• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን የሚያመርተው የጣሊያኑ ቬሮና ፔር ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ

ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን የሚያመርተው የጣሊያኑ ቬሮና ፔር ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ፡፡“ኩባንያው በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ የሚዘጋጁ አውደ ርዕዮችን አብረን እናሰናዳ የሚል ጥያቄ ለአዲሰ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አቅርቧል፤ ሥራው ለኢትዮጵያ የተሻለ ጥቅም ከሰጠ እንቅበለዋለን፤ ካልሆነ ግን ይቀራል ለማለት በጉዳዩ ላይ እየተመከረ ነው” ሲሉ የንግድ ትርዒት ኃላፊው አቶ ጋሻው አባተ ነግረውናል፡፡

ቬሮና ፔር በመጪው ግንቦት 3 በሚጀምረውና ግንቦት 7 በሚጠናቀቀው 10ኛው የግብርና እና ምግብ አለም አቀፍ ኤግዚብሽን ላይ ይካፈላል ተብሏል፡፡በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በመሰል ሥራ የተሰማራው የግብፁ ሹማን ኩባንያም ምርትና አገልግሎቱን ይዞ ይመጣል፤ 11 የአልጄሪያ ኩባንያዎችም ተካፋይ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ በግብርናና በምግብ ሥራ የተሰማሩ 30 የቻይና ኩባንያዎችም በአውደ ርዕዩ ይታደማሉ፡፡እንዲህ ያሉ አለም አቀፍ አውደ ርዕዮች በመሰል ሥራ ላይ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ልምድ በማካፈል ጥቅማቸው የጐላ ነው ያሉት አቶ ጋሻው 30 ኢትዮጵያዊያን ኩባንያዎችም ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ይታደሙበታል የልምድ ልውውጥም ይካሄድበታል ሲሉ ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 18፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ያለፈው ዓመት የብሔራዊ ፈተና ስርቆት ጉዳይ እስካሁን በፖሊስ ተጣርቶ ያልደረሰው መሆኑን ኤጀንሲው ተናገረ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የኢጣልያው ትራክተርና የእርሻ መሣሪያ አምራች ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ከሳውዲ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛቷ ከብዙ የአፍሪካ ሀገሮች የበለጠች ብትሆንም በልግስና የምትሰበስበው የደም መጠን አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ ብሔራዊ ደም ባንክ የምሰበስበው የደም መጠንና ፍላጎቱ እየተመጣጠነልኝ አይደለም ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በተፈጥሮ ወይም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት በነፃ ቀዶ-ጥገና፣ የመልሶ ማስተካከልና ፌዜዮቴራፒ ህክምና የሚሰጠው ኪዮር ኢንተርናሽናል የልጆች ሆስፒታል አዲስ የገነባውን የመልሶ ማስተካከያ ማዕከልን ዛሬ ረፋድ ያስመርቃል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • ኢትዮጵያ የ2017 የአለም ሀይድሮ ፓወር ጉባዔን በመጪው ወር ታዘጋጃለች ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኢትዮጵያና ላቲቪያ አንዷ በሌላኛዋ አገር ኤምባሲዎቻቸውን ሊከፍቱ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የተለያየ ጥፋት ለተገኘባቸው 12 የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የመቃወሚያ ማስረጃቸውን ትላንትና ለፍርድ ቤት ማቅረባቸው ተሠማ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የመቃወሚያ ማስረጃቸውን ትላንትና ለፍርድ ቤት ማቅረባቸው ተሠማ፡፡ከፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ከአቶ ሙላቱ ገመቹ ሸገር ዛሬ አንደሰማው ዶክተር መራራ ለተከሰሱበት ክስ የመቃወሚያ ማስረጃቸውን ትላንትና አቅርበዋል፡፡

የከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት በትላንትና ውሎው ላይ ዶክተር መረራ ጉዲና የተከሰሱበትን ክስ የመቃወሚያ መልስ የሰጡ ሲሆን አቃቤ ህግ ለመልስ መቃወሚያው መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ ለሚያዝያ 26፣ 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ በፍርድ ቤቱ በኩል መሰጠቱን አቶ ንጋቱ ለሸገር ነግረዋል፡፡

ዶክተር መረራን ከተለያዩ ህጋዊ ካልሆኑ ቡድኖች ጋር ተገናኝተዋል በሚል ጠርጥሮ የኢትዮጵያ መንግሥት የከሰሣቸው ሲሆን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስቱ መሆኑ ይታወሣል፡፡ዶክተር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የትላንትናው ለአራተኛ ጊዜ መሆኑንም ከአቶ ሙላቱ ገመቹ ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የ9 ወር የሥራ ሪፖርቱን ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርብ አርፍዷል

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የ9 ወር የሥራ ሪፖርቱን ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርብ አርፍዷል፡፡በትራፊክ አደጋ ምክንያት በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት መቀጠሉ አሳስቦኛል ብሏል መሥሪያ ቤቱ፡፡ ባለፉት 6 ወራት ብቻ 2 ሺ 46 የሞት አደጋዎች እንዲሁም 6 ሺ 416 ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩል የገጠር መንገዶችን እርስ በርስ በማገናኘት የታየዘው እቅድ እብዛም እንዳልተራመደበት መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ምክንያት ያለው ደግሞ የበጀት እጥረት ማጋጠሙን ነው፡፡የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የመሥሪያ ቤታቸውን ሪፖርት ሲያቀርቡ በአዲስ አበባ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር ያቃልላሉ ተብለው የተጠበቁት 400 አዲስ የከተማ አውቶብሶች ግዢ በጊዜ አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

የአውቶቡስ ትራንስፖርት መጠበቂያ ጊዜ 25 ደቂቃ እንደደረሰም ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ ማሻሻያ ጥናት ረቂቅ ህግ ውሣኔ እየጠበቀ እንደሚገኝም ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡በ9 ወራት ጊዜ ውስጥ የጂንካና ሐዋሳ ኤርፖርቶች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ያሉት አቶ አህመድ የሮቤ ኤርፖርት ግንባታ 84 በመቶ እንዲሁም የሽሬ ኤርፖርት 99 ነጥብ 7 እና የሰመራ ኤርፖርት 82 በመቶ ተጠናቋል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የተሽከርካሪዎች ቁጥር በአዲስ አበባ የሚገኙ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች አዲስ መለያ ሊሰጣቸው ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የተሽከርካሪዎች ቁጥር በአዲስ አበባ የሚገኙ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች አዲስ መለያ ሊሰጣቸው ነው ተባለ፡፡የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን እንደተናገረው በአዲስ አበባ ኮድ 2 የሰሌዳ ቁጥር ያላቸው የቤት መኪኖች መለያቸው ከ001 አሃዝ ጀምሮ A 99 ሺ 999 ደርሰዋል፡፡

በመሆኑም ከተያዘው የሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከሰሌዳ ቁጥሮቹ በፊት መለያ B በማድረግ B 0001 በሚል እንደሚሰራጩ አቶ ይግዛው ዳኛው የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ለሸገር ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡ ይህን አውቆ በአዲሱ መለያ ግራ እንዳይጋባ መረጃውን በተለያየ መንገድ እንደሚያሳውቅ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 17፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የተሽከርካሪዎች ቁጥር በአዲስ አበባ የሚገኙ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች አዲስ መለያ ሊሰጣቸው ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ወቅት እየጠበቀ የሚከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የሚመጣውን የእንስሣት መኖ እጥረትና መጥፋት ለማስቀረት ይረዳሉ የተባሉ 2 ማዕከሎች ትናንት በአለም አቀፍ የእንስሣት ምርምር ኢንስቲቲዩት ተመረቁ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ መድሃኒቶችን ለማሰራጨት የሚረዱኝ 57 ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች ገዛሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በድንበር ተሻጋሪ ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ ለመምከር ሱዳን ላይ የተገናኘው ቡድን የመኪና አደጋ ገጠመው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ወደ ተለያዩ ሀገራት ስጋ የሚልኩ ቄራዎች ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያቀርቡ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ሁለት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሽያጭ ወደ ግሉ ዘርፍ ሊዛወሩ ነው ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኦፌኮ የፖለቲካ ማኅበር መሪ ዶክተር መረራ ጉዲና በተከሰሱበት ጉዳይ ለፍርድ ቤት መቃወሚያቸውን ማቅረባቸው ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የትራንስፖርት ሚኒስቴር በትራፊክ አደጋ በዜጎች ላይ የሚደርሰው የሞትና የጉዳት መጠን መጨመር አሳስቦኛል አለ፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀሙን ሪፖርት ለፓርላማው አቅርቧል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሐት)
 • በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ወርቁ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ዛሬ ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ20 ገደማ በአንድ ጋራዥ ላይ የተነሳው እሳት 100 ሺ ብር የተገመተ ንብረት አጥፍቷል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሚያዝያ 17፣2009

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ

በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ፡፡ በ170 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመኪና ማቆሚያ ስፍራው ዘመናዊ ነው የተባለ ሲሆን 15 ፎቆች ላይ እንዲሁም በምድር ላይ መኪኖችን ያሳርፋል ተብሏል፡፡

የመኪና ማቆሚያው በፎቆቹ ላይ 90 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ሲሆን የምድሩ ደግሞ 50 መኪኖችን ማቆም እንደሚያስችል ወይዘሮ ታፈሱ አባይ በትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ለመኪና ማቆሚያዎቹ ሥፍራ ግንባታ በመንግሥት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውም ሰምተናል፡፡

የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የሙከራ ሥራ የጀመሩት የመገናኛ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥፍራው በምን ያህል ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ግን ተመን አልወጣለትም ተብሏል፡፡

የመኪና ማቆሚያ ሥፍራው ለ20 ዜጐች የሥራ እድል እንደፈጠረም ተነግሯል፡፡በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድና ወሎ ሰፈር አካባቢዎች ላይም የተጀመሩት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃሉ የተባለ ቢሆንም መዘግየት አላጋጠመም ወይ ብለን የጠየቅናቸው ወይዘሮ ታፈሱ የወሎ ሰፈሩና የአንዋር ወስጊዱ በቅርቡ ይጠናቀቃል አልዘገየም ያሉ ሲሆን በቸርችል ጐዳና የሚገነባው ደግሞ ከመሬት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ትንሽ ውዝግብ ተነስቶ ነበረ አሁን ችግሩ ስለተፈታ በቅርቡ ሥራው ይጀመራል ብለዋል፡፡

በከተማዋ 60 የተመረጡ ቦታዎች ላይም ሌሎች የመኪና ማቆሚያዎች ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምሕረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን አጡ ተባለ

በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን አጡ ተባለ፡፡ትላንት ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ በአዲስ ከተማ ወረዳ 4፣ 18 ማዞሪያ አካባቢ ከጦር ኃይሎች ወደ ልኳንዳ የሚጓዝ ከባድ መኪና መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበሩ የ70 ዓመት ሰውዬ ገጭቶ ገድሏቸዋል፡፡

ትላንት ከረፋዱ 3 ሰዓት ከ35 ገደማ ደግሞ በቦሌ ወረዳ 12 ቡልቡላ መድሐኒዓለም አካባቢ አንድ ሴኖትራክ የ75 ዓመት ሴትዬን መንገድ ሲያቋርጡ ገጭቷቸው ህይወታቸውም አልፏል ተብሏል፡፡በየካ ወረዳ 13 ካራ ዶሮ እርባታ አካባቢ ደግሞ ትላንት ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በትንሽ አውቶሞቢል የተገጨ የ30 ዓመት ሰው ህይወቱ አልፏል ሲሉ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከደረሱት አደጋዎች ከሦስቱ ሰዎች ሞት በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ለከባድ፣ አንድ ሰው ለቀላል የአካል ጉዳት የተዳረጉ ሲሆን 13 የንብረት አደጋም ተመዝግቧል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዚያ 16፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በባህር ዳር ከተማ ለ6ኛ ጊዜ የተዘጋጀው የአፍሪካ የደህንነት ከፍተኛ ፎረም ጉባዔ ትላንትና ተጠናቀቀ፡፡ ጉባዔው በባህሪው ውሣኔ ሳይሆን ምክረ ኃሣቦችን የሚያቀርብ በመሆኑ በዚያው መሠረት ተጠናቋል፡፡( የኔነህሲሣይ)
 • ድንገተኛ አደጋ ለደረሰባቸው፣ ለካንሰር ህሙማን፣ ለወላድ እናቶችና ለሌሎችም ደም ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ባለፉት 9 ወራት 134 ሺ ዩኒት ደም ማቅረቡን ብሔራዊ የደም ባንክ ተናገረ፡፡ (ትዕግሥትዘሪሁን)
 • አምና ድርቅ ተከስቶባቸው በነበሩና የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አካባቢዎች በቂ ዝናብ አልተገኘም ተባለ፡፡ (ትዕግሥትዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ ምርት ገበያና የመጋዘን አገልግሎት ድርጅት በድጋሚ ሊዋሃዱ ነው፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ በመኪና አደጋ 3 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ ከሚገነቡት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በመገናኛ አካባቢ አገልግሎት መስጠት ሊጀመር ነው፡፡ (ምሕረትስዩም)
 • የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀን ገቢ ግምት ጥናትን ከነገ ጀምሮ ሊያደርግ ነው፡፡ (ምሥክርአወል)
 • የኢትዮጵያና የሩዋንዳ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ጉባዔ ዛሬ በኪጋሊ ተጀመረ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባቀረበው የምርመራ ሪፖርት መሠረት ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት የዜጐችን ሰብዓዊ መብት ጥሰዋል በተባሉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ...

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባቀረበው የምርመራ ሪፖርት መሠረት ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት የዜጐችን ሰብዓዊ መብት ጥሰዋል በተባሉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የውሣኔ ኃሣብ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

የፍትሕ አካላትም ተገቢውን የማጣራት ሥራ በማስቀደም በቸልተኝነት የዜጐች ህይወት እንዲያልፍና ንብረትም እንዲጠፋ ምክንያት ሆነዋል የተባሉት ከፌዴራል እስከ ክልል ያሉ የሥራ ኃላፊዎችን ለህግ እንዲያቀርቡ ተጠይቋል፡፡

የምርመራ ሪፖርቱን ቀድሞ እንደተመለከተው የተናገረውና የውሣኔ ኃሣቡንም ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ያቀረበው የህግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዳለው ያልተመጣጠነ እርምጃ ወስደዋል የተባሉ የፀጥታ አስከባሪዎች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ በኮሚሽኑ የቀረበውን ኃሣብ እንደተስማማበት ለምክር ቤቱ ተናግሯል፡፡

በሣምንቱ መጀመሪያ ኮሚሽኑ ባቀረበው የምርመራ ሪፖርት በኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎች በተከሰተው አለመረጋጋት ከሥድስት መቶ በላይ ዜጎች መሞታቸውን፤ ዘጠኝ መቶ ያህል ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና በመቶ ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረትም እንደወደመ መናገሩ ይታወሣል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers