• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጥር 28፣ 2011/ በበጀት አመቱ የመጀመሪያው መንፈቅ ለነዋሪዎች ይተላለፋሉ ተብለው የነበሩ ከ44 ሺ በላይ ቤቶች አሁንም ጥንቅቅ ብለው አላለቁም ተባለ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ ዣንጥራር አባይ እንዳሉት በመጀመሪያው ግማሽ አመት ለነዋሪዎች ይሰጣሉ ተብለው ከታቀዱት 44 ሺ 200 ቤቶች መካከል 26 ሺ 480ዎቹ የ20/80፤ 17 ሺ 737ቱ ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው፡፡ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የመስሪያ ቤታቸውን የ6 ወር የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ነው፡፡

ግንባታቸው በአብዛኛው ወደ ማለቁ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የአሳንሰርና የማጠናቀቂያ እቃዎች መግጠም እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መሰረተ ልማት ስራቸው ገና አልተጠናቀቀም ብለዋል፡፡የቤቶቹ ስራ ጥንቅቅ ብለው ባያልቁም በዚህ አመት ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ ግን ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ፡፡በዚህ አመት ለነዋሪዎች የሚተላለፉትም ከመካከላቸው 30 ሺህ የሚደርሱት ቤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ በ2006 ዓ/ም የተጀመሩ የ40/60 ቤቶች በግማሽ አመቱ ሙሉ በሙሉ ግንባታቸው ይጠናቀቃል ተብሎ ውጥን ቢያዝም 84 በመቶ ብቻ መድረሳቸውን ሰምተናል፡፡በ2007 መጨረሻ የተጀመሩ 20 ሺ 932 የ40/60 ቤቶች ግንባታም አሁን 65 በመቶ መድረሱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ከእንደራሴዎቹ ለቀረቡላቸው የተለያዩ ጥያቄዎችም ምላሽ ሲሰጡ አርፍደዋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደ ባለው 4ኛ የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡አዋጁን የአልኮል መጠጥን በብሮድካስት አማካይነት ከምሽቱ 3 ሰዓት በፊት ማስተዋወቅን የሚከለክለውን የረቂቁን አንቀፅ እንደገና አሻሽሎ አቅርቧል፡፡

አዋጁን ለማፅደቅ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የአልኮል ይዘቱ ከ10 በመቶ በታች የሆነ የትኛውም አልኮል በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚቻለው ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት እንዲሆን ሆኖ ተሻሽሏል፡፡የውሳኔ ሀሳቡ ሌሎችንም የረቂቁ አንቀፆችን አሻሽሎ የቀረበ ነው፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች አዳዲስ ሀሳቦችንና ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ ያላቸው ተነሳሽነት አነስተኛ ነው ተባለ

ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች አዳዲስ ሀሳቦችንና ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ ያላቸው ተነሳሽነት አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ ቴዎድሮስ ብርሃኑ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከግል ባለሀብቶች ጋር በመሆን በሰፋፊ የልማት ስራዎች የመሰማራት እቅድ እንዳለው እወቁልኝ አለ

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከግል ባለሀብቶች ጋር በመሆን በሰፋፊ የልማት ስራዎች የመሰማራት እቅድ እንዳለው እወቁልኝ አለ፡፡ የንጋቱ ረጋሣን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ ለአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እና ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ተሰየሙለት

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመለመሉ እጩዎች ሹመት እንዲፀድቅ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ለዘመናት ለቁርሾና ለግጭት ምክንያት የሆኑትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ችግሮችን በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ በምክር ቤቱ ለተቋቋመው ኮሚሽን 41 አባላት ለሹመት ቀርበውለታል፡፡

የሃይማኖት አባቶች ፣ ምሁራን ፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ፣ ጋዜጠኞች ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ ፖለቲከኞችና የህግ ባለሙያዎች ይገኙበታል፡፡ ከመካከላቸው ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ፣ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ ፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅያስ አሰፋ ፣ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ፣ አቶ ኦቦንግ ሜቶ ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፣ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ፣ ፕሮፌሰር  መረራ ጉዲና ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከአባላቱ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያዊያን መካከል ለአመታት የቆየውን የቂም በቀል ስሜት በእርቀ ሰላም ለመሻር ይሰራል ለተባለው ለእርቀ ሰላም ኮሚሽንም 42 አባላት ተሰይመውለታል፡፡

ከመካከላቸውም የሃይማኖት አባቶች ፣ አትሌቶች ፣ ምሁራን ፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፣ የህግ ባለሙያዎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ አባ ገዳዎች ፣ ፖለቲከኞች እና በጎ አድራጊዎች ይገኙበታል፡፡

የአገር እርቅና ስምምነትን ያወርዳሉ ተብለው ከተሰየሙ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት መካከል ምፁህ አቡነ አብርሃም ፣ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ፣ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር እድሪስ ፣ መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ ፣ ዶ/ር ምህረት ደበበ ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፣ተዋናይ ደበበ እሸቱ ፣ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ፣ አቶ አባተ ኪሾ ፣ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የአባላቱ ሹመት በምክር ቤቱ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/በህገወጥ መንገድ ወደ የመን በመጓዝ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ባጋጠማቸው የጀልባ መገልበጥ አደጋ 57ቱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ

57ቱ ኢትዮጵዊያን በጀልባ መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት ጥር 21 ቀን 2011 እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ቢሮ እንዳለው አደጋው የደረሰው በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ አቦክ በምትባል አስተዳደራዊ ክልል በሚገኝ ጎዶሪያ በሚል ስፍራ ነው ብሏል፡፡እስካሁን በተገኘው መረጃ መሰረት በአደጋው 57 ኢትዮጵያዊያን እና የመናዊ ዜጋ የሆነ የጀልባው ካፒቴን ሕይወታቸውን ያለፈ ሲሆን ሁሉም ጎደሪያ በሚባለው ስፍራ ቀብራቸው ተፈፅሟል ሲል ቃል አቀባይ ቢሮ ተናግሯል፡፡

ሕይወታቸው ማለፉ ከተረጋገጠው 57 ኢትዮጵያዊያን ሌላ 16 በሕይወት መትረፋቸው ተረጋግጧል የተባለ ሲሆን ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር እና ስደተኞች ድርጅት ጋር በመሆን ህክምና ተደርጎላቸው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ከዚህ አደጋ የተረፉትን ጨምሮ 347 የሚሆኑ ሌሎች ወደ የመን ሊጓዙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ስለ አደጋው አስከፊነት ከተነገራቸው በኋላ በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ወስነዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ህይወታቸው ላጡ 57 ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እመኛለሁ ብሏል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ እስከ ሁለት ሺ ግድም መታወቂያ ያለአግባብ ወጥቶ ተሰጥቷል ተብሏል የቢሮው ሀላፊዎች ሲጠየቁ መልስ መስጠት አልፈለጉም

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ እስከ ሁለት ሺ ግድም መታወቂያ ያለአግባብ ወጥቶ ተሰጥቷል ተብሏል የቢሮው ሀላፊዎች ሲጠየቁ መልስ መስጠት አልፈለጉም ተህቦ ንጉሴ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 28፣2011/ከኮሪያ የመጡ የልብ ሐኪሞች ለኢትዮጵያውያን የልብ ህሙማን ነፃ ህክምና ሰጡ ተባለ

ከቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደሰማነው ኮሪያውያኑ ሐኪሞች ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ለ5 ተከታታይ ቀኖች ነፃ የልብ ህክምና ሰጥተዋል፡፡የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊው አቶ አሸናፊ አምብሬ እንደተናገሩት ኮሪያውያኑ ሐኪሞች በውጪ ሃገር ህክምና ከፍተኛ ወጪ ያስወጣ ለነበረው የልብ ህመም ነፃ ህክምና የሰጡ ሲሆን 10 ሰዎች የነፃ ህክምናው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ሆስፒታሉ ወደፊትም በነፃ ህክምና የሚሰጡ የውጪ ሀገር ሀኪሞችን ይጋብዛል ሲሉ አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/በአዲስ አበባ ካወጡት ፈቃድ የተቃረነ ተግባር ሲያከናውኑ የተገኙ 120 ያህል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቶች ፈቃዳቸው ታገደ

በአዲስ አበባ ካወጡት ፈቃድ የተቃረነ ተግባር ሲያከናውኑ የተገኙ 120 ያህል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቶች ፈቃዳቸው ታገደ፡፡ የበየነ ወልዴን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 16.71 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 16.71 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ፡፡ከዚህም ውስጥ 63.2 በመቶው ገቢ የተገኘው ከሞባይል ተጠቃሚዎች ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው በጊዜ ማዕቀፉ 20.86 ቢሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን የእቅዱን 80.1 በመቶ፣ 16.71 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

በስድስት ወራት ውስጥም ለመንግስት ግብር 4 ቢሊዮን ብር መክፈሉን ተናግሯል፡፡አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥርም 41.1 ሚሊዮን ደርሷል ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህም ውስጥ አብዛኛው ወይንም 39.54 ሚሊዮን የሞባይል ድምፅ ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የዛሬ ስድስት ወር ከፍተኛ ስጋት ላይ ነበር የሚለው የተቋሙ መግለጫ፣ በተሰሩ ስራዎች ከስጋት ወጥቶ ወደ ተረጋጋና ጤናማ አካሄድ ደርሷል ተብሏል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/በኢትዮጵያ ያለው የካንሰር ህክምና ደካማነት የተነሳ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ዜጎች በበሽታው ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ

ከቲቢ እና ወባ በሽታዎች ይልቅም በካንሰር ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡የበሽታው ስርጭትና የሚያደርሰው ጉዳት ከሌሎች ዓለማት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሀ አገራት ላይ ይበረታል ተብሏል፡፡ ህሙማኑ የካንሰር ተጠቂ እንደሆኑ የሚያውቁት እጅግ ዘግይተው በመሆኑና ለህክምና አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም መምጣታቸው ካንሰርን የመከላከል ስራ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡ዛሬ የጤና ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የአለም የካንሰር ቀንን ምክንያት በማድረግ ባሰናዱት ምክክር ላይ ነው ይሄን የሰማነው፡፡

በኢትዮጵያ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ሰዎች በካንሰር ይያዛሉ፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች 65 ሺ ያህል ሰዎችም ይሞታሉ፡፡ለህክምና የሚሆኑ ግብአቶች አለመሟላት እና የህክምና ተቋማቱ አነስተኛ መሆን ካንሰርን ለመከላል የሚሰራውን ስራ ፈታኝ እንዲሆን እንዳደረገው የጤና ሚኒስትር ድኤታዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማስፋፋት ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በ3 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት ግንባታቸው እየተጠናቀቀ እንደሆነና የህክምና ግብአቶች እየተሟሉላቸው ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/አዳዲሶቹ 11 ዩኒቨርስቲዎች የሚያስፈልጋቸው የላብራቶሪ ቁሳቁስ ስላልተሟላላቸው ተማሪዎች ተግባራዊ ትምህርት ለመቅሰም ወደ አጎራባች ዩኒቨርስቲዎች እየሄዱ እንዲሰለጥኑ መወሰኑ ተሰማ

ባለፈው አመት በታህሳስ ወር ትምህርት የተጀመረባቸው አዳዲሶቹ ዩኒቨርስቲዎች ሁሉም የላብራቶሪ እቃ እንዳልቀረበላቸው የ11 ዩኒቨርስቲዎች የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተናግሯል፡፡መፍትሄ ተብሎ የተወሰደውም ተማሪዎቹ ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ በአካባቢያቸው በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እየሄዱ መሰልጠን ነው ተብሏል፡፡የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በዩኒቨርስቲዎቹ ላይ ያደረገውን የክዋኔ ኦዲት ግኝት መሰረት አድርጎ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱን የስራ ሀላፊዎች ጠርቶ አነጋግሯል፡፡

ዩኒቨርስቲዎቹ ለምን የላብራቶሪ ቁሳቁስ አልተሟሉላቸው ለሚለው ጥያቄ የበጀት እጥረት በማጋጠሙ ነው ሲሉ የስራ ሀላፊዎቹ መልሰዋል፡፡የላብራቶሪ እቃዎቹን ከውጪ ገዝቶ ለማስገባት 11 ሚሊዮን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ ብር ከ450 ሚሊየን ብር ያላነሰ ገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ይሁንና መንግስት የፈቀደልን 200 ሚሊየን ብር ወይንም ከሚያስፈልገው ከግማሽ በታች ብቻ ነው ብለዋል የስራ ሀላፊዎቹ፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የግንባታ ጽ/ቤቱ ለዩኒቨርስቲዎቹ የዲዛይን ጥናት ከያዘው በጀት የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ብልጫ ያለው ውል ማሰሩን የኦዲት ግኝቱ አሳይቷል፡፡

ለዲዛይን ቁጥጥር አማካሪ ከተያዘው በጀት በ89 ሚሊየን ብር ብልጫ ያለው ውል መግባታቸው ታውቋል፡፡እንዲሁም የ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የካሳ ክፍያ የተከፈለበት የሰነድ ማስረጃ አለመገኘቱን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ያሳያል፡፡ በኦዲቱ የተገኘው የገንዘብ ልዩነትና ግድፈቶች መስተካከል ይጠበቅባቸዋል፡፡በመሆኑም ስለተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች የአስራ አንዱ ዩኒቨርስቲዎች የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የስራ ሀላፊዎች የተጠየቁ ሲሆን ምላሽም የሚሰጡ ይሆናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers