• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከመላው ሐገሪቱ የተውጣጡ 25 ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር...

ከመላው ሐገሪቱ የተውጣጡ 25 ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር ያደረጉበትን የትላንትናውን የሚሊኒየም አዳራሽ ዝግጅት አስመልክቶ አስፋው ስለሺ የሚከተለውን አጠናቅሯል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሚያዝያ 9፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቢቹ ነጋ ነጋ…አቢቹ ሲታወስ ክፍል ሁለት

ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው በፋሺስት ወረራ ዘመን ስሙ የገነነውንና ለዘመናት የተዜመለትን የኢትዮጵያዊውን ጀግና የአቢቹን ታሪክ የዘከረበትን መሰናዶ ሁለተኛ እና የመጨረሻ ክፍል 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ድንቅነሽ የሴቶች ተሀድሶና ማጎልበቻ ማዕከል ለምን ተዘጋ ?

“ዩኒቨርሲቲ ስገባ ነው ሱስ የጀመርኩት - 12ኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ፡፡ 10 ዓመት ሱስ ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡ መጠጥ እና ሲጋራ ነው ዋንኛው ችግሬ፡፡ ጫትና ሐሺሽም ጀምሬ ነበር ግን ወዲያው ነበር የተውኳቸው፡፡ ከተመረቅኩ በኋላ የራሴን ቢዝነስ ጀምሬ ነበር፡፡ ሙሉ ብሬን በመጠጥ አጠፋሁት፡፡ መጠጥ ወደ ኋላ ጎትቶኛል፡፡ ባህሪዬን አሳጥቶኛል፡፡ ጠዋት ላይ ያሰራኛል ብዬ እጠጣለሁ፡፡ ማታ ላይ እንዲያደነዝዘኝ፡፡ ለመተኛት እጠጣለሁ፡፡ ጠጥቼ ተኝቼ ግን ለሊት ላይ እነቃለሁ፡፡ እንደገና ጠጥቼ እተኛለሁ፡፡ በዚህ መልኩ ቆይቼ ጠዋት ላይ እጄ መንቀጥቀጥ ሲጀምር ደነገጥኩ፡፡ ከዚህ ሱስ መውጣት አለብኝ አልኩ…” የምትለው ስሜ ይቅር ያለችን ወጣት ከሱስ መውጣት የቻለችው ሱስ ውስጥ ያሉ ሴቶች ከሱስ እንዲያገግሙ ለመርዳት በተቋቋመው ድንቅነሽ የሴቶች የተሐድሶና ማጎልበቻ ማዕከል ውስጥ ለ3 ወራት ሕክምና ካገኘች በኋላ ነበር…

የመጠጥ ቤት ባለቤት ሆነው በዛው በመጠጥ ሱስ ውስጥ ገብተው የነበሩ እንዲሁም ለሕክምና አገልግሎት የሚውለውን የሰመመን መስጫ በመውሰድ ሱስኛ ሆና የነበረችውም የሕክምና ባለሞያም ከሱሷ የተገላገለችው በዚሁ በድንቅነሽ የሴቶች የተሐድሶና ማጎልበቻ ማዕከል ውስጥ ነበር፡፡

አሳዛኙ ነገር ግን ለበርካታ ሱስ ውስጥ ላሉ ሴቶች ከሱስ የመላቀቅ ተስፋ የነበረው ይህ ማዕከል አሁን ላይ ተዘግቷል…

ለምን?

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቢቹ ነጋ ነጋ…አቢቹ ሲታወስ

ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው በፋሺስት ወረራ ዘመን ስሙ የገነነውንና ለዘመናት የተዜመለትን የኢትዮጵያዊውን ጀግና የአቢቹን ታሪክ የዘከረበትን መሰናዶ የመጀመሪያ ክፍል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሳይንስ መረጃዎች…

የዓለማችን ቋንቋዎች ሁሉ መነሻ ከአንድ አፍሪካዊ እናት ቋንቋ መሆኑ ተደረሰበት ይሉናል ሳይንቲስቶች፡፡ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የዓለማችን 6ሺ ያህል ዘመናዊ ቋንቋዎች እናት የሆነው ቋንቋ ከዛሬ 50 ሺ እስከ 70 ሺ ዓመታት ግድም በአፍሪካ ይነገር የነበረ ነው፡፡

የጥናት ውጤቱ እንደሚለው ይህ የሁሉ እናት የሆነ ቋንቋ ለሰው ልጅ ስልጣኔ፣ ለሰው ልጅ ወደ አዳዲስ አካባቢዎች መፍለስ እንዲሁም ለኪነትና የቴክኖሎጂ ጅማሮ መሰረት ነው፡፡በኒውዝላንዱ የኦክላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ክዊንቲን አትኪንሰን የተሰራው ጥናት እንዳሳየው የሰው ልጅ ንግግር የጀመረው ከዚህ ቀደም ከሚታሰበው ጊዜ ቀደም ብሎ ነው፡፡

ከዚህ ጥናት በፊት የነበሩ መላ ምቶች የዓለማችን ቋንቋዎች መነሻ ከአንድ በላይ ናቸው ይል ነበር፡፡ ይህ የአሁኑ ጥናት ግን የሁሉም የዓለማችን ቋንቋዎች እናት አንድ ነው ባይ ነው፡፡አትኪንሰን በጥናቱ በ504 የዓለማችን ቋንቋዎች ውስጥ ያሉን የተለያዩ ተነባቢ፣ አናባቢ እና መሰል የድምፅ እና ቋንቋ አለባውያን በመውሰድ ጥናቱን አካሂዷል - በዚህም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ያሉ ቋንቋዎች ሁሉ መነሻ አሁን ፈፅሞ የተረሳ በአፍሪካ በድንጋይ ዘመን ወቅት ይነገር የነበረ ጥንታዊ ቋንቋ ነው ይላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በዚህ አመት ይኖራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ እንደማይካሄድ ተነገረ

በዚህ አመት ይኖራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ እንደማይካሄድ ተነገረ፡፡ምርጫው የሚካሄድበት ቁርጥ ያለ ወርና ቀን ባይታወቅም በመጭው አመት 2011 ዓ.ም እንዲካሄድ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የምርጫው ጊዜውን አራዝሞታል፡፡የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም ለምክር ቤቱ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንደሚያስረዳው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለዚሁም ምርጫ የተሟላ ዝግጅት ለማድረግ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ያጋጠሙ የፀጥታ መደፍረስ እንቅፋት ሆኖበት ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የሃገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እስኪሆንና ቦርዱም ዝግጅቱን እስኪያጠናቀቅ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ ለመጪው አመት ተራዝሟል፡፡እስከመጪው የምርጫ ጊዜ አሁን የስልጣን ጊዜያቸውን የጨረሱና በስልጣን ላይ የቆዩ ባለስልጣናት ይቆያሉ ወይንስ ይነሳሉ የሚለው የምክር ቤቱን አባላት ያከራከረ ቢሆንም መልስ ያላገኘ ጥያቄ ሆኖ አልፏል፡፡

የምርጫ ጊዜው ሲራዘም በደፈናው በ2011 ይካሄዳል የሚለው የውሳኔ ሀሳብም የምክር ቤት አባላትን ዘለግ ላሉ ደቂቃዎች ያነጋገረ ጉዳይ ነበር፡፡ገሚሶቹ ከ6 ወር በላይ መራዘም የለበትም በ2011 ዓ/ም እስከ ታህሳስ ወር መካሄድ አለበት የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው ለምርጫው ምቹ ጊዜ እስኪገኝ ድረስ በመጪው አመት ይካሄዳል የሚለው ተይዞ ድምፅ እንዲሰጥበት አድርገዋል፡፡ምርጫውን ለማራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብም በ8 ድምፀ ተአቅቦና በአብላጭ ድምፅ ፀድቋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ሸገር ልዩ ወሬ:- በእኔ የደረሰው በሰው እንዳይደርስ ትራፊክ አስተናብራለሁ

በደረሰበት የመኪና አደጋ ሳቢያ በዊልቸር የሚንቀሳቀሰው የብርጭቆ ሰፈሩ ሀብታሙ ኃይሌ “በእኔ የደረሰው በሰው እንዳይደርስ፣ ወገኖቼ በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን እንዳያጡ፣ አካላቸውን እንዳይጎድል” በሚል ከጠዋት እስከ ማታ በየቀኑ የሰፈሩን መኪኖች በራሱ ተነሳሽነት እንደ ትራፊክ ያስተናብራል…

ፊቱ ላይ ዘወትር ደስታ የሚነበብበት ሃብታሙ ይህን የመኪኖች ማስተናበር ስራውን ሲሰራ 9 ዓመት አልፎታል፡፡ጠጥታችሁ አታሽከርክሩ፣ ፍጥነት አደጋ ያመጣል፣ እግረኞችም በዜብራ ማቋረጥን ልምድ አድርጉ ሲል ይመክራል ሃብታሙ፡፡

እስከ 7ኛ ክፍል የተማረውና ከአባቱና ከወንድሙ ጋር የሚኖረው ሃብታሙ አሸከራካሪዎች በሚሰጡት አንድም ሁለት ብር ነው ኑሮውን የሚገፋው፡፡የወንድሙ ኃይሉን የልዩ ወሬ ዘገባ ተከታተሉ…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚመለከተው HR 128 ውሳኔ በአሜሪካ ኮንግረስ ትላንትና በሙሉ ድምጽ ያለምንም ተቃውሞ መፅደቁ ተሰማ

የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚመለከተው  HR 128 ውሳኔ በአሜሪካ ኮንግረስ ትላንትና በሙሉ ድምጽ ያለምንም ተቃውሞ መፅደቁ ተሰማ፡፡በምክር ቤቱ የፀደቀውን ውሳኔ 128ን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ሀላፊዎች ውሳኔውን አስገዳጅነትን ያልያዘ በጣም ቀላል የሆነ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ HR 128 ውሳኔ የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊን ሥርዓትን በቻለው መጠን ለማሳደግ በሚጥርበት በዚህ ወቅት መተላለፉ ጊዜውን ያልጠበቁና ተገቢነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡በአሜሪካ መንግስት ኮንግረስ በሙሉ ድምፅ የፀደቀው  HR 128 ውሳኔ በኢትዮጵያ መንግስት የስራ ሀላፊዎች እንደሚባለው እርግጥ ጉዳት አያመጣም ወይ ሲል ሸገር የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩን ዶ/ር መራራ ጉዲናን ጠይቋል፡፡

HR 128 የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታና አጠቃላይ አስተዳደርን ከአሜሪካ ፖሊሲ ጋር ለማቃናት ታልሞ የተዘጋጀ የውሳኔ ሀሳብ መሆኑንም ተሰምቷል፡፡HR 128 የውሳኔ ሀሳብ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ክብር የቆመ ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካን የኮንግረስ አባላት ሙሉ ድምፅ ትላንትና መፅደቁ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎች የውሳኔ 128ን በአሜሪካ ኮንግረስ መፅደቅን በሚመለከት ሙሉና ዝርዝር መግለጫ በቅርቡ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሸገር ሰምቷል፡፡በአሜሪካ መንግስት የኮንግረስ አባላት በሙሉ ድምፅ የፀደቀው HR 128  በዋነኛነት ከያዛቸው ነጥቦች መሀከል የሰብአዊ መብት አያያዝና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከንግግር በዘለለ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠይቅ ሀሳብን በቀዳሚነት የያዘ ውሳኔ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፉት አራት አመታት በወር በአማካይ 2 ሺ 300 ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተነገረ

ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኛ ጣቢያዎች ገብተው የተመዘገቡ መሆናቸውን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ቢሮ ሰምተናል፡፡በወር በአማካይ 2 ሺ 300 ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተናገረው ድርጅቱ በጥቅምትና በመጋቢት ወራት ቁጥሩ ከፍ እንደሚል ተናግሯል፡፡ከስደተኞቹ ውስጥም 39 በመቶዎቹ ህፃናት ናቸው የተባለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 25 በመቶዎቹ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ከአስመራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ስደተኞች በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ገብተው መሰረታዊ ድጋፍ ቢደረግላቸውም አብዛኛዎቹ ግን በጥቂት ጊዜ ውስጥ የመጠለያ ጣቢያዎቹን ጥለው ይወጣሉም ተብሏል፡፡ለምሳሌም ያህል ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ ከገቡ ኤርትራዊያን 80 በመቶዎቹ በ12 ወራት ውስጥ የመጠለያ ጣቢያ ኑሮ በቃን ብለው ጥለው መውጣታቸውን የድርጅቱ ሪፖርት አሳይቷል፡፡

ስደተኞቹ ከመጠለያ ጣቢያዎቹ የሚመጡት የተሻለ ትምህርት በማለም በውጭ አገር ካሉ ዘመዶቻቸው ጋር ለመቀላቀል እና በአስመራ ያሉ ዘመዶቻቸውን የመርዳት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው ተብሏል፡፡አብዛኛዎቹም እነዚህን ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት በተገኘው አማራጭ አውሮፓ ለመግባት እንደሚሞክሩም ተናግሯል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ ከ1 መቶ 66 ሺ በላይ ኤርትራ ስደተኞች በኢትዮጵያ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን ለእነዚህ ስደተኞች በተያዘው የፈረንጆቹ አመት 2018 ከ65 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ከተለያዩ አገራት መጥተው በኢትዮጵያ ያሉት ስደተኞች ብዛት ከ909 ሺ በላይ የደረሰ ሲሆን ኤርትራዊያን በብዛት ሶስተኛ ሲሆኑ ደቡብ ሱዳናዊያን እና ሶማሊያዊያን በአንደኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers