• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጥር 29፣2011/ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በውይይትና በምክክር ሊፈቱ ይገባል ተባለ

በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በውይይትና በምክክር ሊፈቱ ይገባል ተባለ፡፡ የማህሌት ታደለን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 29፣2011/ በኢትዮጵያ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የቡና ተክል ያረጀ በመሆኑ ለምርት መጠኑ ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያት ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የቡና ተክል ያረጀ በመሆኑ ለምርት መጠኑ ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያት ነው ተባለ፡፡ ምህረት ስዩም

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 29፣2011/ በኢትዮጵያ የአመራረት ጉድለትና እንከን በተገኘባቸው 17 የምግብ አምራች ድርጅቶች ላይ በተቆጣጣሪው አካል የተለያዩ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ተነገረ

በኢትዮጵያ የአመራረት ጉድለትና እንከን በተገኘባቸው 17 የምግብ አምራች ድርጅቶች ላይ በተቆጣጣሪው አካል የተለያዩ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ተነገረ፡፡ የወንድሙ ሀይሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 29፣2011/ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር እየተወያዩ ነው

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች አልተመዘገቡም፡፡ ውይይቱ ላይም መሳተፍ የለባቸውም ተብሏል፡፡ የየኔነህ ሲሳይን የስልክ ሪፖርት ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ ለአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች እና ለእርቀ ሰላም ኮሚሽኖች አባልነት የተመረጡትን የተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀ

ለአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች እና ለእርቀ ሰላም ኮሚሽኖች አባልነት የተመረጡትን የተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀ፡፡ አባላቱ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 29፣2011/ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ከነአካቴው እንዳይተዋወቅ የሚከለክለው ሕግ ከ3 ወር በኋላ ተፈፃሚ ይሆናል

የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ከነአካቴው እንዳይተዋወቅ የሚከለክለው ሕግ ከ3 ወር በኋላ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡በአልኮል አምራቾችና ማስታወቂያ በሚሰሩ የሚዲያ ተቋማት መካከል የረጅም ጊዜ የማስታወቂያ የውል ስምምነት ሊፈርሙ እንደሚችሉ ታሳቢ በማድረግ የእፎይታ ጊዜ መስጠሩ አስፈላጊ ሆኗል ተብሏል፡፡

በመሆኑም አዋጁ ከፀደቀበት ከትናንት ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 ወር በኋላ በብሮድካስት አማካኝነት የአልኮል ማስታወቂያ ማስነገር የተከለከለ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ከ3 ወር በኋላ የአልኮል መጠጥን ከሎተሪ እጣ ወይም ከሽልማት ጋር በማያያዝ፣ በቢልቦርድ ማስተዋወቅም የተከለከለ ይሆናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ጥር 28፣2011/ ኢትዮጵያ ካለፉት 3 አመታት ወዲህ ከፍተኛ የእዳ ስጋት ካለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ተነገረ

ኢትዮጵያ ካለፉት 3 አመታት ወዲህ ከፍተኛ የእዳ ስጋት ካለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ተነገረ፡፡ የንጋቱ ረጋሣን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 29፣2011/ በኢትዮጵያ ስኬታማ የፌደራል ሥርዓት እንዲኖር በመንግስትና በክልሎች መካከል የሚደረገው የስልጣንና የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ መሆን አለበት ተባለ

በኢትዮጵያ ስኬታማ የፌደራል ሥርዓት እንዲኖር በመንግስትና በክልሎች መካከል የሚደረገው የስልጣንና የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ መሆን አለበት ተባለ፡፡ የቴዎድሮስ ብርሃኑን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 29፣2011/ በሀገራችን እየተገነቡ ያሉ ሆቴሎች ሀገራዊ መልዕክት ይጎላቸዋል ተባለ

በሀገራችን እየተገነቡ ያሉ ሆቴሎች ሀገራዊ መልዕክት ይጎላቸዋል ተባለ፡፡ በአዲስ አበባ የተገነቡ 30 አዳዲስ ሆቴሎች የደረጃ ምዘና ተሰርቶላቸው እንደተጠናቀቀ ሰምተናል፡፡ የአስፋው ስለሺን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ የቤት የግንባታ ዋጋ በመናሩ ምክንያት አሁን ባለው ዋጋ ሲታሰብ 100 ፐርሰንት የቆጠበ የ40/60 ተመዝጋቢ የለም ተባለ

ምዝገባ ሲካሄድ በካሬ ሜትር 3 ሺህ 333 ብር ዋጋ ውል የታሰረ ቢሆንም አሁን የቤቶች ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ውል ባሰሩበት ዋጋ 100 ፐርሰንት የቆጠቡ በባንክ ውስጥ ያስገቡት ገንዘብ አሁን ላለው የቤቶች ዋጋ ስለማይመጥን ተቀባይነት አይኖረውም ተብሏል፡፡የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ ዣንጥራር አባይ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው ለተነሱ ጥያቄዎች ሲመልሱ እንደተናገሩት ቀደም ብሎ 900 የ40/60 ቤቶች የተላለፉት 3 ሺህ 333 ብር በካሬ የነበረው ዋጋ ወደ 4 ሺህ 918 ብር ከፍ ብሎ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አሁን ግን የግንባታ እቃዎችም ስለተወደዱ ዋጋው ከዛም በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል፡፡በመሆኑም ውል ባሰሩበት ዋጋ 100 ፐርሰንት ቆጥበናል ብለው የሚያስቡ ካሉ ስህተት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡አሁን ያለው የቤቶቹን ዋጋ በሚመጥን ደረጃ 100 ፐርሰንት የቆጠበ የ40/60 ተዘምጋቢም የለም ብለዋል፡፡ መመሪያው ለ40/60 ቤቶች 100 ፐርሰንት ለቆጠበ ቅድሚያ እንዲሰጥ ያዛል፡፡ነገር ግን አሁን ባለው ዋጋ ምን ያህል ለቆጠቡ ቤቱ ይተላለፍ ለሚለው የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ላይ ስለመደረሱ ፍንጭ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፣ የአልኮል ማስታወቂያ በቴሌቪዥንና በሬድዮ ማስተዋወቅ የሚቻልበት ሰዓት ከምሽቱ 3 ሰዓት ወደ 5 ሰዓት እንዲሆን ሆኖ እንደገና ተሻሽሏል

የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፣ የአልኮል ማስታወቂያ በቴሌቪዥንና በሬድዮ ማስተዋወቅ የሚቻልበት ሰዓት ከምሽቱ 3 ሰዓት ወደ 5 ሰዓት እንዲሆን ሆኖ እንደገና ተሻሽሏል፡፡የአልኮል መጠጥን በብሮድካስት አማካይነት ለማስተዋወቅ ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ተደንግጎ ቢቀርብም አብዛኞቹ እንደራሴዎች ሙሉ በሙሉ የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት መተዋወቅ የለበትም የሚል ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

በመሆኑም በሬድዮና በቴሌቪዥን የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎችን ማስነገር እንዲከለከል ሆኖ አዋጁ ፅድቋል፡፡በአዋጁ የአልኮል መጠጥን ከሎተሪ እጣ ወይንም ከሽልማት ጋር በማያያዝ እንዲሁም በቢልቦርድ ማስተዋወቅ የሚከለክል አንቀፅም ተካትቶበት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers