• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የሳውዲ አረቢያ መንግስት የልዑክ ቡድን አባላትን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተሰማ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድን ንግግር ዶ/ር አብይ በቅርቡ በጅዳ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ሁለቱ አገራት በጋራ ለመስራት በተግቡባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮር ነበር ተብለዋል፡፡ሸገር ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈትቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አሪጋ እንደሰማው የኢትዮጵያ እና የሳውዲ አረቢያ ግንኙነት በፍጥነት እያደገ መጥቷል፡፡

በቅረቡ ጠ/ሚ አብይ አህመድ በሳውዲ አረቢያ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተከትሎ በዚያ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መፈታታቸው ይታወሳል፡፡ጠ/ሚ አብይ አህመድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት መሐመድ አላሙዲን በቅርብ ይፈታሉ ሲሉ መናገራቸውን ይታወቃል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የተደራጀ ሌብነትና ዝርፊያን ለመዋጋት እያንዳንዱ ዜጋ ከመንግስትና ጎን እንዲቆም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠየቁ

መንግስትን ፣ የሀይማኖት ተቋማትን እንዲሁም ማህበራዊና ህዝባዊ ተቋማትን የዘራፊዎች መሸሸጊያ ከመሆን ልንጠብቃቸው ይገባልም ብለዋል፡፡ዛሬ በአራተኛው ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጠቅላላ ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዴሞክራሲንና ነፃ ገበያን የሚያቀጭጨውን የተደራጀ ሌብነትና ዝርፊያ ወይም ሙስናን መዋጋት የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት መሆኑን አሳስበዋል፡፡
ዶ/ር አብይ የተደራጀ ሌብነትና ዝርፊያ ነው ያሉት ሙስና አሁን ባለበት መልኩ የሚቀጥል ከሆነ ለሀገሪቱ ከፍተኛ ስጋት ነው ብለዋል፡፡በመሆኑም ሙስናን መዋጋት በመንግስት ብቻ ዳር አይደርስም በማለት ሁሉም ዜጋ በንቃት መንግስትን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መገናኛ ብዙሃንም በሀገሪቱ የሚከናወኑ ያልተገቡ አሰራሮችን ተከታትለው በማጋለጥ አራተኛ የመንግስትነት ሚናቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡የመገናኛ ብዙሃን መጠናከር የመንግስት ፍላጎት መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ መንግስት የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡አራተኛው ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጠቅላላ ጉባኤ “የፀረ ሙስና ጥምረትን በማጠናከር ሙስናን እንከላከል ልማትን እናፋጥን” በሚል መሪ ቃል በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡

በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ የተባለ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ማህበር ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት እውቅና ማግኘቱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ የተባለ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ማህበር ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት እውቅና ማግኘቱ ተሰማ፡፡የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ተስፋዓለም አባይ ቦርዱ እውቅና የሰጣቸው ሁለት ፓርቲዎች ናቸው፤ አንደኛው አገር አቀፍ ፓርቲ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የክልል ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለሁለቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች እውቅና የተሰጠው በተሻሻለው የፖለቲካዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ/ም መሰረት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ቦርዱ እውቅና ከሰጣቸው ፓርቲዎች በተጨማሪ የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ የተባለው ፓርቲ ፈቃድ መሰረዙን ተሰምቷል፡፡

የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ ምዝገባ የተሰረዘው በፓርቲው ጥያቄ መሰረት ነው ተብሏል፡፡ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የእውቅና ሰርተፍኬት ከሰጣቸው ፓርቲዎች በተጨማሪ አሁንም ተመዝግበው ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ፓርቲዎች መኖራቸው ተሰምቷል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአርባ ምንጭ አባያ ሐይቅ ትናንት ሰዎችን በማጥመቅ ላይ የነበረ ግለሰብ በአዞ ተበልቶ ሕይወቱን አጣ

ከነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ሀላፊ ከአቶ ሽመልስ ዘነበ ዛሬ እንደሰማነው ተከታዮቹ ፓስተር እያሉ የሚጠሩት የ45 አመቱ ጎልማሳ ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በአባያ ሐይቅ ውስጥ ገብቶ ሰዎችን በማጥመቅ ላይ ሳለ ነው በአዞ ተበልቶ ሕይወቱን ያጣው ብለዋል፡፡

የአባያ ሐይቅ ብዛት ያላቸው አዞዎች መኖሪያ ሲሆን የዓሣ ሀብት ስለሌለው በውስጡ የሚገኙት አዞዎችም የምግብ እጥረት ስለሚያጋጥማቸው ያገኙትን ነገር ሁሉ ይመገባሉ ያሉት የብሔራዊ ፓርኩ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ከዚህ ቀደምም የሜዳ አህዮች፣ አጋዘኖች እና ብዛት ያላቸው የቤት እንስሳት ውሃ ለመጠጣት ወደ አባያ ሐይቅ እየቀረቡ በአዞ ተበልተዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡ሰዎችን በማጥመቅ ላይ ሳለ አዞ የበላው ግሰለብ ከዚህ ቀደም በዓሣ አጥማጅነት ይተዳደር ነበር ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ / እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር / ኦዴግ / ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት አድርገዋል

ውይይቱ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ሁለቱ በጋራ በሚሰሩበት መንገድ ላይ ያተኮረ እንደነበር የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ /ኦ ቢ ኤን/ መረጃ ጠቅሷል፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ውይይት ነውም ብሏል፡፡
የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሣ የኦዴግ መሪዎችን እንኳን ወደ ሀገራችሁ በደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል፡፡ተቀራርቦ መስራቱ ከሌሎች የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ጋርም እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ በጥላቻ ላይ ተመስርቶ የቆየውን የፖለቲካ ባህል የሚቀይር ነውም ብለዋል፡፡ለኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር /ኦዴግ/ አመራሮች በግላቸው ከፍ ያለ አክብሮት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ፕሬዝዳንት አቶ ሌንጮ ለታ በበኩላቸው ወደ ሀገር ቤት እንዲለመሱ በኦሮሚያ ክልል እና በፌዴራል መንግስት ለተደረገላቸው ዕገዛ አመስግነዋል፡፡

በሀገሪቱ እየመጣ ባለው ለውጥ ውስጥ የራሳችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት መጥተናል ሲሉም አቶ ሌንጮ ተናግረዋል፡፡የኦዴግ አመራሮች በመንግስት የቀረበላቸውን የድርድር ግብዣ በመቀበል በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

‘አደጋ ከጋጠማቸው የበዙት አሽከርካሪዎች ለእቁባቸው እንዲሁም የባንክ ብድራቸውን ለመክፈል በሌላም ምክንያት ከመኪናው እክል ይልቅ ገቢው ብቻ በሚያሳስባቸው የመኪና ባለንብረቶች ተፅዕኖ ብልሽት ያለበትን መኪና ይዘው የወጡ ናቸው…’

በተሽከርካሪ አደጋ የሰዎች ሕይወትም ሆነ ንብረት በሚጠፋ ጊዜ በቀዳሚነት ተጠያቂ የሚደረጉ ቅጥር አሽከርካሪዎች እኛም ችግር አለብን አሉ፡፡የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በተለያዩ ጊዜያት ለአሽከርካሪዎች የትራፊክ ደህንነት ስልጠና በሚሰጥበት ጊዜ ሾፌሮች እንደሚናገሩት በመኪና ባለሀብቶች ተፅዕኖ የቴክኒክ እክል ያለባቸውን መኪኖች ችግራቸውን እያወቅን ይዘን እንድንወጣ እንገደዳለን በዚህም አደጋዎች ያጋጥሙናል ብለዋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ደህንነት ትምህርትና ግንዛቤ ዳይክተሩ አቶ ዮሐንስ ለማ ለሸገር ሲናገሩ በርግጥም አደጋ ከጋጠማቸው የበዙት አሽከርካሪዎች ለእቁባቸው እንዲሁም የባንክ ብድራቸውን ለመክፈል በሌላም ምክንያት ከመኪናው እክል ይልቅ ገቢው ብቻ በሚያሳስባቸው የመኪና ባለንብረቶች ተፅዕኖ ብልሽት ያለበትን መኪና ይዘው የወጡ ናቸው ብለዋል፡፡

ሾፌሮቹም ከስራቸው እንዳይባረሩ በመስጋት በባለሀብቱ ግፊት የተበላሸ መኪና ይዘው በመውጣታቸው በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ብዙ ጉዳት ደርሷል ያሉት አቶ ዮሐንስ ችግሩን ለማስቀረት ይቻል ዘንድ ነገ ከመኪና ባለንብረቶችና ከሚመለከታቸው ጋር የሙሉ ቀን ምክክር እናደርጋለን ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መነሳት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰጡት መግለጫ

የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሀገር እና ህዝብ ያሉበትን ነባራዊ እውነታ እና በቀጣይም እንደ ሀገር ሊገጥም ይችላል ተብሎ የሚገመት አደጋን ለመከላከል በመደበኛው ህግ እና አሰራር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ የሚመርጥ አስገዳጅ አማራጭ ነው።ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት አመታት ባጋጠማት የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲታወጅ ተደርጓል።

ይህንን ተከትሎም በመንግስት ዘንድ በተከናወነው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እና በተከታታይ በተወሰዱ እርምጃዎች ህዝቡ መንግስት ባለው ችግሮችን የመፍታት ፍላጎት እና አቅም ላይ ተስፋን ሰንቋል፤ በዚህም ምክንያት ህዝቡ የሰላሙ ዘብ በመሆን ላለፉት ሁለት ወራት በሀገራችን አንጻራዊ የሰላም ንፋስ መንፈስ ጀምሯል።ዛሬ ያሉበትን እና ነገም የሚደርሱበትን ተፈጥሯዊ የህይወት ኡደት- ሰላማዊ የመሆኑን እንዴትነት ባለማመን ውስጥ መኖር በሰርክ ህይወታችንና በእድገት ስኬታችን ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽእኖ እጅግ ብዙ ነው።

ሀገራችን ገብታበት በነበረው ውስብስብ ቀውስ ሳቢያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በማወጅ ነገሮች መስመር እንዳይስቱ እና መልሶ ለማረቅም እንዳያዳግቱ ውጤታማ ስራ መስራት ችሏል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜያዊ መፍትሄ እንጂ መደበኛና ዘላቂ ሰላምን የሚያመጣ ባለመሆኑ መንግስትም ይህንኑ በመረዳት የሀገራችን እና የህዝቦቿ ሰላም ከውጫዊ አዋጅ እና ክልከላ ሳይሆን ከዜጎች ፍላጎትና የሰላም ወታደርነት የሚፍለቅ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በመላው ሀገራችን አንጻራዊ ሰላምን ማሰፈን ተችሏል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለነበርንበት ችግር ወቅቱ የሚጠይቀው አማራጭ ውሳኔ ሆኖ ቢያሻግረንም ለማደግ መለወጥ እንደሚታትር ታላቅ ህዝብ ደግሞ ያስከተላቸውና የሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መኖራቸው አይካድም።
በመሆኑም የረጅም ዘመን ታሪክ አኩሪ እና በዘመን የተፈተነ የአብሮነት ልክ የማይደራደርበት የሞራል ጥግ ራሱን እና ሌሎችንም ጭምር የሚጠብቅበት ባህላዊ የሰላም መቀነቻ ድግ እና ትላንቱን ዘክሮ፣ ዛሬውን መርምሮ እና ነገውንም ተንብዮ ሀገር አድባሩን በሰላም የሚሞላ ህዝብ ላላት ድንቅ ሀገር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ከቆየችው በላይ ትቆይ ዘንድ አይገባትም።እንደ ኢትዮጵያ ላለች የዲፕሎማቲክ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መናገሻ ለሆነች ሀገር የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቆይታን ለማብቃት የሚደረግ ጥረት እና የጋራ ርብርብ አንድምታው ብዙ ነው።

መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለማንሳት እና ህዝቡንም ወደ መደበኛው የአስተዳደር፣ የህግ እና የፍትህ መስመር ስለመመለስ ሲያስብ አዋጁን ለማወጅ ካስገደዱት ተግዳሮቶች አንጻር ያለውን ችግር በተመለከተ የመፍትሄውን ቁልፍ በማግኘት በኩል ሙሉ እምነቱ ያለው በህዝቡ እና በህዝቡ ላይ ብቻ ነው።መንግስት እና ህዝብ አዋጁን በማንሳት የሀገራችንን ሰላም እና የዜጎችን ደህና ወጥቶ ደህና የመግባት መብት፣ ምኞት እና ጸሎት እውን ለማድረግ በሚታትሩበት ወቅት ጉዳዩን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመግፋት እና ዞረን ተዟዙረን የቀውስ አዙሪት ውስጥ እንድንዳክር ለማድረግ የሚጥሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ሊኖሩ የመቻላቸውን ነገር ለአፍታም ቢሆን ቸል ልንል አይገባም።

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰበር ወሬ፦አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የሐገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሞ፣ ሕግ እና ሥርዓት መስፈኑን በማረጋገጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው፣ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡ ወደ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ይላካል ብለዋል፡፡ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲፀድቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ልዩ ወሬ፦ካሌብን ውሾች ይወዱታል

‘ከእንስሳ ጋር መኖር እኔ መርጫለሁ፣ የብቻ ጓደኛ ውሻ አሳድጋለሁ’

በሸገር ልዩ ወሬው፣ ወንድሙ ኃይሉ፣ ውሾች የሚወደውን፣ ውሾችም የእሱ ነገር አይሆንላቸውም ስለሚባለው ካሌብ ይነግረናል፡፡ቤት ወስጥ 5 ውሾችና 3 ደመቶች ያሉት ካሌብ ውጪ ደግሞ በየሄደበት የሚሸኙት፣ አምሽቶ ሲገባ እንደጋሻ ጃግሬ የሚጠብቁተ 10 ውሾች አሉት፡፡ለውሾቹ ቅንጥብጣቢ ለመግዛት በወር 500 ብር የሚያወጣው ካሌብ የውሾቹን ቁጥር የመጨመር ሐሳብ አለው፡፡
አስሩ የጎዳና ውሾች የሚያመሽበት ግሮሰሪ በር ላይ ከመውጫው ሰዓት ቀደም ብለው ይጠብቁና ቤት አድርሰውት ይመለሳሉ፡፡ አንዳንዴ ግን በጎዳናዎቹ እና ቤት በሚጠብቁት መካከል ፀብ መፈጠሩ አይቀርም ይለናል ወንድሙ ኃይሉ…ሙሉውን ያዳምጡ…

ውድ የሸገር ቤተሰቦች፣የሚቀጥሉትን ክፍሎች በቀላሉ እንድታገኙ ወደ ይፋዊ YouTube ቻናላችን ጎራ ብላችሁ Subscribe, Like አድርጉ እናመሰግናለን።

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የውጭ ምንዛሬ እጥረት

የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ኢትዮጵያን ክፉኛ እንደተፈታተናት ነው፡፡ ከመድሃኒት ጀምሮ ከውጪ የሚገቡ አስፈላጊ ፍጆታዎችን ለማስገባት የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ክምችት በብሔራዊ ባንክ ካዝና እንደሳሳ ይነገራል፡፡ በየአመቱ መክፈል የሚገባት ዕዳም የውጭ ምንዛሬን እጥረት አባብሶታል፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል ? የውጭ ምንዛሬን ክምችት ለማሳደግ መላው ምንድነው? ንጋቱ ሙሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሃብት ምሁር አነጋግሯል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሞያሌ በደረሰው ግጭት አጥቂዎቹ የመከላከያ አባላት፣ ጉዳያቸው በጦር ፍርድ ቤት እንደሚታይ ተነግሮ ነበር

በሞያሌ በደረሰው ግጭት አጥቂዎቹ የመከላከያ አባላት፣ ጉዳያቸው በጦር ፍርድ ቤት እንደሚታይ ተነግሮ ነበር፡፡ የጦር ፍርድ ቤት ምን ማለት ነው? ከመደበኛው ፍርድ ቤትስ በምን ይለያል?
እሸቴ አሰፋ የህግ ባለሙያ ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers