• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሐምሌ 6፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ዘንድሮ በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የቤት ውስጥ ጥቃቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በየመን በችግር ውሰጥ ይኖሩ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት ሊመለሱ ነው፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የአተት በሽታን ለመከላከል ያልበሰሉ ምግቦችን ከመመገብ ተቆጠቡ ሲል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተናግሯል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የዘመናዊው ኪነ-ጥበብ አባት አለ ፈለገሰላም የቀብር ስነ-ሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ምርት ከውጪ ገበያ እየጠፋ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሽንኩርት፣ ቲማቲም እና አትክልቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጁ ነፃ አላደረጋቸውም የ15 በመቶ ታክስ ይጣልባቸዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደንበኞቹ በሰጠው አርኪ አገልግሎት የስካይ ትራክስ ሽልማትን ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፈ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • በግብር ሥወራ፣ ማጭበርበርና ገንዘብ ማሸሽ የተከሰሱ 17 የተለያዩ አገሮች ዜጐችና ድርጅቶች ጉዳይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
 • በዓመት 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኘው የሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፡፡ ግንባታው 250 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ጠይቋል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • ኢትዮጵያ ከአርመንያ ጋር የውጭ ጉዳይ ግንኙነቷን አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት ተነገረ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የአዲስ አበባ ግብርና ቢሮ የርቢ እንስሳት መኖ በነፃ የደጋ ፍራፍሬ ችግኞችን በመጠነኛ ዋጋ እሰጣችኋለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቡድን ሆነው የዘረፋ ወንጀል ከፈፀሙት አምስት ተከሣሾች መካከል ሁለቱ ተከሣሾች እያንዳንዳቸው በአስር አመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሣኔ አስተላለፈባቸው

ድጉማ ኢዴቻ፣ ደምስ አያናው እና ፍቅሩ ደበሌ የተባሉ ተከሣሾች በጊዜው ካልተያዙት ሁለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እድሜዋ ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ጠልፈው ሊያመልጡ ሲሉ በአካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ ተይዘው ለፍርድ ቀርበዋል፡፡ ተከሣሾቹ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ክልል ልዩ ቦታው ገላን ኮንዶሙኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ድርጊቱ እንደተፈፀመ የአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ያስረዳል፡፡ የግል ተበዳይ ተማሪ ዘውድነሽ አትክልቲ ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤቷ በመሄድ ላይ እያለች አንደኛ ተከሣሽ ድጉማ ኢዴቻ የሞባይሉን መብራት ፊቷ ላይ እያበራ እንዳታልፈው በዳንስ እንቅስቃሴ ገቷት እሾክ ላይ እንድትወድቅ አድርጓታል፡፡

ሁለተኛ ተከሣሽ የሆነው ደምስ አያናው ደግሞ ከአንደኛ ተከሣሽ ጋር በጋራ ሆነው የወደቀችዋን ልጅ ወገብና እግሮቿን በመያዝ ፤ ሦስተኛ ተከሣሽ ፍቅሩ ደበሌ ወደ ሚያሽከረክረው ሚኒባስ መኪና ውስጥ እንድትገባ አድርገዋል፡፡ ደሜ ቶሎሳ የተባለው ለጊዜው ያልተያዘው ግብረ አበር ደግሞ ልጅቷ እንዳትጮህ አፍና አፍንጫዋን አፍኗታል፡፡ ሦስተኛው ተከሣሽ ፍቅሩ ደበሌ በፍጥነት መኪናውን አስነስቶ ከአካባቢው ለመሰወር ሲሞክር ከልጅቷ ጋር የነበሩ ተማሪዎች የጠለፋ ድርጊቱን ለማስቆም እየጮሁ ድንጋይ ሲወረውሩ አቡሌ የተባለው ለጊዜው ያልተያዘው ተከሣሽ ሽጉጥ አውጥቶ በማስፈራራት ልጆቹን አባሯል፡፡

በመጪዎቹ አራት ወራት ከአዲስ አበባ ነጋዴዎች 26 ቢሊየን ብር ግብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተናገረ

ገቢውን ለመሰብሰብ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ተባብሬ እሰራለሁ ብሏል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ዘመን ለሚያስፈልጓት የተለያዩ የልማት ሥራዎችና የመሠረት ልማት ግንባታ የከተማዋ አስተዳደር 34 ቢሊየን ብር በጀት አፅድቋል፡፡ ይህንን በጀት 74 በመቶ የሚሆነው ከግብር በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡ ከግብር የሚሰበሰበው ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑ አዲስ አበባ የሚያስፈልጋትን ወጪ አይሸፍንም መባሉን ሰምተናል፡፡ ወሬውን የሰማነው ዛሬ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተገኝተን ነው፡፡

ከሐምሌ 1 ቀን2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ባሉት አራት ወራት 360 ሺህ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ግብር ከፍለው ንግድ ፈቃዳቸውን ያድሣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የከተማዋ የንግድ ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የግብር ገቢ አሰባሰቡም እየጨመረ ቢሆንም ከንግድ እንቅስቃሴው አንፃር አሁንም ገቢው ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 5፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • ሰሞኑን የእንቁላል ዋጋ ከነበረበት ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የእንስሣትና አሳ ሀብት ልማት ሚኒስቴር ችግሩ የቱ ጋር እንዳለ ላጣራ ነው አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የተሽከርካሪ የመለዋወጫ እቃዎችን ለመቆጣጠርና ደረጃቸውን ለማወቅ መቆጣጠሪያ መላ እና ደረጃ ሊዘጋጅ ይገባል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • ኢትዮጵያ ዘንድሮ በቱሪዝሙ መስክ ከቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • ውሃ ያለአግባብ የሚያባክኑት ላይ አስገዳጅ እርምጃ ልንወስድ ነው ሲል የአዲስ አበባ የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ ወቅቱ ክረምት ስለሆነ የዝናብ ውሃን ለተለያዩ የንፅህና አገልግሎቶች ተጠቀሙበት ሲልም መክሯል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ጠብታ አምቡላንስ የሞተር አምቡላንስ አገልግሎት ልጀምር ነው አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ክረምቱ ለሚያፈራርሳቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ጥገና 80 ሚሊዮን ብር ተመድቧል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የሥራ አመራሮች በተለያዩ ጥፋቶች በዚህ አመት ተጠያቂ ሆነዋል፡፡ (ዮሐንሰ የኋላወርቅ)
 • ከአዲስ አበባ ነጋዴዎች 26 ቢሊየን ብር ሊሰበሰብ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በሀገሪቱ ያለውን የጠርሙስ እና ብርጭቆ ፍላጐት ሙሉ በሙሉ መሙላት ባልችልም በቀን 50 ቶን የሚያመርት አዲስ ፋብሪካ ገንብቻለሁ ሲል የአዲስ አበባ ጠርሙስና ብርጭቆ አክሲዬን ማህበር ተናገረ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቀይ ቦሎቄንና ማሾን ማገበያየት ጀመረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነገረ

አቶ ዘላለም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡ በክልሉ በተለያዩ የሥልጣን ደረጃ በሰሩባቸው ጊዜያት በተሰጣቸው ኃላፊነት ሥልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል፡፡የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረትን በመዝረፍ በከፍተኛ የሙስና ወንጀልም ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ መነገሩ ይታወቃል፡፡ አቶ ዘላለም በቁጥጥር ስር የዋሉት ጨፌ ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ያለመከሰሰ መብታቸውን ካነሳ በኋላ ነበር፡፡

ሐምሌ 4፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለጨቅላ ህፃናት የምሰጠውን የህክምና አገልግሎት ፍለጋ የሚመጡና ያለኝ አቅም ሊጣጣምልኝ አልቻለም ሲል ተናገረ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በክረምት በአባይ ተፋሰስ ከ20 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ የሚያስገኙ ችግኞች ይተከላሉ ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የሕዳሴው ግድብ አካባቢያዊ ተፅዕኖን ከሚያጠኑ ተቋማት ጋር የኮንትራት ስምምነቱ ሊፈረም ተቃርቧል ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኝተው ችግረኛ ታማሚዎችን ምሳ ያበላሉ ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ችሎት ቀረቡ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ሁለት ተከሳሾች በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 1፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • መድሃኒት ለተላመደ የቲቢ በሽታ ታካሚዎች አዳዲስ መድሃኒቶችን መስጠት ተጀመረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የሰንሻይን ሪል ስቴት ነዋሪዎች በግልፅ ባላወቅነው ምክንያት ውሃ ተከለከልን እያሉ ነው፡፡ ሪል ስቴቱን የገነባው ተቋም ችግር ካለ እንኳን እኔን መጠየቅ እንጂ እንዴት ውሃ ይከለከላል ይላል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ፈተናዎች ኤጀንሲ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ታትሞ ደርሶኛል ሲል ተናገረ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • ያለ ቅጣት የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ማድረጊያ ጊዜ በአንድ ወር ተራዘመ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከኢትዮጵያ ጋር የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት አለን ያንንም ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ እንሰራለን አሉ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ትውልደ ኢትዮጵያዊ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንቱ እንዲሰማሩ ተጠየቀ፡፡ መታሰቢያ ሙዚየምም ሊገነባላቸው ነው፡፡ (ፋሲል ረዲ) 
 • ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ በቃላቸው መሠረት ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን ወደ ሶማልያ እንዲልኩ የአፍሪካ ህብረት ጠየቀ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በስዕል ስራዎቿ ታዋቂ የሆነችው የጁሊ ምህረቱ የረቂቅ /አብስትራክት/ የስዕል አውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መድሃኒት ለተላመደ የቲቢ በሽታ ታካሚዎች አዳዲስ መድሃኒቶችን መስጠት ተጀመረ

የቲቢ በሽታ ታካሚዎች የሚወስዱት መድሃኒት ከበሽታው ጋር ሲላመድ ሌሎች አማራጮችን ለመፈለግ ይገደዳሉ፡፡ ከእነዚህ አማራጮች አንዱ መድሃኒቶችን እያቀያየሩ መጠቀም ነው፡፡ እነዚህን መድሃኒቶች እንደልብ ማግኘት ግን አስቸጋሪ እንደሆነ በፓርትነርስ ኢን ሄልዝ የኢንድ ቲቢ ዳይሬክተር ዶክተር አንዳርጋቸው ኩምሳ ተናግረዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት አዳዲስ የቲቢ መድሃኒቶችን ባለፈው ቅዳሜ በሀገራችን መሰጠት ተጀምሯል ብለዋል፡፡ በቢሾፍቱ ሆስፒታል መሰጠት የጀመሩት አዳዲሶቹ የቲቢ መድሃኒቶች ቤዳኩልን እና ዴላማናት እንደሚባሉ ከዶክተር አንዳርጋቸው ሰምተናል፡፡

መድሃኒቶቹን በቢሾፍቱ ሆስፒታል ለሙከራ መስጠት የተጀመረው በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኦሮሚያ ጤና ቢሮ እና በፓርትነርስ ኢን ሄልዝ የጋራ ትብብር ነው ብለዋል፡፡ መድሃኒቶቹን በሆስፒታሉ ተገኝተው የወሰዱት ሁለት የቲቢ በሽታ ታካሚዎች እንደሆኑም ነግረውናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“አዲስ በአዲስ አበባ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የጁሊ ምህረቱ የስዕል አውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል ተባለ

በተለያየ የረቂቅ ሥራዎቿ በዓለም ታዋቂ የሆነችው የጁሊ ምህረቱ የጥበብ ሥራዎች ከዚህ በፊት ያልታዩ ስዕሎች ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡ የስዕል አወደ ርዕዩ ከዛሬ ሐምሌ አንድ ጀምሮ ለአንድ ወር እስከ ሐምሌ 30 ድረስ ይቆያል ብለው የነገሩን የአውደ ርዕዩ አስተባባሪ ዶክተር ዳግማዊ ውብሸት ናቸው፡፡ በገብረክርስቶስ ደስታ የስነ-ጥበብ ቤተ-መዘክር የጁሊ ምህረቱ የረቂቅ አብስትራክት ስዕል እና ሌሎችም ካንቫስ ሸራዎች ላይ የሰራቻቸው ስዕሎች ይታያሉ ተብሏል፡፡

ዛሬ በሚከፈተው አውደ ርዕይ ላይ የመጀመሪያው ቀን በመሆኑ የባህል እና የሥነ-ጥበብ ሰዎች፣ አምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ብቻ ይገኛሉ መባሉን ሰምተናል፡፡ ከእሁድ ሐምሌ 3 ጀምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በገብረክርስቶስ ደስታ ሙዚየም መመልከት ይችላል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ኡጋንዳ በቃላቸው መሰረት ተዋጊ ሂሊኮፕተሮችን ወደ ሶማሊያ እንዲልኩ የአፍሪካ ህብረት ጠየቀ

ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ኡጋንዳ በአፍሪካ ህብረት ልዩ ሃይል ስር ጦራቸውን ወደ ሶማሊያ ከላኩ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡ ሶስቱ ሀገራት ጦር ከማዋጣት በተጨማሪ ተዋጊ ሂሊኮፕተሮችንም ወደ ሶማሊያ ለመላክ ባለፈው የካቲት ወር ቃል ገብተው እንደነበር የአፍሪካ ህብረት አስታውሷል፡፡ ሀገራቱ ተዋጊ ሂሊኮፕተሮቹን ወደ ሶማሊያ እንልካን ያሉት በዚያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ሃይል በጽንፈኛው ቡድን አልሸባብ ላይ ለከፈተው ዘመቻ ተጨማሪ አቅም እንዲያገኝ ለማስቻል ነው፡፡

ይሁንና በቃላቸው መሰረት እስከ አሁን ተዋጊ ሂሊኮፕተሮቹን ሀገራቱ ወደ ሶማሊያ እንዳልላኩ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ጠቅሷል፡፡ በገቡት ቃል መሰረት በቶሎ ተዋጊ ሂሊኮፕተሮቹን ወደ ሶማሊያ እንዲልኩም ጠይቋል፡፡ የተዋጊ ሂሊኮፕተሮቹ መገኘት በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ሃይል በአልሸባብ ላይ የሚያካሂደውን ዘመቻ ያህል አስፈላጊ ነው ሲልም ነገሩን አፅንኦት ሰጥቶታል፡፡ ቀደም ብለው የወጡ መረጃዎች ኢትዮጵያና ኬንያ ብቻ ሶስት ተዋጊ እና ዘጠኝ ሁለገብ ሂሊኮፕተሮችን ወደ ሶማሊያ ለመላክ ቃል እንደገቡ ጠቁመው ነበር፡፡

ይህም ከአራት አመት በፊት ኡጋንዳ ወደ ሶማሊያ የላከቻቸውን አራት ሂሊኮፕተሮች ካስወጣች በኋላ ብዙ ሂሊኮፕተሮችን የሰጡ ሀገሮች ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡ ኡጋንዳ በወቅቱ ሂሊኮፕተሮቹን ወደ ሀገር ቤት የመለሰችው ሶስቱ ከኬንያ ተራራ ጋር ከተጋጩባት በኋላ ነበር፡፡ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት በሶማሊያ ለሚገኘው የቡሩንዲ ጦር የአውሮፓ ህብረት የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀነስ መወሰኑም አሳስቦኛል ብሏል፡፡

ህብረቱ ድጋፉን እቀንሳለሁ ያለው የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል በሚል ነው፡፡ ምክር ቤቱ ግን ህብረቱ ይህንን ውሳኔውን እንዲቀይር ጠይቋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ አድርጋችሁ ቦሎ ሳትለጥፉ ጊዜ ላለፈባችሁ አሽከርካሪዎች መልካም ወሬ ነው

ዓመታዊ ምርመራን ያለ ቅጣት ለማድረግ ተጨማሪ የአንድ ወር ጊዜ ተሰጥቷችኋል ተብሏል፡፡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ነው ይህንን ለኛ የነገረን፡፡ ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደሰማነው የ2008 ዓ.ም ዓመታዊ የምርመራ ጊዜና ቦሎ ማድረጊያ ዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ከነገ ጀምሮ ምርመራ አድርገው ቦሎ ለመለጠፍ የሚመጡም የሚስተናገዱት በቅጣት ነበር፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እንደተናገረው በርካታ ተሽከርካሪዎች የዘመቻ ሥራ ላይ ስላሉና ምርመራውን አድርገው ቦሎ ለመለጠፍ ጊዜ ስላላገኙ ጊዜውን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡በዚህም ምክንያት ሰኔ 30 ቀን ያበቃ የነበረው የምርመራና ቦሎ መለጠፊያ ጊዜ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ለአንድ ወር ተራዝሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers