• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል

በሹመቱ ከፌዴራል ወደ ክልሉ የተዛወሩ ባለስልጠናትም አሉ፤ከፌዴራል ወደ ክልሉ ከተዛወሩ ባለስልጣናት መካከል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ይገኙበታል፤ዶክተር ነገሪ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል፤የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ አረጋ - በኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ  ፅህፈት ቤት የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ሆነዋል፤የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴም ወደ ክልሉ የተዛወሩ ሌላው ባለስልጣን ናቸው፤

ዶክተር ግርማ አመንቴ የኦሮሚያ ከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል፤ወይዘሮ ጠይባ ሃሠን ደግሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነዋል፤ወይዘሮ ጠይባ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል፤እስከ አሁን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ኡመር ሁሴን ናቸው፤  የአዳማ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ - የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ፤ አቶ ከፍያለው አያና ደግሞ በኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ  ፅህፈት ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል፤የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶክተር ዓለሙ ስሜም ከፌዴራል ወደ ኦሮሚያ ክልል የተዛወሩ ሌላው ባለስልጣን ናቸው፤
ዶ/ር አለሙ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

አቶ አሰግድ ጌታቸው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሃላፊ - ወይዘሮ ጫልቱ ሣኒ ደግሞ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነዋል፤የፌዴራል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሢሳይ ገመቹም እንዲሁ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ልማት ማስፋፋት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል፤የሞጆ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ወይዘሮ እልፍነሽ በዬቻ የአዳማ ከተማ ከንቲባ -  ወይዘሮ ሃቢባ ሢራጅ የለገጣፎ ከተማ ከንቲባ - ወይዘሮ ጫሊ ቤኛ ደግሞ የቡራዩ ከተማ ከንቲባ ሆነዋል፤በአጠቃላይ የተሿሚዎቹ ቁጥር 23 ሲሆን የተሾሙበት መስፍረትም አቅም፤ ፌዴራል ላይ ያለን ድርሻ መወጣት፤ እንዲሁም የወጣቶች ፤ ሴቶችና ምሁራንን መወጣትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፤   

 ንጋቱ ረጋሳ
 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ድምፃዊ ታምራት ደስታ ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ተነገረ

ድምፃዊ ታምራት ደስታ ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ተነገረ፡፡ድምፃዊው ህመም ተሰምቶት መኪና እየነዳ ወደ ስላሴ ክሊኒክ ሲሄድ ድንገት ራሱን መሳቱንና በኋላም በአምቡላንስ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ተወስዶ ህይወቱ ማለፉ መረጋገጡን ሸገር ሰምቷል፡፡ድምፃዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር፡፡ሸገር ለቤተሰቡና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከመላው ሐገሪቱ የተውጣጡ 25 ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር...

ከመላው ሐገሪቱ የተውጣጡ 25 ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር ያደረጉበትን የትላንትናውን የሚሊኒየም አዳራሽ ዝግጅት አስመልክቶ አስፋው ስለሺ የሚከተለውን አጠናቅሯል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሚያዝያ 9፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቢቹ ነጋ ነጋ…አቢቹ ሲታወስ ክፍል ሁለት

ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው በፋሺስት ወረራ ዘመን ስሙ የገነነውንና ለዘመናት የተዜመለትን የኢትዮጵያዊውን ጀግና የአቢቹን ታሪክ የዘከረበትን መሰናዶ ሁለተኛ እና የመጨረሻ ክፍል 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ድንቅነሽ የሴቶች ተሀድሶና ማጎልበቻ ማዕከል ለምን ተዘጋ ?

“ዩኒቨርሲቲ ስገባ ነው ሱስ የጀመርኩት - 12ኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ፡፡ 10 ዓመት ሱስ ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡ መጠጥ እና ሲጋራ ነው ዋንኛው ችግሬ፡፡ ጫትና ሐሺሽም ጀምሬ ነበር ግን ወዲያው ነበር የተውኳቸው፡፡ ከተመረቅኩ በኋላ የራሴን ቢዝነስ ጀምሬ ነበር፡፡ ሙሉ ብሬን በመጠጥ አጠፋሁት፡፡ መጠጥ ወደ ኋላ ጎትቶኛል፡፡ ባህሪዬን አሳጥቶኛል፡፡ ጠዋት ላይ ያሰራኛል ብዬ እጠጣለሁ፡፡ ማታ ላይ እንዲያደነዝዘኝ፡፡ ለመተኛት እጠጣለሁ፡፡ ጠጥቼ ተኝቼ ግን ለሊት ላይ እነቃለሁ፡፡ እንደገና ጠጥቼ እተኛለሁ፡፡ በዚህ መልኩ ቆይቼ ጠዋት ላይ እጄ መንቀጥቀጥ ሲጀምር ደነገጥኩ፡፡ ከዚህ ሱስ መውጣት አለብኝ አልኩ…” የምትለው ስሜ ይቅር ያለችን ወጣት ከሱስ መውጣት የቻለችው ሱስ ውስጥ ያሉ ሴቶች ከሱስ እንዲያገግሙ ለመርዳት በተቋቋመው ድንቅነሽ የሴቶች የተሐድሶና ማጎልበቻ ማዕከል ውስጥ ለ3 ወራት ሕክምና ካገኘች በኋላ ነበር…

የመጠጥ ቤት ባለቤት ሆነው በዛው በመጠጥ ሱስ ውስጥ ገብተው የነበሩ እንዲሁም ለሕክምና አገልግሎት የሚውለውን የሰመመን መስጫ በመውሰድ ሱስኛ ሆና የነበረችውም የሕክምና ባለሞያም ከሱሷ የተገላገለችው በዚሁ በድንቅነሽ የሴቶች የተሐድሶና ማጎልበቻ ማዕከል ውስጥ ነበር፡፡

አሳዛኙ ነገር ግን ለበርካታ ሱስ ውስጥ ላሉ ሴቶች ከሱስ የመላቀቅ ተስፋ የነበረው ይህ ማዕከል አሁን ላይ ተዘግቷል…

ለምን?

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቢቹ ነጋ ነጋ…አቢቹ ሲታወስ

ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው በፋሺስት ወረራ ዘመን ስሙ የገነነውንና ለዘመናት የተዜመለትን የኢትዮጵያዊውን ጀግና የአቢቹን ታሪክ የዘከረበትን መሰናዶ የመጀመሪያ ክፍል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሳይንስ መረጃዎች…

የዓለማችን ቋንቋዎች ሁሉ መነሻ ከአንድ አፍሪካዊ እናት ቋንቋ መሆኑ ተደረሰበት ይሉናል ሳይንቲስቶች፡፡ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የዓለማችን 6ሺ ያህል ዘመናዊ ቋንቋዎች እናት የሆነው ቋንቋ ከዛሬ 50 ሺ እስከ 70 ሺ ዓመታት ግድም በአፍሪካ ይነገር የነበረ ነው፡፡

የጥናት ውጤቱ እንደሚለው ይህ የሁሉ እናት የሆነ ቋንቋ ለሰው ልጅ ስልጣኔ፣ ለሰው ልጅ ወደ አዳዲስ አካባቢዎች መፍለስ እንዲሁም ለኪነትና የቴክኖሎጂ ጅማሮ መሰረት ነው፡፡በኒውዝላንዱ የኦክላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ክዊንቲን አትኪንሰን የተሰራው ጥናት እንዳሳየው የሰው ልጅ ንግግር የጀመረው ከዚህ ቀደም ከሚታሰበው ጊዜ ቀደም ብሎ ነው፡፡

ከዚህ ጥናት በፊት የነበሩ መላ ምቶች የዓለማችን ቋንቋዎች መነሻ ከአንድ በላይ ናቸው ይል ነበር፡፡ ይህ የአሁኑ ጥናት ግን የሁሉም የዓለማችን ቋንቋዎች እናት አንድ ነው ባይ ነው፡፡አትኪንሰን በጥናቱ በ504 የዓለማችን ቋንቋዎች ውስጥ ያሉን የተለያዩ ተነባቢ፣ አናባቢ እና መሰል የድምፅ እና ቋንቋ አለባውያን በመውሰድ ጥናቱን አካሂዷል - በዚህም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ያሉ ቋንቋዎች ሁሉ መነሻ አሁን ፈፅሞ የተረሳ በአፍሪካ በድንጋይ ዘመን ወቅት ይነገር የነበረ ጥንታዊ ቋንቋ ነው ይላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በዚህ አመት ይኖራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ እንደማይካሄድ ተነገረ

በዚህ አመት ይኖራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ እንደማይካሄድ ተነገረ፡፡ምርጫው የሚካሄድበት ቁርጥ ያለ ወርና ቀን ባይታወቅም በመጭው አመት 2011 ዓ.ም እንዲካሄድ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የምርጫው ጊዜውን አራዝሞታል፡፡የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም ለምክር ቤቱ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንደሚያስረዳው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለዚሁም ምርጫ የተሟላ ዝግጅት ለማድረግ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ያጋጠሙ የፀጥታ መደፍረስ እንቅፋት ሆኖበት ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የሃገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እስኪሆንና ቦርዱም ዝግጅቱን እስኪያጠናቀቅ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ ለመጪው አመት ተራዝሟል፡፡እስከመጪው የምርጫ ጊዜ አሁን የስልጣን ጊዜያቸውን የጨረሱና በስልጣን ላይ የቆዩ ባለስልጣናት ይቆያሉ ወይንስ ይነሳሉ የሚለው የምክር ቤቱን አባላት ያከራከረ ቢሆንም መልስ ያላገኘ ጥያቄ ሆኖ አልፏል፡፡

የምርጫ ጊዜው ሲራዘም በደፈናው በ2011 ይካሄዳል የሚለው የውሳኔ ሀሳብም የምክር ቤት አባላትን ዘለግ ላሉ ደቂቃዎች ያነጋገረ ጉዳይ ነበር፡፡ገሚሶቹ ከ6 ወር በላይ መራዘም የለበትም በ2011 ዓ/ም እስከ ታህሳስ ወር መካሄድ አለበት የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው ለምርጫው ምቹ ጊዜ እስኪገኝ ድረስ በመጪው አመት ይካሄዳል የሚለው ተይዞ ድምፅ እንዲሰጥበት አድርገዋል፡፡ምርጫውን ለማራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብም በ8 ድምፀ ተአቅቦና በአብላጭ ድምፅ ፀድቋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ሸገር ልዩ ወሬ:- በእኔ የደረሰው በሰው እንዳይደርስ ትራፊክ አስተናብራለሁ

በደረሰበት የመኪና አደጋ ሳቢያ በዊልቸር የሚንቀሳቀሰው የብርጭቆ ሰፈሩ ሀብታሙ ኃይሌ “በእኔ የደረሰው በሰው እንዳይደርስ፣ ወገኖቼ በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን እንዳያጡ፣ አካላቸውን እንዳይጎድል” በሚል ከጠዋት እስከ ማታ በየቀኑ የሰፈሩን መኪኖች በራሱ ተነሳሽነት እንደ ትራፊክ ያስተናብራል…

ፊቱ ላይ ዘወትር ደስታ የሚነበብበት ሃብታሙ ይህን የመኪኖች ማስተናበር ስራውን ሲሰራ 9 ዓመት አልፎታል፡፡ጠጥታችሁ አታሽከርክሩ፣ ፍጥነት አደጋ ያመጣል፣ እግረኞችም በዜብራ ማቋረጥን ልምድ አድርጉ ሲል ይመክራል ሃብታሙ፡፡

እስከ 7ኛ ክፍል የተማረውና ከአባቱና ከወንድሙ ጋር የሚኖረው ሃብታሙ አሸከራካሪዎች በሚሰጡት አንድም ሁለት ብር ነው ኑሮውን የሚገፋው፡፡የወንድሙ ኃይሉን የልዩ ወሬ ዘገባ ተከታተሉ…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers