• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ስለምን አብረው በኖሩ ሕዝቦች መሃል መጠላላት እና መገዳደል ሊከሰት ቻለ?

በየቀኑ የምንሰማው ወሬ ጅማት የሚያኮማትር ሆኗል፡፡ በዚህ አካባቢ ግጭት ተነሳ፣ ዜጎች ሞቱ፣ ተፈናቀሉ የሚለው ወሬ አላቋርጥ ብሏል፡፡ሰላም ለአንዱ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ የሰላምን አየር የሚረብሽ ድርጊት የሚፅሙት እየበረከቱ በመምጣታቸው ማስደንገጥ ብቻ ሳይሆን እንቅልፍ የማያስወስድ ስጋት ነው፡፡ አንዱ በሌላው ላይ ክንዱን እያነሳ ሃገር ሲበጠበጥ የማህበረሰቡ የሰላምና የእድገት ጉዞ ተደናቅፏል ማለት ነው፡፡ ስለምን አብረው የኖሩ ሕዝቦች እስከመጠፋፋትና መጠላላት ደረሱ፡፡ እንደ መንግስት፣ እንደ ማህበረሰብ ማድረግ ከሚገባን የተጓደለብን ምንድን ነው? ንጋቱ ረጋሣ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን አዘጋጅቷል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፉት 27 ዓመታት ከሐገር የሸሸው ሐብት ጉዳይ

ኢትዮጵያ በ27 አመት ውስጥ 36 ቢሊዮን ዶላር ወይም አንድ ትሪሊዮን 80 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚገመት ሀብት ሸሽቶባታል፡፡ ይህ የገንዘብ አቅም ወይም የሀብት አቅም በ80 ቢሊዮን ብር ሂሳብ 13 የህዳሴ ግድቦችን ለመገንባት የምችል የገንዘብ መጠን ነው፡፡በተደጋጋሚ የውጭ ምንዛሪ ከጓዳዋ የሚጎልባት፣ ከተሰበሰበውም የሚመነተፍባት ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ በግፍ እና በተጋነነ ዋጋ ሀብቷ ከሀገር ሸሽቷል፡፡ ለአንድ ሀገር ጤናማ ኢኮኖሚ መኖርም የውጭ ምንዛሪን ማስተዳደር እና መቆጣጠር እንደ ዋና ስራ ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን ቸልታው እየበዛ ቁጥጥሩም እየላላ በመቀጠሉ ይዞ የመጣውን ችግር አፍጥጦ እያየነው ነው፡፡ ተህቦ ንጉሴ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ሀብቷ በምን መንገድ ሲሸሽ ቆይቷል ? ይዞ የመጣውስ ችግር ምንድን ነው? ሲል የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሚከበርበት መንገድ በርግጥ ኢትዮጵያውያንን ከነማንነታቸው የሚያተሳስር ነበር ወይ? ሌላስ አማራጭ አለ ወይ?

ዛሬ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለ13ኛ ጊዜ ታስቦ ይውላል፡፡ ህዳር 29 የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሆኖ ላለፉት 12 አመታት ሲከበር ቆይቷል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በልዩነት አንድነትን፣ በአንድነትም ልዩነትን እየሰበከ በተለያዩ አካባቢዎች ሲከበር ቆይቷል፡፡ ይሁንና ልዩነቱ እየሰፋ የሚያስተሳስረው ገመድ እየሰለሰለ መሆኑን አሁን በየእለቱ የምንሰማቸው ዘገባዎች ያረጋግጣሉ፡፡የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሚከበርበት መንገድ በርግጥ ኢትዮጵያውያንን ከነማንነታቸው የሚያተሳስር ነበር ወይ? ሌላስ አማራጭ አለ ወይ? የንጋቱ ሙሉ ዝግጅት ይህን ይመለከታል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የምርጫ ቦርድ ተዓማኒነቱን አግኝቶ የተሳካ የስራ ውጤት ለማሳየት እንዴት ሊሰራ ተዘጋጅቷል?

የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የደጋፊዎቻቸውን አመኔታ አጥቶ የነበረው የምርጫ ቦርድ በአዲስ የሰው ሀይል ተደራጅቶ የሚቀጥለውን ምርጫ እንዲያስተባብር ይጠበቃል፡፡ ቀጣዩ ምርጫ የቀረው ጊዜ የምርጫ ዝግጅት ለማድረግ በቂ አይደለም በሚባልበት በአሁኑ ወቅት የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ተሰይመዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ አባላት ገና ባይሰየሙም ለአዲሷ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር የፖለቲካ ፓርቲዎች አዎንታዊ ድጋፍ እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ ታዲያ የምርጫ ቦርድ ተዓማኒነቱን አግኝቶ የተሳካ የስራ ውጤት ለማሳየት እንዴት ሊሰራ ተዘጋጅቷል? የኔነህ ሲሳይ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ጠይቋቸዋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“ሌላ ሐገር የለንም - ሌላ ሐገር የለንማ” አካባቢውን አፅድቶ ውብ ያደረገው የጦር ሐይሎች ሰፈሩ በኃይሉ ተረዳ

ባህርዳር ሳለ ሶፍት ተጠቅሞ ሲጥል የተመለከተው አንድ የከተማዋ ታዳጊ፣ “ተዉት የአዲስ አበባ ልጅ ስለሆነ ነው” ብሎ እሱ የጣለውን ሶፍት በሶፍት አንስቶ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሲጥል ሲያይ ክስተቱ ጭንቅላቱን ነካው…“ሌላ ሐገር የለንም - ሌላ ሐገር የለንማ” አካባቢውን አፅድቶ ውብ ያደረገው የጦር ሐይሎች ሰፈሩ በኃይሉ ተረዳ…

በኃይሉ ተረዳ የወዳደቁ ካርቶን እና ላስቲኮችን ከየድርጅቶቹ እየገዛ ወደተለያዩ ነገሮች እያለወጣቸው መልሶ በመሸጥ ነው የሚተዳደረው፡፡ እሱ ግን በዚህ አልቆመም…የዛሬ ሁለት ዓመት ባህር ዳር ሄዶ ያጋጠመው ክስተት ነው አመለካከቱን የቀየረው፡፡ ባህርዳር ሳለ ሶፍት ተጠቅሞ ሲጥል የተመለከተው አንድ የከተማዋ ታዳጊ፣ “ተዉት የአዲስ አበባ ልጅ ስለሆነ ነው” ብሎ እሱ የጣለውን ሶፍት በሶፍት አንስቶ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሲጥል ሲያይ ክስተቱ ጭንቅላቱን ነካው፡፡

አዲስ አበባ የሚሰራበት ቦታ ያለውን ቆሻሻ ሲመለከት ከባህርዳሩ ልጅ ንግግር ጋር ተደምሮ እረፍት ነሳው፡፡ ወዲያው በራሱ ጉልበትና ለሚያግዙት ከራሱ ኪስ እየከፈለ አካባቢውን ማፅዳት ጀመረ፤ አካባቢውን ያፀዳል፣ የተቆፈረ መንገድ ይጠግናል፣ ያፀዳው ቦታ ላይ ቆጣሪ አስገጥሞ ቦታውን ብርሃን በብርሃን አድርጎታል - ይህ ሁሉ በራሱ ወጪ እና ጉልበት የተከወነ ነው ይለናል በኃይሉን ያነጋገረው ወንድሙ ኃይሉ፡፡
በኃይሉ ሰዉ በየቦታው እንዳይሸናም መሽኚያ ቦታ አበጅቶ ከቱቦ ጋር አገናኝቶታል፡፡ አካባቢውን የሚጠብቁ ፖሊሶችና ደንቦች ፀሐይ ላይ እንዳይንገላቱ በሚልም መጠለያ አበጅቶላቸዋል፡፡ያፀዳውን አካባቢ ማታ እና ቀን የሚጠብቁ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞችም ቀጥሮ በወር አንድ አንድ ሺ ብር ይከፍላል፡፡ አካባቢውን ሲያፀዳ አብረውት ተፍ ተፍ ለሚሉትም ይከፍላል…ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የሆነው በኃይሉ፣ የምታስተላልፈው መልእክት ሲባል መልሱ ይህ ነው - “ሌላ ሐገር የለንም - ሌላ ሐገር የለንማ !”

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሸንኮራ አገዳ ልማት የትምህርት ዘርፍ ተመርቀው ሥራ ያጡት ተማሪዎች እሮሮ

በስኳር ፋብሪካዎች የመቀጠር ተስፋን ሰንቀው በሸንኮራ አገዳ ልማት የትምህርት ዘርፍ ከ3 አመት በፊት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ወጣቶች ስራ ማግኘት አለመቻላቸውን ተናገሩ፡፡ የበየነ ወልዴን ዘገባ ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ 74.5 ሚሊዮን ሄክታር ለእርሻ አመቺ የሆነ መሬት ቢኖራትም እየታረሰ ያለው ግን ከግማሽ ያነሰ መሆኑ ተነገረ

14 ሚሊዮን የሚሆኑ አባወራ አርሶ አደሮች እያረሱ ያሉት 35 ሚሊዮን ሄክታር ብቻ ነው፡፡ይህን የሰማነው የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ትናንት ምሽት ባካሄደው ወርሃዊ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡መነሻ የጥናት ፅሁፍ ያቀረቡት ዶ/ር መለሰ ተመስገን እንዳሉት አነስተኛ የመሬት ይዞታና የተበጣጠሰ ማሳ ገበሬውን አቅመ ቢስ አድርጎታል፡፡የሀገሪቱን የግብርና ዘርፍም አቀጭጮታል ብለዋል፡፡

የሀገሪቱን የግብርና ዘርፍ በማዘመን የምርት መጠንን ለመጨመር ያስችላሉ የተባሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ለማስገባትም የውጪ ምንዛሬ እጥረትና የአርሶ አደሩ የገቢ አቅም ውስን መሆን ማነቆ እንደሆነበትም አስረድተዋል፡፡መንግስት የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ በዘርፉ እርስ በርሱ እንዲወዳደር በመፍቀድ ግብርናውን ማዘመን ይችላል ያሉት ዶ/ር መለሰ ይሄን በዘርፉ ለማድረግ ግን መንግስት ከተፎካካሪነት ወጥቶ ደጋፊ ሲሆን ነው ብለዋል፡፡


ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጋራ ታሪክና ጀግኖች ላይ መስማማት አንድነትን የማጠናከሪያ አንዱ መንገድ መሆኑ ተነገረ

ትኩረትን በፌዴራሊዝም ዙሪያ ያደረገ አውደ ጥናት በጁፒተር ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡በአውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው፡፡ከእነዚህ ፅሁፎች አንዱ እንዳሳየው የጋራ ታሪክና ጀግኖች ላይ መስማማት የአንድነት ማጠናከሪያ አንዱ መንገድ ነው፡፡

ሕዝቦችን የሚያስተሳስሩ ሰፋፊ መሰረተ ልማቶችን መዘርጋትና ሰዎች በብዛት የሚሳተፉባቸው ሁነቶችን ማዘጋጀት አንድነትን ለማጠናከር እንደሚያግዙ ተነግሯል፡፡ልዩነትን ለመጨፍለቅ መሞከር ግን ውጤቱ አደገኛ እንደሚሆን ፅሁፉ ይጠቅሳል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ትብብር የተዘጋጀው ይህ አውደ ጥናት የተለያዩ የአፍሪካና የአውሮፓ አገራት የአንድነት ተሞክሮዎች ከሰዓት በፊት በነበረው ጊዜ ቀርበውበታል፡፡ከምሳ በኋላ በሚኖረው ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች የተመለከቱ ፅሁፎች እንደሚቀርቡበት የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተማሪዎች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በወቅቱና በአግባቡ አለመመለሳቸው ለግጭት አባባሾች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ እንደሚያሻ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ

በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተማሪዎች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በወቅቱና በአግባቡ አለመመለሳቸው ለግጭት አባባሾች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ እንደሚያሻ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡አስፋው ስለሺ በሐዋሳ ቆይታው ተማሪዎቹንና የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ ሃላፊዎች አነጋግሯቸዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከአንጀትና የውስጥ ደዌ ሕመሞች ጋር በተያያዘ ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት የሐገሪቱን የሕክምና ዘርፍ እያገዝኩ ነው ሲል ላንድ ማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ተናገረ

ከአንጀትና የውስጥ ደዌ ሕመሞች ጋር በተያያዘ ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት የሐገሪቱን የሕክምና ዘርፍ እያገዝኩ ነው ሲል ላንድ ማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ተናገረ፡፡ የምህረት ስዩምን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከጎዳና ተነስተው፣ስልጠና ወስደው፣ተመርቀው ዳግም ወደ ጎዳና

ጎዳና ተዳዳሪዎችን ከጎዳና ሕይወት ማላቀቁ በቋሚ የአስተሳሰብና የተግባር ተሃድሶ ካልተደገፈ ነገሩን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ያደርገዋል፡፡መንግሥት፣ በኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አመቻችነት በአዋሽ በአስቸጋሪ ሁኔታ ስልጠና የወሰዱ ወገኖች የሥራ እድል ስላልተፈጠረላቸው ዳግም ጎዳና ነው ቤቴ እያሉ ነው፡፡ አሁን መንግሥትም ሆነ ኤልሻዳይ ተጠያቂነቱን በየፊናቸው ከራሳቸው የማራቅ ሙከራ ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ችግሩ የቱ ጋር ነው? በየነ ወልዴ ለችግር ተጋልጠናል ያሉትን ወጣቶችና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ጠይቆ የሚከተለውን መረጃ አሰናድቷል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers