• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሐገሪቱ በተስፋ ጎዳና ላይ ናት፤ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የተቀበላቸው ፓርቲዎችም የሚፈተሹበት ጊዜ አሁን ነው

ህዝብ እና ሐገር ባንዲራ ይዘው የተቀበሏቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር ሲገቡ መሬት ጠብባ ነበር፤ እሰይ ለአንድነት ይሁን ለሰላምም ተብሏል፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለሞያዎችም ቢሆኑ የሚፈተሹበትና ልካቸው የሚታወቅበት ጊዜው ደርሷል ተብሏል…በዚህ ዙሪያ ተህቦ ንጉሤ ያዘጋጀውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በመንግሥት በጀት የሚሰሩ ግንባታዎችን የማሰራት እና የመቆጣጠር ሀላፊነት ለከተማዋ የኮንስትራክሽን ቢሮ ተሰጠ

በአዲስ አበባ በመንግሥት በጀት የሚሰሩ ግንባታዎችን የማሰራት እና የመቆጣጠር ሀላፊነት ለከተማዋ የኮንስትራክሽን ቢሮ ተሰጠ፡፡ ቢሮው የነበሩ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሚሰራም ተናግሯል፡፡የማህሌት ታደለን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በበጎ አድራጊዎች ዘንድ የበዛ ቅሬታ ይቀርብበት የነበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተሻሽሎ መፅደቁ ይታወቃል፤ኤጀንሲውም በተሻሻለው ህግ ልክ ስራውን ለማዘመን እየሰራሁ ነው ብሏል

በበጎ አድራጊዎች ዘንድ የበዛ ቅሬታ ይቀርብበት የነበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተሻሽሎ መፅደቁ ይታወቃል፡፡ ኤጀንሲውም በተሻሻለው ህግ ልክ ስራውን ለማዘመን እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ የትዕግስት ዘሪሁንን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሥነ ምግባር ጉድለት ያሳዩ ከ140 በላይ ጠበቆች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተሰማ

የሥነ ምግባር ጉድለት ያሳዩ ከ140 በላይ ጠበቆች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተሰማ፡፡ የንጋቱ ሙሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግስት በማረሚያ ቤቶች የሚያደርገው የግንባታ ማሻሻያ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት ለመጠበቅ እና አያያዛቸውንም ለማስተካከል እንጂ ተጨማሪ ዜጎችን ለማሰር አይደለም ሲል የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተናገረ

መንግስት በማረሚያ ቤቶች የሚያደርገው የግንባታ ማሻሻያ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት ለመጠበቅ እና አያያዛቸውንም ለማስተካከል እንጂ ተጨማሪ ዜጎችን ለማሰር አይደለም ሲል የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተናገረ፡፡ የምህረት ስዩምን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ልዩ ወሬ -የድሬን ምግብ የሚያጣጥሙባት “ሮቃ ካፌ”

የሸገሩ ወንድሙ ኃይሉ ሰሞኑን የድሬን ምግብ የሚያጣጥሙባት፣ የድሬዳዋ ሕይወት መታያ ወደሆነችው የ22 ማዞሪያዋ “ሮቃ ካፌ” ጎራ ብሎ ነበር፡፡ፈጢራ፣ ሹሞ፣ መለዋ፣ ሐለዋ፣ ሙሸበክ እና ሌሎችም የድሬ ምግቦች ብቻ የሚገኙባት ይህች ካፌ ከድሬ ምግቦች ውጪ ሌላ ምግቦች አይሸጡባትም ይለናል…

ለመሆኑ “ሮቃ” ምንድነው?

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢሕአዴግ በኢንዳውመንት ስም ያቋቋማቸው የንግድ ድርጅቶች በሃገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ያላቸው ተፅእኖ ምን ይመስላል?

የፖለቲካ ድርጅቶች በንግድ ተግባር ከተሰማሩ ፖለቲካውንና ኢኮኖሚውን የሚያቃውስ ይሆናል፡፡ በተለይም በስልጣን ላይ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግዱ ላይ ተካፋይ ሲሆኑ አግላይና ተጫኝ አሰራር ስለሚጀምሩ ሚዛን የሌለው የንግድ ሥርዓት ይሰፍናል፤ ህጋዊ ነጋዴዎች እየቆረቆዙ የድርጅቱ ንግዶች እንዲጎብለቱ ይደርጋሉ፤ በታክስና በብድር አሰጣጥም ላይ የተወላገደ አሰራር ለመከተል ምክንያት ይሆናሉ የሚል አስተያየት ይሰጣል፡፡ኢሕአዴግ በኢንዳውመንት ስም ያቋቋማቸው የንግድ ድርጅቶች በሃገሪቱ ምጣኔ ሀብትና ገንዘብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አድርሰዋል ሲባልም ቆይቷል፡፡ትዕግስት ዘሪሁን፣ ኢሕአዴግ የራሱን ስራና ጠንካራ የንግድ ድርጅት በማቋቋሙ ምን ችግር ገጥሟል ስትል የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አነጋግራለች፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለኦነግ የእንነጋገር ጥያቄ የመንግሥት መልስ ምንድነው?

ካለፉት 9 ወራት ወዲህ ኢትዮጵያ የምትመራበትን ሥርዓተ አስተዳደር እየጠገነችና እያፈረሰች በለውጥ ጎዳና ላይ ናት፡፡በየበረሃውና በየውጭ ሃገሩ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም በሰላም ወደ ሃገር ገብተው በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን እንዲያስፋፉ ተደርጎ መልካም ጅምር ታይቷል፡፡ ይሁንና በተለያዩ ዘርፎች ለውጡ እንደሚፈለገው መሰስ ብሎ ሊሄድ አልቻለም፡፡ የዜጎች ግጭት፣ መፈናቀል፣ የሞት ወሬ በየሳምንቱ እየተሰማ ነው፡፡ በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ እንዲህ ዓይነቱ ሰቆቃ ለወራቶች ያህል ሲሰማ ቆይቷል፡፡

በምዕራብ ኦሮሚያ የመንግስት መዋቅር ፈርሶ፣ መንገዶችና ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንዲያም ሲል የነዋሪዎች ሞትና አደጋ መድረሱ ሲሰማ ሰንብቷል፡፡ድርጊቱ መፈፀሙን በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ ድርጅቶች ኦዴፓም ሆነ ኦነግ ያምናሉ፤ የማይተማመኑት “ጥቃቱን ማን አደረሰው” በሚለው ላይ ነው፡፡

ከኤርትራ ትጥቅ የፈቱ አባሎቹን ያስገባው ኦነግ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ያሉት ታጣቂዎቹ እንደሚከላከሉ ይናገራል እንጂ ግጭት አይፈልጉም ይላል፡፡ ኦዴፓ ደግሞ በዚያ አካባቢ ለደረሰው ችግር ሁሉ ተጠያቂው ኦነግ ነው ይላል፡፡በዚህ ሳምንት፣ የኦነጉን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ምን እያደረጋችሁ ነው? በማለት የጠየቀው ንጋቱ ሙሉ የኦዴፓውን የፅህፈት ቤት ሀላፊ በሶስተኛ ወገን እንደራደር ለሚለው የኦነግ ጥሪ ምላሻችሁ ምንድነው? ሲል ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሽሮ ሜዳ ቁስቋም እና የቃሊቲ ቶታል ቱሉ ዲምቱ አደባባይ መንገዶች ግንባታ ነገ ጥር 5፣2011 ይጀመራል ተባለ

የሽሮ ሜዳ ቁስቋም እና የቃሊቲ ቶታል ቱሉ ዲምቱ አደባባይ መንገዶች ግንባታ ነገ ጥር 5፣2011 ይጀመራል ተባለ፡፡ የንጋቱ ሙሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ 67 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ በጀት ተማሪዎችን እየመገበ መሆኑን ተናገረ

የከተማዋ አስተዳደር የመደበው በጀት 51 ሺ ተማሪዎች የቁርስና ምሳ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን በቢሮው የህፃናት ጤና እንክብካቤና ምገባ ስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሪት ሜቲ ታምራት ነግረውናል፡፡ከእነዚህ በተጨማሪ ሌሎች 10 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎችም በረጂ ድርጅቶች አማካኝነት እየታገዙ ነው ተብሏል፡፡ተማሪዎቹም በቂ ምግብ ማግኘት የማይችሉ የደሃ ልጆች መሆናቸው የተለዩ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡የተማሪዎች ምገባ የትምህርት ማቋረጥና መድገምን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ወ/ሪት ሜቲ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት በረጂ ድርጅቶች ይደረግ የነበረው ምገባ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ማድረጉንም ሰምተናል፡፡ተማሪዎች ይገጥማቸው በነበረ የምግብ እጥረትም ከትምህርት ገበታቸው በመቅረት የተለያዩ የቀን ስራዎች ላይ ይጠመዱ እንደነበረም ተናግረዋል፡፡ብዙዎች ረሃቡ አዝለፍልፎ ይጥላቸው እንደነበር ያስታወሱት ወ/ሪት ሜቲ የተማሪዎች ምገባ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለተማሪዎች ምድባ በጀት ሲመድብ የመጀመሪያው ነው፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከ75 በመቶ በላይ የሆነውን የአዲስ አበባ ከተማ በጀት የያዘው የኮንስትራክሽን ዘርፍ በአግባቡ ሊመራ ይገባል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ በመንግስት በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃና በቀጣይ ስራዎች ላይ የአፈፃፀም አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከስራ ተቋራጮችና ከአማካሪዎች ጋር ዛሬ በኢሊሌ ሆቴል ተነጋግሯል፡፡ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ እየተጓተቱ ያሉ ግንባታዎች በአስቸኳይ መፍትሄ ያገኛሉ ብለዋል፡፡ውላቸውን ተግባራዊ ያላደረጉ ተቋራጮች ውላቸው ተቋርጦ በኮንስትራክሽን ሕጉ መሰረት እንዲዳኙ ይደረጋል ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ የከተማውን ከፍተኛ በጀት የያዘው ይኸው ዘርፍ ከዚህ በኋላ በበቂ ትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ለግንባታዎች መጓተት እንደምክንያት የሚጠቀሰው የወሰን ማስከበር ጉዳይም በከተማ አስተዳደሩ በኩል የሚያልቅበት አሰራር ተጀምሯል ብለዋል፡፡243 ነባር ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ መጠናቀቅ አለመቻላቸውን የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers