• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በቡራዩ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ 8 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በቡራዩ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ 8 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ጭነት ጭኖ ወደ አንቦ ይጓዝ የነበረ FSR አይሱዙ ተሽከርካሪ ቡራዩ አሽዋ ሜዳ ሰዎችን በማሣፈር ላይ የነበረ ታክሲ ላይ በመውጣቱ መሆኑን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሰምተናል፡፡

የፖሊስ ኮሚሽንኑ የትራፊክ ፖሊስ ደህንነትና ቁጥጥር የሥራ ሂደት ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ንጉሴ ግርማ እንደሰማነው በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት ስምንት ሰዎች በተጨማሪ አራት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ነው ያሉት ባለሙያው የFSR አይሱዙ መኪና አሽከርካሪ ለጊዜው ከቦታው መሰወሩን ተናግረዋል፡፡

በሌላ ወሬ ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ወደ ደሴ 45 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ 60 ሜትር ርቀት ካለው ገደል ውስጥ ገብቶ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ሰምተናል፡፡ህይወታቸው ካለፈው ሁለት ሰዎች በተጨማሪ 24 ሰዎች ከባድ ጉዳት ገጥሟቸው በስድስት አንቡላንሶች ወደ ደሴ መወሰዳቸውን ከክልሉ የትራፊክ ፖሊስ ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ አንዳንድ ቦታዎች ከትላንት ጀምሮ አለፍ አለፍ እያለ የሚጥለው ዝናብ ለእንስሣት መኖ እና ለሰብል ረዳት ነው ሲል ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ተናገረ

በኢትዮጵያ አንዳንድ ቦታዎች ከትላንት ጀምሮ አለፍ አለፍ እያለ የሚጥለው ዝናብ ለእንስሣት መኖ እና ለሰብል ረዳት ነው ሲል ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ዝናቡ ለሁለትና ሦስት ቀናቶች እንደሚቀጥልም ተናግሯል፡፡የደቡብ ደጋማ አካባቢዎች፣ የምዕራብ ትግራይና አማራ እንዲሁም አብዛኛው የአፋር ምድር ዝናቡ የሚጥልባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ የስምጥ ሸለቆ አዋሳኝ የሆኑ ቦታዎች የሰሞኑ ዝናብ እንደሚያገኛቸውም ሰምተናል፡፡በኤጀንሲው የአየር ትንበያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ታምሩ ከበደ ለሸገር ሲናገሩ ዝናቡ ለክፉ የማይሰጥና ለሰብልና ለእንስሣት ግጦሽና ውሃ ጥሩ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ይኸኛው ዝናብ የበልግ ወቅት አካል አለመሆኑን የተናገሩት አቶ ታምሩ ዝናቡ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ በተፈጠረ እርጥበት እንዲሁም ከሰሜን ህንድ ውቂያኖስ ወደ ኢትዮጵያ በሚነፍሰው እርጥበታማ ንፋስ ተገፍቶ የመጣ እንደሆነ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባ ትላንት ምሽት የጣለው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ የከተማውን ውሃና መብራት ከአገልግሎት ውጪ አደረገ፣ ጐርፍም አስከተለ

በአዲስ አበባ ትላንት ምሽት የጣለው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ የከተማውን ውሃና መብራት ከአገልግሎት ውጪ አደረገ፣ ጐርፍም አስከተለ፡፡ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪው አቶ ወርቁ ማሩ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ትላንት ምሽት የጣለው ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ለአዲስ አበባ በቀን 210 ሺህ ኪዩብ ውሃ የሚያቀርበውን የአቃቂ ከርሰ ምድር ጥልቅ ጉድጓድና በአዲስ አበባ ያሉ የተለያዩ መጋቢ ጉድጓዶችን ከአገለግሎት ውጪ አድርጓቸዋል፡፡

በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ በስቲያ የውሃ አገልግሎቷ ተቋርጦ ይቆያል ብለዋል፡፡ንፋስ ቀላቃዩ የትላንት ምሽቱ ዝናብ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ስላቋረጠ ነው የውሃው ግፊት የቆመው ያሉት አቶ ወርቁ የኤሌክትሪክ ስርጭት ሲጀምር እኛም ጉድጓዶቻችንን ከሁለት ቀኖች በኋላ መልሰው አገልግሎት እንዲሰጡ እናደርጋለን ሲሉም ነግረውናል፡፡

ሸገር የመብራት አገልግሎቱስ ራሱ መቼ ይጀምራል የደረሰበት የጉዳት መጠንስ ምን ይመስላል በማለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊን አቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረን ጠይቋቸዋል እሳቸውም በርግጥ ትላንት ምሽት የጣለው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ የከተማውን ኤሌክትሪክ በመበጣጠስ ከአገልግሎት ውጪ አድርጐታል፣ የኤሌክትሪኩ ችግር ለውሃ አገልግሎቱ መቋረጥ ሰበብ ሆኗል ባለሙያዎቻችን ዛሬ እስከ ምሽት ድረስ የአዲስ አበባን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

ከእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቋጣጠሪያ ባለሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ እንደነገሩን ደግሞ የትላንቱ ዝናብ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ጐርፍ ያስከተለ ሲሆን በተለይም አቃቂ ወረዳ 8 መልካሸዲ አካባቢ፣ ቦሌ ወረዳ 1 አፓርታማ ሰፈር፣ ቦሌ ወረዳ 3 ገርጂ ቴሌ ጀርባ፣ ቦሌ ወረዳ 9 ጐላጐል ጀርባ፣ ንፋስልክ ወረዳ 10 ዳማ ሆቴል ጀርባ፣ ንፋስ ስልክ ወረዳ 11 ፓስታና መኮሮኒ አካባቢ በመኖሪያ ቤት ጐርፍ ገብቶ ብዙ ንብረት አውድሟል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 7፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለሀገር አስገኝተዋል ያላቸውን ደንበኞቹን ትናንት ሸለመ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በኢትዮጵያ ልዩ ፍላጎት ኖሯቸው የሚወለዱ ህፃናት የሚያገኙት እንክብካቤ አናሳ ነው፡፡ ተንከባካቢ ሆነው የሚሰሩትም ስራቸው በብዛት በከተሞች ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በአዲስ አበባ የጉለሌን የውሃ ችግር ያቃልላሉ የተባሉ 20 ጉድጓዶች እየተቆፈሩ ነው ሦስቱ ተጠናቀው ሥራ ጀምረዋል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በቡራዩ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ትናንት ምሽት የጣለ ዝናብ የኤሌክትሪክና የውሃ አገልግሎቶችን አቋረጠ፡፡ የጐርፍ አደጋም አስከትሏል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • መጣል የጀመረው ዝናብ ለበልግ ሰብል፣ ለእንስሣት መኖና ለውሃ አቅርቦት የሚበጀ ነው ተባለ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሥራ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ያደርጋል የተባለው ስኩል ኔት ፕሮጀክት አስፈፃሚ ባለሙያ አልተቀጠረለትም ፕሮጀክቱም ውጤታማ አልሆነም ተባለ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሥራ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ያደርጋል የተባለው ስኩል ኔት ፕሮጀክት አስፈፃሚ ባለሙያ አልተቀጠረለትም ፕሮጀክቱም ውጤታማ አልሆነም ተባለ፡፡ከዓመት በፊት ሥራ የጀመረውና 168 ሚሊዮን ብር የወጣበት ስኩል ኔት ፕሮጀክትን የሚያስፈፅሙ 65 ባለሙያዎች ቢያስፈልጉም እስካሁን አንድም ሰው እንዳልተቀጠረ ሰምተናል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ 65 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በኔትወርክ ያገናኛል፣ ትምህርቱንም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ያደርጋል፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ተማሪዎች ያመለጣቸውን የፕላዝማ ትምህርት በፈለጉበት ሰዓት ያገኙበታል፣ አጋዥ መፅሐፍትንም ያነቡበታል የተባለው ስኩል ኔት ፕሮጀክት በቻይና ኩባንያ የተሰራ እና 6 ወር የተለፋበት ነው፡፡

168 ሚሊዮን ብርም ወጪ ተደርጐበታል፤ ይህ ግን ውጤታማ እንዳልሆነ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሥራ ሂደትን አነጋግረን ከዚህ ቀደምም ነግረናችሁ ነበር፡፡ውጤታማ ካልሆነባቸው ምክንያቶች መካከል የኔትወርክ መቆራረጥና የኢንተርኔት መጥፋት ይገኙባቸዋል፡፡

እነዚህ ችግሮች እስካሁንም ያልተፈቱ ሲሆን ፕሮጀክቱን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ 65 ባለሙያዎች አለመቀጠራቸውም ለፕሮጀክቱ ውጤታማ አለመሆን ዋናው ምክንያት እንደሆነ ሰምተናል፡፡በትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሸን ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ ቸርነትን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው ባለሙያዎችን ለመቅጠር ከከተማ አስተዳደሩ የአቅም ግንባታ ቢሮ ጋር የመዋቅር ጥናት ማድረግ ጀምረን ነበር ይሁንና ካለፈው ወር ጀምሮ መንግሥት ያደረገውን የደሞዝ ማሻሻያ ተከትሎ የመዋቅር ጥናቱ እንዲቆም ተደርጓል ብለዋል፡፡

ባለሙያዎችን ለመቅጠር የዘገየነውም በዚህ ምክንያት ነው የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 6፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከአመት በፊት ሥራ ለጀመረው ስኩል ኔት ፕሮጀክት 65 ባለሙያ ቢያስፈልገውም እስካሁን አንድም ሰው አልተቀጠረለትም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአውቶብሶች ማደሪያ በተነሳ እሳት የንብረት ጉዳት ደረሰ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በመኸር ዝናብ እጥረት ምክንያት ያጋጠመውን ድርቅ ለመቋቋም መንግሥት ያቀረበውን የእርዳታ ጥሪ ተከትሎ ቃል የገቡ ቢኖሩም እስካሁን እጃቸውን የዘረጉ የሉም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ኢትዮጵያ ከራሷም አልፋ ለውጭ ገበያ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል ለማምረት ማሰቧ ተሰማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በሀገራችን በግንባታ ላይ እያሉ በሚደርስ አደጋ ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጐችን ቁጥር ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የሬዲዮ ቀን እየተከበረ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በፌዴራልና በክልል መንግሥታት መሀከል ያለውን ግንኙነትና አሰራር ህጋዊ ለማድረግ ህግ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሐገራት ማግኘት የነበረበትን 220 ሚሊየን ዶላር ማግኘት እንዳልቻለ ተሰማ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሐገራት ማግኘት የነበረበትን 220 ሚሊየን ዶላር ማግኘት እንዳልቻለ ተሰማ…አየር መንገዱ ከናይጄሪያና ግብፅ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ሐገሮች ነው 220 ሚሊየን ዶላሩን ማግኘት ያልቻለው ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያና ግብፅ እንዲሁም ሌሎች የአፍሪካ ሐገራት አገልግሎት የሰጠበትን ክፍያ ማግኘት ቢኖርበትም ሐገራቱ በነዳጅ ዘይት ዋጋ ማሽቆልቆል የተነሳ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላጋጠማቸው የአገልግሎቱን ክፍያ በዶላር መቀበል እንዳልቻለ ነው የተወራው፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ጉዳዩ ፈተና ሆኖብናል ሲሉ ነግረውኛል ብሎ መረጃው ፅፏል፡፡ዩናይትድ ኤይርላይንስ እና ኤምሬትስ የመሳሰሉት አየር መንገዶች ናይጄሪያ የገጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት አድርገው ወደዚያች ሐገር አንበርም ባሉበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ናይጄሪያን በክፉ ጊዜዋ ከጎኗ አልርቅም፣ በረራዬም አይቋረጥም ማለቱ ይታወሳል፡፡

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለወሬው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የካቲት 2፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • መንግስት ስደተኞች በሚበዙባቸው አካባቢዎች የደን ጭፍጨፋን ለመከላከል አማራጭ የሐይል ምንጭ እያቀረበ ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • ከኢህአዴግ ጋር በቅርቡ ለመደራደር ተዘጋጅተናል ያሉ 11 ፓርቲዎች አራት ነጥብ የያዘ ሞዳሊቲ ማዘጋጀታቸውን ተናገሩ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሐገራት ማግኘት የነበረበትን 220 ሚሊየን ዶላር ማግኘት እንዳልቻለ ተሰማ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በአዲስ አበባ ከተደራጁ 100 የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበራት 33ቱ ቤታቸውን እየገነቡ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የምስራቅ አፍሪካ ኢጋድ አባል ሐገራት ዜጎቻቸውን ከረሀብና ከድርቅ ለመጠበቅ የዓየር ትንበያን መሰረት በማድረግ መስራት ይገባቸዋል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሐገራት ማግኘት የነበረበትን 220 ሚሊየን ዶላር ማግኘት እንዳልቻለ ተሰማ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 1፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችን ለውጭ ገበያ ልታቀርብ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • አራት ክልሎች የተሽከርካሪ አደጋ ለደረሰባቸው ሰዎች የተመደበውን የአስቸኳይ ሕክምና ገንዘብ እየተጠቀሙ አይደለም ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
 • የሐይማኖት አክራሪነትንና ግጭትን ለመከላከል የጀመርኩትን ስልጠና ከቀናት በኋላ ወደ አፋር እወስዳለሁ ሲል የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተናገረ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የቅንጦት ምርቶች ናቸው በሚባሉት ላይ የሚጣለው የኤክሳይስ ታክስ ሊሻሻል ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ኢትዮጵያ ከቆዳ የውጭ ንግድ የምታገኘው ገቢ አሁንም ከፍ አላለም ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥር 16፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 30፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የወጣቶችን ተዘዋዋሪ ፈንድ ተቋማዊ አሰራር የሚዘረጋበት አዋጅ አፀደቀ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የዛሬ 5 ወር ግድም ወደ ሐገር ቤት የገቡት የአዲስ አበባ ሜትር ታክሲዎች ከነገ ጀምሮ መንግስት በተመነላቸው የታሪፍ ዋጋ ስራ ይጀምራሉ ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ ለመጀመር እየተዘጋጀሁ ነው ብሏል፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
 • የካቲት 10 ቀን 2009 በአዲስ አበባ የጃዝ ኮንሰርት ይደረጋል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ኢትዮጵያ በሐገር ቤትና በውጭ ሐገር አልኮልና አረቄ ሸጣ ከ1.5 ቢሊየን ብር በላይ ለማግኘት አስባለች፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ) 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers