• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ግንቦት 2፣2011/ የቀድሞው የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ እና አራት የአገልግሎቱ ሰራተኞች የነበሩ እጃቸው ተይዞ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ

ትዕዛዙን የሰጠው ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ያቀረበውን ክስ የሚመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡ፍርድ ቤቱ በትናንቱ ችሎቱ በአቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተከሰሱትን 26 ተከሳሾች ጉዳይ ተመልክቷል፡፡

ከ20 እስከ 26 ተራ ቁጥር ላሉት ተከሳሾችም ክሳቸው በንባብ ተሰምቷል፡፡ተከሳሾቹ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክደው ተከራክረዋል፡፡ የዋስትና መብታቸውም እንዲጠበቅላቸው አመልክተዋል፡፡ ዐቃቤ ሕግ ግን የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት አያስጠብቅም፣ ከተለቀቁ መረጃ ያሸሹብኛል ብሎ አመልክቷል፡፡ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ ለመወሰን ለግንቦት 8፣ 2011 ቀጥሮ ሰጥቷል…

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ 993 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የሻምቡ ባኮ መንገድ፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶ አለመነሳት እክል ፈጠረበት ተባለ

993 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የሻምቡ ባኮ መንገድ፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶ አለመነሳት እክል ፈጠረበት ተባለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ሀይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ ሞያሌና ጅግጅጋ 95 በመቶ ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ዝውውር የሚካሄድባቸው ናቸው ተባለ፡፡ ለህግ አካላት ዛሬ ስልጠና እየተሰጠ ነው

ሞያሌና ጅግጅጋ 95 በመቶ ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ዝውውር የሚካሄድባቸው ናቸው ተባለ፡፡ ለህግ አካላት ዛሬ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ሀይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ሀይል ስምሪቱ ሙያዊ ክህሎትን የጠበቀ እንዲሆን ወደ ጎንና በተዋረድ እስከፖሊስ ጣቢያ የሚደርስ የማሻሻያ ስራ እንዲከውን ተወሰነ

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ሀይል ስምሪቱ ሙያዊ ክህሎትን የጠበቀ እንዲሆን ወደ ጎንና በተዋረድ እስከፖሊስ ጣቢያ የሚደርስ የማሻሻያ ስራ እንዲከውን ተወሰነ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ የኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ቁጥጥር አድርጌ ደህንነታቸውና ጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብና የመድሃኒት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር አውዬ አስወገድኩ አለ

የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በመግቢያና መውጫ ኬላዎች ባደረገው ቁጥጥር ከ3 ሺ 187 ቶን በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው፣ በጉዞ ወቅት የተበላሹና የአምራች ድርጅታቸው ስም የማይታወቁ የምግብ፣ ጥሬ ዕቃ፣ ሩዝ፣ አኩሪ አተርና ዘይት መያዙን ተናግሩዋል፡፡

ከ44 ሜትሪክ ቶን በላይ የተበላሸ ስኳር፣ የጥራትና ደህንነት መጓደል ያለባቸው የምግብ ምርቶችም ይዤ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡና አጣርቼ እንዲወገድ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡የፈዋሽነት፣ የደህንነትና የጥራት ደረጃቸውን የማያሟሉ ሃያ ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺ ብር በላይ የሚገመቱ መድሃኒቶች የህክምና መሳሪያዎችና የመዋቢያ ምርቶችንም፣ በመግቢያና መውጫ ኬላዎች እንዲሁም በኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ወቅት በቁጥጥር ስር በማዋል እንዲወገዱ ማድረጉንም ጠቅሷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በ17 መግቢያና መውጫ ኬላዎች ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የመድሃኒትና የምግብ ምርቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸው እንዲሁም የመድሃኒቶችን ፈዋሽነት በማረጋገጥ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ፈቃድ በመስጠትና በመቆጣጠር ስራዬን ከምን ጊዜውም በተሻለ መልክ አጠናክሬ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 30፣2011/ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በግጭቶች ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ያልተከታተሉ ተማሪዎች የብሔራዊና ክልላዊ ፈተናዎችን ለመፈተን ዝግጁ አይደሉም ሲል የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተናገረ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በግጭቶች ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ያልተከታተሉ ተማሪዎች የብሔራዊና ክልላዊ ፈተናዎችን ለመፈተን ዝግጁ አይደሉም ሲል የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተናገረ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ አለም አቀፉ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ቀን በአለም ለ72ኛ በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ ዛሬ ይከበራል

ዕለቱ በአለም ዙሪያ ፍቅር በሚል መሪ ቃል በሀገር ቤት ደግሞ ሠብዓዊነት ለሰላም በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ሰምተናል፡፡የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመታደግ ሰላም ያለውን ፋይዳ የምናሳይበት ዕለት ነው ሲል በላከልን መግለጫ ጠቅሷል፡፡

በሀገሪቱ 3 ሚሊዬን የሚሆኑ ዜጎች በተፈናቀሉበት በዚህ ወቅት ዕለቱ መከበሩም የሰብዓዊነትን አላማ ከፍ አድርጎ ለማሳየት ይረዳ ሲል ማህበሩ በመግለጫው አስፍሯል፡፡የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሀገሪቱ ያሉትን የ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን አባላት ቁጥር ለማሳደግ ውጥን መያዙንም ተናግሯል፡፡የዚሁ ውጥን አካል የሆነ ንቅናቄም ዛሬ በይፋ ይጀመራል ብሏል ማህበሩ፡፡ 

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ የጫኑትን ብረት በመቀነስ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል የተጠረጠሩ 11 አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጉምሩክ አዋጅ የተደነገገውን የአጓጓዥ ግዴታዎች በመጣስ በቅሸባ ወይም በመቀነስ ድርጊት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩት ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ብረት በማጓጓዝ የተሰማሩ 11 አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡የገቢዎች ሚኒስቴር እንደተናገረው ግለሰቦቹ የተያዙት በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በድምሩ 3 ሺህ 700 ኪሎ ግራም ብረት ቀንሰዋል ተብሏል፡፡በአንድ ድርጅት ስም ከጅቡቲ አዲስ አበባ እንዲገባ ፍቃድ የተሰጠውን የላሜራ ብረት በማጓጓዝ ላይ የነበሩ አሽከርካሪዎች የላሜራ ብረቱን በመንገድ ላይ በመቀነስ የሚዛን ልዩነት እንዳያመጣባቸው በተቀነሰው ብረት ምትክ ድንጋይ ከ200 ሊትር በላይ ውሃ እንዲሁም እስከ 20 ኩንታል የሚሆን ከሰል ጭነው ተደርሶባቸዋል፡፡በዚህ ጥርጣሬም በቁጥጥር ስር ውለው ለተጨማሪ ምርመራ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ እንደተላለፉ ከገቢዎች ሚኒስቴር ገፅ ላይ ተመልክተናል፡፡

አስፋው ስለሺ 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 30፣2011/ ሳውዲ አረቢያ 1 ሺ 400 ኢትዮጵያዊያን ከእስር ለቀቀች

ሳውዲ አረቢያ 1 ሺ 400 በእስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ከማረሚያ ቤት የለቀቀቻቸው የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ በምህረት መሆኑንን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቢሮ ሰምተናል፡፡ከእስር የተለቀቁት ኢትዮጵያዊያም ረጅም ጊዜ ተፈርዶባቸው የነበሩ ናቸው ተብሏለ፡፡

በምህረት ከተፈቱ በተጨማሪ በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ ታራሚዎች የእስር ጊዜያቸውን በ75 በመቶ እንደሚቀንሳቸውም የሳውዲ ባለስልጣናት ተናግረዋል ተብሏል፡፡በምህረት ከተፈቱ 1 ሺህ 400 ውስጥ 300 ያህሉ ትላንት ሌሊት አገራቸው መግባታቸው ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 1፣2011/ በድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለማከም በቂ የሆኑ ማዕከላት ባለመኖራቸው ተጎጂዎች በቀላሉ ህይወታቸውን እንዲያጡ እያደረጋቸው ነው ተባለ

በድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለማከም በቂ የሆኑ ማዕከላት ባለመኖራቸው ተጎጂዎች በቀላሉ ህይወታቸውን እንዲያጡ እያደረጋቸው ነው ተባለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 30፣2011/ በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ከወደብ የሚገባው ማዳበሪያ ላይ መስተጓጎል መከሰቱ ተነገረ

በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ከወደብ የሚገባው ማዳበሪያ ላይ መስተጓጎል መከሰቱ ተነገረ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers