• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የዓለም ባንክ ወደ 8 መቶ 29 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 18 ቢሊየን የሚጠጋ ብር አበደረ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 5 የተለያዩ ፕሮጀክቶች መርጃ የሚሆን ወደ 8 መቶ 29 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 18 ቢሊየን የሚጠጋ ብር አበደረ… ከዚህ በፊትም ከፍተኛውን ብድር የሚወስደው የትራስፖርት ሥርዓቱን ማሻሻል ሲሆን 3 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 በታዲያስ አዲስ ፕሮግራም የስም ማጥፋት ክስ የተመሠረተበት ሰይፉ ፋንታሁን ለፍርድ ቤቱ ትላንት ሰጥቶት የነበረው ቃል እንዲሻርለት ጠየቀ

በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 በታዲያስ አዲስ ፕሮግራም በተላለፈ ዝግጅት የስም ማጥፋት ክስ የተመሠረተበት ሰይፉ ፋንታሁን ለፍርድ ቤቱ ትላንት ሰጥቶት የነበረው ቃል እንዲሻርለት ጠየቀ… ፍርድ ቤቱ ተከሣሽ ትላንት በሰጠው የእምነት ቃል መሠረት የቅጣት ውሣኔ ለመስጠት ይዞት የነበረው ቀጠሮ ቢኖርም በተከሣሽ የቀረበውን መቃወሚያ ተከትሎ አከራክሯል፡፡

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎች የቀረበው ሰይፉ ፋንታሁን የህግ ባለሞያ ሳያማክር በጉዳዩ ብዙ ሊከራከርበት የሚችል ማስረጃ እያለው ፕሮግራሙ ተላልፏል ብሎ በሰጠው ቃል ፍርድ ቤቱ አምኗል ብሎ የጥፋተኝነት ውሣኔ የወሰነበት በመሆኑ ተከሣሹ የሰጠው ቃል አንቀፅ 135 መሠረት እንዲሻርለት ሲል ጠበቃው ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 8፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 በታዲያስ አዲስ ፕሮግራም በተላለፈ ዝግጅት የስም ማጥፋት ክስ የተመሠረተበት የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ለፍርድ ቤቱ ትላንት ሰጥቶት የነበረው ቃል እንዲሻርለት ጠየቀ፡፡
 • የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ አደጋ ጨምሯል፤ የትራፊክ ፖሊሶች ህግ ከማስከበር ግላዊ ጥቅማቸውን ማስቀደማቸው አሁንም ያልተፈታ ችግር ነው፤ የኮምኒቲ ፖሊሲንግ መቋቋም ደግሞ ወንጀል እንዲቀንስ አድርጓል ተባለ፡፡
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዲዩቲ ፍሪ እና ሌሎች የማኔጅመንት ሥራዎችን እንዲያከናውንለት ከቱርቬስት ኩባንያ ጋር ስምምነት መፈራረሙ ተነገረ፡፡
 • ለአዲስ አበባ አደጋ መከላከል ሥራ በ9 ሚሊየን ብር ክሬን ተገዛ፡፡
 • የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን የህፃናትን የመብት ጉዳይ ቸል ብለውታል ሲል የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ተናገረ፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች ደግሞ ቢሮው ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ያለው ተባብሮ የመሥራት ፍላጐቱ የወረደ ነው ብለዋል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በድጐማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸው የምግብ ሸቀጦች በድብቅ ለነጋዴዎች እንደሚሸጡ ደርሼበታለሁ

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም መንግሥት በድጐማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸው የምግብ ሸቀጦች በድብቅ ለነጋዴዎች እንደሚሸጡ ደርሼበታለሁ አለ… ባለፉት አስር ወራት በ278 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር ማድረጉንም ሰምተናል፡፡ በህዝብ የእንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ የሆኑት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ዛሬ የተቋሙን የአስር ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደሰማነው በድጐማ ለህዝቡ የቀረቡ የምግብ ሸቀጦች በተገቢው መንገድ ለተጠቃሚው እየደረሱ አይደለም፡፡

እንደ ዘይት፣ ስኳር እና የዳቦ ዱቄት ያሉ የምግብ ሸቀጦች አቅርቦት ከህዝቡ ፍላጐት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም፤ የቀረቡትም ቢሆን በድብቅ ለነጋዴዎች እንደሚሸጡ በተደረገው ቁጥጥር እንደተደረሰበት ዋና እንባ ጠባቂዋ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት በድጐማ ለህዝቡ ያቀረበውን የምግብ ሸቀጥ ለነጋዴው ይሸጣሉ ከተባሉ ክልሎች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ ጋምቤላና ደቡብ ክልሎች ይገኙበታል፡፡ በህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂዋ እንዳሉት ይህ ወንጀል ስለመፈፀሙ ከሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጐ ችግሮቹ መኖራቸውን አምነዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኞች ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ ኃሣባቸውን ለማስረዳት አይቸገሩም

ከእንግዲህ መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኞች ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ ኃሣባቸውን ለማስረዳት አይቸገሩም ተባለ…የሚናገሩትን የሚያዳምጧቸው እና ለችግራቸውም መላ የሚሰጡ የጤና ባለሞያዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች የምልክት ቋንቋ ሥልጠና ወስደው እየሰሩ ነው ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡በፌዴራል እና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚገኙ ሆስፒታሎች እንዲሁም የጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ 150 የሚደርሱ ባለሞያዎች የምልክት ቋንቋ ሥልጠናን ወስደው መስማት የተሳናቸውን አካል ጉዳተኞች እያስተናገዱ ነው ሲሉ የነገሩን የሚኒስቴሩ የሴቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ ያምሮት ዓንዱአለም ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኛ ሬዲዮ ፕሮግራም

በፆታዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የኛ ሬዲዮ ፕሮግራምን ከ3 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች ይከታተሉታል ወደ 9 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ፕሮግራሙን ያውቁታል ተባለ፡፡ ይህን የሰማነው የኛ ሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅቶቼን ምን ያህል ሰው ያደምጠዋል፣ የታሰበለትን ግብ መትቷል ወይ የሚል ጥናቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡ ከጥናቱ እንደተሰማው የኛ ሬዲዮ ዝግጅትን የሚያደምጡ ፆታዊ ጥቃትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን የመቃወም አቅማቸው የተሻለ ነው ተብሏል፡፡የወጣት ሴቶች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራው የኛ የሬዲዮ ፕሮግራም ያለ እድሜ ጋብቻና ፆታዊ ጥቃትን ለማስቀረት አጋዥ እንደሆነም ጥናቱ ተናግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 7፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የኢትዮጵያ መግሥት በኤርትራ መንግሥት ላይ የወሰደውን የአፀፋ እርምጃ ትላንት ከሰዓት አቁሟል፡፡ ከዚህ በኋላም የሚፈፀም ትንኮሰ ካለ መንግሥት እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ አይልም ተባለ፡፡
 • በድጐማ ለህዝብ የሚቀርቡ የምግብ ሸቀጦች በተገቢው መንገድ ለህዝብ እየቀረቡ አይደለም ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
 • ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ለማሣደግ የጋራ ፍላጐት እንዳላቸው ተሠማ፡፡
 • በደም እጦት የሚሞቱ ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ በመደበኛነት በበጎ ፈቃድ ደም የሚለግሱ ያስፈልጋሉ ተባለ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ድምጻዊት መክሊት ሐደሮ ግንቦት 25፣2008

በ“ከመከም” እንዲሁም በ“አባይ ማዶ” ዜማዎቿ የምናውቃት ድምጻዊት መክሊት ሐደሮ ግንቦት 25፣2008 በተላለፈው የሐሙስ ዕለት የምሳ ሰዓት የለዛ ፕሮግራም ላይ ከአዘጋጁ ብርሃኑ ድጋፌ ጋር ቆይታ አድርጋ ነበር፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በድርቁ ምክንያት የውሃ እጥረት ላጋጠማቸው ክልሎች የሚሆኑ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጓትተዋል ተባለ

በድርቁ ምክንያት የውሃ እጥረት ላጋጠማቸው ክልሎች የሚሆኑ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጓትተዋልተባለ፡፡ ምክንያት የተደረገው የኮንትራክተሮች አቅም ማነስ ነው ተብሏል፡፡ ለሰው እና ለእንስሣት የመጠጥ ውሃ እጥረት ካጋጠሙባቸው ክልሎች መካከል በቤንሻንጉል ጉሙዝ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታና በሶማሌ ክልል የሀረዋ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጓትተዋል ከተባሉት መካከል ናቸው፡፡ ወሬውን የሰማነው ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎችን የ11 ወር እቅድ አፈፃፀም ሲመረምር ነው፡፡

ፕሮጀክቶቹ በተጓተቱ ቁጥር ህብረተሰቡ የሚያስፈልገውን አገልግሎት በወቅቱ ካለማግኘቱ በተጨማሪ የሚያስፈልገው ወጪውም መናሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች መጓተት ፈተና እንደሆነበት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከ6 ሺህ በላይ የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች አገልግሎት መስጠት አቁመው እንደነበርም ሰምተናል፡፡ በውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ጀምስ ዴንግ እንዳሉት አገልግሎት ካቆሙት መካከል ለ1 ሺህ 729 ያህሉ የጉድጓድ ጠረጋና እድሣት ተደርጓል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አምስት የአባልነት መቀመጫ ወንበሮችን በጨረታ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ሸጠ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አምስት የአባልነት መቀመጫ ወንበሮችን በጨረታ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ሸጠ፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአባላት መቀመጫ ወንበሮችን በጨረታ ያስተላልፋል፡፡ እስከ አሁንም በአስራ ዘጠኝ ዙር ወንበሮችን አስተላልፏል፡፡ ሰሞኑን ባካሄደው አስራ ዘጠነኛ ዙር ጨረታ አምሰት ወንበሮችን ከአስራ አንድ ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ዋጋ ማስተላለፉን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣አቶ ዘላለም ጀማነህ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በሙስና ተጠርጥረው የተያዙት አቶ ዘላለም ጀማነህ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሠማ…ሸገር ከኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች እንደሰማው የፀረ ሙስና ኮሚሽኑ በተጠርጣሪው ላይ የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁን ነው፡፡አቶ ዘላለም ጀማነህ የክልሉ መንግሥትና ድርጅት ኃላፊ በነበሩበት ጊዜ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ህዝባዊ አደራ በመተው የተሰጣቸውን ሥልጣን ያለአግባብ ለግል ጥቅም አውለዋል በሚል ያለመከሰስ መብታቸው ወርዶ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፓርቲያቸው ኦህዴድ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሸገር ዛሬ እንደሰማው በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማዕረግ የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ በመሆን ይሰሩ የነበሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ ዛሬ አቃቂ ወረዳ ፍርድ ቤት ለምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ቀርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers