• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሰኔ 10፣ 2011/ በአማራ ክልል በተፈጠረ ግጭት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰባ በመቶዎቹ ወገኖች ወደተዘጋጀላቸው አምስት አዳዲስ ከተሞች እንዲገቡ መደረጉ ተሰማ

በአማራ ክልል በተፈጠረ ግጭት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰባ በመቶዎቹ ወገኖች ወደተዘጋጀላቸው አምስት አዳዲስ ከተሞች እንዲገቡ መደረጉ ተሰማ፡፡ወንድሙ ሀይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣2011/ ለነባርና አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያስፈልገው የሀይል አቅርቦት በግሉ ዘርፍ ይሸፈናል ተባለ

ይህ የተነገረው በመጀመሪያው የውሃና የኢነርጂ ሳምንት መክፈቻ ላይ ነው፡፡ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ለነባርና አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያስፈልገው 1 ሺ 500 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በግሉ ዘርፍ እንዲሰራበት እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል ብለዋል፡፡

አገሪቱ የጀመረችውን ለውጥ ለማስቀጠል የውሃና የኢነርጂ ሀብቶችን አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ፕሬዝዳንቷ ከታዳሽ ሀይል ኤሌክትሪክ የማመንጨት ጉዳይም ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል፡፡በስካይ ላይት ሆቴል የተከፈተው የውሃና የኢነርጂ ሳምንት በውሃ፣ በመስኖና ኢነርጂ ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት ሲሆን መንግስት ለእነዚህ ዘርፎች የሰጠው ትኩረትና ሊከተላቸው የሚገቡ አቅጣጫዎች በተለያዩ ውይይቶች ይዳሰሳሉ ተብሏል፡፡

ማህሌት ታደለ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣ 2011/ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የብፌ ደላጋር ሆቴል ሙሉ ለሙሉ አልፈረሰም አለ

ቢሮው ሆቴሉ ከአካባቢው ልማት ጋር በተያያዘ የፈረሰ ቢኖርም የአካባቢው የያን ጊዜውን ታሪክ የሚያስታውሰው ክፍል ግን እንዳልተነካ ለሸገር ተናግሯል፡፡የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ዋና ስራ ሀላፊ ነብዩ ባዬ ብፌ ደላጋር ሆቴል ጀርባ የነበሩ የቆዩ የባቡር ነጅዎች ማደሪያም እንዳልፈረሰ ነግረውናል፡፡

በለገሀር፣ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ባለሀብቶች ጋር መልሶ በሚለማው አካባቢ የሚሰራው ባለ አምስት ኮከብ ሆቴልም ስያሜ ብፌ ደላጋር እንደሚባልም ከዋና ስራ ሀላፊው ሰምተናል፡፡በለገሃር የብፌ ደላጋር ሆቴልም ሙሉ በሙሉ ፈረሰ የተባለው ሀሰት እንደሆነ ባህልና ቱሪዝም ተናግሯል፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣2011/ አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ከጥቂት ወራት በፊት ለተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መውደቅ ጥፋቱ የአብራሪው ነው ማለታቸውን አየር መንገዱ በፅኑ ተቃወመው

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም የኮንግረስ አባሉን አስተያየት በማስረጃ ያልተደገፈ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ከ3 ወራት በፊት ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 አውሮፕላን የ157 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፎበታል፡፡አደጋውን ተከትሎ በአለም ዙሪያ የዚህ ስሪት አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት ከበረራ ታግደዋል፡፡

ከኢትዮጵያው አደጋ 5 ወራት ቀደም ብሎ ደግሞ ንብረትነቱ የኢንዶኔዢያው ላየን ኤየር ንብረት የሆነ ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ ለ189 ሰዎች ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል፡፡የሁለቱም አውሮፕላኖች የአደጋ ፍጹም ተመሳሳይነት በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ 8 የአደጋ ምርመራ የቅድሚያ ሪፖርት በምህፃሩ ኤምካስ የተሰኘው የአውሮፕላኑ አውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት እክል ያስከተለው እንደሆነ ማሳየቱን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ይሁንና የአሜሪካ ኮንግረስ አባሉ ሳም ግሬቭስ የቅድሚያ ሪፖርቱ የአብራሪው ስህተት ለአደጋው አንዱ ምክንያት እንደነበር ያሳያል ሲሉ በዚሁ ጉዳይ ላይ በተደረገ ምክክር ወቅት መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

አብራሪው አሜሪካ ውስጥ የሰለጠነ ቢሆን ኖሮ ሁኔታውን በቀላሉ ይቆጣጠረው ነበር ሲሉም አክለዋል እንደራሴው፡፡ስለ ጉዳዩ ቢቢሲ የጠየቃቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፃሚ ተወልደ ገብረ ማርያም የሳም ግሬቭስን አስተያየት መሰረት የለሽ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡የኮንግረስ አባሉ በእጃቸው አንድም ማስረጃ እና የተጨበጠ ነገር የላቸውም ብለዋል፡፡አቶ ተወልደ ኢትዮጵያዊው አብራሪ አደጋውን ለማስቀረት ማድረግ ያለበትን ሁሉ ማድረጉን የምርመራ ቀዳሚ ሪፖርቱ ማሳየቱን አስታውሰዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ 380 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ከበረራ ውጭ መዳረጋቸውን ያነሱት አቶ ተወልደ ሰዎች ይሄ ስለምን ሆነ ብለው መጠየቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡የኮንግረስ አባሉን አስተያየትም ችግሩን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የማላከክ ሙከራ አድርገው እንደሚያዩትም አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡ቦይንግ ኩባንያ ራሱ የኢትዮጵያውም ሆነ የኢንዶኔዥያው ማክስ 8 አውሮፕላኖች አደጋ ከኤምካስ አውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ እክል ጋር ተያያዥነት እንዳለው በተደጋጋሚ ሲናገር መቆየቱን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣2011/ አንጋፋው ደራሲ አውግቸው ተረፈ በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ደራሲው ዛሬ ከለሊቱ 11 ሰዓት በቤተዛታ ሆስፒታል አርፏል፡፡አውግቸር ተረፈ፤ ወይ አዲስ አበባ፣ እብዱ፣ ያንገት ጌጡ፣ ጩቤው፣ ፅኑ ፍቅር፣ ደመኛው ሙሽራ (በጋራ)፣ የፍቅር ረመጥ፣ ሚስኪኗ ከበርቴ፣ ጣፋጭ የግሪም ተረቶች፣ የዓለም ምርጥ ተረቶች (1፣ 2 እና 3)፣ የግሪክ እና የሩሲያ ተረቶች እንዲሁም የትውልድ እልቂት (ትርጉም) እና ሌሎች መፅሐፍትንም ያሳተመ እንደነበር የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ነግሮናል፡፡

አውግቸው ተረፈ የደራሲው የብዕር ስም ሲሆን ሕሩይ ሚናስ ትክክለኛ መጠሪያ ስሙ ነበር፡፡ ሸገር ለአውግቸው ተረፈ ቤተሰቦች፣ ዘመድ ወዳጆች እና አድናቂዎች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 7፣ 2011/ ማዳበሪያ በጊዜ አለመድረስ ሰበቡ ምን ይሆን?

ክረምቱ መጣሁ መጣሁ እያለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የክረምት ወቅት የእርሻ ምርቶችን የሚዘሩበት ጊዜ ነው፡፡ ለገበሬዎች ይኽ ወቅት ከመኖር አለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ “አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተክለውም” እየተባለ የሚነገረውም ለዚህ ነው፡፡ ለእርሻ ስራ የሚያገለግለው ማዳበሪያ በአሁኑ ወቅት በገበሬው እጅ መግባት አለበት፡፡

ግን በአንዳንድ አካባቢ ያሉ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዳልደረሳቸው ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ጅቡቲ ላይ የደረሰው ማዳበሪያ በማጓጓዣ ችግር እዚያው እንደተከማቸ ነው ይባላል፡፡ ንጋቱ ረጋሣ የማዳበሪያ በጊዜ አለመድረስና ችግሩስ ምንድን ነው? ሲል ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣ 2011/ በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያረገው የተማሪዎች ምገባ 300 ሺህ ተማሪዎችን ሊያካትት እንደሆነ ተሰምቷል

በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያረገው የተማሪዎች ምገባ 300 ሺህ ተማሪዎችን ሊያካትት እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ይህን ያህል ብዛት ያላቸውን ተማሪዎች ለመመገብ ምን ያህል ዝግጁ ነው ሲል በየነ ወልዴ ተከታዩን መረጃ አሰናድቷል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣ 2011/ ድጎማ ተደርጎበት የሚገዛውን ነዳጅ ከፍ ባለ ዋጋ ለጎረቤት ሀገራት ለመሸጥ የሚሰራው አሻጥር ቢቀንስም ገና ሙሉ ለሙሉ እንዳልቆመ ተነገረ

ድጎማ ተደርጎበት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚገዛውን ነዳጅ ከፍ ባለ ዋጋ ለጎረቤት ሀገራት ለመሸጥ ታስቦ የሚሰራው አሻጥር ቢቀንስም ገና ሙሉ ለሙሉ እንዳልቆመ ተነገረ፡፡


ህይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣2011/ በአዲስ አበባ ከተማ 51 ህንፃዎች ያለመጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ መገኘታቸው ተሰማ

ሌሎች 66 ህንፃዎች ደግሞ የተለያዩ መሰረታዊ ነገሮችን ሳያሟሉ ከአዋጁ ውጭ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በ2010 ዓ/ም በፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በተደረገ የክዋኔ ኦዲት ተረጋጧል፡፡በናሙና ተወስደው ከታዩ የአዲስ አበባ ህንፃዎች መካከል 66 ህንፃዎች አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙት ሊፍት ሳይኖራቸው፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ሳይገጠምላቸው፣ ከተፈቀደው ውጭ ወለል ጨምረው ገንብተው፣ አደጋ በሚያደርስ መልኩ በውስጥና በውጭ የማጠናከሪያ ስራዎችን በመስራት መሆኑን ታዝቤያለሁ ብሏል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ፡፡

ሌሎች 37 ህንፃዎች ደግሞ ለመኪና ማቆሚያ የተፈቀደላቸውን የህንፃውን የስረኛው ወለል ለሌላ አገልግሎት ማለትም ለባንክ አከራይተው፣ ለእቃ ማከማቻ አድርገውና የመጋዘን አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 7፣ 2011/ በተማሪዎች እሮሮ የሚቀርብበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን ግንኙነት

ዩኒቨርስቲዎቻችን የመማር ማስተማር ሂደቱ በጥንቃቄ የሚመራባቸው አልሆኑም የሚሉ የተማሪዎች እሮሮ አለ፡፡ አንጋፋውና የብዙ ነገሮች ምሳሌ ሆኖ የሚጠቀሰው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችሉ መሰናክሎች ይታይበታል እየተባለ ይተቻል፡፡ የተማሪዎችና የመምህራን ግንኙነት የሰመረ አይደለም፤ አንዳንድ መምህራን በብቃት ችግር የተተበተቡ በመሆናቸው ዩኒቨርስቲውን የምርምር ምንጭ ለማድረግ አስቸግረዋል የሚል አስተያየት በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡

በየነ ወልዴ አስተያየቶቹን ሰብስቦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርን ጠይቋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 5፣ 2011/ በዓይን ጠባሳ ምክንያት የዓይን ብርሃናቸውን ላጡ ከ200 በላይ ዜጎች ከለጋሾች በተገኘ የዓይን ብሌን ብርሃናቸው እንዲመለስ ተደርጓል

በዓይን ጠባሳ ምክንያት የዓይን ብርሃናቸውን ላጡ ከ2 መቶ በላይ ዜጎች ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች በተገኘ የዓይን ብሌን ብርሃናቸው እንዲመለስ ተደርጓል ተባለ፡፡ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers