• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

2010 ሲታወስ…ባለፈው አመት በተለያዩ አካባቢዎች በታየው ግጭት የሃገሪቱ ምጣኔ ሐብት ክፉኛ እንደተጎዳ መረጃዎች ያረጋግጣሉ

ባለፈው አመት በተለያዩ አካባቢዎች በታየው ግጭት የሃገሪቱ ምጣኔ ሐብት ክፉኛ እንደተጎዳ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ የኢንቨስትመንቱ ፍሰት ከ2009 በእጅጉ ቀንሷል፡፡ እንኳንስ ከውጭ ሊመጡ ያሉትም እንዳይሄዱ መስራት አስፈላጊ ነበር፡፡ ንጋቱ ረጋሣ የ2010 ፀጥታ መታወክ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ያደረሰው ጉዳይ ይመለከታል - እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

2010 ሲታወስ…በ2010 በአብዛኛው ወራቶቹ ኢትዮጵያውያን ለሰብአዊ መብት ጥሰት የተጋለጡበት እንደነበረ ይነገራል

በ2010 በአብዛኛው ወራቶቹ ኢትዮጵያውያን ለሰብአዊ መብት ጥሰት የተጋለጡበት እንደነበረ ይነገራል፡፡ እዚያም እዚህም ግድያን ያስከተሉ ግጭቶች፣ እስራት፣ የንብረት መውደም የታዩበት አመት ሆኗል፡፡ ባለፉት አመታትም ዜጎች በእስራትና እጅግ በሚዘገንን ስቃይ ግርፋትና አካል ጎጂ ቅጣቶች በእስር ቤት ይፈፀምባቸው እንደነበር ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን የምትነግራችሁ በሰብአዊ ጥሰት ዙሪያ የተፈፀሙትን ድርጊቶች ናቸው - እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

2010 ሲታወስ…2010 ከሚታወስባቸው ክስተቶች ብሔር ተኮር ግጭቶቹ መቀስቀሳቸው ነው

2010 ከሚታወስባቸው ክስተቶች ብሔር ተኮር ግጭቶቹ መቀስቀሳቸው ነው፡፡ በተለያዩ ቦታዎች በብሔር እየተቧደኑ ዜጎች ርስ በርስ መጋደላቸውና በግጭቱ መንስኤም አንድ ሚሊየን የሚደርስ ሕዝብ መፈናቀሉ አሳዛኙ ወሬ ነበር፡፡ መንግስት ረብሻውን ለማስቆም፣ ፀቡን ለማብረድና ቤት ንብረታቸው የወደመባቸውን በመርዳት አሁን ድረስ እንደተጠመደ ነው፡፡ ምህረት ስዩም የደረሱት ጥቃቶችን ለመቆጣጠር የተወሰደውን ርምጃ ታስታውሳለች - እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

2010 ሲታወስ…2010 የሃገሪቱ ሰላም የጎሸበት፣ አብዛኛው እንቅስቃሴዎች የተገቱበት አመት ነበር

2010 የሃገሪቱ ሰላም የጎሸበት፣ አብዛኛው እንቅስቃሴዎች የተገቱበት አመት ነበር፡፡ ገና ከመግቢያው የከረመው የህዝቡ አመፅ ተጋድሎ በመቀጠሉ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል፡፡ ግን የህዝቡን የአመፅ ግፊት ሊያቆመው ባለመቻሉ ከፍተኛ ውጣ ውረድ አልፏል፡፡ የንጋቱ ሙሉ ዝግጅት ኢትዮጵያ ያሳለፈቸውን ብጥብጥ ያስታውሳል - እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን 1.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውሎችን ዛሬ ተፈራረመ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን 1.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውሎችን ዛሬ ተፈራረመ፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዛሬ ከ8 የመንገድ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች ጋር የተዋዋለው የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ፣ ዲዛይን ጥናትና ማማከር አገልግሎቶችን ያካተተ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሲነገር እንደሰማነው ውል ከተገባባቸው ስራዎች መካከል በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አጠቃላይ ርዝማኔው 5.32 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪትና የጠጠር አክሰስ መንገድ ግንባታ ይገኙበታል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ተኩሰው መግደላቸው ተነገረ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ተኩሰው መግደላቸው ተነገረ፡፡የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ኢንጂነር ስመኘው ራሳቸውን መግደላቸውን አረጋግጧል፡፡ ኢንጂነር ስመኘው በ2000 ዓ/ም ከፖሊስ ፈቃድ ባወጡበት ኮልት ሽጉጥ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች መገኘታቸውን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማልና የስራ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

በቀኝ ጆሮዋቸው ኋላ በቅርብ ርቀት የተኮሱት ጥይት በግራ ጆሮዋቸው በኋላ ባለው ጭንቅላታቸው መውጣቱ፣ ሽጉጣቸው የወደቀበት ቦታ፣ ራሳቸውን መግደላቸውን አመላክቷል ተብሏል፡፡ ግድያው ሲፈፀም የመኪናው ሞተር ያልጠፋና ግን ተቆልፎ መገኘቱንም አንስተዋል፡፡ ቪ8 መኪና ሞተሩ ሳይጠፋ በሾፌሩ መቀመጫ በኩል ካልሆነ መቆለፍ እንደማይቻል በባለሙያ መረጋገጡን ፖሊስ ተናገሩዋል፡፡ ኢንጂነሩ ከመሞታቸው በፊት በስልክ ከማን ጋር እንደተነጋገሩ መመርመሩንም ተነግሯል፡፡ ኢንጂነር ስመኘው በመጨረሻ ያነጋገሩት ልጃቸውን መሆኑንና በርታ አጥና የሚሉ የስንብት ቃሎች መናገራቸው ተደርሶበታል፡፡ ለፀሐፊያቸውም የስንብት የሚመስሉ ንግግሮች በስልክ ነግረዋት እንደነበረ ተጠቁሟል፡፡

በመኪናቸውም ውስጥ ፊርማቸውን ያስቀመጡባቸው ሰነዶችና ማስታወሻ መገኘቱን፣ ማስታወሻውም የስንብት አይነት መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን በማስታወሻው ላይ ለሞት ያበቃቸውን ምክንያት አልገለፁም ተብሏል፡፡ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ልጃቸውን ከአነጋጋሩ 6 ደቂቃ በኋላ እንደሞቱ ተደርሶበታል፡፡ ፖሊስ ሲደርስ ነፍሳቸው አለመውጣቱንና ሕይወታቸውን ለማትረፍ መስታወት መስበሩን አስታውሰዋል፡፡ ኢንጂነር ስመኘው ራሳቸው ለመግደል ያበቃቸውን ምክንያት ለመመርመር ፖሊስ ስራውን መቀጠሉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ወደ ጅቡቲ እያቀኑ ነው

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ወደ ጅቡቲ እያቀኑ ነው፡፡ በሶስቱ ሐገራት የጋራ ጉባዔ ላይ፣ በሐገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልናት ደረጃ በተዋቀረው ኮሚቴ እንዲሁም በጉባዔው ላይ በተፈረመው የጋራ ትብብር ስምምነት ላይ ተመርኩዞ የተካሄደ ጉብኝት መሆኑን ስምተናል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመጪዎቹ 10 ቀናት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ተባለ

በመጪዎቹ 10 ቀናት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ተባለ፡፡ የወንድሙ ሀይሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ልሸልም ነው አለ

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ልሸልም ነው አለ፡፡ ተሸላሚዎቹ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ620 በላይ ያመጡና በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በእያአንዳንዱ የትምህርት አይነት ከ95 በላይና በአጠቃላይ ውጤት 100 ያስመዘገቡት ናቸው ተብሏል፡፡ በዚሁ መሰረት የከተማዋ 3 የ8ኛ ክፍልና 7 የ12 ክፍል ተማሪዎች የሚሸለሙ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ከተማሪዎቹ በተጨማሪ ባስመዘገቡት የተሻለ ውጤት መሰረት ከ1ኛ-3ኛ ለወጡ ትምህርት ቤቶች፣ ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞችም ማበረታቻ ይበረከትላቸዋል በማለት የነገሩን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ናቸው፡፡ ቢሮአቸው ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ በአዲስ መንፈስ እንሰራለን በሚል መሪ ቃል 27ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ዛሬና ነገ እንደሚካሄድ ነግረውናል፡፡ ጉባኤው ባለፈው በጀት አመት የተከናወኑ የትምህርት ስራዎች እቅድና አፈፃፀማቸው ላይ የሚመክር መሆኑን ሰምተናል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለአዲስ አመት የተጀመረውን የአዲስ ተስፋ ቀመር የስጦታ ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ለ600 ህሙማን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተነገረ

ለአዲስ አመት የተጀመረውን የአዲስ ተስፋ ቀመር የስጦታ ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ለ600 ህሙማን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተነገረ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆየውን ይህንኑ ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልን ጨምሮ ሁሉም የመንግስትና የግል የህክምና ተቋማት እንደሚሰጡ ተነግሯል፡፡የኩላሊት እጥበት የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ እንደነገሩን አገልግሎቱ የሚሰጠው ድርጅታቸው ከሆስፒታሎቹ ጋር በፈፀመው የወጪ መጋራት አሰራር አማካይነት ነው፡፡

በዚህም መሰረት ድርጅታችን ስድስት መቶ ሺህ ብር ወጪ ያደረገ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በሆስፒታሎቹ የተሸፈነ ነው ተብሏል፡፡በተለያዩ ሆስፒታሎች በሳምንት እስከ ሁለት ሺህ ብር ድረስ ይከፍሉ የነበሩ ህሙማን በጊዜው ገንዘቡን ለበዓል እንዲጠቀሙበት በማሰብ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ የበጎ አድራጎት ስጦታ ፕሮግራም ላይ ህሙማኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጎብኝተው ያበረታቷቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም አንድም ባለስልጣን ባለመገኘቱ ህሙማን ቅሬታ እንደተሰማቸው ነግረውናል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተመራው የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን በኤርትራ ሲያደርግ የነበረውን የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝቱን አጠናቅቆ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተመራው የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን በኤርትራ ሲያደርግ የነበረውን የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝቱን አጠናቅቆ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ በሁለት ቀናት ቆይታ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ እና ሶማሊያ ጋር የሦስትዮሽ ስምምነት፣ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የሁለትዮሽ ንግግር እንዲሁም ወደ አሰብና ምፅዋ ወደቦች ጉብኝቶች ተካሂደዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers