• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የእሥራኤል ፖሊስ የህዝብ እንቅስቃሴ አስተጓጉለዋል ያላቸውን ለተቃውሞ የወጡ 12 ኢትዮጵያዊያን ቤተ-እሥራኤላውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተሠማ

ቤተ-እሥራኤላውያኑ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በኢትዮጵያዊያን አይሁዶች ላይ ያነጣጠረና አመታት የዘለቀ በደል እየደረሰብን ነው በማለት ለተቃውሞ ወደ ጐዳና በመውጣታቸው ነው፡፡ ፖሊስ የትራፊክ እንቅስቃሴን በማወክ ህዝብን ለደህንነት ስጋት ዳርጋችኋል በሚል በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል፡፡ ቤተ-እሥራኤላዊው ዮሴፍ ሳልማ የተባለው ወጣት ራሱን አጥፍቶ ተገኝቷል ቢባልም ኢትዮጵያዊያኑ ግን በፖሊስ በደረሰበት ጥቃት ተገድሏል በማለት ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡

ቤተ-እሥራኤላውያኑ ለአገሬው ሰዎች የሚሰጠው የጤና ሽፋን ፣ የትምህርት እድል እንደማያገኙና በሃይማኖታቸውም መገለል እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል፡፡ የእሥራኤል የፖሊስ ኃላፊዎች ቤተ-እሥራኤላውያኑ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና ኃሳባቸውን የመግለፅ መብት እንዳላቸው ተናግረው በቁጥጥር ስር የዋሉት መንገዶችን በመዝጋትና ህዝብን ለስጋት በመዳረጋቸው ነው ማለታቸውን ጄሩሳሌም ፖስት አውርቷል፡፡
 
ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 27፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ውሻዎች ሊመዘገቡና መለያ ሊሰጣቸው ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ለዘመናት በሚኒሊክ ሆስፒታል ብቻ ይሰጥ የነበረው የአስክሬን ምርመራ በተደራጀ መሳሪያ እና ባለሙያ በመቐሌ አይደር ሆስፒታል እየተሰራ ነው፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ከትናንት በስቲያ ከመቐሌ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ከ2 ሰዓት በላይ መዘግየቱ ደንበኞችን አማረረ፡፡ የአየር መንገዱ የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተመካክረን ምላሽ እንሰጥበታለን ብለዋል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በዚህ ዓመት ብቻ በተለያየ ምክንያት የተዘጉ የአንድ መቶ አሥራ ሦስት ያህል በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ንብረት ለተመሣሣይ ድርጅቶች ማስተላለፉን የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሐኪምዎ መልዕክት ዶ/ር ሰለሞን ተፈራ፣የምርምር ወረቀቶች የቢራ ፋብሪካዎችን አዲሶቹ ቀኝ ገዢዎች እያሏቸው ነው

“የምርምር ወረቀቶች የቢራ ፋብሪካዎችን አዲሶቹ ቀኝ ገዢዎች እያሏቸው ነው፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ ስላላቸው መንግሥታትን በተፅእኗቸው ስር ማድረግ ይችላሉ፡፡ ብልጦች ናቸው፡፡ ከገበሬው ገብስ ገዝተን ኑሮውን አሻሻልንለት ይሉሃል … ግን ለመሆኑ ገበሬው ከእነሱ በፊት ገብሱን አምርቶ መሬት ላይ ያፈስሰው ነበር ? ገበሬው ገብሱን የሸጠበትን ገንዘብ ድራፍት ስለሚጠጣበት ገንዘቡን መልሰው ይቀበሉታል…” ዶ/ር ሰለሞን ተፈራ፣ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በሥነ አእምሮ ሕክምና ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር…

በሸገር “የሐኪምዎ መልዕክት” መሰናዶ ላይ በተከታታይ ስለሱስና ሱሰኝነት የነገሩን ዶ/ር ሰለሞን ተፈራ በዛሬው ማለዳ ደግሞ ስለቢራ ፋብሪካዎች የተሰማቸውን አካፍለውናል፡፡ “በማስታወቂያቸው የሀገራችንን ማንነት ቀምተውናል፣ እንደፈለጋቸው እንዲሆኑ ተለቅቀዋል” የሚሉት ዶ/ር ሰለሞን፣ “ወሳኔ ቦታ ላይ የተቀመጡ ኃላፊነት ተሰምቷቸው አደብ ሊያስይዟቸው ይገባል” ብለዋል፡፡

ሱስ አስያዥና ለጤና ጎጂ የሆኑትን ቢራና ትምባሆ የሚሸጡ ፋብሪካዎች ለትርፍ የሚሰሩ ስለሆኑ ምርታቸውን በስፋት መሸጥና ማትረፍ ነው አላማቸው እነሱ ካተረፉ እኛ ምኑን ተረፍን የሚል መልዕክታቸውን አካፍለውናል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ስንክሳር፣በኢትዮጵያ ስላለው መልከ ብዙ የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ሰኔ 26፣2008

ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ህፃናት ወንዶችና ሴቶችመነሻ፤ በተወሰነም ደረጃም መዳረሻ ሀገር ናት፡፡ ከሀገሪቱ የገጠር አካባቢዎች የሚወጡ ህፃናት በቤት ሠራተኝነት እና አልፎ አልፎም በሴተኛ አዳሪነት ተገደው ይበዘበዛሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት እንደሚያመለክተው ዕድሜቸው እስከ ስምንት ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ ቤቶች በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰማሩ ተደርጓል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 23፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • 2 የፖሊስ አባላት በሞቱበት የትላንትናው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውና ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ቁጥር በውል አይታወቅም ሲል ፖሊስ ተናግሯል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ኢትፍሩት ሽንኩርት፣ ቲማቲምና የተለያዩ አትክልቶችን ማግኘት አልቻልኩም አለ፡፡ (መሰረት በዙ)
 • ሰሞኑን የተመረቀው የደምቢ ዶሎ ዓየር ማረፊያ በቅርቡ ማስተካከያ ይደረግለታል ተባለ፡፡ (ተሕቦ ንጉሴ)
 • ብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ለሕይወት አድን ስራዬ ደም ተቸግሬያለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢጋድ ኢትዮጵያ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል መሆንዋ የምሥራቅ አፍሪካም ስኬት ነው አለ

ድርጅቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ እንደተናገረው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬት ያበረከተችው አስተዋፅኦ አባልነቷ የሚገባ ነው ብሏል፡፡ የኢጋድ ፀሐፊ ማሀቡብ ማሊም እንዳሉት ኢጋድ የኢትዮጵያን አባል ሆና መመረጥ ከመደገፉ በላይ እንደ ስኬት ይቆጥረዋል ብለዋል፡፡ ፀሐፊው ጨምረውም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥትን በኢጋድ ስም እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡ የሞዛምቢኩ ፕሬዝዳንትም ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አልባ በመሆንዋ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን በተለዋጭ አባልነት ለመምረጥ 127 ድምፅ ያስፈልግ የነበረ ቢሆንም ከ190 ድምፅ ሰጪዎች 185 ድምፅ አግኝታለች፡፡ የአፍሪካ ሀገሮች በሙሉ ለኢትዮጵያ ድምፅ መስጠታቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ከአፍሪካ ግብፅና ሴኔጋል አባል መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ፋሲል ረዲ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዓለም ባንክ በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያን መርጃ የሚሆን ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ሰጠ

በ50 አመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ኢትዮጵያን አግኝቷታል ያለው ባንኩ በዚህን ሳቢያ 18 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል፡፡ የዛሬው የብድር ስምምነት በተለይም በሴፍትኔት ለታቀፉትና በድርቁ ሳቢያ ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል፡፡

በሴፍትኔት ፕሮግራሙ በቀጥታ የምግብና የገንዘብ ድጋፍ ለ8 ሚሊየን ሰዎች እስካሁን እየተደረገላቸው እንደሆነም ሰምተናል፡፡ የዛሬው የብድር ስምምነትም የሴፍትኔት ፕሮግራሙ ተጨማሪ ጊዜ ማራዘሚያ ሲሆን በተለይም በከፋ ችግር ውስጥ ናቸው የተባሉ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ገደማ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአርሲ ቀጣሪዎቼ የሆኑት ባልና ሚስት የወር ደሞዜን በአግባቡ አልከፈሉኝም ያለ አንድ አርሶ አደር ለሊት በተኙበት በገጀራ ገደላቸው ተባለ

የዞኑ ፖሊስ የመረጃ ባለሞያ ዋና ኢንስፔክተር ጐሳ አማን ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ባልና ሚስቱ በግብርና ሥራ የቀጠሩት አርሶ አደር በወር ሊከፍሉኝ የተነጋገርንበትን ገንዘብ ሳያሟሉ እየቆራረጡ ይሰጡኛል በማለት ቅሬታ ውስጥ በመግባት ወደ ባልና ሚስቱ ሽማግሌዎች ይዞ በሄደ ጊዜ ሚስቲቱ ገንዘቡ በአግባቡ ተከፍሎታል ቅሬታው ባለቤቴ ወጣ ባለ ጊዜ በሌላ ፆታዊ ፍላጐት እያስቸገረኝ አለመስማማቴ ነው ብላ ለሽማግሌዎቹ በመናገሯ ብስጭት ውስጥ ገባሁ አለ የተባለው አርሶ አደር ግንባት 14/2008 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን ገጀራ በመጠቀም ባልና ሚስቱ በተኙበት ጭንቅላታቸውንና አንገታቸውን በመምታት ገድሏቸዋል ብለዋል፡፡

ወንጀሉ ሲፈፀም ጩኸት የሰሙ ጐረቤቶች ነቅተው ለአካባቢው ፖሊስ በመጠቆማቸው አርሶ አደሩ በቁጥጥር ሥር ውሎና ሰኔ 7፣ 2008 ዓ.ም አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ቤቱ በ25 ዓመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጣ በይኖበታል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 24፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ-ግብር ልጀምር ነው አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለነዋሪው የማሰራጨው ውሃ ንፅህናው መጠበቁን አረጋግጬ ስለሆነ ስጋት አይግባችሁ ብሏል፡፡ ከአተት ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ አፍልታችሁ ጠጡ የተባለው ከምንጭ፣ ከኩሬና ንፅህናው ባልጠበቀ ውሃ መቅጃ የሚቀዳ ውሃን ነው ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በአትክልት ተራ ህገ-ወጥ ንግድ እንዳይስፋፋ እና የተበላሹ አትክልትና ፍራፍሬዎች ለተጠቃሚው እንዳይቀርብ የዘመቻ ሥራ እየተሰራ ነው፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ የግብር ክፍያዎችን ደረጃ አሻሽሏል ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ህገ-ወጥ መድኃኒቶችን እና ምግቦችን ለመቆጣጠር የህግ ድጋፍ እየጠበኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የጤና አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናገረ…

ምግብን፣ መድሃኒትን፣ ጤና ባለሙያን፣ ጤና ተቋምን እና የአካባቢ ጤናን እንዲሁም የጤና አገልግሎትን ለመቆጣጠር ተጨማሪ የህግ ድጋፍ እና የአለም አቀፍ አሰራርን መከተል ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ በሀገር ውሰጥ የሚመረቱና ከውጪ የሚገቡ ምግብ እና መድኃኒቶችን ለመቆጣጠር ቴክኖሎጂ ያስፈልጋል፤ አለም አቀፍ አሰራር ምንድነው የሚለውን መቃኘት ያሻል ሲሉ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ የሁሉ ደነቀው ተናግረዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በሚቀጥለው ሀምሌ ወር ስለዚሁ የሚመክር ዓለም አቀፍ የምክክር ጉባኤ አዘጋጅቷል ተብሏል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተሻሽሎ በተዘጋጀው የመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ የህዝብን ገንዘብ አባክነዋል በተባሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የተደነገገው የቅጣት መጠን በቂ አይደለም ተባለ

ረቂቅ አዋጁ በወቅቱ የሂሣብ ሪፖርት ያላቀረቡ፣ እክል አለበት የተባለን የሂሣብ ምርመራ ግኝት በወቅቱ ያላስተካከሉ የሥራ ኃላፊዎች ከ5 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ይደነግጋል፡፡ ጉዳዩ ያገባቸዋል የተባሉ ከተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሚቀርቡ የሂሣብ ምርመራ ሪፖርቶች እንደሚያሣዩት በቢሊዮንና በሚሊየን የሚቆጠር የመንግሥት ብር በወቅቱ አልተወራረደም፤ መሰብሰብ ያለበት ሂሣብም በጊዜው አልተሰበሰበም ወይንም በጊዜ ሂሣቡ አልተዘጋም የሚሉ የኦዲት ግኝቶች በተደጋጋሚ እንደሚሰሙ ተወያዬቹ ተናግረዋል፡፡

በሚሊየን የሚቆጠር ብር ይባክናል እየተባለ የአስር ሺህ ብር ቅጣት ማስቀመጥ በቂ አይደለም፤ ቅጣቱ ከገንዘብ ውጪ ቢሆን የተሻለ ተጠያቂነት ይፈጥራል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ በተሻሻለው የመንግሥት ፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ መሠረት ባለ በጀት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ኦዲተሮች ተጠሪነታቸው ለሚሰሩበት መሥሪያ ቤት መሆኑ ቀርቶ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር እንዲሆን ያስገድዳል፡፡
ይህም ለውስጥ ኦዲተሮች የሙያ ነፃነት ይፈጥራል ይላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers