አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎችን ለመለየት ጥናት ተጀምሯል ተባለ

ሸቀጦችን በመደበቅ እና እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት ምክንያት የሚሆኑ ነጋዴዎች አሉ ያሉት አቶ አልቃድር እነዚህም ተለይተው ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ነግረውናል፡፡ፍትሃዊ ያልሆነ የመሸጫ ዋጋ ወስነው የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች እንዳሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ነጋዴዎቹ ፍትሃዊ ያልሆነ የመሸጫ ዋጋ ወስነው እየሰሩ ያሉት ያለምንም ኢኮኖሚያ ምክንያት ነውም ብለዋል፡፡ጥናቱን እያካሄደ ያለው ግብረ ሃይል ስራውን ከጀመረ ሶስት ሣምንት አንዳለፈው ሠምተናል፡፡
በቀጣዩ ሣምንት ስራውን አጠናቆ ውጤቱን እንደሚያስረክብ አቶ አልቃድር ነግረውናል፡፡በጥናቱ ህግ መተላለፋቸው የሚረጋገጥ ነጋዴዎች በባለስልጣኑ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል፡፡ህብረተሰቡም በግብይት ወቅት የሚያስተውላቸውን ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች በነጻ የስልክ ቁጥር 8478 እና 8077 ጥቆማ መስጠት ይችላል ተብሏል፡፡
ንጋቱ ረጋሳ