ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች
ሐምሌ 28፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን
Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.
- በአዲስ አበባ ለአተት ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም የተባሉ 20 ሕክምና መስጫዎች ታሸጉ፡፡ ማስጠንቀቂያም የተሰጣቸው አሉ፡፡ (መሠረት በዙ)
- የአዲስ አበባን ሁለት ትላልቅ ወንዞች የማፅዳት ሥራ ሊከናወንላቸው ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
- የኢትዮጵያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2008 በጀት ዓመት ከንብረት ጉዳት ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የካሣ ክፍያ አግኝቻለሁ አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
- የአርባ ምንጭ የአዞ ቄራ በመጪው ዓመት የእንስሣቱን ሥጋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይጀምራል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
- የSOS ሳልሕ ዓለም አቀፍ ተቋም የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ በአዲስ አበባ ይከፈታል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
- በአዲስ አበባ የድጋፍ ሰጭ የመጓጓዣ አገልግሎት አቅራቢዎች ሥራው አላዋጣንም ሲሉ ከአስተዳደሩ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር እየተወዛገቡ ነው፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
- የጥራት መሥፈርታቸውን ያላሟሉ የታሸጉ የመጠጥ ውሃ በሚያቀርቡ አምራቾች ላይ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
- የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሊካሄድ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)