• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ግንቦት 3፣2011/ በስልጣን ላይ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኦህዴድ ከወራት በፊት ስያሜውን ቢቀይርም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እሱም ሆነ የቀድሞው ብአዴን እውቅናና ምዝገባ አልተሰጣቸውም

በስልጣን ላይ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኦህዴድ ከወራት በፊት ስያሜውን ቢቀይርም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እሱም ሆነ የቀድሞው ብአዴን እውቅናና ምዝገባ አልተሰጣቸውም፡፡ አጠቃላይ ቦርዱ ምን እየሰራ ነው?

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ ወደ ግል ለማዛወር ጥናት እየተካሄደባቸው ያሉ 13 የስኳር ፋብሪካዎች ጉዳይ

ሙሉ በሙሉ በመንግስት ስር የነበሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም በአጠቃላይ ወደ ግል ለማዛወር በተወሰነው መሰረት በየተቋማቱ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡ከነዚሁም የልማት ድርጅቶች ውስጥ በስኳር ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ 13 የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዛወር ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴርና የስኳር ኮርፖሬሽን በጋራ መጠይቅ አዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡ፋብሪካዎቹ ወደ ግል የሚዛወሩት በከፊል ይሁን በሙሉ እስካሁን አልታወቀም፤ ግን ሂደቱ ተጀምሯል፡፡ ንጋቱ ሙሉ ወደ ግል ይዞራሉ ስለተባሉት ፋብሪካዎች ሂደትና ምክንያት ባለሙያ አነጋግሯል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ የብድር ወለድ ምጣኔ እና የግብር ጫና ማነቆ

አሁን ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ጎርበጥባጣ የበዛበት አስቸጋሪ መንገድ መሆኑ ይነገርለታል፡፡የብድር ወለድ ምጣኔ እና የግብር ጫና ማነቆ ሆነዋል በሚል በግሉ ሴክተር የሚንቀሳቀሱት የንግድ ተሳታፊዎች ይናገራሉ፡፡ብሔራዊ ባንክም ይኸን አስተያየት ይጋራል፡፡ መፍትሄዎችንም ይጠቁማል፡፡ይኽ ሁሉ የተሰማው ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ዛሬ በሸራተን አዲስ በተዘጋጀበት ወቅት ነበር፡፡ ተህቦ ንጉሴ በስፍራው ተገኝቶ ተከታትሏል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣ 2011/ “የሕግ የበላይነት በዲሞክራሲ ሽግግር ላይ ባለችው ኢትዮጵያ”- አዲስ ወግ አንድ ሐሳብ የውይይት መድረክ

በኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ሂደት እየተዳከመ በመሆኑ በተለያዩ አቅጣጫዎች ጉዳቶች እየታዩ መሆኑ ይነገራል፡፡መንግስትም ሕግ የማስከበር ሀላፊነቱን ሊወጣ አልቻለም የሚል እሮሮ ይሰማበታል፡፡መንግስት ደግሞ ትዕግስት ማድረግ ይሻለኛል ይላል፡፡በነዚህ ጉዳዮች ላይ የተንተራሰ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምሁራን በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡ምህረት ስዩም ተከታትላዋለች

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ ትምህርት ሚኒስቴር የአገር አቀፍ ፈተናዎች መስጫ ጊዜ ማራዜሜን እወቁልኝ አለ

የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት የኢድ በዓልን አስመልክቶ ባደረገው ውይይት ነው የፈተናዎቹ መስጫ ጊዜ እንዲራዘም የተወሰነው።በውሳኔውም መሰረተረ የ10ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲሰጥ ቀጠሮ ተይዞለታል።

የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ደግሞ ሰኔ 6፣7፣10፣እና 11/2011ዓ.ም እንደሰጥ መወሰኑንም ከሚኒስቴሩ ሰምተናል። የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲሰጥ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል።

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ ሁለተኛው የአዲስ ወግ የባለሙያዎች የውይይት መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተካሄደ ነው

ውይይቱ “የሕግ የበላይነት በዲሞክራሲ የሽግግር ሂደት” በሚል የተሰናዳ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሰምተናል፡፡ ዛሬ እየተካሄደ ባለው በዚህ ውይይት ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ፣ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የፍልስፍና መምህረሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እንዲሁም ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ ሀሳብ አቅራቢ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ በጥረት ኮርፖሬት የሀብት ምዝበራና ብክነት ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ በረከት ስምዖን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

በባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በቀጠሯቸው መሰረት የቀረቡት አቶ በረከት ስምዖን የተባለውን ወንጀል አልፈፀምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው መናገራቸውን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡ሌላኛው ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ ግን ቃላቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሏል፡፡

ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተነግሯል፡፡ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደም ክሱ ውድቅ እንዲሆንላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ ብይን ሰጥቷል ተብሏል፡፡የክስ መቃወሚቸውንም ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሐይል ሽያጭ 5.3 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናገረ

መስሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 5 ነጥብ 365 ቢሊየን ብር አግኝቻለሁ ብሏል፡፡157 ሺህ 643 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ተናግሯል፡፡ተቋሙ 119 አዳዲስ ከተሞች ሀይል እንዲያገኙ ማድረጉንና የ11 ከተሞችን ሀይል ማሻሻሉን አስታውቋል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2025 ሁሉንም የሀገሪቱ ክፍሎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ውጥን እንዳለው ይታወቃል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በአሶሳ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል፤ በወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታ ላይ በመወያየትም የአቋም መግለጫ አውጥቷል

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በአሶሳ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል፤ በወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታ ላይ በመወያየትም የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 2፣2011/ማህበራዊ ፍትህን እና የዜግነት ፖለቲካን መሰረት አድርጎ ትናንት መስራች ጉባኤውን የጀመረው ንግግር ዛሬ ሊቀመንበሩን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል

ማህበራዊ ፍትህን እና የዜግነት ፖለቲካን መሰረት አድርጎ ትናንት መስራች ጉባኤውን የጀመረው ንግግር ዛሬ ሊቀመንበሩን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ ከቀያቸው የተፈናቀሉ 900 ሺ ሰዎች ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸው ተነገረ

ከቀያቸው የተፈናቀሉ 900 ሺ ሰዎች ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸው ተነገረ፡፡ ዜጎችን አፈናቅለዋል፣ ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ 1300 ሰዎች ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ነው ተብሏል፡፡ የሸገር ገበታ ከ10 ቀናት በኋላ እንደሚደረግ ሰምተናል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በእነዚህ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መግለጫውን የተከታተለው ንጋቱ ሙሉ የሚከተውን አዘጋጅቷል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers