• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሰኔ 16፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በገብረ ክርስቶስ ደስታ ማዕከል አዳዲስ የሥነ-ጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ ተባለ፡፡
 • የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ፡፡
 • የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት ዛሬ አፀደቀ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣የመብት ጥሰት ደርሶብኛል ብለው ወደ ኢትዮጵያ ከደረሱ ከ1 ሺህ 419 አቤቱታዎች 999 ያህሉ ተቀባይነት እንዳላገኙ ተሰማ

የመብት ጥሰት ደርሶብኛል ብለው ወደ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደጃፍ ከደረሱ ከ1 ሺህ 419 አቤቱታዎች 999 ያህሉ ተቀባይነት እንዳላገኙ ተሰማ… ባለፉት 11 ወራት ከዜጐች ለኮሚሽኑ የቀረቡ አቤቱታዎች በቁጥርም በዓይነትም ካለፉት ጊዜያት ጋር ሲነፃፀሩ መብዛታቸውን ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እንዳሉት ከቀረቡት 1 ሺህ 419 አቤቱታዎች መካከል 999 ያህሉ ተቀባይነት ያላገኙባቸው ምክንያቶች መካከል፣ አቤቱታዎቹ ከወንጀል ወይም ከሙስና ጋር የተገናኙ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው፡፡በተጨማሪም ከመልካም አስተዳደር ጋር በተገናኘ የደረሱ ተደራራቢ በደሎች ሆነው ከዚህ ቀደም ለእንባ ጠባቂ የቀረቡ ሆነው ስለተገኙ አቤቱታዎቹ በኮሚሽኑ ተቀባይነት አላገኙም ብለዋል፡፡ አንዳንዶቹ አቤቱታዎች ደግሞ የቀረቡት ከአዕምሮ መታወክ እና ከስነ-ልቦና ችግር የመነጩ ሆነው አግኝተናቸዋል፡፡ በመሆኑም 999ኙ አቤቱታ አቅራቢዎች የተሸኙት የምክር አገልግሎት ብቻ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ከኮሚሽነሩ ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኬንያ ናይሮቢ ይፋዊ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኬንያ ናይሮቢ ይፋዊ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀመሩ…ትናንት ምሽት ከዱባይ ናይሮቢ የገቡት አቶ ኃይለማርያም በኬንያ ለ3 ቀናት እንደሚቆዩም የኬንያ መንግሥት ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በ3 ቀናት ቆይታቸው ስለ ሁለቱ አገሮች ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት፣ ስለ አካባቢያዊ ሁኔታ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የዜጐችን ደህንነት አስጠብቄ ሥምሪቱን ለመጀመር የአቅሜን እየጣርኩ ነው

የውጪ ሀገር የሥራ ስምሪትን መልክ ለማስያዝና የዜጐችን ደህንነት አስጠብቄ ሥምሪቱን ለመጀመር የአቅሜን እየጣርኩ ነው ያለው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው… የሥራ ፈላጊዎችን ደህንነት የሚያስጠብቅ አዋጅም መውጣቱን ተከትሎ ለአፈፃፀሙ እንዲረዳ ደንብና መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡ በቅርቡም ተቋርጦ የነበረው የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ህግና ደንቡን ጠብቆ የዜጐች መብት ሳይጣስ እንደሚጀምር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ተናግረዋል፡፡

በውጭ አገር ሄደው መሥራት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ህጉን ተከትለው ጥቅማቸውና ደህንነታቸውን እንዲጠበቅላቸው ከተለያዩ የአረብ አገሮች ጋር ስምምነቶችን እንደተፈራረመም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ እስካሁንም ከኳታር፣ ኩዌትና ጆርዳን አገሮች ጋር በደህንነት ዙሪያ እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ ተፈራርሜያለው ብሏል መሥሪያ ቤቱ፡፡

ከሌሎች ተቀባይ አገሮች ከነዱባይ እና ሳዑዲ አረቢያ ጋርም ስምምነቱን ለመፈራረም መንገዶቼን እያጠናቀቅኩ ነው ብሏል፡፡ እግረ መንገዴንም በውጭ አገር ሥራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የሚደርሱበትን አገር ባህል እንዲያውቁ በፕሮጀክቴ አካትቼዋለው ማለቱን ሰምተናለ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 15፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ፈጥረዋል በሚል ጉዳያቸው ካለፈው በጀት አመት ወደዚህኛው በጀት አመት የተላለፉ 206 የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተባለ፡፡
 • የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አንድ ግለሰብ ከነተባባሪው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊያስገባቸው የነበሩ ከ5 ሺህ በላይ የሞባይል ቀፎዎችና መለዋወጫዎችን ያዝኩኝ አለ፡፡
 • የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፉት 11 ወራት ከቀረቡልኝ ከ1 ሺህ 400 በላይ አቤቱታዎች ሁለት ሦስተኛዎቹ ውሃ የሚያነሱ ሆነው አላገኘኋቸውም አለ፡፡
 • በአዲስ አበባ በተወሰኑ አካባቢዎች የ24 ሰዓት የትራፊክ ቁጥጥር ሊደረግ ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ያቀረቧቸው የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አባላት

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ያቀረቧቸው የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አባላት ሹመት በአንድ ተቃውሞ በዘጠኝ ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ… የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሹመት ጥያቄ በመንግሥት ረዳት ተጠሪ በኩል ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቦ ነው የፀደቀው፡፡ በቀረበው የውሣኔ ኃሣብ መሠረትም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የኮሚሽኑ ሰብሣቢ ሆነው ተሹመዋል፡፡የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትሩ አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱን ጨምሮ 23 ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የኮሚሽኑ አባል ሆነው ተሹመዋል፡፡

ሹመታቸው ከፀደቀላቸው የኮሚሽኑ አባላት መካከል የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት ወ/ሮ ሱአድ አህመድ ብቸኛዋ ሴት ተሿሚ ናቸው፡፡ አንዳንድ ሴት የምክር ቤቱ አባላትም ኮሚሽኑን ለመምራት ከተሾሙት መካከል የሴቶች ቁጥር አንሷል ሲሉ ተቃውመዋል፡፡ ተሿሚዎቹ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በሆኑት አቶ መድህን ኪሮስ አማካኝነት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከእንስሳት መድኃኒት የውጪ ገበያ ከፍ ያለ ገንዘብ አገኘች ተባለ

ኢትዮጵያ ከእንስሳት መድኃኒት የውጪ ገበያ ከፍ ያለ ገንዘብ አገኘች ተባለ… የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የማርኬቲንግና ሽያጭ ክፍል ኃላፊው አቶ መስፍን ታደሰ ለሸገር ሲናገሩ ዘንድሮ ለቤት እንስሣት የሚሆኑ መድኃኒቶች ወደ ኒጀር፣ ኮትዲቭዋር፣ ደቡብ ሱዳን እና ቡርኪናፋሶ ተልከው 1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የምግብ ንጥረ ነገር ማነስ ዛሬም ያልተፈታ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ችግር ነው ተባለ

የምግብ ንጥረ ነገር ማነስ ዛሬም ያልተፈታ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ችግር ነው ተባለ… ከተጀመረ ብዙ ዓመታት የሆነው በአዬዲን የበለፀገ ጨውን የማቅረብ ሂደት እንኳን በተደረገ ፍተሻ በቂ የአዬዲን ይዘት ያለው የጨው መጠን 26 በመቶ እንኳን እንደማይሞላ በጥናት ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

ይህ የተሰማው ዛሬ በደሣለኝ ሆቴል በተጀመረውና በስንዴ የምግብ ማቀናበር ሥራ ላይ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በንጥረ ነገር የበለፀገ ምግብን እንዲያቀርቡ  ለማድረግ በጉዳዩ ላይ በተሰናዳ ስልጠና ላይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ሌሎችም ተቋሞች በትብብር ባሰናዱት ሥልጠና ላይ በቀረቡ የጥናት ፅሁፎች አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም እንደ ቫይታሚንና ሚኒራል ያሉ ንጥረ ነገሮች ድብቅ ርሃብ አለበት፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃም የነዚህ ንጥረ ነገሮች በምግብ ውስጥ መኖርና ማጠርን የተመለከተ ጥናት መደረጉ በዝግጅቱ ላይ ተነስቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ አስመጪና ላኪዎች እንዲሁም የጉዞ ወኪል ቢሮዎች በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሣታፊዎች ናቸው

በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ አስመጪና ላኪዎች እንዲሁም የጉዞ ወኪል ቢሮዎች በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሣታፊዎች ናቸው ተባለ… የተሳሳተ ሰነድ በማዘጋጀት፣ ያልተጨበጠ ተስፋ በመስጠት በሀገር ውስጥ ደላሎች ዜጐች ወደማያውቁት እና ወዳልተመቻቸላቸው ሀገር እየተሰደዱ ለችግርና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በአገር ውስጥ በህገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ወይም /ሂውማን ትራፊኪንግ/ ከሚያጧጡፉ መካከልም አስጐብኚ ድርጅቶችና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በተለያዩ ምክንያትና መንገድ ቁጥራቸው ይህን ያህል ነው ተብሎ የማይታወቅ ሰዎች ወደተለያዩ የአረብ ሀገራትና የዓለም ጥግ እንደሚሰደዱ ተነግሯል፡፡

ወሬውን የሰማነው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ከሚመለከታቸው ጋር በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳይ ላይ በመከሩበት ጊዜ ነው፡፡ በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል፣ በሃጂና ዑምራ የጉዞ ቪዛ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በነፃ ቪዛ፣ በንግድና ትራንዚት ቪዛ፣ በሥራና በሌሎችም ቪዛ ዓይነቶች የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ በምክክሩ ላይ የቀረበ ጥናት ተናግሯል፡፡ በየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ብዙ ኢትዮጵያውን ወደ ውጪ አገር ለመሄድ ሲወስኑ በደላሎች እጅ ላይ እየወደቁ ለተለያዩ እንግልትና መብት ጥሰት እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡ ወደ ውጪ አገር ሄደው ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ ክብራቸው፣ ደህንነታቸው፣ የስነ-ልቦና እና አካላዊ ጥቃት ሳይደርስባቸው በህግ ማዕቀፍ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 14፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የምግብ ንጥረ ነገር ማነስ ዛሬም  ያልተፈታው የኢትዮጵያውያን ችግር ነው ተባለ፡፡ 
 • በተፈጥሮ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ያለባችሁ ነፃ ህክምና ተዘጋጅቶላችኋል ተብላችኋል፡፡
 • በኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እየበዛ ነው፡፡ አስመጪና ላኪ ተቋማትና የጉዞ ወኪሎች በዚሁ ተግባር ይሣተፋሉ ተብሏል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር በአንዳንድ አካባቢዎች በዝናብ መቆራረጥ ሳቢያ በእርሻ ስራው ላይ ችግር ሆኗል

የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር በአንዳንድ አካባቢዎች በዝናብ መቆራረጥ ሳቢያ በእርሻ ስራው ላይ ችግር ሆኗል አለ፡፡የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለሸገር ሲናገሩ ሰሞኑን በሰሜን ጐንደር፣ በደቡብ ወሎ እና በምሥራቅ አማራ አካባቢዎች የዝናብ መቆራረጥ አጋጥሟል ይህም ሰብል በወቅቱ እንዳይደርስ የሚያደርግ መሆኑ አሳስቦን የመፍትሄ ሥራ እያከናወንን ነው ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers