• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከዛሬ ነገ ይፈርሣል ሲባል የነበረው ኢምፔሪያል አካባቢ የሚገኘው የቦብ ማርሌይ አደባባይ በቅርብ ቀን መፍረሱ አይቀርም ተባለ

ከዛሬ ነገ ይፈርሣል ሲባል የነበረው ኢምፔሪያል አካባቢ የሚገኘው የቦብ ማርሌይ  አደባባይ በቅርብ ቀን መፍረሱ አይቀርም ተባለ፡፡በአደባባዩ አካባቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ አያጋጠመ የመጣውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ አደባባዩ ይፈርሳል ከተባለ የቆየ ሲሆን ሳይፈርስ ለመቆየቱም አደባባዩ ላይ የቆመው የቦብ ማርሌይ ሃውልት የት ይደረግ የሚለው ነበር አሁን ግን ችግሩ ተፈቷል ሲል የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡

የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው ሲናገሩ እንደሰማነው የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያደነቃቅፉ ሁኔታዎችን ለመቅረፍ ኤጀንሲው ባለፈው አንድ አመት የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየተከናወኑ ከሚገኙ ሥራዎች መካከል አንደኛው ለትራፊክ ፍሰቱ ችግር ሆኗል የተባሉና በጥናት የተለዩ አደባባዬችን ማፍረስ ሲሆን በቅርቡም ጃክሮስ አደባባይን ማፍረስ ተጀምሯል፡፡ የቦብ ማርሌይ አደባባይ የሚፈርስበት ቀንም ሩቅ አይሆንም ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በተቃዋሚ ጐራና በኢህአዴግ መሀከል በተደረገው ውይይት ላይ በአደራዳሪ ጉዳይ ትላንትና ልዩነት በመያዝ የታዩት ስድስቱ የፖለቲካ ፖርቲዎች በውይይቱ መቀጠል አለመቀጠላቸውን በተመለከተ በዛሬው ዕለት አቋማቸውን ያሳውቃሉ መባሉ ተሰማ

በተቃዋሚ ጐራና በኢህአዴግ መሀከል በተደረገው ውይይት ላይ በአደራዳሪ ጉዳይ ትላንትና ልዩነት በመያዝ የታዩት ስድስቱ የፖለቲካ ፖርቲዎች በውይይቱ መቀጠል አለመቀጠላቸውን በተመለከተ በዛሬው ዕለት አቋማቸውን ያሳውቃሉ መባሉ ተሰማ፡፡ሸገር ለፓርቲዎቹ ቅርበት ካላቸው ታማኝ ምንጮቹ እንደሰማው ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ ኢራፓ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ በጉዳዩ ዙሪያ ከውስጥ አባሎቻቸው ጋር እየመከሩ መሆኑን ነው፡፡

የስድስቱ ፓርቲዎች አቋም የሆነውን በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መሀከል በሚኖረው ድርድር ዙሪያ አደራዳሪ መኖር አለበት ያላደራዳሪ የሚደረግ ድርድር ውጤት አያመጣም በሚል ትላንትና በድርድሩ ላይ ከተናገሩ በኋላ ወደ ቤታቸው በመመለስ ከአባሎቻቸው ጋር ከመከሩ በኋላ ውጤቱን እናሣውቃለን ማለታቸውን ለአድማጮቻችን ትላንትና መንገራችን ይታወሣል፡፡

ስድስቱ ፓርቲዎች ዛሬ ያደርጋሉ ተብሎ በሚጠበቀው ንግግርና የውስጥ ውይይታቸው ላይ አቋማቸውን መለወጥ ካልቻሉ በውይይቱ የማይቀጥሉ ከሆን በድርድሩ ውስጥ የሚቆዩ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅ ይላል ማለት ነው፡፡ ትላንትና በታየው ውይይት ላይ አራት ፓርቲዎችን የያዘው መድረክ ፓርቲ በውይይቱ አለመቀጠሉ የታወቀ ሲሆን ስድስቱ ፓርቲዎች የሚቀላቀሉ ከሆነ በአጠቃላይ ከወይይቱ 10 ፓርቲዎች ይወጣሉ ማለት ነው፡፡ በኢህአዴግና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረው ቀጣይ ንግግር ለሚያዚያ 2 መቀጠሩ ታውቋል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ ለ6 ወራት ሥራ ላይ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጪዎቹ አራት ወራት እንዲራዘም የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ወሰነ

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ ለ6 ወራት ሥራ ላይ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጪዎቹ አራት ወራት እንዲራዘም የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ወሰነ፡፡በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡም አዋጁ እንዲራዘም ያለውን ፍላጐት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወር መራዘሙን አዋጁን ለማራዘም ለምክር ቤቱ የቀረበው መግለጫ ያስረዳል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስቱ ፀሐፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሣ እንዳሉት አዋጁ ባለፈው መስከረም 28/2009 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከታወጀና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ አንፃራዊ ሰላም አስገኝቷል፡፡ይሁንና አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች በህቡእ የሚንቀሣቀሱ ኃይሎች አሉ፤ ህገ-ወጥ የመሣሪያ ዝውውርም ይታያል ብለዋል፡፡

አንዳንድ አካባቢዎችም የፀጥታ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር ስላልዋሉ ለአዋጁ መራዘም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል፡፡አዋጁ ከዛሬ ጀምሮ ለመጪዎቹ አራት ወራት ሲራዘም ለማስፈፀም ወጥተው የነበሩ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል ያሉት አቶ ሲራጅ አብዛኛዎቹ ክልከላዎችም እንዳልተነሱ አስታውሰዋል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ ዘመን 21ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መራዘም በሙሉ ድምፅ ከማፀደቁ በተጨማሪ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴርን የ8 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ሲያደምጥ አርፍዷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 21፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ 4 ወራት አራዘመው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በአዲስ አበባ አላስፈላጊ የሆኑ አደባባዮች መፍረሳቸው የትራፊክ መጨናነቁን እያስተነፈሰው ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ቱርክ ከኢትዮጵያም ሆነ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት የንግድና ምጣኔ-ሐብታዊ ግንኙነት በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሠረተ እንደሆነ በአገሪቱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተናገሩ፡፡ በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አያሌው ጐበዜ በሁለቱ አገሮች መካከል የንግድና የምጣኔ-ሐብት ግንኙነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው ብለዋል፡፡ (የኔነህ ከበደ)
 • የመንግሥትን የበጀት አጠቃቀም የተመለከቱ ጥያቄዎች መበርከታቸውን ተከትሎ ኃላፊዎች በህግ የሚጠየቁበት ስርዓት ተፈጥሯል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ቡክ ወርልድ መፅሀፍትን በሆቴሎችና በባዛሮች ለገበያ እንደሚያቀርብ ተናገረ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • ስድስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ማህበራት ከኢህአዴግ ጋር በተጀመረው የውይይት ሂደት ስለመቀጠል አለመቀጠላቸው ዛሬ አቋማቸውን ያሣውቃሉ ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም መጋቢት 19፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ የልብና የካንሰር ህሙማንን ይረዳል የተባለው ማዕከል በ1 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ የልብና የካንሰር ህሙማንን ይረዳል የተባለው ማዕከል በ1 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ነው ተባለ፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኢንጂነሪንግና የኮንስትራክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኢንጂነር አስፍሃ ሰለሞን ለሸገር ሲናገሩ በሆስፒታሉ ግቢ እና በአቅራቢያው በ6 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል የተባለው የልብና ካንሰር ማዕከሉ ሥራ በግንባታው ከፊል ሥፍራ ላይ ያሉ ነዋሪዎች ተለዋጭ ቦታ እስኪያገኙ ተጓትቶ የቆየ ነበር አሁን አብዛኛው ቦታ ተለቆለት ግንባታው ተጀምሯል ብለዋል፡፡

የህክምና ማዕከሉን በ2 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ሥራ ለማስጀመር አስበናል ያሉት ኢንጂነር አስፍሃ ተመሳሳይ የልብና የካንሰር ማዕከል ግንባታዎችን በጐንደር፣ በመቐሌ፣ በሃዋሳና በድሬዳዋ እያስገነባን ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡ የህክምና ማዕከሉ ለኩላሊት ህሙማንም አገልግሎት እንደሚሰጥ ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 20፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ገንዘብ ሚኒስቴርና ውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር በጋራ ሆነው በውሃ ላይ ሊመክሩ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮ ጅቡቲ ድንበር ተሻጋሪ ከባድ መኪኖችን ከአደጋ ለመከላከል ይረዳል የተባለ ሥልጠና ለጭነት መኪኖቹ ባለንብረቶች ማህበር እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ የሚከናወኑ ዐውደ ርዕዮች የውጪ ባለሃብቶችን እየሳቡ፣ ለኢትዮጵያውያን የውጭ ገበያ እየፈጠሩ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ወደ ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከሚሄዱ ጉዳዮች የበዙት በሚስቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ናቸው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ኢትዮጵያ ስለ ግድቦቿ ደህንነት መረጃ የሚሰጥ መሣሪያ እየተከለች ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የልብና የካንሰር ማዕከል በ1 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የተቃዋሚና የገዥ ፓርቲው ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 የሱኳር ፋብሪካ በቀን 6 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት ሥራ ጀመረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ቦሌ ወረዳ 7 ጃክሮስ አደባባይ አለፍ ብሎ በሚገኘው ዳና የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ ላይ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ከ10 አካባቢ የተነሣ እሣት 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት አጠፋ

በአዲስ አበባ ቦሌ ወረዳ 7 ጃክሮስ አደባባይ አለፍ ብሎ በሚገኘው ዳና የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ ላይ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ከ10 አካባቢ የተነሣ እሣት 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት አጠፋ፡፡ መንስዔው ያልታወቀውና በጥጥ ፋብሪካው ላይ የተነሣውን እሣት ለማጥፋት የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን ከአራት ቅርንጫፎቹ የአደጋ መከላከያ መኪኖች ያሰማራ ሲሆን 40 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት አድኛለሁ ብሏል፡፡

አደጋው በሰዎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሰም ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ዜጎች መካከል ከ4 ሺ 500 በላይ የሚሆኑት ፈፅመውታል በተባለው የጥፋት ደረጃና ክብደት ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ተናገረ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ዜጎች መካከል  ከ4 ሺ 500 በላይ የሚሆኑት ፈፅመውታል በተባለው የጥፋት ደረጃና ክብደት ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ተናገረ፡፡ባለፈው አመት ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ከ26 ሺ በላይ ዜጐች በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር መርማሪ ቦርዱ አስታውሷል፡፡

ከመካከላቸው ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑት ትምህርት ተሰጥቷቸው መፈታታቸውን፤ 4 ሺ 996ቱ ግን ጉዳያቸው በህግ ፊት መቅረቡን ቦርዱ ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርብ ሰምተናል፡፡ጉዳያቸው በህግ ከተያዙትም 475 ተጠርጣሪዎች በእድሜና በጤና ምክንያት መለቀቃቸውን ሰምተናል፡፡

መርማሪ ቦርዱ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች በአካል ተገኝቶ የተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ መታዘቡንም ተናግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በደም ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን ለክቶ የሚቀጣው የትራፊክ ደንብ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ

በደም ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን ለክቶ የሚቀጣው የትራፊክ ደንብ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ…አሽከርካሪዎች ከነገ ጀምሮ በደማችሁ ውስጥ ያለው የአልኮል መጠን ተለክቶ መሆን ካለበት በላይ ከሆነ ቅጣት ይጠብቃችኋል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነው፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ ዛሬ ረፋድ ላይ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ሲናገር እንደሰማነው በደም ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን የሚለካው (አልኮል ቴስተር) መሣሪያ በበቂ ሁኔታ ተገዝቷል፤ ባለሙያዎቹም ሰልጥነዋል ተብሏል፡፡የፖሊስ ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዬ ደንደና በደም ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን ለክቶ አሽከርካሪዎቹን የሚቀጣው ደንብ ለወራት ያለ ቅጣት በሙከራ ላይ መቆየቱን አስታውሰዋል፤ ከነገ ጀምሮ ግን ወደ ቅጣት እንገባለን ብለዋል፡፡በደም ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን ከሚለካውና ተላልፈው የሚገኙትን ከሚቀጣው ደንብ በተጨማሪ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ወይንም ራዳርም በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የመንገድ ትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ ህብረተሰቡን ማስተማርና ማስገንዘብ የሚያስችል አቅማቸውን ተግባር ላይ እንዲያውሉት ጥሪ ቀረበላቸው

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የመንገድ ትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ ህብረተሰቡን ማስተማርና ማስገንዘብ የሚያስችል አቅማቸውን ተግባር ላይ እንዲያውሉት ጥሪ ቀረበላቸው…በየአመቱ የሺዎች ኢትዮጵያዊያንን ህይወት የሚቀጥፈውና የሚሊዮኖች ንብረት የሚያወድመው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ብዙ ቢሰራበትም በሚፈለገው ልክ ለውጥ እንዳልመጣበት በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታው አቶ ደሣለኝ አንባው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

አቶ ደሣለኝ የትራፊክ አደጋ የሁሉንም በር የሚያንኳኳና በእኛም ላይ መች እንደሚመጣ የሚታወቅ ባለመሆኑ ህዝቡን ማስተማር እንደ መፍትሄ አይተነዋል ብለዋል፡፡ህብረተሰቡን በተለያዩ መንገዶች የሚያገኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በሙያችሁ ግንዛቤ ፍጠሩልን፣ አግዙን የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ 700 ሺ አካባቢ ተሽከርካሪዎችና ንፅፅሩም 8 ተሽከርካሪ ለ100 ሺ ሰው ሆኖ ሳለ የመንገድ ትራፊክ እንቅስቃሴዋ ከዜጐቿ አልፎ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሰዎች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተነግሯል፡፡በኢትዮጵያ ጐዳናዎች እንዳታሽከረክሩ የሚል መልዕክት እስከ መናገር የደረሱ ወገኖች መኖራቸውን ሲነገር ሰምተናል፡፡

ዛሬ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ግንዛቤ ኖሯቸው በሥራቸው እንዲያግዙ የተጠየቁ ሲሆን ከነገ በስቲያ ለፌዴራል ተቋማት የህዝብ ግንኙነትና መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እንዲሁም መጋቢት 22 ከ400 በላይ የፌዴራል ተቋማት ሾፌሮች ግንዛቤ እንዲኖራቸውና እንዲወያዩ ማቀዱን የትራንስፖርት ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers