• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መጋቢት 11፣2011/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሒሳብ ምርመራ የተገኘበትን በመቶ ሚሊየን ብር የሚቆጠር ግኝት ለማስተካከል እየሰራሁ ነው አለ፡፡

የማስተካከያው እርምጃው ግን የሂሳብ ጉድለቱን ባገኘው መስሪያ ቤት ሳይረጋገጥ ተቀባይነት አይኖረውም ተብሏል፡፡በፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በ2009 በተደረገው የሒሳብ ምርመራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠር ብር ጉድለት አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ሀላፊዎች ጠርቶ በእያንዳንዱ ግኝት ላይ ስለወሰዱት የማስተካከያ እርምጃ ጠይቋቸዋል፡፡የስራ ሀላፊዎቹ በምክር ቤቱ ተገኝተው ዛሬ በሰጡት መልስ የስራ መርሃ ግብር ወጥቶ በኦዲት ግኝቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል፡፡

ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ በሒሳብ ምርመራ አግኝቸዋለሁ ካለው ጉድለት መካከል ሁለተኛው የዲያስፖራ በዓል ዝግጅት ላይ የወጣ የ7 ሚሊዮን ብር ወጪ ማስረጃ አልቀረበበትም፡፡ለ28ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወጪ ተደርጓል የተባለ 14 ነጥብ 9 ሚሊየን ብርም ማስረጃ ያልቀረበበት ነው ተብሏል፡፡ከበጀት አስተዳደር መምሪያ ውጪ በጀት ስለመኖር አለመኖሩ የሚያረጋግጥ ስምና ፊርማ ሳይኖርም 183 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ለአፍሪካ ህብረት አባል አገራት መዋጮ ክፍያ በሚል ወጪ ተደርጓል ይላል የኦዲት ግኝቱ፡፡የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በጀትን በእቅድ ከመምራትና ወጪዎችን በትክክል ከመመዝገብ አኳያ ጉድለት አለበት የሚል ወቀሳም ከቋሚ ኮሚቴው ቀርቦበታል፡፡እንደምሳሌም በ2009 በጀት አመት ከአጠቃላይ በጀቱ ጋር ሲነፃፀር በድምሩ 330 ሚሊየን ብር ከበጀት ብልጫ ያለው ገንዘብ ወጪ እንደተደረገ ተመዝግቧል ተብሏል፡፡የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች ግኝቶቹን ለማስተካከል ስራ ጀምረናል ብለዋል፡፡

የኦዲት ግኝቱ የገዘፈው ግን ከኢትዮጵያ የፋይናንስ ሕግ ጋር የማይጣጣም ህግ ባላቸው የተለያዩ አገራት የሚገኙ 60 ሚሲዮኖቻችንን ሒሳብ ስለምናስተዳድር ነው የሚል ሀሳብም አቅርበዋል፡፡የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ግን የሂሳብ ጉድለቱ በአገር ውስጥ የሚደረጉ ግዢዎችንም የሚያካትት ነው በሚል ሀሳባቸውን ሳይቀበሏቸው ቀርተዋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኦዲት ግኝቱን ለማስተካከል እየወሰድኩ ነው የሚለው እርምጃ በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ እስካልተረጋገጠ ድረስም ተቀባይነት እንደማይኖረው በቋሚ ኮሚቴው አባላት ተነግሯቸዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 11፣2011/ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዋጋቸው የማይታወቅ ንብረቶች በመጋዘን ተከማችተው እንደሚገኙ ተነገረ

በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዋጋቸው የማይታወቅ ንብረቶች በመጋዘን ተከማችተው እንደሚገኙ ተነገረ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ንጋቱ ረጋሳን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 11፣2011/ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የእግረኛና የመኪና ማቋረጫ መንገዶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ውጥን ተይዟል ተባለ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የእግረኛና የመኪና ማቋረጫ መንገዶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ውጥን ተይዟል ተባለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁንን ዘገባ ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 11፣2011/ በውላቸው መሰረት ቡና ለውጭ ገበያ ያላቀረቡ ላኪዎች ከግብይት መታገዳቸው ተሰማ

በውላቸው መሰረት ቡና ለውጭ ገበያ ያላቀረቡ ላኪዎች ከግብይት መታገዳቸው ተሰማ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምህረት ሥዩምን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 11፣2011/ ኢትዮጵያ ያልተጠቀምችባቸው ብዙ የራሷ መድሃኒቶች እንዳሏት ይነገራል

ኢትዮጵያ ያልተጠቀምችባቸው ብዙ የራሷ መድሃኒቶች እንዳሏት ይነገራል፡፡ የት ይሆን የሚገኙት? ለምን አገልግሎት የሚውሉ ይሆኑ? የተሰጣቸውስ ትኩረት?

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ቴዎድሮስ ብርሃኑን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 10፣2011/ በአዲስ አበባ በሕንፃ መወጣጫ መደርመስ አራት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ

በአዲስ አበባ በሕንፃ መወጣጫ መደርመስ አራት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ፡፡ 5ኛውን ሰው ከወደቀበት ጉድጓድ እስካሁን ማውጣት አልተቻለም፡፡ 5ኛውን ሰው 8፡07 ሰዓት ላይ ከጉድጓዱ ማውጣት ተችሏል፡፡ ጉዳት ደርሶበት ወደ አለርት ሆስፒታል ተወስዷል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ሀይሉን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 10፣2011/ የሰላም ሚኒስቴር በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ 1.7 ሚሊየን ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ስራው የሚያግዝ ቡድን ከነገ ጀምሮ ላሰማራ ነው አለ

የሰላም ሚኒስቴር በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ 1.7 ሚሊየን ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ስራው የሚያግዝ ቡድን ከነገ ጀምሮ ላሰማራ ነው አለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁንን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 10፣ 2011/ በኢትዮጵያ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉትን ጨምሮ 8.3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል

በኢትዮጵያ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉትን ጨምሮ 8.3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል፡፡ የእርዳታ አሰጣጡ ምን መሳይ ነው? ንጋቱ ሙሉ የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነርን አነጋግሯል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 10፣ 2011/ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኳታር ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ወደ ዶሃ ሄደዋል

የኳታሩ አሚር ሼክ ተሚም ቢን አህመድ አልታኒ፤ ዶሃ እንደደረሱ ተቀብለው ሊያነጋግሩዋቸው መዘጋጀታቸውን ፔንንሱላ ኳታር ዘግቧል፡፡ሁለቱ መሪዎች ባለፈው ህዳር ወር በስልክ ተነጋግረው እንደነበረ ተጠቅሷል፡፡በስልክ ውይይታቸውም ፣ በሁለቱ አገሮች መካከል መኖር ስለሚገባው ግንኙነትና ትብብር አንስተው ነበር፡፡ከሁለት አመታት በፊት፣ በህዳር ወር 2009 ዓ.ም. በመከላከያ ትብብር፣ ዲፕሎማቶች ወደየአገሮቹ ሲገቡ የቪዛ አስፈላጊነትን መሰረዝና ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ላይ የተመረኮዘ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 10፣2011/ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙና ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚበልጡ ድጋፍ ፈላጊዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙና ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚበልጡ ድጋፍ ፈላጊዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ተባለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ንጋቱ ረጋሳን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 10፣2011/ ኢትዮጵያ እና ዲሞክራሲ ሆድና ጀርባ የሆኑት ለምንድነው?

ኢትዮጵያ እና ዲሞክራሲ ሆድና ጀርባ የሆኑት ለምንድነው?

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ንጋቱ ሙሉን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers