወጣት የሰጡት ጣሊያናዊ ካህን አረፉ…

የ72 ዓመቱ ጣሊያናዊው ካህን ጁሴፔ ቤራርዴሊ በኮሮና ክፉኛ ከተጠቁት የጣሊያን ከተማ አንዷ በሆነችው ካስኒኞ ውስጥ ካህን ነበሩ፡፡በኮሮና ታምመው ሎቭር በተባለ ሆስፒታል ተኝተውም ነበር፡፡ ሕመሙ መተንፈስን አዳጋች ስለሚያደርገው በሕይወት ለመቆየት የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያ ግድ ይላል፡፡

የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያ ከፍተኛ እጥረት አለ፡፡ካህኑ የሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ምዕመን የካህኑን ሕይወት ለማዳን የመተንፈሻ አጋዥ መሳሪያውን ገዝቶ ለአባ ጁሴፔ ቤራርዴሊ ቢሰጣቸውም፣ እሳቸው ግን ለአንድ አይተውትም ለማያውቁት ወጣት ታማሚ አሳልፈው ሰጥተዋል የእሳቸው ሕይወት አልፏል፡፡የካህኑ የደግነት ተግባር የብዙዎችን ጣሊያናውያን ልብ ነክቷል፡፡

ምንጭ - ቢቢሲ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers