• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ባሳለፍነው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10 ሰዓት ከ56 ደቂቃ ገደማ በደብረ ብርሃን አቅራቢያ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል መለኪያ 4 ነጥብ 6 ሆኖ ተመዘገበ ተባለ

ባሳለፍነው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10 ሰዓት ከ56 ደቂቃ ገደማ በደብረ ብርሃን አቅራቢያ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል መለኪያ 4 ነጥብ 6 ሆኖ ተመዘገበ ተባለ…በሥፍራው አሁንም መጠነኛ የመሬት እንቅስቃሴ እየተስተዋለ ነው ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ኃላፊ ዶክተር አታላይ አየለ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ የመሬት መንቀጥቀጡን የመዘገብነው ፉሪ ባለው ዋና ጣቢያ ነው፡፡ አደጋው የተፈጠረበት ቦታ ከአዲስ አበባ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ሲሆን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አቆመ ማለት ባይቻልም ትንሽ ትንሽ እየታየ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር አታላይ ከዚህ የበለጠ ሊመጣም እንደሚችል በመገመት ህንፃዎች ሲገነቡ ጠንካራ መሠረት ሊኖራቸው ይገባል ሲሉ መክረዋል፡፡በደብረ ብርሃን ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው ንዝረት በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎችም የተሰማ እንደነበር ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሀገሪቱ አጋጥሞ በነበረው ሁከትና የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ከትራንስፖርት አልግሎት ራሱን ያቀበ ባለንብረት አለመኖሩን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተናገረ

በሀገሪቱ አጋጥሞ በነበረው ሁከትና የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ከትራንስፖርት አልግሎት ራሱን ያቀበ ባለንብረት አለመኖሩን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ከባለንብረቶች መካከል ተሽከርካሪዎቻችን ወድመውብናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ከዘርፉ የወጡ የሉም የሚሉት የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ ካሣሁን ኃይለማርያም ናቸው፡፡

በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት 44 ተሽከርካሪዎች የቃጠሎ ሰለባ መሆናቸውን አቶ ካሁን ለሸገር  ተናግረዋል፡፡በዚሁ ምክንያት ተሽከርካሪዎቻቸው ለወደሙባቸው ባለንብረቶች መንግሥት ተገቢውን ማጣራት ፈፅሞ ከጉዳታቸው የሚያገግሙበት አማራጭ ይመለከታል ይላሉ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ የማተኩረው መብትን በማሳወቅ ላይ ነው ብሏል

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ የማተኩረው መብትን በማሳወቅ ላይ ነው ብሏል…ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ በተሰጠው ሥልጣን የመመርመርና የመክሰስ ተግባራትን ያከናውን ነበር፡፡የመመርመር ኃላፊነት ወደ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመክሰሱ ሥልጣን ደግሞ ወደ ፌዴራል ዐቃቤ ሕግ እንዲተላለፍ በመደረጉ አሁን ትኩረቱ በዘርፉ ተወዳዳሪነት እንዲኖር መስራት ነው ተብሏል፡፡በባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ እንደነገሩን አንዳንድ ሰዎች ይህን ባለማወቅ አሁንም ጥቆማዎችን ይዘው ይመጣሉ፡፡

ባለሥልጣኑም ጥቆማውን ተቀብሎ ወደ ፌዴራል ፖሊስና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እያስተላለፈ ይገኛል ብለዋል፡፡የባለሥልጣኑ ትኩረት ግን ከዚህ በኋላ ፀረ ውድድር ተግባራትን መካላከል፣ ግንዛቤ መፍጠርና መብትን ማሳወቅ እንደሚሆን ነግረውናል፡፡በዘርፉ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በነገው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን የዓለም የንግድ ውድድር ቀን እንደሚከበርም ከአቶ እንዳልካቸው ሰምተናል፡፡

ቀኑ የሚከበረው “የንግድ ተወዳዳሪነት ለኢኮኖሚያችን ዕድገት” በሚል መሪ ቃል ነው ብለዋል፡፡ከተለያዩ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች የተወከሉ ተሳታፊዎችና ሌሎች ታዳሚዎች በዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡በዓለም እቀፍ ደረጃ ደግሞ ቀኑ ዛሬ እየተከበረ እንደሚገኝ ነው የሰማነው፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 26፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ ትኩረቴ በዘርፉ ተወዳዳሪነት እንዲኖር መስራት ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከት የሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎቻቸው ለወደሙባቸው መንግሥት የማገገሚያ አማራጮችን እየመረመረ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በደብረ ብርሃን አቅራቢያ ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 4 ነጥብ 6 ሆኖ የተመዘገበ ነበር ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ የነጋዴዎችን የግብር ከፋይነት ደረጃ አሻሽሏል፡፡ በአዋጁ መሠረት የነጋዴዎቹን ደረጃ ለማስተካከልም ዓመታዊ ገቢያቸው ሊጠና ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ሮትራክት አቦጊዳ ክለብ የደም አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የደም ልገሳ አደረግኩ አለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የነዳጅ ፍጆታን እና የተበከለ ጋዝ መጠን የሚቀንስ መሣሪያ በቅርቡ ሥራ ላይ እንደሚያውል ተናግሯል፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ሩዝ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ትላንት ተፈፅሟል፡፡ በተለያዩ ሀገሮችም ታስበው ውለዋል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት ሚኒስቴር ወጣቶች በፈለጉት የፖለቲካ አስተሳሰብ ቢደራጁ የሚያግዝና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስትራቴጂ ተግባራዊ ላዳርግ ነው አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • አዲስ ይሰራል የተባለው የቄራዎች ድርጅት ግንባታ ከተመደለበት ጊዜ ሊጓተት ይችላል ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 23፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ “የመጥፋት ስጋት በተጋረጠባቸው ባህላዊ ቅርሶች ዙሪያ” በሚመክረው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ትናንት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መግባታቸው ተነገረ፡፡
 • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚመሩት የልዑካን ቡድን ጋር ትናንት አቡዳቢ ከተማ መድረሳቸውን የፃፈው የኢሚሬትስ ዜና አገግሎት ነው፡፡
 • የኢሚሬትስ ከፍተኛ ሹሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮýላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ተነግሯል፡፡
 • “የመጥፋት ስጋት በተጋረጠባቸው ባህላዊ ቅርሶች ዙሪያ” የሚመክረው ጉባዔ ዛሬ ዱባይ ውሰጥ ተጀምሯል፡
 • በጉባዔው ላይ የሌሎች ሀገራት መሪዎችም እየተሳተፉ ናቸው ተብሏል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት ጋር አጣጥመው የቤተሰብ ህጐቻቸውን ያላሻሻሉ ክልሎች የሴቶችንና የህፃናትን መብት ለማስጠበቅ ሲባል ህጐቻቸን እንዲያሻሽሉ ይደረጋል ተባለ

ከኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት ጋር አጣጥመው የቤተሰብ ህጐቻቸውን ያላሻሻሉ ክልሎች የሴቶችንና የህፃናትን መብት ለማስጠበቅ ሲባል ህጐቻቸን እንዲያሻሽሉ ይደረጋል ተባለ፡፡በግለሰቦች ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ ሴቶችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅም ደንብ እየተረቀቀ ነው ተብሏል፡፡ወሬውን የሰማነው ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ አምስት የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲመክር ተገኝተን ነው፡፡ስድስት ምዕራፎችን በያዘው ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት መርሃ-ግብር ሰነድ ላይ ምክር ቤቱ ዛሬ ለሦስተኛ ቀን ሲመክር ውሏል፡፡

ሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን፣ የአዕምሮና የአካል ጉዳት ያለባቸውና የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ዜጐችን መብቶች ተፈፃሚነታቸው እንዲበረታ በሰነዱ አዳዲስ መርሃ-ግብሮች መካተታቸውን ሰምተናል፡፡በህፃናት ላይ የሚደርስን የወሲብ ጥቃት፣ የጉልበት ብዝበዛና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የፍትህ አካላት በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚያገግሙባቸው ማዕከላት በጣት የሚቆጠሩ በመሆናቸው ማስፋፋት እንደሚያስፈልግም ተነግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በለጋ እድሜ ላይ ያሉ ህፃናት የአልኮል መጠጥን አለ ከልካይ በቀላሉ ከግሮሰሪዎች እያገኙ ነው ተባለ

በለጋ እድሜ ላይ ያሉ ህፃናት የአልኮል መጠጥን አለ ከልካይ በቀላሉ ከግሮሰሪዎች እያገኙ ነው ተባለ…በአዲስ አበባ በ15 ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት 64 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች በቀላሉ የአልኮል መጠጦችን ከመደብሮች እንደሚገዙ ተነግሯል፡፡

መጠጥ ቸርቻሪዎቹ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት መሸጥ የተከለከለ መሆኑን ቢያውቁም ጥቅማቸውን በማስቀደም እየሸጡ ነው ተብሏል፡፡ይህን የሰማነው የአዲስ አበባ የምግብ የመድኃኒት የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ከሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ጋር በመሆን ከተፈቀደው እድሜ በታች አልኮል መጠጥ መጠጣትን ለመቀነስ ባዘጋጀው ምክክር ላይ ነው፡፡ባለሥልጣኑ ይህንን ለመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው ቢሆንም ህጉን ለማስፈፀም ያስችላል የተባለው መመሪያ ገና እየተሰናዳ መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ወረቴ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 22፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ የአልኮል መጠጥን መሸጥ የተከለከለ ነው ቢባልም ታዳጊዎቹ ያለ ከልካይ መጠጥ እየገዙ ነው ተብሏል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ከውጭ የሚገቡ የእፅዋት ዝርያዎች በአገር በቀሎቹ ላይ የሚያደርሱትን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና ለማስቀረት ኧረ መላ ምቱ እየተባለ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የትራፊክ አደጋ የሚበዛበት 18 ማዞሪያ ጊዜያዊ መፍትሄ እየተበጀለት ነው ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤላውያን በኢትዮጵያ የቀሩ ዘመዶቻቸው ወደ እሥራኤል እንዲመጡላቸው ለአገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሠማ፡፡ (የኔነህ ከበደ)
 • XCMG የተባለ የቻይና ኩባንያ ከፍተኛ ውጤት ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እረዳለሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊታችን ጥር መጨረሻ አንስቶ ወደ ጊኒ ኮናክሪ በረራ ሊጀምር ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ተመዘገበ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የሴቶችና የሕፃናት መብት ለማስጠበቅ የየክልሎቹ ሕጐች ከሕገ መንግሥቱ ጋር መጣጣም እንዳለባቸው ተጠየቀ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሣኔ ከተላለፈበት በኋላ ከወንጀሉ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተገኘ ግለሰቡ የሚካስበት ህግ ሊወጣ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሣኔ ከተላለፈበት በኋላ ከወንጀሉ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተገኘ ግለሰቡ የሚካስበት ህግ ሊወጣ ነው ተባለ…ይህንን ያሉት የፌዴራል ምክትል ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ምትኩ ማዳ ናቸው፡፡

እስካሁን ይህን የመሰለ የህግ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ የለም ያሉት አቶ ምትኩ በመጪው ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው በሁለተኛው የሰብዓዊ መብት መርሃ-ግብር በስህተት የተፈረደባቸው ግለሰቦች ከወንጀሉ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተገኘ ለደረሰባቸ በደል የሚካሱበትና ስህተት የፈጠሩ የፍትህ አካላትም ተጠያቂ የሚሆኑበት የህግ ማዕቀፍ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አቶ ምትኩ ይህንን ያሉት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ሰነዱን መነሻ አድርገው የምክር ቤቱ አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው፡፡ከዚህ ቀደም የተለያየ የህግ ማዕቀፍ ያልተበጀላቸው፣ ለከባድ ወንጀሎች ምስክር ለሆኑና ለጠቋሚዎች የሚደረግ የህግ ከለላ ጠንካራ አይደለም ይህንን ችግር ለመፍታት ሰነዱ ምን ፋይዳ አለው በኢትዮጵያ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የሰብዓዊ መብቶች መካከል በህይወት የመኖር መብት አንዱና ዋናው ነው፤ በህይወት ያለመኖር መብትስ ለምን ወንጀል ይሆናል እንደ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ለምን አይታይም የሚሉ ጥያቄዎችም ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተው ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየመከሩ ነው

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየመከሩ ነው…ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በፌዴሽን ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ 30 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ሲመክሩ ይውላሉ፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴርና የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬቴርያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የፖለቲካ ፖርቲዎቹን ሲያወያዩ አንደሚውሉ ሰምተናል፡፡የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው በፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተነሳሽነትና ጥያቄ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

ውይይቱ ለጋዜጠኞች ክፍት ባለመሆኑ ዝርዝሩን ልንነግራችሁ አልቻልንም፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 21፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በማህበራዊ ግልጋሎት አሰልጥኖ በየወረዳ ለሥራ የመደባቸው ሠራተኞች ብንመደብም ሥራ እየሰራን አይደለም አሉ፡፡ ቢሮው ግን በየወረዳው የመደብኳቸው እስከ ሥራ ድርሻቸው ነው ይላል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ጥጥ አሰባሰቡ ላይ በሚፈጠር የጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በሚመረቱት የፋብሪካ ውጤቶች ላይ የጥራት ማነስ እንደሚያስከትል ተነገረ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • ከፍርድ በኋላ ከወንጀል ነፃ መሆናቸው የሚረጋገጥ ፍርደኞች የሚካሱበት ሕግ ሥራ ላይ ሊውል ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ የባሕል ልብሶች በአሜሪካ ፈላጊ በዝቶላቸዋል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር ሽር ጉድ ላይ የምትገኘው ሐረር ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ነው ብላለች፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ቤተ-ሙከራዎች አቅም ያንሣቸዋል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየመከሩ ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers