• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጥር 27፣2011/በአዲስ አበባ ካወጡት ፈቃድ የተቃረነ ተግባር ሲያከናውኑ የተገኙ 120 ያህል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቶች ፈቃዳቸው ታገደ

በአዲስ አበባ ካወጡት ፈቃድ የተቃረነ ተግባር ሲያከናውኑ የተገኙ 120 ያህል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቶች ፈቃዳቸው ታገደ፡፡ የበየነ ወልዴን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 16.71 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 16.71 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ፡፡ከዚህም ውስጥ 63.2 በመቶው ገቢ የተገኘው ከሞባይል ተጠቃሚዎች ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው በጊዜ ማዕቀፉ 20.86 ቢሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን የእቅዱን 80.1 በመቶ፣ 16.71 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

በስድስት ወራት ውስጥም ለመንግስት ግብር 4 ቢሊዮን ብር መክፈሉን ተናግሯል፡፡አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥርም 41.1 ሚሊዮን ደርሷል ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህም ውስጥ አብዛኛው ወይንም 39.54 ሚሊዮን የሞባይል ድምፅ ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የዛሬ ስድስት ወር ከፍተኛ ስጋት ላይ ነበር የሚለው የተቋሙ መግለጫ፣ በተሰሩ ስራዎች ከስጋት ወጥቶ ወደ ተረጋጋና ጤናማ አካሄድ ደርሷል ተብሏል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/በኢትዮጵያ ያለው የካንሰር ህክምና ደካማነት የተነሳ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ዜጎች በበሽታው ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ

ከቲቢ እና ወባ በሽታዎች ይልቅም በካንሰር ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡የበሽታው ስርጭትና የሚያደርሰው ጉዳት ከሌሎች ዓለማት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሀ አገራት ላይ ይበረታል ተብሏል፡፡ ህሙማኑ የካንሰር ተጠቂ እንደሆኑ የሚያውቁት እጅግ ዘግይተው በመሆኑና ለህክምና አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም መምጣታቸው ካንሰርን የመከላከል ስራ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡ዛሬ የጤና ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የአለም የካንሰር ቀንን ምክንያት በማድረግ ባሰናዱት ምክክር ላይ ነው ይሄን የሰማነው፡፡

በኢትዮጵያ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ሰዎች በካንሰር ይያዛሉ፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች 65 ሺ ያህል ሰዎችም ይሞታሉ፡፡ለህክምና የሚሆኑ ግብአቶች አለመሟላት እና የህክምና ተቋማቱ አነስተኛ መሆን ካንሰርን ለመከላል የሚሰራውን ስራ ፈታኝ እንዲሆን እንዳደረገው የጤና ሚኒስትር ድኤታዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማስፋፋት ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በ3 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት ግንባታቸው እየተጠናቀቀ እንደሆነና የህክምና ግብአቶች እየተሟሉላቸው ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/አዳዲሶቹ 11 ዩኒቨርስቲዎች የሚያስፈልጋቸው የላብራቶሪ ቁሳቁስ ስላልተሟላላቸው ተማሪዎች ተግባራዊ ትምህርት ለመቅሰም ወደ አጎራባች ዩኒቨርስቲዎች እየሄዱ እንዲሰለጥኑ መወሰኑ ተሰማ

ባለፈው አመት በታህሳስ ወር ትምህርት የተጀመረባቸው አዳዲሶቹ ዩኒቨርስቲዎች ሁሉም የላብራቶሪ እቃ እንዳልቀረበላቸው የ11 ዩኒቨርስቲዎች የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተናግሯል፡፡መፍትሄ ተብሎ የተወሰደውም ተማሪዎቹ ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ በአካባቢያቸው በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እየሄዱ መሰልጠን ነው ተብሏል፡፡የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በዩኒቨርስቲዎቹ ላይ ያደረገውን የክዋኔ ኦዲት ግኝት መሰረት አድርጎ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱን የስራ ሀላፊዎች ጠርቶ አነጋግሯል፡፡

ዩኒቨርስቲዎቹ ለምን የላብራቶሪ ቁሳቁስ አልተሟሉላቸው ለሚለው ጥያቄ የበጀት እጥረት በማጋጠሙ ነው ሲሉ የስራ ሀላፊዎቹ መልሰዋል፡፡የላብራቶሪ እቃዎቹን ከውጪ ገዝቶ ለማስገባት 11 ሚሊዮን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ ብር ከ450 ሚሊየን ብር ያላነሰ ገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ይሁንና መንግስት የፈቀደልን 200 ሚሊየን ብር ወይንም ከሚያስፈልገው ከግማሽ በታች ብቻ ነው ብለዋል የስራ ሀላፊዎቹ፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የግንባታ ጽ/ቤቱ ለዩኒቨርስቲዎቹ የዲዛይን ጥናት ከያዘው በጀት የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ብልጫ ያለው ውል ማሰሩን የኦዲት ግኝቱ አሳይቷል፡፡

ለዲዛይን ቁጥጥር አማካሪ ከተያዘው በጀት በ89 ሚሊየን ብር ብልጫ ያለው ውል መግባታቸው ታውቋል፡፡እንዲሁም የ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የካሳ ክፍያ የተከፈለበት የሰነድ ማስረጃ አለመገኘቱን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ያሳያል፡፡ በኦዲቱ የተገኘው የገንዘብ ልዩነትና ግድፈቶች መስተካከል ይጠበቅባቸዋል፡፡በመሆኑም ስለተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች የአስራ አንዱ ዩኒቨርስቲዎች የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የስራ ሀላፊዎች የተጠየቁ ሲሆን ምላሽም የሚሰጡ ይሆናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“አንተ ከነሃሳብህ ትበተናለህ እንጂ ኢትዮጵያ አትበታተንም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን በተካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ወቅት ከጥናት ፅሁፍ አቅራቢዎች መካከል አንደኛው ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ዲሞክራሲዊ ባህል በኢትዮጵያ” በሚል ፅሁፋቸው “አንተ ከነሐሳብህ ትበተናለህ እንጂ ኢትዮጵያ አትበታተንም” ብለዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፅሁፍ ተመልክቶታል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በየቦታው እየተሰሩ ያሉ የመስሪያ ቦታዎች (ሼዶች) ጉዳይ

በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ለምርት መስጫ የሚሆኑ መጠለያዎች ተገንብተው እድል ለደረሳቸው ነዋሪዎች ተላልፈዋል፡፡ ነገር ግን ቀድመው የያዙት ስራቸውን ሲያሳድጉና ለሌሎች ሲያስረክቡ አይታይም፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የሚቆጣጠረው አካል ቸል ብሏል ተብሎ ተተችቷል፡፡ አሁንም መጠለያዎቹ መሰራታቸው አላቋረጠም ለመሆኑ ግንባታው ማን እንደሚመራው ይታወቃል? ማስተር ፕላኑን ተከትለው የሚሰሩ ናቸው? የምህረት ስዩም ዝግጅት ይህን ይመለከታል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/የጊዳቦ ግድብ በትናንትናው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተመረቀ

የጊዳቦ ግድብ በትናንትናው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተመረቀ፡፡ የየኔነህ ሲሳይን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/ቀይ መስቀል ከቀያቸው ተፈናቅለው በምስራቅ ወለጋ ላሉ አባወራዎች ድጋፍ እያደረግኩ ነው አለ

ቀይ መስቀል ከቀያቸው ተፈናቅለው በምስራቅ ወለጋ ላሉ አባወራዎች ድጋፍ እያደረግኩ ነው አለ፡፡ የወንድሙ ኃይሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 27፣2011/በአዲስ አበባ ለከባድ መኪናዎች ጊዜያዊ የመኪና ማቆሚያዎች እየተሰሩ ነው ተባለ

በበአዲስ አበባ ለከባድ መኪናዎች ጊዜያዊ የመኪና ማቆሚያዎች እየተሰሩ ነው ተባለ፡፡ የወንድሙ ኃይሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ምርጫው ይራዘም ወይስ በጊዜው ይካሄድ?

በኢትዮጵያ በየአምስት አመቱ የሚደረገው የምርጫ ጊዜ የቀረው ከ15 ወራት በታች ነው፡፡ በእነዚህ ወራት ምርጫውን አዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ያስቸግራል የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ካልተሻሻለና አስተማማኝ ካልሆነ ምርጫ ለማካሄድ አይቻልም የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በምንም ይሁን በምን፣ ምርጫው በተያዘለት ጊዜ መደረጉ ለቀጣዩ ሰላም ወሳኝ ነው ይላሉ፡፡ የኔነህ ሲሳይ በቅርቡ ከውጭ ወደ ሃገር ቤት ከገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱን ይህንና ሌሎቹንም ጥያቄዎች ጠይቋቸዋ፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 25፣2011/ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ያቀረቡት የጉዲፈቻ ጥያቄ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቷል

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ያቀረቡት የጉዲፈቻ ጥያቄ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተቀባይ መሆኑን ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የትዊተር ገጽ ለመረዳት ችለናል፡፡የቀዳማዊቷ እምቤት ጥያቄ እንደሌሎች ባለጉዳዮች በፍርድ ቤት ቀርቦ መስተናገዱ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል የመሆኑን መርህ የሚያንፀባርቅ ነው፣ የፍርድ ቤቱ ተልእኮም የመንግሥት ሃላፊዎችን ጨምሮ ሁሉንም ሰው በሕግ ፊት በእኩል በመዳኘት የህግ የበላይነትን ማስከበር ነው ብለዋል ፕሬዝደንቷ በመልዕክታቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሕፃናት የሐገር መሰረት መሆናቸውን በመረዳት አሳዳጊ ወላጅ የሌላቸውን ሕፃናት የማሳደግና ለሐገር የሚጠቅሙ አድርጎ መቅረፅ የሁሉም ዜጋ ሐላፊነት ነው፤ በዚህም ረገድ ቀዳማዊው ቤተሰብ ምሳሌያዊ እርምጃ መውሰዱ የሚበረታታ ነው ማለታቸውን ተመልክተናል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers