• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ኮካ ኮላ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት አለፈ

ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ኮካ ኮላ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት አለፈ…ምሽት 1፡40 አካባቢ ከኮካ ኮላ ወደ ጦር ኃይሎች ይጓዝ የነበረ ሲኖ ትራክ መኪና በተመሳሳይ አቅጣጫ ይጓዙ የነበሩ ሁለት እንዲሁም በቀኝ በኩል ቆመው የነበሩ ሌሎች ሁለት መኪኖች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በአደጋው፣ በአካባቢው የነበረ የ11 አመት ታዳጊ ህይወት ያለፈ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ ምክትል ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ለሸገር ተናግረዋል፡፡መንገዱ ብዙም አስቸጋሪ የሚባል እንዳልሆነ የተናገሩት ምክትል ኢንስፔክተሩ ነገር ግን አሽከርካሪዎች የመንገድ ዳር ላይ ምልክቶችን ስለማያከብሩና በፍጥነት ስለሚያሽከረክሩ በቦታው ላይ ተደጋጋሚ አደጋ ይደርሳል ብለውናል፡፡

በሌላ በኩል ትናንት ምሽት 5 ሰዓት አካባቢ ቸርችል ጎዳና አካባቢ በደረሰ ሌላ አንድ የትራፊክ አደጋ የአንድ አዛውንት ህይወት ሲያልፍ የአደጋው መንስዔ እየተጣራ እንደሆነም ሰምተናል፡፡አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን ቀንሰው በመጓዝ እየደረሰ ያለውን አደጋ እንዲቀንሱና ለሰው ህይወት እንዲሁም ለንብረት መጥፋት መንስዔ ከመሆን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ብለውናል ምክትል ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 29፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ ትላንት ማክሰኞ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ዛሬ በዓለም ደረጃ የጤና ቀን ይከበራል፡፡ ትኩረቱም የድብርት ህመም ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በኮንዶሚኒየም ቤቶች ጥራት ላይ ብዙዎች ቅሬታቸውን ያነሳሉ፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች አገናዝበው ተሰሩ የሚባሉት ቤቶች አሁን ላይ የገንዘብ አቅማቸው በፈረጠሙት እየተያዙ ነው ይባላል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በእኔ ስም የሚዘጁ ሃሰተኛ ደረጃዎች እንዳሉ አውቃለሁ፤ ለመቆጣጠርም እየሰራሁ ነው አለ፡፡ ኤጀንሲው ትናንት ከሚመለከታቸው ጋር እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ መክሯል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የሚሻሻሉ እና አዲስ የሚወጡ ደረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በማሳወቅ በኩል የሚጠበቅብኝን ያህል እየሰራሁ አይደለም አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለን አብላጫ ድምፅ በአፍሪካም ሆነ በዓለም ከቀዳሚዎቹ ተርታ ነን ይላል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኤርፖርት ጉምሩክ በፈጣን መልዕክት ከውጭ ሃገር በሚመጡ ዕቃዎች ላይ ገደብ ሊጥል እንደሚችል ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የኢህአዴግ ምክር ቤት ጉባዔ ዛሬ ተጀመረ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክት ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በግብፅ ባለፈው እሁድ የሆሳዕናን በዓል ሲያከብሩ በአሸባሪዎች ህይወታቸውን ላጡ 44 ሰዎች የተሰማትን ሀዘን ገለፀች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክት ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በግብፅ ባለፈው እሁድ የሆሳዕናን በዓል ሲያከብሩ በአሸባሪዎች ህይወታቸውን ላጡ 44 ሰዎች የተሰማትን ሀዘን ገለፀች፡፡የቅዱስ ፓትሪያርኩ ፕሮቶኮል መምህር ሙሴ ሃይሉ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ለግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ቴዎድሮስ ትናንት የሀዘን መግለጫ ደብዳቤ ልከዋል ብለዋል፡፡

ፓትሪያርኩ አሸባሪነት ለአለም ህዝቦች ሁሉ የማይበጅ አስነዋሪ ሥራ ነው ህዝበ ክርስቲያኑም ሆኑ የአለም ህዝቦች ይህንን ማውገዝ አለባቸው ብለዋል በደብዳቤያቸው፡፡I.S ኃላፊነቱን የወሰበደት የቦንብ ጥቃት በግብፅ 2 የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ የደረሰ ሲሆን 44 ሰዎችን ገድሏል፡፡

የግብፅ መንግሥት በዚሁ ሰበብ ለ3 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል፡፡አዋጁ የፀጥታ ሃይሎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር እንዲያውሉ የሚፈቅድ ነው፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታዬን በተቻለ መጠን እየሰራሁ ቢሆንም አገልግሎት ፈላጊው በጠየቀው መሠረት አልተሣካልኝም ብሏል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታዬን በተቻለ መጠን እየሰራሁ ቢሆንም አገልግሎት ፈላጊው በጠየቀው መሠረት አልተሣካልኝም ብሏል፡፡ቢሮው ዛሬ በጊዮን ሆቴል በሥሩ ከሚገኙ የአስተዳደሩ አመራሮች ጋር የዘጠኝ ወር አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት እንደሰማነው የ10/90፣ የ20/80 እና የ40/60 የቤት ግንባታዎች በተያዘላቸው ቀነ ገደብ እየሄዱ ቢሆንም መሥራት በፈለኩት ፍጥነት አይደለም ብሏል፡፡የቢሮው ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ እንደተናገሩት ከሆነ የቢሮው የግዢ ፖሊሲ ከጨረታ አወጣጥ ጋር የሚፈጥረው መጓተት አንዱ ግንባታው እንዳይፋጠን ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ገንዘብ ከባንክ ቶሎ ያለመለቀቁም ሌላ ችግር ሆኖብን ነበር ያሉት አቶ ይድነቃቸው ገንዘብ ከባንክ ቶሎ ባለመለቀቁ ምክንያት ተቋራጮች ሥራ አቁመው ወጥተው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ችግሩ አሁን ተፈቷል ያሉት አቶ ይድነቃቸው በቀጣዩ አመት ልናስተላልፍ በእቅድ የያዝነው የኮዬ ፈጨ የ20/80 የኮንዶሙኒዬም ግንባታን ጨምሮ በሌሎች ሳይቶች የሚገኙ ግንባታዎች የሚገጥሙ ችግሮችን ተቋቁመን ለማፋጠን እየተረባረብን ነው ብለዋል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ኢትዮጵያ በጥራት መጓደል ምክንያት ከተላኩበት ተመላሽ የሚሆኑ ምርቶቿ እየበዙ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በጥራት መጓደል ምክንያት ከተላኩበት ተመላሽ የሚሆኑ ምርቶቿ እየበዙ ነው ተባለ፡፡ይህ የተባለው ዛሬ የሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ብሔራዊ የጥራት ፎረም ምክክር ላይ ነው፡፡ከታሸገ ውሃ ጀምሮ እስከ ሌሎች ምርቶች ድረስ የጥራት መጓደሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ተነግሮ የምትጠቀሙት ምርት በጥራት ስለመመረቱና ማስረጃም ስለመኖሩ ሳታረጋግጡ እንዳትጠቀሙ ተብላችኋል፡፡የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በ2010 ዓ.ም የጥራት አመት አዋጅ ሊያውጅ እንደሚችልም ተናግሯል፡፡

በጥራት ያልተመረቱ ምርቶች በሰው ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት በተጨማሪ በከፍተኛ ሁኔታ በሀገሪቱ ወጪ ምርቶች ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገራት የምትልካቸው የግብርና ምርቶች ላይ ቅሬታ እየተነሳ ምርቶቹ እየተመለሱ በመሆኑ በጥራቱ ዙሪያ ሊታሰብበት ይገባል ተብሏል፡፡ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን ደረጃ መጨመር፤ ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡትን ደግሞ ማሣነስ በአንዳንድ ግለሰቦች ይታያል ይህም መስተካከል እንደሚገባው ተነግሯል፡፡

በሀገሪቱ የሚመረቱ ምርቶች በጥራታቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተቋቋመው ብሔራዊ የጥራት ፎረም በምርት ጥራት ዙሪያ ከሚሰሩና ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡በምክክሩ የጥራት ፎረም አባላት የሆኑ የመንግሥት ተቋማትና በጥራት ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ተገኝተዋል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት አንዲት የ4 ዓመት ህፃን መንገድ ስታቋርጥ በአንበሳ የከተማ አስውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ

በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት አንዲት የ4 ዓመት ህፃን መንገድ ስታቋርጥ በአንበሳ የከተማ አስውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ፡፡አደጋው ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ገደማ ያጋጠመ ሲሆን የአውቶቡሱ ሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 19127 አዲስ አበባ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ከኮተቤ ወደ መገናኛ ሲያመራ የነበረው አውቶብስ ሾፌር በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሆነም ረዳት ኢንስፔክተሩ ነግረውናል፡፡ስለ ህፃኗ ቤተሰቦችና እንዴት ብቻዋን ወደ መኪና መንገድ እንደገባች ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሚያዝያ 3፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የትራንስፖርት ባለሥልጣን ተቆጣጣሪዎች የሚጠቀሙበትን የተሽከርካሪ ማስቆሚያ ታፔላ በአዲስ መቀየሩን እወቁት ብሏል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በመጪዎቹ 25 ዓመቶች ኢትዮጵያ ለአፍሪካ፣ ለመካከለኛው ምሥራቅና ለአውሮፓ ሀገሮች ኤሌክትሪክ ለመሸጥ አቅዳለች፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • 40 የግል ክሊኒኮች በተመሣሣይ ስም አገልግሎት መስጠት ሊጀምሩ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ማርስና ጁፒተርን፣ ክዋክብቶችንና ጨረቃን፣ ፀሐይንና ሌሎችንም ፕላኔቶች እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ሆናችሁ እንድትጎበኟቸው ሊደረግ ነው ተባለ፡፡(ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ልማቷ የምታገኘውን ጥቅም ለማሣደግ የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት እስከ ማቋቋም ተጉዛለች፡፡ ሆኖም ዘርፉ የሰለጠነና የተማረ በቂ የሰው ኃይል እንደሌለው ይነገራል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም የዘርፉ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ኃላፊነት ተረክቧል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • ግንባታው ከተጀመረ 6ኛ አመቱን ላስቆጠረው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአዲስ አበባ ደረጃ በተያዘው አመት ለግድቡ ግንባታ በከተማ ደረጃ 150 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ  ማሳካት የተቻለው 118 ሚሊዮን ብሩን ነው ተብሏል፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ማደግ ሀገራት አስተማማኝ የኢኮኖሚ መሠረት እንዲኖራቸው ይረዳል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኢትዮጵያ በጥራት መጓደል ምክንያት ከተላኩበት ተመላሽ የሚሆኑ ምርቶቿ እየበዙ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በግብፅ ኦርቶዶክት ቤተ-ክርስቲያን ላይ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታዬን በተቻለ መጠን እየሰራሁ ቢሆንም አገልግሎት ፈላጊው በጠየቀው መሠረት አልተሣካልኝም ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት አንዲት የ4 ዓመት ህፃን መንገድ ስታቋርጥ በአንበሳ የከተማ አስውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሚያዝያ 3፣2009

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የበጋው መብረቅ - ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ

ኢትዮጵያ የሞተላትንና የተጋደለላታን ልጇን እሁድ በማህፀነ ምድሯ ከተተች፡፡ ለነፃነቷና ለክብሯ ደሙን ለማፍሰስ፣ አጥንቱን ለመከስከስ ወዶና ፈቅዶ ዘብ ሲቆምላት የኖረውን ልጇን በክብር ወደ አፈሯ መለሰችው፡፡ሌተና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ በወጣትና በጉልምስና ጊዜያቸው የጉልበትና የህይወት፣ በሽምግልናቸው የኃሣብና የተማፅኖ ስጦታ ለሀገራቸው አበርክተው ታሪካቸውን በጀብዱና በሞገስ ቀለም አድምቀው በባንዲራዋ ተሸፍነው እሁድ እስከ ወዲያኛው በክብር ተሸኝተዋል፡፡ሀገራቸው በውርደት ቀንበር እንዳትጠመድ፣ ህዝባቸው በቅኝ ገዢዎች የፍዳ ማጥ እንዳይሰምጥ በደማቸው የዋዧት ሌተና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ የጀግና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፅሞላቸዋል፡፡

ከ15 ዓመት እድሜያቸው ጀምሮ ጠመንጃ አንስተው፣ ተራራዋን መሽገው፣ ጫካዋን ተግነው፣ እሾህና ቁንጥር ጥሰው፣ ሱፋጫ ድንጋይና ገደል ቧጥጠው፣ ነዲድና ቁር ሳይበግራቸው ከአርበኝነት እስከ ጦር አዛዥነት፣ ከሽምቅ ተዋጊነት እስከ ሠራዊት አዝማችነት ባገለገሏት የሀገራቸው ምድር ጀብዷቸውንና አገልግሎታቸውን በጥቂቱም ቢሆን የሚያስታውስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነበረ የተከናወነላቸው፡፡ የመጨረሻው የአርበኞች መሪ፣ የመጨረሻው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት ሌተና ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ አስክሬን ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጉዞ ሲያደርግ የኢትዮጵያን ባንዲራ ተሸፍኖ ነበረ፡፡የምድር ጦር የሙዚቃ ጓድም የሀዘን ማርሽ እያሰማ ተከትሏል፡፡

ሙሉ የደንብ ልብሳቸውን የለበሱ 30 የሚሆኑ የመከላከያ ሠራዊት አባሎች ስለ ሀዘኑ መግለጫ በግራ ክንዳቸው ጥቁር ቱቢት አጥልቀው፣ ሳንጃ በአፈሙዝ ወድረው አጅበዋል፡፡ ሁለቱ የሰልፉ መሪዎችም ሻምላቸውን መዘው ሰልፉን ይመራሉ፡፡አርበኞች ጦርና ጐራዴ ይዘው ተከትለዋል፡፡ ከነዚህ በኋላ ሀዘንተኛው ታድሟል፡፡ከካቴድራሉም እንደደረሱ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች ማህበር ፕሬዝዳንትና የቀድሞ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የሌተና ጄኔራል ጃጋማን ታላቅነት የሚጠቁም ንግግር አስምተዋል፡፡የበለጠ ግን ባልተለመደ ሁኔታ ወ/ሮ ሙሉ ያሰሙት የፉከራ ግጥም ለጀግናው የአርበኞች መሪ የተገባ ሆኖ በሀዘን ተካፋዬቹ ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡ፉከራው በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋ የተነገረ ሲሆን የጄኔራሉን ገድል የሚያደምቅ ወኔ የሚቀሰቅስ ነበር፡፡

እድሜና ድካም የተጫጫናቸው አርበኞች የወ/ሮ ሙሉን ቀስቃሽ የፉከራ ግጥም ሲሰሙ መታገስ አልተቻላቸውም፡፡ ወኔያቸው ተፈንቅሎ ፉከራቸውን ማንደቅደቅ ጀምረዋል፡፡ይሁንና ለዘመናዊ የቀብር ሥርዓት አፈፃፀም ትኩረት የሰጠው አስተናባሪ የአርበኞቹን የወኔ ፉከራ በውትወታ አስቁሟቸዋል፡፡በዚያም ድርጊቱ ሥርዓቱ የአርበኞች መሪ ሆኖ ሳለ የአርበኞቹን ስሜት ቅድሚያ መስጠት ይገባው ነበር ሲሉ አንዳንድ የሀዘን ተካፋዬች ሲተቹ ሰምተናል፡፡ይሁንና አርበኞቹ የፀሎቱ ሥርዓት ተፈፅሞ አስክሬኑ ወደ መቃብር ቦታ ሲሄድ ፉከራና ሽለላቸውን ቀጥለዋል፡፡ እራሳቸውም ሌተና ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ በአርበኝነት ዘመናቸው “ገዳይ በልጅነቱ ዶቃ ሳይወጣ ካንገቱ ጃጋማ ጃጋማቸው እንደደረሰም ሚገጥማቸው እንደ ግጥምም ሚፈጃቸው” እያሉ ይፎክሩ ለነበሩት ገናን የጀግና ስም ላላቸው ጃጋማ ኬሎ የተገባ አሸኛኘት ነው ተብሏል፡፡

አስክሬኑ ግባ መሬት ከሚፈፀምበት ቦታ እንደደረሰ የሙዚቃ ጓዱ የሀዘን ማርሽ አሰምቷል፡፡ሥለ ጦር አዛዥነት ክብራቸውም የተሰለፈው ዘብ የህብረት ሰላምታ ሰጥቷል፡፡ በዚያን ጊዜም የግብዓት ተኩስ ተተኩሷል፡፡ይህም ለጦሩ አዛዦች የሚደረግ የክብር መግለጫ ነው፡፡ በአንድ ወቅት በሜጀር ጄኔራልነት ማዕረግ ሀገራቸውን ያገለገሉት የአሁኑ አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ የግብዓተ መሬቱ ሥርዓት እስኪፈፀም በሥፍራው ቆመው ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎን አክብረዋቸዋል፡፡እንዲህ በማድረጋቸው የመንግሥት ሹማምንት የሀገር ባለውለታቸውን አክብረው ማስከበር ለአሁኖቹ ማነቃቂያ ምሣሌ ይሆናልና የአፈ-ጉባዔው ድርጊት የተገባ ነው ተብሏል፡፡

ከ15 ዓመታቸው ጀምሮ ጡረታ እስከወጡበት 54 አመት ዕድሜያቸው ድረስ በውትድርና ሙያ ያገለገሉት ሌተና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት መጋቢት 29/2009 ዓ.ም ነበር፡፡ስለ ጀግንነታቸው “የበጋ መብረቅ” የሚል ቅፅል ስም የወጣላቸው ሌተና ጄኔራል ጃጋማ የሀገራቸውን የኢትዮጵያን የነፃነት ሸማ ለመግፈፍ ባሕር ተሻግሮ፣ ወሰን ሰብሮ የመጣውን የኢጣሊያ ኃይል ለመስበር ጫካ ሲገቡ የመንግሥት ሹም አልነበሩም፡፡ ወይም ሰላ ገደደን ለይተው በሚያውቁበት እድሜ ላይ አልነበሩም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በኢትዮጵያና በሱዳን የድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ የነፃ የንግድ ዞን ሊመሠረት ነው ተባለ

በኢትዮጵያና በሱዳን የድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ የነፃ የንግድ ዞን ሊመሠረት ነው ተባለ፡፡ሸገር ወሬውን የሰማው ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቃል አቀባይ ጽ/ቤት ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ መለስ አለም ነው፡፡ኃላፊው እንደነገሩን ከትላንትና አንስቶ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሱዳኑ ýሬዝዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ የግንኙነት ደረጃዎች ላይ በመከሩበት ጊዜ፤ በነፃ የንግድ ዞኑ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚደረገውና በቅርቡ የተጀመረው የህዝብ ትራንስፖርት እንዲሰፋና የባቡር ሥራውም እንዲፈጥን መሪዎቹ መነጋገራቸውን ከቃል አቀባዩ ሰምተናል፡፡ሱዳን ከህዳሴው ግድብ የኤሌክትሪክ ብርሃን የምታገኝበትን መንገድ በተመለከተ ከመግባባት ተደርሷል የሚሉት ቃል አቀባዩ አቶ መለሰ አለም ኢትዮጵያ ፖርት ሱዳንን ዋነኛ የቁሣቁስ ማስገቢያ መንገድ አድርጋ ልትጠቀም ማሰቧንም ነግረውናል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ግብዣ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ለ3 ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የመጡት ኡመር ሀሰን አልበሽር በደቡብ ኢትዮጵያ በሀዋሳ አካባቢ በመገኘት ዛሬ ጉብኝት ያደርጋሉ መባሉን ከቃል አቀባዩ ሰምተናል፡፡እለቱ በውል ባይታወቅም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በሱዳን ጉብኝት እንዲያደርጉ ከýሬዝዳንት አልበሽር ግብዣ መቅረቡንም አቶ መለሰ ለሸገር ተናግረዋል፡፡  

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መጋቢት 27፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በመብራት ችግር ለሚቋረጠው ውሃ መላ እየተበጀለት ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ሠራተኞች በማህበር እንዲደራጁ በሚደረገው ጥረት አንዳንድ አሰሪዎች እንቢተኛ ሆነው ተቸግሬአለሁ አለ፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬና ነገ ያደርጋል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በቅርቡ በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የደረሰው አደገኛው የበቆሎ ተምች አስቸኳይ መፍትሄ እየተፈለገለት ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስየኋላወርቅ)
 • በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች መንግሥት ነፃ ጠበቆች ያቆመላቸው ለተወሰኑ ተከሳሾች ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች የንግድ ቀጠና ሊመሠረት ነው ተባለ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን 37ኛው የጠቅላይ ምክር ቤት ስብሰባ እያካሄደ ነው፡፡ (አስፋው ስለሺ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers