• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተባለ

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 2 ቀን በኢትዮጵያ ይገኛሉ ተብሏል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በሁለቱ ሀገራት ፖለቲካዊና ምጣኔ ሐብታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመካከሩ ተነግሯል፡፡

አየርላንድ በኢትዮጵያ በምጣኔ ሐብታዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዘርፎች ድጋፍ የምታደርግ ሲሆን በነዚህ ዘርፎች በአይሪሽ የልማት ተራድኦ ድርጅት በኩልም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማዘጋጀት ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች ተብሏል፡፡በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ እና በአካባቢው ሀገራት ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት አውሮፓዊቱ አገር አጋር ሆና ቆይታለች ተብሏል፡፡ኢትዮጵያ እና አየርላንድ ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የተሽከርካሪ ታርጋ አሰጣጥ ወጥ አለመሆን ችግር ደቅኗል ችግሩን ለማስተካከልስ ምን ለመስራት ታስቧል?

የተሽከርካሪ ታርጋ አሰጣጥ ወጥ አለመሆን ችግር ደቅኗል፡፡ ችግሩን ለማስተካከልስ ምን ለመስራት ታስቧል ሲል ንጋቱ ሙሉ የሚመለከታቸውን አነጋግሮ ያዘጋጀውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በህክምና ስህተት ጉዳት ሲደርስ የህግ አሰራር ሥርዓቱ ምን ይላል?

በሽታችን በዝቷል፡፡ ሐኪሞቻችንና ታማሚዎቻችን አልተመጣጠኑም፡፡ ይሁንና ሐኪም ማግኘት ብርቅ በሆነባት ሃገርም ቢሆን፣ “ሐኪም ምን ሰራ፣ ምን አጠፋ” ብሎ መጠየቅ አይቀርም፡፡ ሐኪሞቻችን በዙም አነሱም፤ የሙያ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ታካሚ በዝቷል ሐኪም አንሷል ተብሎ በግድየለሽነት የሚፈጥሩ ስህተቶች ለሚያስከትሉት አደጋ አይጠየቁም ማለት አይቻልም፡፡ በተለያዩ ጊዜ በሐኪሞች ስህተት የሞቱና፣ በማይድን የአካል ደዌ የወደቁ መኖራቸውን እንሰማለን፡፡ ታዲያ ሐኪሞቻችን በሚፈጥሩት ስህተት ጉዳት ሲደርስ የሚታረሙበት የህግና የአሰራር ሥርዓት ምን ይመስላል?ምህረት ስዩም ዝግጅት ይህን ይመለከታል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የታቀደውን ያህል ግብር ለመሰብሰብ ምን አይነት አሰራር ተቀይሷል?

የግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት በየአመቱ ይህን ያህል የግብር ገንዘብ እሰበስባለሁ ብሎ እቅድ ማውጣትና በአመቱ መጀመሪያ ዕወቁልኝ ስሙልኝ የሚል መግለጫ ማሰማትን ልምድ አድርጎታል፡፡ነርገ ግን ማስረጃዎች እንደሚያመለክቱት አንድም ጊዜ በእቅዱ የተነደፈውን ያህል ግብር ተሰብስቦ አያውቅም፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አመት የገቢዎች ሚኒስቴር እሰበስበዋለሁ ብሎ ካቀደው ውስጥ 50 ቢሊየን ብር የሚሆነው አለመሰብሰቡ ተነግሯል፡፡ ገንዘቡ አለመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን በግለሰቦች ለመመዝበርም የተጋለጠ ሆኗል ተብሏል። አሁንስ፣ ወደፊትስ፣ እንደታቀደው የግብር ገንዘብ ለመሰብሰብ ምን ዓይነት አሰራር ተቀይሷል? ማህሌት ታደለ የገቢዎች መስሪያ ቤት ሀላፊን አነጋግራ ያዘጋጀችውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል።

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለሙስናና ለብልሹ አሰራር በተለየ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑት የፍትህ አካላት ፍትህ ፈልገው የሚሄዱ ዜጎች ከሚያነሱት የዘወትር ሮሮ ነፃ እንዲሆኑ በፍርድ ቤቶች ላይ የሚደረገው የለውጥ ስራ አሁንም ይቀጥላል ተባለ

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አለም አቀፉን የፀረ ሙስና ቀን አስመልክቶ በተሰናዳ ምክክር ላይ ተገኝተን እንደሰማነው የፍትህ ዘርፉ ከዛም ውስጥ ፍርድ ቤቶች ለሙስና የተጋለጡ በመሆኑ ወደ ፍርድ ቤቶች የሚሄዱ አገልግሎት ፈላጊዎችን በፍትህ አካላት ላይ ያጡትን አመኔታ ለማስመለስ ሙስናን መከላከል ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡በየቀኑ በርካታ ሚሊዮን ብሮችን በሙስና ምክንያት በልጆቿ የምትነጠቀው ኢትዮጵያ በሙስና ከምታጣው ገንዘብ በተጨማሪ ዜጎቿ ፍትህ ተነፍገው አንዳንድ የፍትህ ተቋማት ፍትህ በገንዘብ ሲቀየር በመኖሩ ፍርድ ቤቶች ለተበደለ ፍርድ የሚሰጡ ሳይሆኑ ፍትህ በገንዘብ የሚቀየርባቸው ሆኗል እየተባሉ በሕብረተሰቡ አመኔታ አጥተው ቆይተዋል ተብሏል፡፡

ይህንንም ለማስተካከል በፍርድ ቤቶች ላይ አሁን የተጀመረውን የለውጥ ስራ በማጠናከር፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲሁም በስሩ በሚገኙ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችና ሌሎች የፍትህ ተቋማት ላይ ለዳኞችና በዘርፉ ለሚያገለግሉ ባለሙያዎች የስነ ምግባር ክትትል በማድረግ፣ በፍርድ ቤቶች የሚታይ ሙስናን በማስወገድ በርካታ ስራዎች እየተሰራ ነው ሲሉ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ መሐመድ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሚቻለው ቅድሚያ አገር ሰላም ስትሆን እንደሆነ መምህራን ተናገሩ

ይሄን የሰማነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ከተውጣጡ መምህራን ጋር ውይይት ሲያደርጉ ነው፡፡ቁጥራቸው ከ4 ሺ በላይ የሚሆኑ መምህራን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተገኝተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡የመምህራን የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጉዳይ፣ አገሪቱ ያለችበት አለመረጋጋትና ግጭቶች እንዲሁም የትምህርት ጥራት በመምህራኑ የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

መምህራንን የአገር ዋርካ ናችሁ ያሉዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትኛውም ዓይነት ክፍያ የእናንተን ዋጋ የሚመጥን አይደለም ብለዋቸዋል፡፡መምህራን በብዙ ችግር ውስጥ ናችሁ ነገር ግን የእናንተ ውጤት የተማሪዎቻችሁን ፍሬ ማየት ነውና ተባብረን አገራችንን እንገንባ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መምህራንን ጠይቀዋል፡፡ውይይቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የመምህራን ጥያቄ እንዳበቃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተነሱ ጉዳዮች ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ረቡዕ እለት በታጠቁ ሀይሎች የታገቱት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደላሣ ቡልቻ ከእገታው መለቀቃቸው ተሰማ

ረቡዕ እለት በታጠቁ ሀይሎች የታገቱት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደላሣ ቡልቻ ከእገታው መለቀቃቸው ተሰማ፡፡የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ከእገታው የተለቀቁት ትናንትና ማታ በጊዳሚቲ ቀበሌ መሆኑን የኦዴፓ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገፃቸው ፅፈዋል፡፡

ዶ/ር ደላሣ በታጠቁ ሀይሎች የታገቱት ረቡዕ እለት ከደምቢዶሎ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ ከነሾፌራቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በማን እገታ ስር እንደቆዩ እና ስለ ደህንነታቸው ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው? ምሁርስ የሚባለው የትኛው ነው?

ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው ? ምሁርስ የሚባለው የትኛው ነው? ኢትዮጵያ በተለያዩ ግጭቶች እንደንፍፊት በተወጠረችበት በአሁኑ ጊዜ ወይም የድህነት ማቅ እየሞዠቀ በእምብርክክ በሚያስኬድባት ጊዜ የምሁራኖቹ ሚና ምን ነበር ? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምሁራን መሽገውባቸዋል የሚባሉት ዩኒቨርስቲዎቻችን በብሔር ዘውገኛነት እየተናጡ የሚገኙበት ምክንያት ሲታይ ወይም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንታኔ በጦዘ የብሔር ወገንተኝነት ተቆልምመው ሲነጉዱ ይታያሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ድርጊቶችም ኧረ ለመሆኑ ምሁር ማለት ምን ማለት ነው የሚል ጥያቄ ያጭራል፡፡ በየነ ወልዴ ይህኑ ጥያቄ ይዞ አንድ ፕሮፌሰር አነጋግሯል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባንኮቻችን የፈጠራ ሐሳብን እንደመያዣነት ወስደው ማበደር መጀመር አለባቸው…

ባንኮቻችን ለማበደር ማስያዣ ይጠይቃሉ፡፡ አስተማማኝ መያዣ አድርገው የሚቆጥሩትና የሚቀበሉት ቁሳዊ ንብረት ነው፡፡ ተበዳሪዎቹ በተለመደው አሰራር ገንዘባቸውን የቁሳዊ ሀብት ለማስፋፋት ይጠቀሙበታል፡፡ ይሁንና ለሃገርና ለሕብረተሰብ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርገው፣ የፈጠራ ሀሳብ፣ በኛ ሃገር ለመያዣነት አይበቃም፡፡ የብዙ ሰዎችን ሕይወት የሚለውጠው የፈጠራ ሀሳብ እንደዋስትና ተቆጥሮ ማበረታቻ ስለማይደረግለት ሊበረታታም አልቻለም፡፡ ንጋቱ ረጋሣ ይህንን አስመልክቶ ያዘጋጀውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የገቢ ደረሰኝ ሽያጭ ስርዓት (IVF) አተገባበር ላይ ለመወያየት ባለድርሻ አካላት በትግራይ መሰባሰባቸውን ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የትዊተር መልዕክት ለመረዳት ችለናል

የገቢ ደረሰኝ ሽያጭ ስርዓት (IVF) አተገባበር ላይ ለመወያየት ባለድርሻ አካላት በትግራይ መሰባሰባቸውን ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የትዊተር መልዕክት ለመረዳት ችለናል፡፡ ሥርዓቱ - ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና ውጤታማነትን ይዞ አነስተኛ ይዞታ ላላቸው ገበሬዎች የብድር እና የግብዐት አቅርቦትን ለማዳረስ ያለመ መሆኑንም ተመልክተናል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ብዙ የተማሩ ጋዜጠኞች ያሉባት አገር ነች ቢባልም የትምህርት ጥራቱ ግን መጠየቅ ያስፈልገዋል ተብሏል

በአደጉ አገሮችም ጠና ጠና ያሉ ጋዜጠኞች በየሚዲያው አሉ የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን የጋዜጠኝነት ሙያው የወደቀው 90 በመቶ በአማካይ 30 አመት እድሜ ባላቸው ጋዜጠኞች ትከሻ ላይ ነው ተብሏል፡፡ከ40 አመትና ከዚያ በላይ እድሜ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችም ከ10 ፐርሰንት በታች ናቸው ተብሏል፡፡እነዚህንም ጋዜጠኞች የተሻለ የገንዘብ ክፍያ ፍለጋና በተለያዩ ምክንያቶች ማቆየት አልተቻለም መባሉን ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ ባቀረቡት የጥናት ወረቀት አስረድተዋል፡፡በኢትዮጵያ የሚዲያና መረጃ የማያገኙ ማህበረሰቦች አሉ የተባለ ሲሆን መንግስት የቅንጦት ጉዳይ እንዳልሆነ አውቆ አትኩሮ ሊሰራበት ይገባልም ብለዋል፡፡

የምርመራ ጋዜጠኞችም ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው በጥናቱ ተካትቷል፡፡በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የመረጡልንን ነገር ነው የምናነበው፣ የምንሰማው እንጂ ያልተከለሰ ያልተጨመረ መረጃ መስጠት አልተቻለምም ተብሏል፡፡ የፕሬስ ነፃነቱ ከመወለዱ ከአፄ ምኒለክ ዘመን ጀምሮ በሀይለስላሴም ዘመን ቢሆን በተፈራረቁት መንግስቶች በጉያቸው ውስጥ ማኖራቸው ፕሬሱን በቅርብ ለመቆጣጠር አስበው እንዳደረጉት ይጠቁማል ተብሏል፡፡በደርግ ጊዜም በወቅቱ ከነበሩት 17 የህትመት ውጤቶች ውስጥ ከአንዱ የቤተ ክርስቲያን ልሳን በስተቀር ሁሉም ተወርሰው በማስታወቂያ ሚኒስቴር ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን ጥናቱ ተናግሯል፡፡

የውጪ መገናኛ ብዙሃንም ከአገር መባረራቸውንም አስመልክቷል፡፡መገናኛ ብዙሃን በኢህአዴግ ዘመንም ከ1984 እስከ 85 አዲስ የነፃነት አየር የታየበት ሲሆን፣ 85 እስከ 89 የግል ህትመት ተበራክቶ፣ ከ1990 እስከ 1992 በሚዲያው ላይ የመንግስት ጉልበት ያየለበት ነው ተብሏል፡፡ከ1992 እስከ ምርጫ 97 ድረስም ሚዲያው ላይ የብዝሃነትና የጥራት ማንሰራራት የታየበት ጊዜ ነበር ተብሏል፡፡ከምርጫ 97 በኋላም ሰቆቃው ያገረሸበት መሆኑን ጥናቱ አስመልክቷል፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers