• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ግብይት ሲፈፅሙ ነበር የተባሉ 15 ድርጅቶችና ተቋማት ላይ እጅ ከፍንጅ ደረስኩባቸው አለ

የገቢዎች ሚኒስቴር ዛሬ በመስሪያ ቤቱ ባለፈው የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በሚኒስቴሩ የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ዘመዴ ተፈራ ናቸው መግለጫውን የሰጡት፡፡በመግለጫቸውም ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈፅሙ የነበሩ 15 ድርጅቶችን በ18 ቦታዎች ላይ በዘመቻ በተደረገ ምርመራ በደረሰኝ ግብይት እንደማይፈፅሙ ደርሰውባቸው እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

35 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል፡፡ከእነዚህም አብዛኛዎቹ ድርጅቶች በአጠቃላይ ንግድ፣ በአስመጪና ላኪ፣ በካፌ እንዲሁም በሆቴል ስራዎችና በመሳሰሉት ዘርፎች እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡በተለይም ምስራቅ ፒ.ኤል.ሲ የተባለ አምራች ድርጅት በአራቱም ቅርንጫፎቹ ደረሰኝ ሳይቆርጥ ግብይት ሲፈፅም መያዙን የተናገሩት አቶ ዘመዴ፤ ደሚር የተባለ ድርጅት ደግሞ ጠዋት ተይዞ ከሰዓትም በተመሳሳይ የማጭበርበር ድርጊት ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ይዘነዋል ብለዋል፡፡
ከእነዚህ ከተያዙት 15 ድርጅቶች ውስጥ ስምንቱ ተመላሽ የጠየቁ ናቸው ሲሉ አቶ ዘመዴ ተናግረዋል፡፡

ያለ ደረሰኝ የሚደረግ ግብይት መጠኑ ስለማይታወቅ የእነዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፃሚዎች ያደረሱት ኪሳራ አልታወቀም ሲሉ ተናግረዋል፡፡አብዛኛዎቹ የማጭበርበር ስራዎች በተቀጣሪ መሰራታቸው ከባለቤቶቹ እውቅና ውጪ ስለሚሆን ተቋማት ሰራተኞቻቸውን በሚቀጥሩበት ወቅት አጣርተው ማወቅና መፈተሽ ይገባቸዋልም ብለዋል አቶ ዘመዴ፡፡በቀጣይ ክትትላችንን አጠናክረን በመቀጠል ህጋዊ ነጋዴውን የማሳወቅ እና የማስተማር ስራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በ9 ወራት እድሳቱ ይጠናቀቃል ተብሎ አመታትን የዘገየው የአንበሳ ግቢ እድሳት በቅርቡ ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል ተባለ

ለ2 አመት የዘገየው አንበሳ ግቢ በአዲሱ ስሙ (አዲስ ዙ ፓርክ) በሚል በቅርቡ አገልግሎት ይሰጣችኋል ተብላችኋል፡፡ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት አቁሞ የነበረው (የአዲስ ዙ ፓርክ) በውስጡ 10 አናብስት፣ (6 ሴትና 4 ወንድ) ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ኤሊ፣ የአእዋፍ ዝርያዎችና ሌሎች እንስሳት ያሉት እንደሆነ ይታወቃል፡፡በእድሳቱ ምክንያት አገልግሎቱን ካቆመ በኋላ 7 አናብስት በህክምና እና በምግብ እጥረት መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ያሉትም ቢሆን በምግብ እጥረት ከስተውና ተጎሳቁለው እንደነበር ከዚህ ቀደም ነግረናችኋል፡፡ባለፉት ጥቂት ወራትም የፓርኩን አሰራር በመቀየርና የእንስሳቱን አመጋገብ በማዘመን ከስተው ለበሽታም እየተጋለጡ የነበሩ እንስሳት አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሰምተናል፡፡ በቅርቡ ስራ ይጀምራል የተባለው “አዲስ ዙ ፓርክ” የንግድ ሱቆች፣ ምግብ ቤት፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የአእዋፍ ዝርያዎች ማሳያ ወስከምት (ኬጅ) ተገንብተውለታል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የስራ ሀላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ፡፡

ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል፡፡ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል ነው ተብሏል፡፡ዘርፉ እየተለየ ምርመራ የማድረግና ተጠያቂዎችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የ100 ቀን እቅድ አውጥቶ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በሚሰሩበት ወቅት በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩን ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅን እና አቶ ተስፋዬ ገብረፃድቅን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክሩ ሰነዶችን አሽሽተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በሚሰሩበት ወቅት በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩን ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅን እና አቶ ተስፋዬ ገብረፃድቅን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክሩ ሰነዶችን አሽሽተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ…ንጋቱ ሙሉን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በድሬዳዋ ከተማ የሁለት ሰዎች ሕይወት ስለጠፋበት ግጭት

በድሬዳዋ ከተማ የሁለት ሰዎች ሕይወት ስለጠፋበት ግጭት ንጋቱ ሙሉ ያዘጋጀውን እንድታዳምጡ እንጋብዛለን…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች አስተያየት:- ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸውን በተመለከተ

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸውን በተመለከተ የኔነህ ሲሳይ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ሀላፊን አቶ አፍሬም ማዴቦን፣ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ አካሉን እንዲሁም የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታን አናግሯቸዋል - በቅደም ተከተል ይቀርባል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በተለያዩ የምጣኔ ሀብት ክንውኖች በመሳተፍ ማህበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚቻል ተነገረ

በተለያዩ የምጣኔ ሀብት ክንውኖች በመሳተፍ ማህበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚቻል ተነገረ፡፡ የማህሌት ታደለን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ህብረተሰቡ ራሱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ማግኘት እንዲችል እየሰራ መሆኑን ተናገረ

ማህበሩ የህክምና ባለሞያዎች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና በስነ ምግባር የተሞላ አገልግሎት ለማህበረሰቡ እንዲሰጡ ተከታታይ ስልጠናዎችን እሰጣለሁ ነው ያለው፡፡የህክምና ማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ሲናገሩ እንደሰማነው ከሆነ የህክምና ዘርፉን ለማሳደግ የሚረዱ ጥናቶች በማህበራቸው በኩል ይሰራሉ፡፡የሐኪሞችን የሙያ ክህሎትና ብቃት ማሳደግ እንዲሁም የሙያ ጥቅማቸውን የማስጠበቅ ዓላማ ያለው ማህበሩ ከተመሰረተ 56 አመታትን አስቆጥሯል፡፡

3 ሺ አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የህክምናው ዘርፍ የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያሉበት ችግሮች ላይ የሚመክር ጉባኤ በየአመቱ ያካሂዳል፡፡ዘንድሮ ለ55ኛው ጉባኤ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 15 እስከ 17 አካሂዳለሁ ብሏል፡፡ለሶስት ቀናት ለሚቆየው ጉባኤ በኢትዮጵያ የህክምና ሙያ ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከማህበሩ ሀላፊዎች ሰምተናል፡፡ከዚህ ጎን ለጎን ወደፊት የአገር ውስጥ የህክምና ትምህርትና የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲኖረው ከመንግስት ጎን ሆኖ የመስራት ውጥን እንዳለው ተናግሯል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ችሎት:- የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ሶስት የአመራር አባላት ጉዳይ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ሶስት የአመራር አባላት የተጠረጠሩበትን ጉዳይ የሚያየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ በዛሬው ችሎቱ ፖሊስ እስከ ዛሬ ያከናወነውን ምርመራ ተመልክቷል፡፡መርማሪ ፖሊስ፣ ከ2004 ጀምሮ የሶማሌ ክልል አሰራርን የተቃወሙ፣ 200 የሚሆኑ የክልሉ ተወላጆች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ከሐምሌ 26 እስከ ሐምሌ 30/2011 ድረስ፣ በዘርና በሃይማኖት እየተለየ፣ በክልሉ የተፈፀመውን ወንጀልና የተቀበሩበትን፣ ከጳውሎስ ሆስፒታል በተወሰደ ባለሙያ አስክሬን ማስመርመሩን፣ በፎቶ ማስረጃ አስደግፎ፣ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

በጅግጅጋና በአካባቢው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ላይ በደረሰ ጉዳት 300 ሚሊየን ብር፣ በክራውን ሆቴል 42 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ ተናግሯል፡፡ፖሊስ፣ የተገደሉ ዜጎች ቤተሰቦችን ለማፈላለግና ተጨማሪ የምርመራ ስራ አልተጠናቀቀልኝም ብሎ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠውም አመልክቷል፡፡ጠበቆች፣ ፖሊስ ተመሳሳይ ምክንያት እያቀረበ ስለሆነ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ብለው ተከራክረዋል፡፡ፍርድ ቤቱም፣ ግራ ቀኙን አዳምጦ የ14 ቀን ጊዜ መስጠቱ ያስፈልጋል ብሎ፣ ለህዳር 27/2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠበቆች ከዚህ በኋላ የአስፈፃሚ ተፅዕኖ ይኖርብናል ብላችሁ እንዳትሰጉ ተብላችኋል

የአስፈፃሚ አካል ተፅዕኖ ጉዳያችንን ያዛባብናል ብለው ጠበቆች እንዳይሰጉ የተናገሩት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ናቸው፡፡በፍርድ ቤት አካባቢ እንደገና ማዋቀር አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ፍርድ ቤቶች የአስፈፃሚውና የሕግ አውጭው ተፅዕኖ የማይደፍቃቸው ሆነው እንዲደራጅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ለአዲስ ዘመን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሀላፊነቱን ሲቀበሉ ለመሪዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ “የፍርድ ቤት ነፃነትን ለማስከበር ሙሉ ነፃነት ይኖራል ወይ ?” የሚለውን እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

“የሃገሪቱ መሪዎች” ይላሉ ወይዘሮ መዓዛ “የሃገሪቱ መሪዎች በዚህ ረገድ ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው ተረድቻለሁ” ብለዋል፡፡የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትነቱን ስራ ከጀመሩ ወዲህ ዳኞችን ሲያነጋግሩ፣ “ስራችንን በነፃነት መስራት አልቻልንም” የሚል አስተያየት እንደሰሙ ጠቅሰዋል፡፡ዳኞቹ ከፖሊስ፣ ከዐቃቤ ሕግ እና ከተለያዩ ቦታ ጫና እንደነበረባቸው መናገራቸውን፤ ወ/ሮ መዓዛ ግን ከዚህ በኋላ የዳኝነትን ነፃነት ለማረጋገጥ ዳኞችም ራሳቸው ለራሳቸው መቆም አለባቸው ይላሉ፡፡“ሲታዘዙ አቤት ከማለት ወጥተው የዳኝነት ነፃነትን ለማስከበር እያንዳንዱ ዳኛም መቆም መቻል አለበት” ብለዋል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ሀብታቸውን አስመዘገቡ

በቢሮው ስር የሚገኙ ተጠሪ መስሪያ ቤቶችም የስራ ኃላፊዎች የሀብት ምዝገባና እድሳት አድርገዋል ተብሏል፡፡ይህ አሰራርም ለሌብነት እና ንቅዘት የሚመቹ መንገዶችን ይዘጋል መባሉ ተሰምቷል፡፡የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እስከ ህዳር 30፣ 2011 ዓ.ም የሀብት ማስመዝገቡ ስራ ይቀጥላል ብሏል፡፡ወሬውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ከላከልን መግለጫ አግኝተነዋል፡፡

ተህቦ ንጉሤ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers