• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ህዳር 5፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡ተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር አያሌ ዜጐችን በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት ተምረው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ማስቻሉ በጥናት ተደርሶበታል፡፡

ይሁን እንጂ የተከታታይ ትምህርት አሰጣጡና ተመራቂዎች ጥራትና ውጤታማነት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ከትምህርት ተቋማቱ ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የሚደረግላቸው ክትትል ዝቅተኛ ነው፡፡

የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሩን ጥራት ከሚፈታተኑት ውስጥ የትምህርት መስኮች አግባብ ያለው ጥናት ሳይደረግባቸው መከፈትና ለሚሰጡ ትምህርቶች በቂ መርጃ መሣሪያዎች አለመኖራቸው ነው፡፡ለተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ደግሞ በአብዛኛው ከሚፈለገው ደረጃ በታች የሆኑና በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ መምህራንን መድቦ ማሰተማር በዋናነት ጥራቱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱት መሆኑን ነው ጥናቶች የሚያስረዱት፡፡

የፈተናና የነጥብ ወይንም ማርክ አሰጣጥ ስርዓቱም የላላ ነው ተብሏል፡፡የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለው የትምህርት አሰጣጥ ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን መዋቅር አዘጋጅቶ ለትምህርት ሚኒስቴር ቢልክም ምላሹ እንደዘገየበት መናገሩን መዘገባችን ይታወሣል፡፡የተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብሩ በመደበኛው የትምህርት ጊዜ ለመማር እድል ያላገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡ 

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከአዲስ አበባ ከተማ ከ10 ዓመት በላይ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ የሚያስመልስበት ህግ የለውም

ከአዲስ አበባ ከተማ ከ10 ዓመት በላይ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ የሚያስመልስበት ህግ የለውም፡፡በመሆኑም ለልማት ተሰጥተው በከተማዋ ለአመታት ታጥረው የከረሙ ቦታዎች በ6 ወር ውስጥ እንዲለሙ በከተማ አስተዳደሩ በኩል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማስፃፉን ሰምተናል፡፡

ቢሮው ለሸገር እንደተናገረው በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች 138 ቦታዎች ከ10 ዓመት በላይ ታጥረው ተቀምጠዋል፡፡ ከመካከላቸው 13ቱ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ስም የተያዙ ናቸው፡፡የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮው ለዘመናት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን ማምከን ወይንም ለመሬት ባንክ እንዲመለሱና ለሌላ ልማት እንዲውሉ ማድረግ ያልቻለው ቦታዎቹ ከሊዝ አዋጅ በፊት የተሰጡ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡

አልሚዎቹ ግንባታ እንዲጀምሩ ለ6 ወር የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ባያደርጉ ቢሮው በየትኛው ህግ ማስፈፀም ይችላል ስንል ጠይቀናል፡፡ የሊዝ አዋጁ ይሄንን ችግር እንዲፈታ ሆኖ ተሻሽሏል በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላም ሥራ ላይ ይውላል የሚም ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ቢሮው ለአመታት የታጠሩ የከተማዋ ውድ ቦታዎችን ለማስመለስ ወይም እርምጃ ለመውሰድ ገና ባልፀደቀ ህግ ላይ ተስፋ አድርጓል፡፡ መሬት አጥረው አስቀምጠዋል ከተባሉት መካከል ባለሃብቶች፣ ኤምባሲዎችና የመንግሥት ተቋማት ይገኙበታል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ህዳር 5፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ዝርያቸው እየጠፋ ነው የተባሉ ከብቶችን የማባዛት ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡  (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በመንገድ ዳር ያሉ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ለትራፊክ አደጋ እንዳይጋለጡ የበኩሌን እየሰራሁ ነው አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኳታር ዶሃ ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውሃ ሃብት ሚኒስትሮች በካይሮ ያደረጉት ስብሰባ ያለ ስምምነት መቋጨቱ ተሠማ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ የደረጃ ሀሌታው “ሀ” ግብር ከፋዮች 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ሰብስቤአለሁ አለ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • የብድር ጣሪያ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በሚሰጥ ድጋፍ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርስቲ ከቀዳማዊ ምኒልክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት የሚሰጡ ትምህርቶች ከሥፋታቸው አንፃር ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • በኦሮሚያ ክልል ከሥራ ውጭ ይሁኑ ተብለው የነበሩ የአፋን ኦሮሞ የአንደኛ ደረጃ መማሪያ መፃሕፍት ዳግም ለማስተማሪያነት እንዲውሉ እየታተሙ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ ሆቴሎች የመብዛታቸውን ያህል አገልግሎት አሰጣጣቸው ገና ብዙ ይቀረዋል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚሆን አዲስ የታሪክ መማሪያ መፅሐፍትን ለማውጣት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ...

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚሆን አዲስ የታሪክ መማሪያ መፅሐፍትን ለማውጣት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ ለ2010 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን ተማሪ የተመደበባቸው አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎችም ገና ለመማር ማስተማር ዝግጁ እንዳልሆኑ ሰምተናል፡፡ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትምህርት ሚኒስቴር ለታሪክ ትምህርት ራሱን የቻለ ክፍልና ሥርዓተ ትምህርት አልነበረውም፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የታሪክ ትምህርት ክፍል ከተዘጋ ቆይቷል፡፡አሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝቦችን ታሪክ የያዘ አዲስ የታሪክ መፅሐፍ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እያሰናዳሁ ነው ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፡፡መፅሐፎቹን ለማዘጋጀትም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ድጋፍ አንደተደረገለት ተናግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ፈተናን ውጤት እስካሁን አትሞ ያላሰራጨው ባጋጠመው...

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ፈተናን ውጤት እስካሁን አትሞ ያላሰራጨው ባጋጠመው የማተሚያ ማሽን ብልሽት ምክንያት መሆኑን ተናገረ፡፡ሲጠቀምባቸው የቆዩ ማተሚያ ማሽኖች በእድሜ ምክንያት መበላሸታቸውንም ተናግሯል፡፡

አዲስ የማተሚያ ማሽን ለመግዛት ዱባይ ስለመኖሩ ቢያረጋግጥም በምንዛሬ እጥረትና በአቅም ችግር ገዝተን ማስገባት አልቻልንም ያሉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ናቸው፡፡በ2009 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸው በየአካባቢው በሮስተር ቢላክም በካርድ አትሞ ለመስጠት ግን እስካሁን አልተቻለም ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡የ80 በመቶ ተማሪዎች ውጤት በካርድ ታትሟል ያሉት አቶ አርአያ የሁለት ክልል የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ግን ገና ከአታሚዎች በኪራይ ለማሳተም የግዢ ኤጀንሲን ደጅ እየጠናን ነው ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬው ህዳር 4፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • አዲስ የታሪክ መማሪያ መፀሐፍ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እየተዘጋጀላቸው መሆኑ ተሰማ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ራሱን ችሎ እንዲተዳደር የማሻሻያ ቻርተሩ ምክክር ተደረገበት፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች ከአፍ እስከ ገደፋቸው ሞልተው፣ ህፃናቱን አጭቀው  ነው፡፡ ስለዚሁ ድርጊት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣንን ጠይቀናል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ከድርጅቶቼ ሽያጭ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ አገኘሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በገዛ ደሞዛቸው ፍዳቸውን ያዩት ግለሰብ ፍትህ አገኙ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ፈተናን ውጤት እስካሁን አትሞ ያላሰራጨው ባጋጠመው የማተሚያ ማሽን ብልሽት ምክንያት መሆኑን ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በአዲስ አበባ ለልማት የተሰጡ ናቸው የተባሉ መሬቶች ለአመታት ታጥረው ይታያሉ፡፡ ወይ አለሙም ወይ አልተነጠቁም፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የሲውዘርላንዱ ኩባንያ ሲካ ኤድ አካል የሆነው ሲካ አቢሲኒያ የግንባታ ኬሚካሎች ማምረቻ ፋብሪካውን ቅዳሜ ዕለት አስመረቀ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ከዚህ በኋላ ከተማሪዎች ብዙ ደም እሰበስባለሁ አለ፡፡ (አንተነህ ሃብቴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽህፈት ቤት በገንዘብ አቅም ማነስ ምክንያት ጠበቃ ማቆም ላልቻሉ...

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽህፈት ቤት በገንዘብ አቅም ማነስ ምክንያት ጠበቃ ማቆም ላልቻሉ ከ800 በላይ ተከሣሾች የህግ ድጋፍ አገልግሎት መስጠቱን ተናገረ፡፡ጽህፈት ቤቱ በ2010 ሩብ ዓመት ነው ለ858 ተከሣሾች ነፃ የጥብቅናና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሰጠው፡፡

የነፃ የህግ አገልግሎቱ የተሰጠው በፌዴራል ከፍተኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎትና በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ነው ተብሏል፡፡ተከሣሾቹ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠባቸው ሲሆኑ በተከሰሱበት ወንጀል በገንዘብ አቅም እጥረት በግላቸው ጠበቃ ማቆም የማይችሉ እንደሆኑ ከጽህፈት ቤቱ የሩብ ዓመት ሪፖርት ተመልክተናል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽህፈት ቤት ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ለ47 ሺ 789 የወንጀል ተከሣሾች የጥብቅና እና የምክር አገልግሎት መስጠቱን ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ህዳር 1፣ቀን 2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በመገናኛ ብዙሃን መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የዜና ሽፋንን በተመለከተ መራራቅ እየታየ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የትራፊክ አደጋን ለመቆጣጠር ይረዳል የተባለው የራዳር ቁጥጥር ሥራ ሊጀምር ነው፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያለአንዳች ምክንያት በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠነቀቁ፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
 • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽህፈት ቤት በገንዘብ አቅም ማነስ ምክንያት ጠበቃ ማቆም ላልቻሉ ከ800 በላይ ተከሣሾች የህግ ድጋፍ አገልግሎት መስጠቱን ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥቅምት 30፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍላችሁ፣ ያለ ፌርማታችሁ የሚያስወርዳችሁ፣ የሚሰድባችሁና የሚያንጓጥጣችሁ የታክሲ ሹፌርና ረዳት ከገጠማችሁ በነፃ የስልክ መስመር 888 ጠቁሙኝ እስከ 1 ሺ ብር ድረስ እቀጣችኋለው አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የወደፊቱ መንገዶች ግንባታ የእግረኞችንም ወዲህ ወዲያ ታሳቢ የሚያደርግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊ ተናገሩ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • ናይል ኢንሹራንስ የባለፈው ዓመት ትርፍ በትርፍ የሆንኩበት ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በአዲስ አበባ በየመንደሩ በእጅ እየተገፉ ቆሻሻ የሚሰበሰብባቸውን ጋሪዎች ያስቀራሉ ተብለው የተገዙት ተሽከርካሪዎች እስካሁን ድረስ አገልግሎት መስጠት አልጀመሩም፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ 58 አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የዩኒቨርስቲዎችና ኢንዱስትሪዎች ትስስር ለሀገሪቱ እድገት ያለው ድርሻ ዝቅተኛ ስለሆነ ብዙ መሰራት እንዳለበት ተነገረ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በቅርቡ አዲስ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ አለ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)
 • ለአዲስ አበባ የመልካም አስተዳዳር ችግር መፍትሄ ኧረ መላ ምቱ እየተባለ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሕዳሴውን ግድብ ቦንድ በብዛት እየገዙ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እወቁልኝ አለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥቅምት 28፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers