• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ እንደአሸን የፈሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተዋህደው አንድ መሆን ይችሉ ይሆን?

ኢትዮጵያ ውስጥ እንደአሸን የፈሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተዋህደው አንድ መሆን ይችሉ ይሆን? የንጋቱ ሙሉን ዝርዝር ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በቡራዩ በተከሰተው ግጭት ሰዎች መሞታቸውና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮምሽን ተናግሯል

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በቡራዩ በተከሰተው ግጭት ሰዎች መሞታቸውና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮምሽን ተናግሯል፡፡ የአስፋው ስለሺን ዝርዝር ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከቡራዩ ከታና ከአጎራባች ወረጃዎች የተፈናቀሉ ሰዎች በአዲስ አበባ አንዳንድ ቦታዎች በግዜያዊነት ተጠልለዋል ተባለ

ከቡራዩ ከታና ከአጎራባች ወረጃዎች የተፈናቀሉ ሰዎች በአዲስ አበባ አንዳንድ ቦታዎች በግዜያዊነት ተጠልለዋል ተባለ፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትናንት ጎብኝተዋቸዋል፡፡ የአስፋው ስለሺን ዝርዝር ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ ኦባንግ ሜቶን:-አጀማመሩ በጋምቤላ ሕዝቦች ሆኖ እያደር ወደ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት ተከራካሪነት የተሸጋገረው ተቋም

ባለፉት 11 ዓመታት በአሜሪካና በካናዳ የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥረት ማድረጉ የሚነገርለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አመራሮች ሰሞኑን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ አጀማመሩ በጋምቤላ ሕዝቦች ሆኖ እያደር ወደ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት ተከራካሪነት የተሸጋገረው ተቋም ስለአመሰራረቱና ስለሥራ አፈፃፀሙ የኔነህ ሲሳይ መሥራቹን አቶ ኦባንግ ሜቶን አነጋግሯል፡፡ 

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዳኞች በፖለቲካ አቋማቸው ሳይሆን በችሎታቸው ሊመረጡበት በሚችሉበት ደረጃ ላይ ተደርሷልን?

መቼም የሁሉም ዲሞክራሲያዊ ሂደት መክደኛ ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ስርዓት መኖር ነው፡፡ ታዲያ የፍትህ ስርዓቱ ተጠናክሯል? የፍርድ ቤቶችስ ነፃነት እርግጥ ተረጋግጧልን ? ዳኞች በፖለቲካ አቋማቸው ሳይሆን በችሎታቸው ሊመረጡበት በሚችሉበት ደረጃ ላይ ተደርሷልን? ትዕግስት ዘሪሁን ይህን አስመልክቶ ያዘጋጀችውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኦነግ አቀባበል አስተባባሪ ኮሚቴ የአቀባበል ዝግጅቱ ወደ መጠናቀቁ ነው ብሏል

የኦነግ አቀባበል አስተባባሪ ኮሚቴ የአቀባበል ዝግጅቱ ወደ መጠናቀቁ ነው ብሏል፡፡ ንጋቱ ረጋሳ በዚህ ዙሪያ ያጠናቀረውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ እየታዩ ባሉ የርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ እየታዩ ባሉ የርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል፡፡ ዜጎችም በስጋት እንዲኖሩ አድርጓል፡፡ ለማህበራዊ ቀውስ የሚዳርጉ እንዲህ ያሉ ግጭቶች መንስዔያቸው ምን ይሆን? መፍትሄያቸውስ? የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያ አነጋግራ ትዕግስት ዘሪሁን ያዘጋጀችውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል...

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ ቀመር ተስፋ በሚል ጷግሜ ውስጥ የተጀመረው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከአዲሱ ዓመት በኋላም ቀጥሏል

የአዲስ ቀመር ተስፋ በሚል ጷግሜ ውስጥ የተጀመረው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከአዲሱ ዓመት በኋላም ቀጥሏል፡፡ የአስፋው ስለሺን ዘገባ ያዳምጡ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ…

በስብሰባው፣ ባሳለፍነው ሳምንት በኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግመው ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ በተመሩት አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር እንዲሁም ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ለሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የሚቀርብ ሪፖርት ላይም እንደሚወያይ ተመልክተናል፡፡ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በሐገሪቱ እና በድርጅቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም እንደሚመክር ሸገር ለመረዳት ችሏል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ ለማ መገርሳ:- ወደ አገር ቤት ለሚመለሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሚደረግን አቀባበል የሚያስተባብሩ ሰዎች የፀጥታ ችግርም እንዳይፈጠር ሀላፊነት መውሰድ አለባቸው

ወደ አገር ቤት ለሚመለሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሚደረግን አቀባበል የሚያስተባብሩ ሰዎች የፀጥታ ችግርም እንዳይፈጠር ሀላፊነት መውሰድ አለባቸው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ፡፡ የንጋቱ ረጋሣን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ነዋሪም የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል ከኦሮሚያ ክልል የሚመጡ ወንድሞቹን በእንግዳ ተቀባይነት ስሜትና በፍቅር ተቀብሎ እንዲያስተናግዳቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል

የአዲስ አበባ ነዋሪም የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል ከኦሮሚያ ክልል የሚመጡ ወንድሞቹን በእንግዳ ተቀባይነት ስሜትና በፍቅር ተቀብሎ እንዲያስተናግዳቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በነገው እለት ለኦነግ አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን የከተማ አስተዳደሩ ስላደረገው ቅድመ ዝግጅት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የከተማዋ ነዋሪ ከአገር ውጭ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና ቡድኖችን በሰላማዊ መንገድ ሲቀበል እንደነበረው ሁሉ የኦነግ አመራር የሆኑ ወንድሞቹንም በፍጹም ጨዋነት እንዲቀበል ጠይቀዋል፡፡

አቀባበሉንና ሰንደቅ ዓላማን ምክንያት በማድረግ በህዝቦች መካከል አላስፈላጊ ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ ያሉ አካላት ላይም አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪም የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል ከኦሮሚያ ክልል የሚመጡ ወንድሞቹን በእንግዳ ተቀባይነት ስሜትና በፍቅር ተቀብሎ እንዲያስተናግዳቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ አቀባበሉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን መላው የከተማዋ ህዝብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና የከተማዋ ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ሀይል የከተማ አስተዳደሩ እንደማይታገስ አሳውቀዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers