• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሐምሌ 15፣ 2011/ ስራ አቁሞ የቆየው የኢትዮጵያ መዓድን ነዳጅና ባዮ ፊዩል ኮርፖሬሽን በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስር ሊጠቃለል ነው ተባለ

ስራ አቁሞ የቆየው የኢትዮጵያ መዓድን ነዳጅና ባዮ ፊዩል ኮርፖሬሽን በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስር ሊጠቃለል ነው ተባለ፡፡ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 15፣ 2011/ በኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ትችት የሚቀርብበት ህገ መንግስት ዛሬም ምሁራኑ ይህ ቢቀነስ ይህ ቢሻሻል ይላሉ

በኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ትችት የሚቀርብበት ህገ መንግስት ዛሬም ምሁራኑ ይህ ቢቀነስ ይህ ቢሻሻል ይላሉ፡፡ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 15፣ 2011/ በቂ ቅድመ ስልጠና ከተሰጠ በህክምና ትምህርት ተመርቆ ስራ ማጣት እንደማያሳስብ ተነግሯል

በቂ ቅድመ ስልጠና ከተሰጠ በህክምና ትምህርት ተመርቆ ስራ ማጣት እንደማያሳስብ ተነግሯል፡፡ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 15፣ 2011/ የኢትዮጵያ የሥራ ፈጠራ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ የሚወጣውን ወጣት ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት ተነገረ

የኢትዮጵያ የሥራ ፈጠራ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ የሚወጣውን ወጣት ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት ተነገረ፡፡ ዛይራይድ የተባለ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የቴክኖሎጂ ትምህርት በተማሩ እና በተመረቁ ተማሪዎች በዘርፉ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘሁ ነው ብሏል፡፡አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 12፣ 2011/ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃኑ እና የሐገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ

በዘንድሮው አመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ስለተመረቁ ወደ ስራ ለመግባትና ሃገራቸውን ለመረከብ የተዘጋጁ ሆነዋል፡፡ግን እነርሱ ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው የምትቀበላቸው ሃገራቸው በርስ በርስ መጠቃቃት፣ በመፈናቀል በፖለቲካ ሽኩቻ ክፉኛ የተደቆሰች ሆናለች፡፡እነዚህ ምሩቃን ወደ ሰላማዊ ስራ ለመግባት የተደላደለ ሁኔታ የሚያገኙ አይመስልም፡፡ ትምህርታቸውስ ችግሮቹን ለማለፍ ምን ያህል ይረዳቸዋል ? የሚረዳቸው ካልሆነስ ተስፋ ወደ መቆረጥ የሚያደርስ ግርታ አይፈጥርባቸውም ወይ? ቴዎድሮስ ብርሃኑ ባለሙያ ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 12፣ 2011/ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ፈራሚ እንደመሆናችን ምን ዝግጅት ተደርጓል?

የአፍሪካ ነፃ ቀጠና ስምምነት ሰነድ ኢትዮጵያ ቀዳሚ ፈራሚ ሆናለች፡፡ የአፍሪካ ነፃ ቀጠና ስምምነት በተፈራሚ ሃገሮች መካከል ምርቶቻቸውን በማስገባትና ንግዳቸውን በማስፋፋት በኩል ጠቃሚ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡እንዲህ ዓይነቱ የገበያ ልውውጥ ጥቅም አለው ቢባልም በሌላ በኩል የሌሎች አፍሪካ ሃገሮች ምርት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በዋጋ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ቅናሽ ስለሚኖር ለሃገር ውስጥ ነጋዴዎች ጉዳት ይሆንባቸዋል፡፡ ታዲያ ምን ለማድረግ ታስቧል? ንጋቱ ረጋሣ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አነጋግሯል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 15፣ 2011/ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባልተፈቀደላቸው መስክ ተማሪዎችን እንዳይመዘግቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባልተፈቀደላቸው መስክ ተማሪዎችን እንዳይመዘግቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 15፣ 2011/ የተያዘው ክረምት ለመኸር እርሻ የተመቸ ሆኗል ተባለ

ሸገር ከግብርና ሚኒስቴር እንደሰማው አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ የተቆራረጠ ባለመሆኑ የመኸር እርሻ ተጠቃሚ በሆኑት በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ለግብርናው አመቺ ሆኗል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለሸገር ሲናገሩ በጥሩ ሁኔታ እየጣለ ያለውን ዝናብ በመጠቀም ዘንድሮ ከኢትዮጵያ እርሻዎች የሚጠበቀውን 406 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማግኘት መንግስት ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እና 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርጥ ዘር ገዝቶ ለአርሶ አደሩ አቅርቧል ብለዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶች እና መፈናቅሎች ግብርናውን ጎድተውት ነበር ያሉት አቶ አለማየሁ በአሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ምርጥ ዘር ሳይሰበሰብ ቀርቶ ከውጭ አገር 6 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ገዝተን ለማስገባትም ተገደናል ብለዋል፡፡አሁን ያለውን ሁኔታ ለግብርው አመቺ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ ለአርሶ አደሮችና ለልማት ጣቢያ ሰራተኞች የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠን ነው ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 15፣ 2011/ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው፣ ተሾሙ

የአቶ ተመስገን ጥሩነህን የርዕሰ መስተዳድርነት ሹመት ያፀደቀው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት በ5ኛ ዙር በ4ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤው ነው፡፡ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ክልሉን በሚመራው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ሰኔ 15/2011 በግፍ በተገደሉት ዶ/ር አምባቸው መኮንን ምትክ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆኑ በዕጩነት አቅርቧቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡አቶ ተመስገን፣ ከተሾሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር ክልሉ አሁን የተጋረጡበትን ወቅታዊ ችግሮች፣ በብቃት ለመወጣት ቁርጠኛ አቋም ያላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ችግሮቹን በዘላቂነት ለማስወገድ የፀጥታ ሀይሉን አቅም የማሳደግና የመገንባት ስራ እንደሚሰራ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚሰራን የፖለቲካ ሴራ ለማስወገድ፣ ከሕዝቡ ጋር በቅንጅት ለመስራት ማሰባቸውን አረጋግጠዋል፡፡የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ለግጭት ምክንያት ሳይሆኑ በሕግ እንዲመለሱ ለማድረግ እንደሚሰሩ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ “የህግ የበላይነት ማስፈን ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም” ብለዋል፡፡ርዕሰ መስተዳድር፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ወደ ፌደራል መንግስት የስራ ምድብ ቀደም ሲል ከመዛወራቸው በፊት በአማራ ክልል የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪና የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሰርተዋል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 12፣ 2011/ በፖለቲካ ታማኝነት ተይዘው ውዥንብር የሚነዙ የመገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ

አሁን በኢትዮጵያ የሚታዩት የመገናኛ ብዙሃን በአብዛኛው አድሏዊ እየሆኑ ነው እየተባለ ነው፡፡ ትክክለኛውን መረጃ ከማሰራጨት ይልቅ ባሉበት አካባቢ ፖለቲካ እየተደፈቁ በመሆኑ ውዥንብር እየፈጠሩ ነው እየተባሉ ይተቻሉ፡፡መገናኛ ብዙሃን ሙያቸውን መሰረት አድርገው ካልሰሩ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ስለሚታመን በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ታዲያ የመቆጣጠር ስልጣኑ የተሰጠው የብሮድካስት ባለስልጣን እንደነዚህ ዓይነቶችን መገናኛ ብዙሃን እንዴት እየተቆጣጠራቸው ነው? ሊቆጣጠራቸው በሚችልበት አቅም ላይ ነው ወይ? የተህቦ ንጉሴ ዝግጅት ይኽን ይመለከታል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 12፣ 2011/ ምሁራን የትምህርታቸውን ልክ፣ በየክልሎቻቸው ሲወስኑት መታየታቸው ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ምን መልዕክት ያስተላልፋል?

የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎቻችን፣ የአካባቢ ፖለቲካ የሚነዳቸው እየሆኑ ነው የሚል ስጋት ተፈጥሯል፡፡ አሁን በሃገራችን፣ በክልል መንግስታትና በፓርቲች መካከል የሚታዩ አንጃ ግራንጃዎች፣ የዩኒቨርስቲ መምህራን የሚደግፏቸው ወይም የሚተችዋቸው ዩንቨርስቲው ያለበትን የክልል መንግስታት አቋም መሆኑ ይታያል፡፡ ሰሞኑን በትግራይና በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መምህራን የሚሰጡት ቃለ መጠይቅ ይኽንኑ ያረጋግጣል፡፡ ምሁራን የትምህርታቸውን ልክ፣ በየክልሎቻቸው ሲወስኑት መታየታቸው፣ ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ምን መልዕክት ያስተላልፋል? ተፅዕኖስ አያሳድርም ወይ? የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው፡፡ በየነ ወልዴ በዚህ ጉዳይ የሚከተለውን አዘጋጅቷል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers