• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአፍቃሪ ኢትዮጵያው ቤተሰብ የመጨረሻ ሰው፣ ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ አረፉ…

እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እ.ጎ.አ በመጋቢት 5 ቀን 1935 የተወለዱት ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ አባታቸው የሙዚቃ ሊቅ እናታቸው ደግሞ የአባታቸው የሙዚቃ ተማሪ ነበሩ፡፡ አፍቃሪ ኢትዮጵያ የሆኑት የፕሮፌሰር አብይ ወላጆች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በ1923 የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን የዘውድ በዓል ለማክበርና ለኢትዮጵያም የተቻለውን ለማድረግ በሚል ከመጣው የካሪቢያን ቡድን አባላት ጋር በመሆን ነበር፡፡

ጥንዶቹ ትዳር መስርተው ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ፎርድን እና አብይ ፎርድን ወልደው ኢትዮጵያ ውስጥ ኑሯቸውን ቀጠሉ፡፡ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ የተከታተሉት ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ በአሜሪካ በፓኔ ውድስ ጁኒየር ኮሌጅ በኢለመንታሪ ኢዱኬሽን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ ከዚያም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሰቲ ስኩል ኦፍ ጀኔራል ስተዲስ በፊልም ጥናቶች የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

በሃዋርድ ዩኒቨርስቲም የሙሉ ፕሮፌሰርንትን ማዕረግ እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ለ33 አመታት ያህል አገልግለዋል፡፡ሮፌሰር አብይ ፎርድ የቀድሞው የአ.አ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምኒኬሽን የድህረ ምረቃ ት/ቤት ዲን፤ የዩኒቨርስቲው ፐሬዚዳንት ፅ/ቤት ከፍተኛ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከ26 የሚበልጡ ዶክመንታሪ ፊልሞችንም ሰርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘው፣ ተከታታይ ትውልዶች የተማሩበት በፕሮፌሰር አብይ ፎርድ እናት የተሰራው ሚስስ ፎርድ መታሰቢያ የአፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የዚህ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መታሰቢያ ሆኖ አሁንም ድረስ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

በፋሽስት ወረራ ጊዜ የውጭ ሐገር ዜጎች ኢትዮጵያን ጥለው ሲወጡ የፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ቤተሰቦች ግን ኢትዮጵያን በችግሯ ጊዜ ጥለን አንሄድም ብለው እዚሁ ቆይተዋል፡፡የፕሮፌሰር አብይ አባት በሚወዷት ኢትዮጵያ ነው ኖረው፣ ሞተው የተቀበሩት፡፡እናታቸው ሚስ ፎርድም ልጆቻቸውን ለመጠየቅ አሜሪካ ሄድው ህይወታቸው እዚያ ቢያልፍም መቃብራቸው ግን ኢትዮጵያ ሆኗል፡፡ የፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ወንድምም በተመሳሳይ አሜሪካ ሞተው በኢትዮጵያ መሬት ነው ያረፉት፡፡

እነሆ በዛሬው ዕለት የሚስ ፎርድ ቤተሰብ፣ የዚህ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የመጨረሻው ሰው ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ በአሜሪካ ሐገር ማረፋቸውን ሰማን…ሸገር ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል…

ነፍስ ይማር!
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሚያዝያ 30፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ላይ በህክምና አሰጣጥ፣ በመድኃኒት አቅርቦት እና ሌሎችም አገልግሎቶች ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎች...

በኢትዮጵያ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ላይ በህክምና አሰጣጥ፣ በመድኃኒት አቅርቦት እና ሌሎችም አገልግሎቶች ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎች ትክክል ናቸው ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ከክልል የጤና ቢሮዎች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለማስተካከል ትላንት ምክክር አድርጓል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ የህሙማን አቀባበልና አያያዝ ችግር፣ የመድኃኒት እጥረት፣ የህክምና አሰጣጥ እና ሌሎች ቅሬታዎች ይነሳሉ እነሱንም ለማስተካከል ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለህክምና የሚመጡ ታካሚዎች በተለይ ቅሬታ የሚያነሱ ሲሆን በአዲስ አበባ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ላይ የሚነሱትን ቅሬታዎች በማስተካከል ጥናት ተደርጎ በከተማዋ በሚገኙ 12 ሆስፒታሎች እና 36 የጤና ጣቢያዎች ላይ ለሚነሱ ችግሮች ማስተካከያ እንዲደረግ ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች ለመተግበር የታቀደው የተሟላ የጤና አገልግሎት መስጠት አሁን የሚገኝበት ደረጃም የታሰበውን ያህል ባለመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል መባሉ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች የአገር የኢኮኖሚ እድገት አንኳር የሚባሉ የማይክሮ ኢኮኖሚ ችግሮችን መፍታት አለበት ይላሉ

የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች የአገር የኢኮኖሚ እድገት አንኳር የሚባሉ የማይክሮ ኢኮኖሚ ችግሮችን መፍታት አለበት ይላሉ፡፡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ታዲያ እንደ ስራ አጥነት የዋጋ ግሽበት የመሳሰሉትን የማይክሮ ኢኮኖሚ ችግሮች ፈቷል? ንጋቷ ሙሉ ባለሞያ አነጋግሯል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ካፌ

የኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ በየጊዜው እየፈታቸው የመጣቸው ችግሮች ቢኖሩም ከ40 ዓመታት በኋላም ለምንድነው አሁንም ድረስ የዲሞክራሲ፣ የፍትህ እና የእኩልነት ጥያቄዎች ጥሩ ማሳረጊያ ያላገኙት? በዚህ ነጥብ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደጊዮርጊስ እና ዶ/ር ዮናስ አሽኔ እንዲሁም ከኒውዮርክ ስቶኒ ብሩክ ዩኒቨርሲቲ በስካይፕ ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ ከመዓዛ ጋር ያደረጉትን ውይይት 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቡነ ጴጥሮስ በጥይት ተደብድበው የወደቁበት ቦታ የሚገኘው መታወሻቸው ተሰባብሯል

ኢትዮጵያዊያን ለፋሽስት ኢጣሊያ እንዳይንበረከኩ እስከ መጨረሻው ሰማዕታዊ ሕቅታቸው ያስተማሩት አቡነ ጴጥሮስ የፀረ ፋሽስት ውጊያው ከፍተኛ ተምሳሌት ናቸው፡፡አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስቶቹ በጥይት ተደብድበው በወደቁበት ስፍራ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ መታወሻ ሰሌዳ ተደርጎላቸው ኖሯል፡፡

የቅርስነት ፋይዳ ያለው የመታወሻ የእምነበረድ ሰሌዳ ተሰባብሮ እንዳልሆነ በመሆኑ አረ እናንተ የት ሄዳችሁ ነው?

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሚያዝያ 23፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ዛሬም ስብሰባውን በዝግ የቀጠለ ሲሆን የአመራር ሽግሽግና ምናልባትም አዲስ አመራር ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሸገር ከውስጥ ምንጮቹ ሰምቷል

ከቀናት በፊት በተጀመረው የብአዴን ኮንፍረስ ላይ የዞንና የወረዳ መሪዎችን ጨምሮ ሁሉም የክልሉ ወኪሎች የተገኙበት ነው ተብሏል፡፡ብአዴን በጠራው ጉባኤው ላይ በሀገር ደረጃ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ከመመልከት አንስቶ ክልላዊ አስተዳደሩንም ይመለከታል ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰጡት አዲስ ሹመት ከብአዴን የጽህፈት ቤት ሀላፊነት በመነሳት የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ሀላፊ በሆኑት አለምነው መኮንን ምትክ ብአዴን የፅህፈት ቤት ሀላፊውን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከጽ/ቤት ሀላፊው ሹመት በተጨማሪ በብአዴን ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ሽግሽግና ሹም ሽር ሊደረግ እንደሚችልም ሸገር ሰምቷል፡፡

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ከትላንት በስቲያ የጀመረውን ኮንፍረንስ ውሳኔዎችን በማሳለፍ በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ ሊያጠናቅቅ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ዛሬም ስብሰባውን በዝግ የቀጠለ ሲሆን የአመራር ሽግሽግና ምናልባትም አዲስ አመራር ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሸገር ከውስጥ ምንጮቹ ሰምቷል፡፡

ከቀናት በፊት በተጀመረው የብአዴን ኮንፍረስ ላይ የዞንና የወረዳ መሪዎችን ጨምሮ ሁሉም የክልሉ ወኪሎች የተገኙበት ነው ተብሏል፡፡ብአዴን በጠራው ጉባኤው ላይ በሀገር ደረጃ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ከመመልከት አንስቶ ክልላዊ አስተዳደሩንም ይመለከታል ተብሏል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰጡት አዲስ ሹመት ከብአዴን የጽህፈት ቤት ሀላፊነት በመነሳት የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ሀላፊ በሆኑት አለምነው መኮንን ምትክ ብአዴን የፅህፈት ቤት ሀላፊውን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከጽ/ቤት ሀላፊው ሹመት በተጨማሪ በብአዴን ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ሽግሽግና ሹም ሽር ሊደረግ እንደሚችልም ሸገር ሰምቷል፡፡የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ከትላንት በስቲያ የጀመረውን ኮንፍረንስ ውሳኔዎችን በማሳለፍ በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ ሊያጠናቅቅ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ደንበኞቼ ፓስፖርት ለማውጣትና ለሌላም አገልግሎት በቀጠሮና በረዥም ሰልፍ የሚገላቱበትን አሰራር ያስቀራል...

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ደንበኞቼ ፓስፖርት ለማውጣትና ለሌላም አገልግሎት በቀጠሮና በረዥም ሰልፍ የሚገላቱበትን አሰራር ያስቀራል ያለውን በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ሥርዓት ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡ደንበኞች ወደ ኢሚግሬሽን ቢሮ በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው በአቅራቢያቸው ባለ ንግድ ባንክ በኩል ምዝገባ የሚፈፅሙበት ፣ የአገልግሎት ክፍያቸውን የሚፈፅሙበትና ቀጠሮ የሚይዙበትን ሥርዓት የዘረጋው ከባንኩ ጋር በጋራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በሁለቱ ተቋማት ኢንጂነሮችና በአይቲ ባለሙያዎች ተዘጋጅቶ ዛሬ ይፋ የተደረገው ይኸው አዲስ የአሰራር ሥርዓት ደንበኞች ፓስፖርት ለማውጣት ረዥም ሰልፍና ቀጠሮ መንገላታቸውን ያስቀራል፡፡ገንዘብ ፣ ጊዜና ጉልበታቸውንም እንዲቆጥቡ ይረዳል ተብሏል፡፡

በኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ስለሺ ደምሰው ለሸገር እንደተናገሩት አዲሱ የአሰራር ሥርዓት ረዥም ሰዓት የሚፈጀውን የወረቀት ሥራ ለማስቀረት ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያራምድ ሲሆን የገንዘብ ዝውውሩም በባንክ በኩል ብቻ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል፡፡

ፓስፖርት ለማውጣት የሚፈልጉ ለመመዝገብ ገንዘብ ለመክፈልና ቀጠሮ ለመያዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የተጀመረው አዲስና ዘመናዊ አሰራር በአገር ደረጃ ተግባራዊ ሲደረግም ደንበኞች ኢሚግሬሽን ቢሮ የሚገኙት አሻራ ለመስጠትና ፎቶ ለመነሳት ብቻ ይሆናል ብለዋል አቶ ስለሺ፡፡

የተዘጋጀው አዲስ የአሰራር ሥርዓት በአሁኑ ወቅት በመጀመሪያ ዙር አዲስ አበባ በሚገኙ 30 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ሥራ ጀምሯል ተብሏል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቢሮ ከአዲስ አበባ ውጪ በድሬዳዋ ፣ ሐዋሳ ፣ ጅማ ፣ ባህር ዳር ፣ ደሴና መቀሌ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አቶ ስለሺ አስታውሷል፡፡በቅርቡ በጅጅጋ ፣ በአዳማ ፣ ሰመራና አሶሳ ቢሮ ለመክፈት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሰምተናል፡፡

ትግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“ጭፈራችንን መልሱ፣” “እግር ኳሳችንን መልሱ” - ኤፍሬም እንዳለ

‘የፒያሳ ልጅ’ መጽሐፍ ላይ.. ፍቅሩ ኪዳኔ እንዲህ ጽፈዋል… “የፉትቦል ክለቦች በጎሳና በሀይማኖት ስሜት እንዳይመሩ ፌዴሬሽኑ የማሰተማር ሀላፊነት አለበት በማለት ነው ጋሼ ይድነቃቸው ስማቸውን ያስቀየረው፡፡ በዚሀ መሰረት ሐማሴን… አስመራ ተባለ፣ አካለ ጉዛይ… ‘እምባሶይራ፣’ የሶዶ ምንጭ… ‘አዋሽ ምንጭ’፣ ሠራዬ… ‘መንደፈራ፣’ ሎጎጨዋ… ‘መይለሀም’ ሆነ፡፡ የወታደር ቡድኖችም ችግር እንዳያሰከትሉ ተብሎ የጦር ሠራዊት… ‘መቻል፣’ የክብር ዘበኛ… ‘መኩሪያ፣’ የአየር ሀይል… ‘ንብ’ እና የፖሊስ … ‘ኦሜድላ’ በማለት ተሰየሙ፡፡”
“ጭፈራችንን መልሱ፣” “እግር ኳሳችንን መልሱ”Disgraceful‚ (የሚያሳፍር፣) disgusting‚ (አስፀያፊ፣) appalling (አስደንጋጭ)… እነኚህ ከባባድ ቅጽሎች ናቸው የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሰሞኑን እኛን በተመለከተ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ቅጽሎች፡፡

እስካሁን የተከማቹት እኛን ማጣጣያ፣ እኛን መጐንተያ፣ በአኛ መሳለቂያ ምክንያቶች አይበቁ ይመስል አሁነ ደግሞ ኳሱ ተጨመረ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በቀደም አዲስ አበባ ስቴደየም በዛ ሁሉ ሀዝብ ፊት፣ በቴሌቪዥን ካሜራዎች ፊት የተፈጠረውን ድርጊት ስናይ ግን እነኚህ ቅጸሎች ይሄን ያህል ከባድ ናቸው? በጭራሽ! እውነትም አሳፋሪ ነበር እኮ! እውነትም እስጸያፊ ነበር እኮ! እውነትም አስደንጋጭ ነበር እኮ!

እንደውም አንዱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ድረ ገፅ ርእሱ ላይ ድርጊቱን Official Lunacy: ነው ያለው፡፡ ‘ኦፊሴላዊ እብደት’ እንደማለት፡፡ ከዚህ በላይ ምን ልንባል እንችላለን!

ፊኛ በእንጨት ውል በገባ
ጎበዝ አጉል እየባባ 
ነገሩ እንዲህ ከጠነባ
አፍና ደም ከተቀባ…
ጭንቅላት እንደ ኳስ ሞልቶ፣ በኳስ ተሳክሮ ቢታወር
እርስ በእርስ ሲሰባበር
እረግ እያለን የጎል መከር
ዝም ብለን ከማየት በቀር
አያስችለን የእሱ ነገር
የተነፋ ሩር ማባረር፡፡… ብሏል ጸጋዬ ገብረ መድኅን፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers