• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ትናንት ምሽት በብሄራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ የጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት 9 ድርጀቶች የዋንጫ አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል

በ6ኛው አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር አድርገዋል፡፡የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠበቃ የሆኑት ፕሬዝዳንቷ የጥራት ጉዳይ ሲመቸን ብቻ የምናነሳው ሳይሆን ባህላችን ልናደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ በ6ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ከተወዳደሩ 52 ተቋማት መካከል 9ኙ የዋንጫ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ጋምቢ የህክምና እና ቢዝነስ ኮሌጅ፣ ጋምቢ አጠቃላይ ሆስፒታል እና አላማጣ ሆስፒታል የ3ኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ፡፡

በላይአብ ኬብል ማምረቻ ፣ ሲኖ ኢቶጵ አሶሽዬት እና ኦሪጅን ውሃ ሁለተኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ አማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት እንዲሁም ሐረር ቢራ የ1ኛ ደረጃ የዋንጫ ሽልማት አግኝተዋል፡፡በተከታታይ ለ3 አመታት 1ኛ ደረጃ የዋንጫ ሽልማት ያገኘው ጎንደር ዩኒቨርስቲ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል፡፡7ኛው አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ከ2 ምንታት በኋላ ምዝገባው እንደሚጀምር ሰምተናል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች፣ ወደፊት ሊወያዩባቸውና ሊደራደሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል

በትናንቱ ምክክራቸው፣ 32 የድርድር አጀንዳዎች ቀርበዋል፡፡ከ32ቱ አጀንዳዎች መካከል፣ የክልሎች አደረጃጀት፣ የ2012 ምርጫ፣ ስለ ምርጫ መራዘም፣ ስለ ሰላምና መረጋጋት፣ ስለ ሕገ መንግስት ማሻሻያ፣ ስለ ስራ ቋንቋ፣ ስለ አዲስ አበባ እና ሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ይገኙበታል፡፡

በተጨመሪ 16 አንቀፅ ያለው ረቂቅ ደንብ ተረቅቆ እየተወያዩበት ነው፡፡በውይይቱ ረቂቅ፣ የአወያይ እና የታዛቢዎች ተግባር ተካቶበታል፡፡ውይይቶች፣ በፓርቲዎች ይሁንታ በሚመረጡ ገለልተኛ አወያዮች እንደሚመራም በረቂቁ ላይ ተመልከቷል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕግን የሚያከብርና ግዴታውንም የሚወጣ ትውልድ ይቀርፃል የተባለ የሕገ መንግሥት እና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ሊቋቋም ነው

ሕግን የሚያከብርና ግዴታውንም የሚወጣ ትውልድ ይቀርፃል የተባለ የሕገ መንግሥት እና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ሊቋቋም ነው፡፡ የትዕግስት ዘሪሁንን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ከዚህ ወዲያ ማህበራዊ ሃላፊነታችንን ተወጥተናል በሚል ሪፖርት ብቻ አታልለው ማለፍ አይችሉም ተባለ

የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ከዚህ ወዲያ ማህበራዊ ሃላፊነታችንን ተወጥተናል በሚል ሪፖርት ብቻ አታልለው ማለፍ አይችሉም ተባለ፡፡ በሁሉም ዘርፍ ተቆጥሮ የተሰጣቸውን ተግባራት ቆጥሮ የመረከብ አሰራር ተዘርግቷልም ተብሏል፡፡ የአስፋው ስለሺን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የመጥፋት ስጋት ያንዣበበበትን የአቢያታ ፓርክ እና በውስጡ የሚገኙ ሀይቆችን ለመታደግ ጥረት እያደረግኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ተናገረ

በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የመጥፋት ስጋት ያንዣበበበትን የአቢያታ ፓርክ እና በውስጡ የሚገኙ ሀይቆችን ለመታደግ ጥረት እያደረግኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ተናገረ…የምህረት ሥዩምን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የመከላከያ እና የኦነግ ፍጥጫ

በምዕራብ ወለጋ የታየውን የሰላም መደፍረስና የግጭት ቀጠና መሆኑን አስመለክቶ በመንግስት በኩል የተለያዩ መግለጫዎች ሲሰጡ እንሰማለን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ምክትል ኢታማዦር ሹሙ እንደተናገሩት፣ ስምም ባይጠቅሱ ችግሩን የጎተተው ኦነግ መሆኑን የሚያመለክቱ መግለጫዎችን እየሰጡ ነው፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርስ ምን ይላል? ንጋቱ ሙሉ የኦነግን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጠይቋል፡፡


አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በታራሚዎች ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን ችግር ለማስቀረት ቀደም ሲል በየማረሚያ ቤቶች የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ አመራሮችን ከሃላፊነት ማንሳቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተናገረ

አስተዳደሩ እንደተናገረው በፍትህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች ሲፈፀሙ ቆይተዋል፡፡ ከነዚህም ተቋማት ውስጥ ማረሚያ ቤቶች እንደሚገኙበትና ይህንንም ለማስተካከል በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው ሲነገሩ እንደሰማነው በየማረሚያ ቤቶቹ ላይ ከዚህ ቀደም ሲፈፀም እንደነበረው የመብት ጥሰት እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዳይኖር ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡አሁን ላይም ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከዚህ ቀደም የነበረው ችግር አለመኖሩን ባደረግነው ክትትል አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥም የዳሰሳ ጥናት መደረጉንና ይህም ራሳቸውን ታራሚዎች፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች ወገኖች የተሳተፉበት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ዋነኛ የለውጥ ስራ ለማድረግም በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ሀላፊዎችን በአዲስ እንዲተኩ መደረጉን ተናግረዋል፡፡በማረሚያ ቤቶች ያለውን የታራሚዎች አያያዝ ይበልጥ ለማሻሻልም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የሚገኙ አራት ማረሚያ ቤቶች በአዲስ እየተገነቡ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ተናግረዋል፡፡በአዲስ አበባ የሚገነባው ማረሚያ ቤት ግንባታው 96 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን በዚህ አመት ስራ ይጀምራል ተብሏል፡፡በዚህ አመት ከየማረሚያ ቤቶቹ ከ6 ሺ በላይ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ተደርጓል መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሴቶችና ወጣቶች ሚኒስቴር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ማኑዋል አዘጋጅቻለሁ አለ

የሴቶችና ወጣቶች ሚኒስቴር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ማኑዋል አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡ የማህሌት ታደለን ዘገባ  ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢንዱስትሪ ፓርኮች በኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት መቸገራቸው ተነገረ

በዚህም የተነሳ የአቅማቸውን ያህል እያመረቱ አይደለም ተብሏል፡፡በሀይል መዋዠቅ የተነሳ የማምረቻ መሳሪያዎቻቸው ከጥቅም ውጪ እየሆኑባቸው መሆኑን ሰምተናል፡፡ያለው የሀይል አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ከከፍተኛ ሀይል ተጠቃሚዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ ሰምተናል፡፡ከተለያዩ ፋብሪካዎች የተገኙ የውይይቱ ተሳታፊዎች በኤሌክትሪክ ችግር ምክንያት ለብልሽት የሚዳረጉ የማምረቻ መሳሪያዎች ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡

እስካሁን ድረስም የካሳ አከፋፈል ሥርዓት ባለመዘርጋቱ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡በራሳቸው ወጪ ለማስጠገንም የውጪ ምንዛሪ እጦት እክል እንደሆነባቸው ጠቅሰዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በቅርብ ጊዜ ማሻሻያ የተደረገበት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍም ዳግም ቢፈተሽ የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡርም በተደጋጋሚ የሀይል እጥረት እንደሚያጋጥመው ተናግሯል፡፡በዚህም ምክንያት የትራንስፖርት ሥርዓቱ እየተስተጓጎለ ነው ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ከደንበኞች ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሰራለን ብለዋል፡፡መስሪያ ቤታቸው ለተነሱት የሀይል ችግሮች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለማበጀትና ለኢንዱስትሪስ የሚመጥን ሀይል ለማቅረብ የሀይል ማመንጫዎችንና ማሰራጫዎችን እያስገነባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በሚል አዲስ ስያሜ ተሻሽሎ ረቂቁ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀረበ

ከዚህ ቀደም በበጎ አድራጊዎች ዘንድ በርካታ ተቃውሞና ምሬት ሲቀርብበት የነበረው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ገዳቢ አንቀፆችን በመሻር ተሻሽሏል፡፡በቀደመው አዋጅ በሰብአዊ መብት ጉዳይና ዲሞክራሲ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶችና ማህበራት ከውጪ ሀገር ገንዘብ ማግኘት የሚፈቀድላቸው ከአጠቃላይ ገቢያቸው 10 በመቶ ብቻ ነበር፡፡ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን ለማስከበርና ለማክበር የፈረመቻቸውን አለም አቀፍ ስምምነቶች የሚጥስ እና ገዳቢም በመሆኑ በአዲሱ ረቂቅ ተሽሯል፡፡ይህም የሥራ ማከናወኛ እያጠራቸው የሚዘጉ ምግባረ ሰናይ ማህበራትና ድርጅቶችን ይታደጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ረቂቅ አዋጁን ለማዘጋጀት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በየአመቱ ከመቶ የማያንሱ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሲዘጉ እንደነበር በረቂቅ አዋጁ ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡በሰብአዊ መብት አጠባበቅና በዲሞክራሲ ላይ የሚሰሩ በጎ አድራጊ ድርጅቶች የሉም ለማለት እስከሚያችል ድረስ ቁጥራቸውም ተመናምኗል ተብሏል፡፡በቀደመው አዋጅ ለአስተዳደራዊ ወጪና ለአላማ ማስፈፀሚያ ከገቢያቸው 30 በመቶና 70 በመቶ እንዲጠቀሙ ይፈቀድ ነበር፡፡በተሻሻለው አዋጅ፣ ከገቢያቸው ለአስተዳደራዊ ወጪ 20 በመቶ ለአላማ ማስፈፀሚያ 80 በመቶ እንዲሆን ተደንግጓል፡፡

በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ማህበራትን የሚያስተዳድረው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ላይ ብቻ አተኩሮ ይሰራ ነበር ተብሏል፡፡በረቂቁ ኤጀንሲው ለበጎ አድራጊዎቹ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር፣ የማብቃትና እንደአስፈላጊነቱም የመቆጣጠር ስራ በመስራት ሚዛናዊ ተቋም እንዲሆን ተደርጎ አላማው ተሻሽሏል፡፡የተሻሻለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት ለዝርዝር እይታ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ የህገ መንግስትና የፌድራሊዝም አስተምህሮ ማዕከልን ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅም ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ነባር ስሙን እንደያዘ እንደ ገና ሊቋቋም ነው

ኢዜአ ተወዳዳሪ እንዲሆን በብቁና በበቂ የሰው ሀይል እንዲደራጅ የራሱን ገቢ የሚያገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ተቋሙን እንደ አዲስ ማቋቋም አስፈልጓል ተብሏል፡፡መንግስት ከሚመድብለት በጀት በተጨማሪ በህትመት ሚዲያ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማማከር ስራ ላይ በመሳተፍ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ መፈቀዱን ኢዜአን እንደገና ለማቋቋም ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የማቋቋሚያ አዋጅ መግለጫ ያስረዳል፡፡

ማስታወቂያ መስራትም ይጀምራል የተባለ ሲሆን ገቢውን ማሳደጉ ተወዳዳሪ ሞያተኞች ቀጥሮ ተልዕኮውን ለመወጣት እንደሚያስችለው ታምኖበታል፡፡የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን አፍርሶ እንደገና ለማቋቋም የቀረበው አዋጅ ከመፅደቁ በፊት በደንብ እንዲፈተሽ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers