• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መንግሥት ከተማሪዎች ፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ጋር የሚያካሂደው ውይይት ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መሆኑ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናገሩ

መንግሥት ከምሁራንና ተማሪዎች እንዲሁም ከወላጆችና የትምህርት ባለሙያዎች ጋር ለውይይት እንደሚቀመጥ አውርቷል፡፡የትምህርት ዘመኑ ሥራ ከመጀመሩ አስቀድሞ በሀገሪቱ ሁነኛ ጉዳዮች ላይ መንግስት ውይይት ለማድረግ መምረጡን የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊትም ቢሆን ተመሣሣይ ሥልጠናዎችና ውይይቶች ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በትምህርት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሠራተኞች ይሰጥ እንደነበር የተናገሩት አቶ ሽፈራው የዘንድሮው ውይይትና ሥልጠና በወቅታዊ ጉዳዮችና ጥያቄዎች ላይ ሰፋ ያለ ነፃ የኃሳብ ክርክር የሚደረግበት ስለመሆኑ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ነው ያሉትን ኃሳብ ሰጥተዋል፡፡ከጥያቄዎቹ መካከል መንግሥት ዓመት እየጠበቀ ከሚያካሂደው ተመሣሣይ ስልጠናና ውይይት ምን ጠብ አለለት? በሀገሪቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ላይ ስጋት ተደቅኗል የሚሉ ጥያቄዎች ለሚኒስትሩ ተሰንዝረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ከአገር ውስጥና ከውጭ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

ባለቀው 2008 ዓ.ም ከኤሌክትሪክ ሽያጭ ወደ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ተሠማ፡፡ከውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር እንደተሰማው ባለፈው ዓመት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ኤሌክትሪክ ተሸጦ የተገኘው ገቢ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ነው ሲሉ የነገሩን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብዙነህ ቶልቻ ናቸው፡፡

አቶ ብዙነህ እንዳሉት ከሆነ ከተገኘው ገቢ ውስጥ 300 ሚሊዮን ብሩ የተገኘው ለውጪ ሀገር ከተሸጠው ኤሌክትሪክ ነው፡፡ ለጅቡቲ 60 ሜጋዋት ፣ ለሱዳን ከ100 ሜጋ ዋት በላይ እንዲሁም ለኬኒያ የድንበር አካባቢዎች ከ10 ሜጋ ዋት በታች የተሸጠ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ይሁን እንጂ በአመቱ ገቢ ይገኛል ተብሎ የታቀደው 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ነበረም ተብሏል፡፡ የጐረቤት ሀገሮቹ ኤሌክትሪክ የሚሸጠው በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ፍላጐት በማይኖርበት እና በአብዛኛውም ሌሊት ላይ እንደሆነም አቶ ብዙነህ ነግረውናል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እርጅና የተጫጫናቸውን የከተማዋን መንገዶች የመጠገኑን ነገር አልዘነጋሁትም አለ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በዘንድሮ የሥራ ዘመኔ የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማረሩትን አሮጌ አውራ ጐዳናዎች ለመጠገን አስቤያለሁ አለ፡፡ በለሥልጣኑ ለጊዜው ችግር መፍቻ ሳይሆን የማያዳግሙ እና የተሻለ ዘመን አገልግሎት እንዲሰጡ አጠግናቸዋለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡

አብዛኛዎቹ የመሀል አዲስ አበባ አውራ ጐዳናዎች አገልግሎታቸው እንዳበቃ አና እንዳረጁም ባለሥልጣኑ ነግሮናል፡፡ ይሄንኑ  አስፋልትም በተሻለ መንገድ ለመጠገን ሰለጠኑ ከሚባሉት ሀገሮች ልምድ እና ስልጠና እንደተወሰደ የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሲሳይ ወርቅነህ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ አሽከርካሪውንም እግረኛውንም እያማረር ያስቸገሩትን አውራ መንገዶችን ጨምሮ የፍሳሽ ማስወገጃ የእግረኛ መንገድ የመንገድ ላይ መብራት እና ሌሎችንም ትኩረት ሰጥቼ ለመጠገን አስቤያለው ብሏል ባለሥልጣኑ፡፡ ጥገና ያገኙት መንገዶች ለዘመናት እንዲቆዩም አሁን ሥራዬን ለመጀመር ጥናቴን አጠናቅቄያለሁ ብሎናል የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን፡፡

ተኅቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ እና የአካባቢው ሀገሮች ሶማልያ ሰላም እንድትሆን ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ የነበረውን ጥረት ይቀጥላሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናገሩ

ኢትዮጵያ እና የአካባቢው ሀገሮች ሶማልያ ሰላም እንድትሆን ከዚህ ቀደም ሲያርጉ የነበረውን ጥረት ይቀጥላሉ ሲለ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናገሩ፡፡ ኢጋድ ስለ ሶማልያ ሰላም እና የወደ ፊት እጣ ፈንታ ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን ስብሰባ አድርጓል፡፡

በስብሰባው ላይ የኢጋድ ሊቀ መንበር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አደረጉ በተባለው ንግግር የሶማልያ ሰላም እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ኢትዮጵያና የኢጋድ አባል ሀገሮች ድጋፋቸው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከፍ ብሎ ይታይ ብለዋል፡፡

ሶማልያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች በኋላ የመጀመሪያው የሆነው ነው የተባው ስብሰባ በሞቃድሾ ከተማ መካሄዱን የተናገሩት የሶማልያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቡዱልሰላም ኡመር ለሬውተርስ በሰጡት መግለጫ የስብሰባው በሞቃድሾ መካሄድ አለም አቀፍ ሽብርተኝነት ከጐረቤቶቻችን ጋር በመተባበር፡፡ ሶማልያ በቅርቡ ለማካሄድ ላሰበችው ምርጫም የኢጋድ አባል ሀገሮች ድጋፍ እንደማይለያትም በስብሰባው ተነግሯል፡፡

ፋሲል ረዲ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 4፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የኮምፒውተር ማደሻና ማሰልጠኛ ማዕከል በእርዳታ ያገኛቸው ከ4 ሺህ በላይ ኮምፒውተሮች ፈላጊ አጥተው መጋዘን አጣበውብኛል አለ፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን
 • እጅግ ከፍተኛ የስዕል ቅርሶች ያሉበት የሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ የነበረው ቪላ አልፋ ለቤተ-መዘክርነት እንዲሆን ተደርጎ ይታደሳል ቢባልም እስካሁንም እድሳቱ አለመጀመሩ ተሠማ፡፡ ተህቦ ንጉሴ
 • በ2008 ዓ፤ም በመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተቸግራ የነበረችው ሀረር በ2009 መፍትሄ ታገኛለች እየተባለ ነው፡፡ በ2009 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ ሀረር የብሔር ብሔረሰቦችን በአል ለማክበር ሽርጉድ እያለች መሆኑ ትኩረት ለማግኘቷ ምክንያት ሆኗላታል... አስፋው ስለሺ
 • በአህጉራዊ ፍልሰት ላይ የሚመከር ጉባዔ በአዲስ አበባ ይዘጋጃል ተባለ፡፡ የኔነህ ሲሣይ
 • ኢትዮጵያ እና የአካባቢው ሀገሮች ሶማልያ ሰላም እንድትሆን ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ የነበረውን ጥረት ይቀጥላሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናገሩ፡፡ ፋሲል ረዲ
 • ባለፈው ዓመት ከአገር ውስጥና ከውጭ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡ ዮሐንስየኋላወርቅ
 • መንግሥት ከተማሪዎች ፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ጋር የሚያካሂደው ውይይት ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መሆኑ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናገሩ፡፡ ሕይወት ፍሬሰብሃት
 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እርጅና የተጫጫናቸውን የከተማዋን መንገዶች የመጠገኑን ነገር አልዘነጋሁትም አለ፡፡ ተኅቦ ንጉሴ
 • በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሁለት ሰዎችን በጭካኔ የገደሉ ሦስት ተከሳሾች በዕድሜ ልክ እሥራት ተቀጡ፡፡ ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግብፅ የአባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን እንድትቀላቀል ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ

ግብፅ የአባይ ተፋሰስ አባል አሀገራት የትብብር ማዕቀፉን ብትቀላቀል ለአካባቢው ሰላም አስፈን ትልቅ ዕድል ይሰጣል ተባለ፡፡የአባይ ውሃ ክፍፍልን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መጠቀም የሚያስችለውን የትብብር ማዕቀፍ ለመፈረም እና የህብረቱ አባል ለመሆን ፍላጐቷን ያሣየችው ግብፅ ቃሏን ጠብቃ ወደ ስምምነቱ ብትመጣ አባይ ያለመግባባት ምክንያት ከመሆን ይልቅ ወደ ዕድገት ምንስኤነት ይቀየራል፡፡

ይህን ያሉት ኢንጅነር ተሾመ አጥናፌ በውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የወሰን እና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ግብፅ ወደ ማዕቀፉ የምትመለሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ እና ከዚህ በፊት የነበሩ ስምምነቶችን በማሻሻል ነው የሚል ወሬ ይሰማል በዚህ በኩል የኢትዮጵያ አቋም ምንድነው ያልናቸው ኢንጂነር ተሾመ ምንም የሚቀየር ነገር የለም ብለዋል፡፡

መነሻው ከጣና ኃይል የሆነው አባይ ወንዝ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን ወንዙ የሚያልፍባቸው አስራ አንድ ሀገሮች የተፋሰሱ አባል ሀገሮች ናቸው፡፡

ፋሲል ረዲ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጨሞጋ የዳ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሊዘጋ መሆኑ ተሠማ

የጨሞጋ የዳ የኃይል ማመንጫ ýሮጀክት ሊዘጋ መሆኑ ተሠማ፡፡ፕሮጀክቱ በአዲስ መልኩ ዳግም ይሰራል ተብሎ ይገመታል፡፡ከውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የ2008 ዓ.ም ሪፖርት ላይ እንደሰፈረው የጨሞጋ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ግብፅ ጥያቄ አንስታለች፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን የገንዘብ ብድር እሰጣለሁ ያለችውም ቻይና የብድር ስምምነቱን ያልፈረመች በመሆኑ ስራው ሊሰራ አልቻለም ተብሏል፡፡ሲኖ ሃይድሮ የተባለው ኮንትራክተር ምንም አይነት ስራ ሊሰራ ባመቻሉ እና የኮንትራት ቅድመ ሁኔታዎችን ስላልተሟሉ ስምምነቱ ተቋርጧል፡፡

ከዚህም በኋላ ፕሮጀክቱን ለማልማት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች ለማስተላለፍም ጨረታ ወጥቶ የነበረ ቢሆንም መንግሥት ýሮጀክቱን ለመስራት አዲስ ዘዴ ስላሰበ ፕሮጀክቱ ይዘጋል ተብሎ ታስቧል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ቀናት አዲስ አበባ 83 የትራፊክ አደጋዎችን አስተናግዳለች

ከአዲስ አመት ዋዜማ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ቀናት አዲስ አበባ 83 የትራፊክ አደጋዎችን አስተናግዳለች፡፡ የሞት አደጋ ግን አለመመዝገቡ ከአምናው የዘመን መለወጫ በዓል የተሻለ የትራፊክ እንቅስቃ እንደነበር ያሳያል ተብሏል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለሸገር እንደተናገረው በዘመን መለወጫ ዋዜማ በከተማዋ 23 የትራፊክ አደጋ ደርሷል፡፡ 20 የንብረት አደጋና 3 ከባድ የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡

አምና በዘመን መለወጫ እለት 2 የሞት አደጋ ደርሶ እንደነበር ያስታወሱት በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ናቸው፡፡በዘንድሮው በዓል ግን የሞት አደጋ አልተመዘገበም 20 የንብረት እንዲሁም 2 ከባድና 1 ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡

ትናንት የአረፋ በዓል በተከበረበት እለትም 20 የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን 2 ከባድ የአካል ጉዳትና 18 የንብረት አደጋ ደርሷል መባሉን ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን በኢንቨስትመንቱም እየተሳተፍኩ ነው አለ

የግል ድርጅቶች ማህበራ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን በኢንቨስትመንቱም እየተሳተፍኩ ነው ብሏል፡፡ኤጀንሲው ለኢንቨስትመንት የሚያውለው ለጡረተኞች ከሚከፍለውና ለአስተዳደራዊ ስራዎች ከሚያወጣው ገንዘብ የሚቀረውን ነው፡፡

የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጋሻው ለሸገር እንደተናገሩት በተጠናቀቀው 2008 በጀት ዓመት ከኢንቨስትመንት ብቻ ከ107 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል፡፡ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ ከ4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ የጡረታ መዋጮ መሰብሰቡንም ከዳይሬክተሩ ሰምተናል፡፡ ከ18 ሺህ በላይ የግል ድርጅቶችንና ከ143 ሺህ የሚበልጡ ሠራተኞችን መዝግቧልም ብለዋል፡፡

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ ገቢ ካላደረጉ ድርጅቶች በቅጣትና ወለድ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ኤጀንሲው ማግኘቱን አቶ ተስፋዬ ጨምረው ነግረውናል፡፡ ሌሎች ድርጅቶች ደግሞ የሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ ገቢ ባለማድረጋቸው ለባንክ በተፃፈ ደብዳቤ ከባንክ ሂሳባቸው ተነቅሶ ለጡረታ ፈንዱ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ተደርጓልም ብለውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሣ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 3፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ደም በመስጠት በደም እጦት የሚሞቱ ወገኖችን መታደግ እንደሚገባ ተነገረ፡፡ የአዳማ ብሔራዊ ደም ባንክ ከ1 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ከኢትዮጵያ ተልዕኮ ለትውልድ አገልግሎት አባላት ሰብስቧል፡፡ አስፋው ስለሺ
 • የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የጭንቅላት የህብለ ሰረሰር እና የነርቭ ህክምናን ዛሬ ልጀምር ነው አለ፡፡ መሠረት በዙ
 • ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 2008 በውጭ ጉዳይ ፖለሲዋ እንዴት አሳልፋ ይሆን ገዥው መንግሥት ዓመቱ በጣም የተዋጣለት ነበር ይላል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ደግሞ እንደውም 2008 ኢትዮጵያ በዲጵሎማሲው መስክ ዝቅ ብላ የታየችበት ነው የላሉ፡፡ የኔነህ ሲሣይ 
 • ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ቀናት አዲስ አበባ 83 የትራፊክ አደጋዎችን አስተናግዳለች፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን
 • የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን በኢንቨስትመንቱም እየተሳተፍኩ ነው አለ፡፡ ንጋቱ ረጋሣ
 • በአዲስ አበባ ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ሥልጠና ሊሰጣቸው ነው፡፡ የዘንድሮ ትምህርት መስከረም 18 ይጀመራል ተብሏል፡፡ ህይወት ፍሬስብሃት
 • የጨሞጋ የዳ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሊዘጋ መሆኑ ተሠማ፡፡ ዮሐንስ የኋላወርቅ
 • ግብፅ የአባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን አግድትቀላቀል ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ፡፡ ፋሲል ረዲ
 • በአርሲ ዞን የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ የሰው ህይወት ጠፋ፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለመጪዎቹ በዓላት የበግ አቅርቦት እጥረት ገጥሞኛል ፣ የበሬ ነገር ግን አያሰጋኝም ብሏል

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለዘመን መለወጫ በዓል 2 ሺህ 500 በጐችን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለማቅረብ ብወጥንም የበግ አቅርቦት እጥረት አጋጥሞኛል አለ፡፡ እስካሁን እጄ ውስጥ የገቡት በጐችም 7 መቶ ብቻ  ናቸው ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ንብረት በቃ ለሸገር እንደተናገሩት በዘመን መለወጫ በዓል የተለመደው በሰፊው በግ ማቅረብ ነው ይሁን እና በዚህ ዓመት የዘመን መለወጫና የአረፋ በዓል በአንድ ቀን ልዩነት በመዋላቸው ምክንያት የበግ አቅርቦት እጥረት አጋጥሞናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለአረፋ በዓል ብቻ ለእስልምና እምነት ተከታዬች የቀረበለትን የ5 ሺህ በጐች እርድ ፈፅሞ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ለዘመን መለወጫ በዓል የተለመደው የበግ ሥጋ ቢሆንም የአቅርቦት እጥረት አጋጥሟል ያሉት ዳይሬክተሩ የበሬ አቅርቦት ችግር ግን ስለሌለ 2 ሺህ በሬዎች ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መዘጋጀታቸውን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers