• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መንግስት የመምህራን ትምህርትን በልማት አጀንዳነት ለማካተት መስራት ይኖርበታል ተባለ

ይህም ለትምህርት ጥራቱ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡ይህን የሰማነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አገር አቀፍ የትምህርት ፖሊሲን አስመልክቶ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩም ስላጋጠሙ ችግሮችና ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች በተለያዩ ሙህራን ቀርቧል፡፡ያለ መምህራን ጥናት የተማሪ ውጤታማነትም ሆነ ጥራት ያለው ፖሊሲን ማስጠበቅ ስለማይቻል መንግስት ለመምህራን ስልጠና ትኩረት መስጠት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ለትምህርት ተደራሽነት የተሰራውን ያህልም ጥራት ላለው ትምህርት መሰራት ይኖርበታል ሲሉ ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡

ተቀባይነት እያጣ የመጣው የመምህርነት ሙያ ወደነበረበት ለመመለስም ከፍተኛ ነጥብ ያላቸውን ተማሪዎች ወደ ሙያውን እንዲቀላቀሉ ማድረግ ሌላኛው የመፍትሄ እርምጃ ነው ተብሏል፡፡

በየኔ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቀደሙ አገራዊ መልካም እሴቶች ለአሁኗና ለውደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት ሊሆኑ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ

ፕሬዝዳንቱ በአሁኑና በወደፊቱ የአገር ግንባታ ያለፉት የጋራ አኩሪ የታሪክ እሴቶች ወደጎን ሊተው እንደማይገባ የተናገሩት ዛሬ በቢሾፍቱ በዚሁ ጉዳይ ላይ አትኩሮ የተሰናዳን አውደ ጥናት ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

አውደ ጥናቱ ሲካሄድ አሁን ለ3ኛ ጊዜ ነው፡፡ፕሬዝዳንቱ በመክፈቻ መልዕክታቸው የጋራ ታሪካዊ እሴቶችን ለአገር ግንባታው ማዋል የሚቻለው በፖለቲካ ስራ ብቻ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል፡፡የባህልና የኪነ-ጥበቡ ሰዎችም በየጥበብ ውጤቶቻቸው ለዚሁ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

አገር ማቅናት በኢትዮጵያ በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት በሚካሄደው አውደ ጥናት ተያያዥነት ባላቸው ቁም ነገሮች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች በምሁራንና በታዋቂ ግለሰቦች እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡በሚቀርቡት ፅሑፎች ላይ ምክክር እንደሚደረግባቸው ከስብሰባው ምንጮቻችን ሰምተናል፡፡

የኔነህ ከበደ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ አብዱል መሐመድ እና መዓዛ፣ በቀይ ባሕር አካባቢ ፖለቲካ፣ በአፍሪካ ቀንድ ሐገራት እንዲሁም ከመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ሐገራት ጋር ባለ ግንኙነት ዙሪያ፣ የወደብ ጉዳይንም አስመልክተው

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ሸገር ካፌ

ለመሆኑ የኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ በየጊዜው እየፈታቸው የመጣቸው ችግሮች ቢኖሩም ከ40 ዓመታት በኋላም ለምንድነው አሁንም ድረስ የዲሞክራሲ፣ የፍትህ እና የእኩልነት ጥያቄዎች ጥሩ ማሳረጊያ ያላገኙት?

በዚህና በተዛማጅ ነጥቦች ዙሪያ፣ ባሳለፍነው እሁድ፣ በሸገር ካፌ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደጊዮርጊስ እና ዶ/ር ዮናስ አሽኔ እንዲሁም ከኒውዮርክ ስቶኒ ብሩክ ዩኒቨርሲቲ በስካይፕ ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ ከመዓዛ ብሩ ጋር የተወያዩበትን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባ ውስጥ በአፋን ኦሮሞ ትምህርት የሚሰጡ አምስት ተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ተባለ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ አራት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባለፈው ሐምሌ ወር መመረቃቸው ይታወሳል፡፡በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ከአምስት መቶ እስከ አንድ ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ የሚል ግምት እንደነበር የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ተሠማ ተናግረዋል፡፡በአራቱ ትምህርት ቤቶች ለመማር የተመዘገቡት ግን ከስድስት ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሆኑ አስታውሰዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ስድስት ትምህርት ቤቶችን ለመከራየት ተገደናል ብለዋል፡፡በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ ተጨማሪ አምስት ትምህርት ቤቶች በከተማዋ እንደሚገነቡ ነግረውናል፡፡ትምህርት ቤቶቹን እንዲገነባ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥያቄ ቀርቦ ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል፡፡

አቶ ኤፍሬም ተሰማ እንዳሉት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለትምህርት ቤቶቹ መምህራን እና የመማሪያ ቁሳቁሱችን ያሟላል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆችና የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በአፋን ኦሮሞ ትምህርት የሚሰጡ ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ ከረጅም ጊዜ አንስቶ ሲጠይቁ መቆየታቸው ተነግሯል፡፡ይህንኑ ጥያቄ መነሻ በማድረግ የተገነቡ እና በቀጣይም የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግስት የልማት ድርጅቶች ከዓለም ሃገራት ለሚወስዱት ብድር ዋስትና መስጠት አቁሜያለሁ አለ፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እንዳለው የመንግስት ልማት ድርጅቶች በመንግስት ዋስትና በወሰዱት ብድር የጀመሯቸው ፕሮጀክቶች እየተጓተቱና ኪሳራም እያስከተሉ ነው፡፡ የሒሳብ አያያዛቸውም ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑና የወሰዱትን ብድርም በውሉ መሰረት በጊዜው የማይከፍሉ ስላሉ መንግስት ለልማት ድርጅቶቹ ዋስ ሆኖ ብድር እንዲያገኙ የሚያደርገውን ድጋፍ ለጊዜው አቁሜአለሁ ብሏል፡፡

በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት  አቶ ሐጂ ኢብሳ እንዳሉት በብድር እየተገነቡ ያሉና ይጠናቀቃሉ ተብለው ከሚጠበቁት አመታት ከዘገዩ የስኳር ፕሮጀክቶች መማር አለብን ብለዋል፡፡ከመንግስት የልማት ድርጅቶች መካከል ያለ መንግስት ዋስትና የውጪ ብድር ማግኘት ይችላሉ የተባሉ 2 ብቻ እንደሆኑ አቶ ሐጂ ተናግረዋል፡፡እነሱም የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው፡፡

ከነዚህ ሁለት የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሒሳብ አያያዛቸው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በመሆኑና አትራፊም በመሆናቸው የአለም ተቋማትና መንግስት ያለ መንግስታት ዋስትና አምነው ብድር እንደሚሰጧቸው ሰምተናል፡፡ኢትዮጵያ ከአለም አገራት የምትወስደው የብድር መጠን ጫናው ዝቅተኛ ከተባለበት ደረጃ አሁን ወደ መካከለኛ ከፍ ብሏል፡፡በመሆኑም አጠር ባለ ጊዜና በዛ ባለ ወለድ የሚከፈለውን ኮሜርሻል የተሰኘ ብድር መውሰድ አቁማለች ተብሏል፡፡

ለጊዜውም ለረጅም ጊዜ ክፍያና በአነስተኛ ወለድ የሚከፈልን ኮንሴሽናል የተሰኘ ብድር እየወሰደች ነው፡፡ይህንንም እንዳናጣ  ገቢው እያሽቆለቆለ የመጣውን የኤክስፖርት ጉዳይ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል የገንዘብና ኮሚኒኬሽን ትብብር ሚኒስትር የኮሚኒኬሽን ዳይሬከተሩ፡፡ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት ከተለያዩ አለም ሃገራት በብድርና በእርዳታ 78 ነጥብ 42 ቢሊዮን ዶለር አግኘታለች የተባለ ሲሆን ሌላ 120 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እርዳታና ብድር ቃል እንደተገባላት ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ወርቃማው በሬ…

ለቀብር ማስፈፀሚያ በ13 ሺ ብር የተገዛው በሬ ሲታረድ ሀሞቱ ውስጥ የ10 ሺ ብር ወርቅ ተገኘ ይለናል ወንድሙ ኃይሉ በልዩ ወሬው…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በህገ-ወጥ የንግድ ተግባር ላይ ተሰማርተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ከ6 ሺ በላይ የንግድ ድርጅቶችን ማሸጉን ተናገረ

ቢሮው ይህን ያለው የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን አስመልከቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቀት ነው፡፡በከተማዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 6ሺ 589 የንግድ ድርጅቶችን ህገ-ወጥ የንግድ ተግባር ሲፈፅሙ አግኝቻቸው አሽጌያቸዋለሁ ያለው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከዚህ ውጪ ጥፋታቸው የከፋ 164 ድርጅቶችን ደግሞ የንግድ ፈቃዳቸው ሰርዤያለሁ ብሏል፡፡

ቢሮው በተመሳሳይ ጊዜ ለ11 ሺህ የንግድ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተናግሯል፡፡የንግድ ድርጅቶቹ እሸጋው እና ማስጠንቀቂያው የደረሰባቸው ከፍተኛ ዋጋ በመጨመር፣ ደረሰኝ ሳይቆርጡ በመነገድ እና በሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው ተብሏል፡፡በተመሳሳይ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በኮንትሮባንድ ንግድ ውስጥ የተገኘ ከ1 መቶ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ዕቃ በመንግስት መወረሱን ሰምተናል፡፡

መግለጫውን የሰጡት ትናንት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሀላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ መስፍን አሰፋ 22 ሺ መደበኛ ያልሆኑ ወይንም በጎዳና ላይ ወዲህ ወዲያ እየተሯሯጡ የሚነግዱ ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡ነጋዴዎቹን በህጋዊ ንግድ ውስጥ ለማስገባት ህግና መመሪያዎች መውጣታቸውና በቅርቡም ስራ እንደሚጀምሩ አቶ መስፍን ተናግረዋል፡፡ሰሞኑን በዳቦ መሸጫ እና ዱቄት ፋብሪካዎች ስለተስተዋለው የአቅርቦት እጥረት እና ዋጋ መናር ምክንያት የተጠየቁት ሀላፊው ችግሩ የተፈጠረው ስንዴ የሚገዛው የመንግስት መስሪያ ቤት በጊዜ ስንዴ ከውጭ ሀገር ባለመግዛቱ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በዳቦ እና በስንዴ ዱቄት ዋጋ ላይ ጭማሪ ተስተውሏል ያሉት ሀላፊው ከመጠባበቂያ ክምችት ያለውን ስንዴ በመጠቀም ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ከውጭ ሀገር የሚገዛው ስንዴ በዚህን ግዜ ባይባልም በቅርቡ ሀገር ውስጥ ገብቶ ይከፋፈላል ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሐዋሳ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል

በሐዋሳ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት ከተናገሯቸው ንጋቱ ሙሉ የሚከተለውን አዘጋጅቷል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ምርምሮችን በአለማቀፍ መፅሔቶች በማሳተምና ተፅዕኖ በመፍጠር ከአለም 1 ሺ 3ኛ

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ምርምሮችን በአለማቀፍ መፅሔቶች በማሳተምና ተፅዕኖ በመፍጠር ከአለም 1 ሺ 3ኛ ከኢትዮጵያ ደግሞ የቀዳሚነቱን ደረጃ መያዙ ተሰማ፡፡ሸገር ከዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንደሰማው ዩኒቨርስዎችን በትምህርታዊ አቅማቸው በሚለካው ተቋም መሰረት ዩኒቨርሰቲው ከአፍሪካ 19ኛ ደረጃ ስለመያዙ ነው፡፡

ከአሁን በፊት ከነበረው ደረጃ አንፃር በንፅፅር እንዲነግሩን የጠየቅናቸው አቶ አሰማኸኝ በፈረንጆቹ በ2017/18 የተገኘው ደረጃ ከፍተኛና የዩኒቨርስቲውን ማህበረሰብ ይበልጥ የሚያበረታ ነው ብለዋል፡፡ከዩኒቨርስቲው ባገኘነው መረጃ መሰረት አዲስ አበባ ኒቨርስቲን የተከተሉት የሀገር ቤት ዩኒቨርስቲዎች ጥናትና ምርምሮችን በማስተምና ተፅዕኖ በመፍጠር መቀሌ፣ ጎንደር ፣ባህር ዳር፣ ጅማ ፣ሀዋሳ ዩኒቨርስቲዎች ደረጃቸው ከ1663 እስከ 2355 ባለው ነው፡፡

እነዚሁ ዩኒቨርስቲዎች በአፍሪካ ደረጃ ከ48-102ኛ ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በምስራቅ አፍሪካ የሚበልጠው መካረሬ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሆኗል ሲሉ ነግረውናል፡፡በ1943 የተቋቋመ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሲሆን በአሁኑ ወቅት በ15 ካምፓሶች ከ52 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

ከነዚህም ውስጥ 16 ሺህ የሚደርሱት የማስተርስ ድግሪና 2 ሺ 5 መቶዎቹ የዶክትሬት ድግሪ ተማሪዎች ስለመሆናቸው ከአቶ አሰማኸኝ ሰምተናል፡፡ዩኒቨርስቲው በ2025 በአፍሪካ ካሉ ምርጥ 10 የምርምር ተቋም አንዱ ለመሆን አልሞ እየሰራ ስመሆኑም ነግረውናል፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአገራችን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚከሰቱ የስራ ላይ አደጋዎች እየጨመሩ ነው ተባለ

በእነዚህ የስራ ላይ አደጋዎች ከሚጎዱት የህብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶች የበዛውን ቁጥር እንደሚሸፍኑ ተነግሯል፡፡የአለም የሙያ ደህንነትና ጤንነት ቀን አከባበርን አስመልክቶ የተዘጋጀው የፓናል ውይይት በካፒታል ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡በውይይቱ ላይ የተገኙት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምስጋናው አድማሱ እንዳሉት ኢትዮጵያ በስራ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ እስካሁን የተለያዩ ህጎችን አውጥታለች፡፡

ነገር ግን አደጋው ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡አደጋውን መቀነስ የሚቻለው ሁሉም በትብብር ሲሰራ እንደሆነም ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል፡፡በአለም ላይ ከ3 በመቶ 30 ሚሊየን በላይ ሰዎች የስራ ላይ የአካል ጉዳት እንደሚደርስባቸው በፓናል ውይይቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡1 መቶ 70 ሚሊየን የሚጠጉ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ከስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና ጉዳቶች ይገጥማቸዋል ተብሏል፡፡

2 መቶ 34 ሚሊየን ሰዎች በስራ ላይ አደጋ እንደሚሞቱ ተነግሯል፡፡ 37 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ለጤና ጎጂ በሆኑ ቦታዎች ላይ ይሰራሉ ተብሏል፡፡የዓለም የሙያ ደህንነትና ጤንነት ቀን ዘንድሮ በአገራችን የሚከበረው ለ15ኛ ጊዜ እንደሆነ በፓናል ውይይቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers