• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ግንቦት 19፣2011/ በቅርቡ በመተከል ዞን ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ያረጋጋል፣ በቤንሻንጉል ጉምዝና በአማራ ክልል ህዝቦች መካከልም የነበረውን ወዳጅነት ያጠናክራል የተባለ የሰላም ኮንፍረስ ትናንት ተካሄደ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ኢዮብ ሰንበታ እንደሰማነው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በተገኙበት በግልገል በለስ በተከናወነ የሰላም ኮንፍረስ ላይ ግጭቱን የፈጠሩ በህግ እንዲጠየቁ በግጭቱ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደየቄያቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ምክክር ተካሂዷል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና እና የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል ሲሉ አቶ ኢዮብ ነግረውናል፡፡በሰላም ኮንፍረንሱ ላይ በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝም እና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን ተገኝተው የህግ የበላይነትን ለማስጠበቀው ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እንሰራለን ማለታቸውንም ሰምተናል፡፡በመተከል ዞን ከሚያዝያ 17 ጀምሮ በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ሕይወት ማለፉንና የአካል ጉዳት ማጋጠሙን አቶ ኢዮብ አስታውሰዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 19፣2011/ የኢትዮጵያን እድገት ለማቀልጠፍ መንግስት ለጥናትና ለምርምር የሚመድበውን በጀት ከፍ ማድረግ እንደሚኖርበት ተናገረ

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለዘርፉ የምትበጅተው የገንዘብ መጠን ከአለም አገራት የመጨረሻዎቹ ተርታ የሚያሰልፋት መሆኑን ሰምተናል፡፡በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ የሚጠበቀውን እድገት ማረጋገጥ ዳገት እንደሚሆንባት ነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የጥናትና ምርምር መድረክ ላይ ተገኝተን የሰማነው፡፡የአለም አገራት ለጥናትና ምርምር የሚመድቡት የአመታዊ በጀታቸውን በአማካይ 2 ነጥብ 29 በመቶ ሲሆን የኢትዮጵያ 0 ነጥብ 27 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ይህም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ተመራማሪዎች እንዳይበረክቱ ምክንያት መሆኑን ሰምተናል፡፡

የተመራማሪዎች ቁጥር መመናመን ለአገርም ሆነ ለትምህርት ተቋማት እድገት ማሽቆልቆል ምክንያት ነው ተብሏል፡፡የአለም አገራት የተመራማሪዎች አማካይ ቁጥር 1 ሺ 461 በአንድ ሚሊዮን ሕዝብ ሲሆን የኢትዮጵያ 45 ነው ተብሏል፡፡ስለሆነም አገሪቱ በጥናትና ምርምር ላይ የምትሰራው ዘርፈ ብዙ የቤት ስራ አለባት ነው የተባለው፡፡ዛሬ በተከፈተው የጥናትና ምርምር ሳምንት ፕሮግራም ላይ የሰላም ሚኒስትርና የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 19፣2011/ ማንን ምን እንጠይቅልዎ

“በሰባት ወራት ውስጥ 1.3 ቢሊዮን የሚገመቱ ገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ እና ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ይዘናል” አቶ ደበሌ ቀበታ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነርግርማ ፍስሃ 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 19፣2011/ ብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ቁጥር እየጨመረ ነው አለ

ብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ቁጥር እየጨመረ ነው አለ፡፡ የእነ ህፃን ካሌብን ህይወት በእነ ዳዊት ደም መታደግ ተችሏል፡፡ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 19፣ 2011/ መንግስት ከመደበው የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ለአዲስ አበባ ወጣቶች ስራ ፈጠራ እንዲሆን 263 ሚሊየን ብር ብድር ተሰጥቷል ተባለ

መንግስት ከመደበው የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ለአዲስ አበባ ወጣቶች ስራ ፈጠራ እንዲሆን 263 ሚሊየን ብር ብድር ተሰጥቷል ተባለ፡፡ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 19፣ 2011/ የተሽከርካሪ አደጋ ከሚደርስባቸው ውስጥ የሶስተኛ ወገን ካሳ የሚያገኙት ከ60 በመቶ ይበልጡም ተባለ

የተሽከርካሪ አደጋ ከሚደርስባቸው ውስጥ የሶስተኛ ወገን ካሳ የሚያገኙት ከ60 በመቶ ይበልጡም ተባለ፡፡ የመድህን ፈንድ ኤጀንሲ ባለፉት ዘጠኝ ወራት፣ ለትራፊክ አደጋ 23 ሟች ቤተሰቦች ካሳ መክፈሉን ተናግሯል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 16፣ 2011/ የፌድራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤት እሰራለሁ እቅድ ከምን ደረሰ?

አዲስ አበባ ዋና ችግሯ፣ መፍትሄ ለመሻትም እንደሰማይ የራቃት ለነዋሪዎቿ ወጥቶ መግቢያ ገብቶ መተኛ ቤት ማግኘት ነው፡፡ የቤት ችግር፣ የሰራተኛውም፣ ስራ የሌለውም፣ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውም ሁሉ ችግር እንደሆነ ነው፡፡ ታዲያ ምን ታስቧል ? የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በውርስና ጥቂቶችን ሰርቶ የሚያስተዳድራቸውን ቤቶች ከማከራየት አልፎ ተጨማሪ ግንባታ አካሄዳለሁ ብሎ ነበር፡፡ እቅዱን እምን አደረሰው፡፡ ምህረት ስዩም ጠይቃለች፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 16፣2011/ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባንኮች ያላቸው ድርሻ ጉዳይ

በትውልድ ኢትዮጵያውያን ሆነው የሌላ ሃገር ዜግነት የያዙ ግለሰቦች ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ባንኮች ያላቸውን ድርሻ እንዲሸጡ የተወሰነውን ውሳኔ የሚያሻሽል አዋጅ ከጥቂት ቀናት በፊት ፀድቋል፡፡ አዋጁ ቀደም ሲል የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች በፋይናንስ ተቋሙ ከገቡ ገና “ግልገል” በሆኑት የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሚዛን ያጎድላሉ፣ ለፖለቲካውም እጃቸው ይረዝማል ተብሎ ነበር፡፡ ታዲያ አሁን በምን ብያኔ ያ ስጋት ተገፈፈ? የአሁኑ ሕግ መሻሻል ምን ጥቅም ያስገኛል? ንጋቱ ረጋሣ የባንክ ባለሙያ አነጋግሯል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ልዩ ወሬ - የሰላም ሰባኪው ሰይፈ አማኑዔል

በቦሌ ጎዳናዎች ጡሩምባ እየነፋ፣ በሚለብሰው ባነር ጭምር ሰላምን የሚሰብከው ሰይፈ አማኑኤል የሰላም ስብከቱን ከጀመረ 8 ወር ሞላው፡፡የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ሲያነጋግረው፣ ለዚህ ያነሳሳው በሰላም እጦት ለልመና የተዳረጉ የሶርያ ስደተኞችን ማየቱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡የሰላም ሚኒስትሯም ጠርተው አነጋግረውታል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 16፣ 2011/ ኢትዮጵያውያን በቻይና እስር ቤት የመታሰራቸው ምክንያት ምንድነው?

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ናዝራዊት ከአውሮፕላን ወርዳ እግሩዋ የቻይናን ምድር እንደነካ በያዘቻቸው በውበት መጠበቂያ እቃዎች አደንዛዥ እፅ በመገኘቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋላት፡፡ ናዝራዊት፣ በእቃዋ ውስጥ ስለተገኘባት አደንዛዥ ዕፅ የምታውቀው ነገር የለም፣ ቢባልም ፖሊስ ግን በርካታ ምርመራዎችን አደርጋለሁ ብሎ አሁንም ጉዋንዦ በሚገኘው እስር ቤት ናት፡፡ በቻይና፣ ናዝራዊት ብቻ ሳትሆን ሌሎችም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው እስር ቤት ታስረዋል፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያውያኑ በቻይና እስር ቤት የመገኘታቸው ምክንያት ምንድነው? በዚያ ያለው ኤምባሲያችንስ ጉዳዩን ምን ያህል ይከታተላል? እሸቴ አሰፋ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደርን አነጋግሯል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 16፣ 2011/ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እየዘገኑ የሚሰጡት ብር ምንጩ ከየት ይሆን ?

በኢትዮጵያ እንደልማድ የተያዘ የፋይናንስ አሰራር መታረሚያ የጠፋበት ይመስላል፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በጀት ተመድቦላቸው፣ ባቀረቡት አመታዊ የትግበራ እቅድ መሰረት ገንዘብ የተለቀቀላቸው ሆኖ ሳለ፣ ከዚያ አልፈው ርዳታና ስጦታ ሰጪ መሆናቸውን በየመገናኛ ብዙሃኑ ከሚያስነግሩት እንሰማለን፡፡ በበጀት የሚተዳደርና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በጀቴ አነሰኝ ገንዘብ ጨምሩልኝ የሚለው ሁሉ ይኽን ያህል መቶ ሺዎች፣ ሚሊየኖች ስጦታ ሰጠ ሲባል ይሰማል፡፡ እነዚያ መስሪያ ቤቶች እያፈሱ የሚሰጡት ገንዘብ ካስያዙት እቅድ የተረፈ ነው ? አሳልፈውስ ለመስጠት ይችላሉ ? ሰጪና ፈቃጅ የሆኑበትስ የማን ገንዘብ ነው? ቴዎድሮስ ብርሃኑ እንዲህ ያለውን አሰራር ተመልክታችሁታል? ብሎ ለመጠየቅ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ብቅ ብሎ ነበር፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers