• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሚያዝያ 30፣2011/ ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ላጋጠመው የአገልግሎት ማስፋፊያ አንቴናዎች መትከያ ቦታ እጦት መፍትሄ ፍለጋ ከአስተዳደሩ ጋር እየተነጋረግኩ ነው አለ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ላጋጠመው የአገልግሎት ማስፋፊያ አንቴናዎች መትከያ ቦታ እጦት መፍትሄ ፍለጋ ከአስተዳደሩ ጋር እየተነጋረግኩ ነው አለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 30፣2011/ ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፈው ሳምንት ለደም ካንሰር ህሙማን የሚሰጠው የደም ተዋፅኦ እጥረት አጋጥሞኝ ነበር አለ

ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፈው ሳምንት ለደም ካንሰር ህሙማን የሚሰጠው የደም ተዋፅኦ እጥረት አጋጥሞኝ ነበር አለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 30፣2011/ ጣሊያን የቀበረው ወርቅ አለ ተብሎ የተቆፈረው ጉድጓድ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል

ጣሊያን የቀበረው ወርቅ አለ ተብሎ የተቆፈረው ጉድጓድ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ ኢትዮጵያ በበጀት አመቱ 9 ወራት ከልማት አጋሮቿ ያገኘችው ገንዘብ ከጠበቀችው በላይ ነው ተባለ

በ9 ወሩ 4.2 ቢሊየን ዶላር ከልማት አጋሮች መገኘቱ ተነግሯል፡፡ገንዘቡ ከሁለትዮሽና በይነ መንግስታዊ የልማት አጋሮች የተገኘ እንደሆነም ሰምተናል፡፡ተጠብቆ የነበረው 3.4 ቢሊየን ዶላር እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል፡፡የልማት አጋሮቹ ቀደም ሲል ለመስጠት ቃል ከገቡት 2.86 ቢሊየን ዶላሩን በ9 ወሩ ወደ መንግስት ግምጃ ቤት ገቢ ማድረጋቸውንም ዶ/ር እዮብ ዛሬ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ደግሞ ኢትዮጵያ በ9 ወሩ መክፈሏን ሰምተናል፡፡የተለያዩ የታክስ ህጎች እየተሻሻሉ ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ማሻሻያዎቹን ተከትሎ ከ20 እስከ 30 ቢሊየን ብር ተጨማሪ ገቢ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በዘንድሮው የ10ኛና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች ላይ እንደሚቀመጡ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ

1 ሚሊዮን 2 መቶ 75 ሺ 4 መቶ 65ቱ የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ሲሆኑ የተቀሩት 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው ብሏል፡፡ የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2 ሺ 866 የፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን የ12ኛ ክፍሉ ደግሞ በ1 ሺ 66 የፈተና ጣቢያዎች ይሰጣል፡፡

ከፊታችን ግንቦት 21 እስከ ግንቦት 30 የሚሰጡትን ብሔራዊ ፈተናዎችን ለመስጠት ከ66 ሺ 6 መቶ በላይ የጣቢያ ሀላፊዎች፣ ተቆጣጣሪዎችና ፈታኝ መምህራን እመድባለሁ ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር፡፡የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 5 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ/ም እንደሚሰጥም ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

በመላው አገሪቱ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ትምህርታቸውን በአግባቡ የማይከታተሉ በርካታ ተማሪዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ይህንን የተመለከተው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትም ክልላዊና ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የማካካሻ ትምህርት ተሰጥቷቸው ለፈተና እንዲቀመጡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣ 2011/ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ ተከበረ

ማህበሩ ዛሬ 50ኛ ዓመቱን ቢያከብርም በዝግጅቱ ግን ብዙ ጥሪ የተደረገላቸው አንግዶች ያልተገኙበት ሆኖ ተከብሯል፡፡የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር የዛሬ 50 ዓመት በሶስት ጋዜጠኞች መቋቋሙንም በዝግጅቱ ላይ ሰምተናል፡፡ማህበሩ ሲመሰረት የጋዜጠኝነትን ሞያ ማሳደግ፣ ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት፣ የጋዜጠኞችን መብት እና ጥቅም ማስከበር እንዲሁም ለፕሬስ ነፃነት መታገልን ዓላማው አድርጎ እንደተነሳ ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር በ50 ዓመታት ጊዜው ለዋና ዋናዎቹ የመንግስት መገናኛ ብዙኋን የሙያ መሳሪያዎችንና ቁሳቁሶች በመለገስ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል ተብሏል፡፡ማህበሩ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ያደረገው ጥረት ደካማ እንደነበርም በዛሬው የማህበሩ 50ኛ ዓመት በዓል አከባበር ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡ ለማህበሩ መስራች አባል ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑት ማዕረጉ በዛብህ እና የመጀመሪያው የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ከበደ አደይ ተገኝተዋል፡፡ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡ማህበሩ 450 አባላት አሉኝ ሲልም ተናግሯል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ ለ2020 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ያመለከታችሁ ውጤታችሁን ከዛሬ ጀምሮ ማየት ትችላላችሁ ተብላችኋል

የአሜሪካ መንግስት በሚያዘጋጀው ነፃ የቪዛ እድል ለመጠቀም ዲቪ ሎተሪ ሞልተው የሚጠባበቁ ኢትዮጵያውያን እድለኛ መሆናቸውን ከዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ማወቅ ይችላሉ ተብሏል፡፡አመልካቾች ፎርም በሞሉበት ጊዜ የተሰጣቸውን የማረጋገጫ ኮድ በማስገባት ውጤቱን መመልከት እንደሚችሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተናግሯል፡፡በዚህም የዲቪ ሎተሪ እድለኛነታችሁን ለማወቅ dvlottery.state.gov ድረ ገፁ ላይ በመግባት ማረጋገጥ ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡የዲቪ ሎተሪ እድለኛነትን ማረጋገጥ የሚቻለው በዚህ ድረ ገፅ በመግባት ብቻ መሆኑንም ኤምባሲው አሳስቧል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ “ኢትዮጵያ ሰብዓዊነት ለሰላም” በሚል የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ቀንን ልታከብር ነው

“ኢትዮጵያ ሰብዓዊነት ለሰላም” በሚል የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ቀንን ልታከብር ነው፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ሀይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ወንድም ሕዝቦች ያለ ምንም ስጋት ተረጋግተው ሕይወታቸውን እንዲመሩ ለማስተማመን የተጠራው ኮንፍረስ ዛሬም በክልሉ 334 ወረዳዎች ቀጥሏል

በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ወንድም ሕዝቦች ያለ ምንም ስጋት ተረጋግተው ሕይወታቸውን እንዲመሩ ለማስተማመን የተጠራው ኮንፍረስ ዛሬም በክልሉ 334 ወረዳዎች ቀጥሏል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ንጋቱ ረጋሣ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ ባለፉት አመታት ሕዝብ ያፈናቀሉና ያንገላቱ የቀድሞ ሹሞችና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአለም አቀፉ የፖሊስ ድርጀት ኢንተርፖል ጋር ጭምር በጋራ እየተሰራ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ተናገረ

እስካሁን 468 ከክልል የካቢኔ አባላት ከእስከ ቀበሌ የስራ ሀላፊ ድረስ ያሉበት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉት የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው፡፡ከ420 የማያንሱ ተጠርጣሪዎችም ገና በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉ ጠቁመዋል፡፡ክትትሉ ግን ቀጥሏል ተብሏል፡፡በወንጀሉ ተሳትፈው ከአገር የወጡትንም ጭምር ህግ ፊት ለማቅረብ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሏቸውን የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የፀጥታ አስከባሪ አባላትን ቁጥር እንደ አብነት ጠቅሰዋል፡፡ ሚኒስትሯ እንዳሉት በአዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ ከተከሰተው ጥቃት ጋር በተያያዘ ከ108 ተጠርጣሪዎች 85 ያህሉ ተይዘዋል፡፡

ከመካከላቸው አንዱ የወረዳ አስተዳዳሪ ሲሆን ሌላ አንድ የፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡ከዜጎች መፈናቀልና ግጭቶችና ጥቃት ጋር በተያያዘ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 23ቱ ከክልል የካቢኔ አባላት እስከ ሚሊሻ ያሉ የፖለቲካና የፀጥታ አስከባሪ አመራሮች ይገኙበታል ተብሏል፡፡ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት የመስሪያ ቤታቸውን የ9 ወር የስራ ክንውን ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አቅርበው ከአባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ነው፡፡ሸካ አካባቢ ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 10 የፖለቲካ አመራርና የፀጥታ አስከባሪ አባላት ይገኙበታል ብለዋል፡፡

ከጉጂና ጌዲኦ ጋር በነበረው ግጭት ግን 312 ተጠርጣሪዎች ቢለዩም እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት 9 ብቻ ናቸው፡፡ይህም በየደረጃው ያለ የፖለቲካ አመራር ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ስላልሆነ ነው ብለዋል፡፡እስካሁን በትብብር ወንጀለኞችን አሳልፎ እንዲሰጡ ክልሎችን ታግሰናል ያሉት የሰላም ሚኒስትሯ አሁን ግን ይህን ደረጃ አልፈን ከፌደራል መንግስቱ ጋር በመተባበር ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ስምሪት ተጀምሯል ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 29፣2011/ ከኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር በተያያዘ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ነጋዴዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይፋ አደረገ

1ኛ አቶ ክፍሌ አብርሃም ፣ 2ኛ አቶ ደጉ ተካ ፣3ኛ አቶ ዕቁባይ ዮሀንስ ፣4ኛ አቶ ጥጋቡ ኃ/ኢየሱስ እና 5ኛ አቶ ይስሐቅ ወ/ፃድቅ የኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የርብ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ ከነበሩት ከአቶ ሽመልስ ገ/ሥላሴና አቶ አሳየኸኝ ወልዴ ጋር በጥቅም በመመሳጠር፤ የርብ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት ለማቅረብና አገልግሎት ለመስጠት በሚል ሰበብ ያልተገባ ውል በመዋዋል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ስለተጠረጠሩ ክስ እንደተመሰረተባቸው ዐቃቤ ህግ በድረ ገጹ ጠቁሟል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ በልዩ ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡ዐቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ የተመሰረተው የክስ ጭብጥ በችሎቱ ለቀረቡ ተከሳሾች ተነቦ እንዲረዱት እያደረገ ሲሆን ተከሳሾቹም በቀረበው ክስ ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ ተደርጎ ተከሳሾችም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ተፈፀመ የተባለው ወንጀል የዋስትና መብትን የሚያስከለክል በመሆኑ የዋስትና መብት ሊፈቀድላቸው አይገባም በማለት ተቃውሞውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15 ወንጀል ችሎትም በፍርድ ቤቱ ያልቀረቡ ሌሎች ተከሳሾችን የፌደራል ፖሊስ በቀጣይ ቀጠሮ ይዞ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት ለግንቦት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers