• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በኦሮሚያና በሶማሌ አካባቢዎች በተነሣውና ብዙ ሰዎችን ለሞትና ለመፈናቀል የዳረገውን ግጭት በተመለከተ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች...

በኦሮሚያና በሶማሌ አካባቢዎች በተነሣውና ብዙ ሰዎችን ለሞትና ለመፈናቀል የዳረገውን ግጭት በተመለከተ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ተጨማሪ መግለጫ ዛሬ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከሣምንት በፊት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሬ ሌንጮ ግጭቱን በሚመለከት በሰጡት መግለጫቸው ላይ ወቅታዊ የሆነውን የግጭቱን መንስዔ መንግሥት አለማወቁን ተናግረው ነበር፡፡

ከአመታት በፊት በሁለቱ አካባቢዎች የድንበር ጉዳይን የተመለከተ ህዝበ ውሣኔ ቢደረግም ውጤቱ መሬት ላይ ባለመሰራቱ ግጭቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲታዩ ነበር ያሉት ኃላፊ ሚኒስትሩ በቅርቡ የደረሰውን ግጭት በተመለከተ የመገናኛ ብዙኃኖችና ማኅበራዊ ድረ-ገፆች ጉዳዩን ከማባባስ መጠንቀቅ አለባቸው ብለው ነበር፡፡

በሶማሌና በኦሮሚያ አካባቢዎች የተነሳው ግጭት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር አለመዋሉንና የግጭቱንም መንስዔ መንግሥት አለማወቁን ሚኒስትሩ ባለፈው መግለጫቸው ላይ የተናገሩ ሲሆን በዛሬው መግለጫቸው ላይ መንግሥት የደረሰበትን ውጤት ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መንግሥት ባለፈው ሣምንት በሰጠው መግለጫው በግጭቱ ከሁለቱም ክልሎች 20 ሺ ሰዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል ማለቱ የሚታወስ ሲሆን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃኖች ግን የተፈናቃዩን ቁጥር 140 ሺ አድርሰውታል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ለዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል ጥንቃቄ ይደረግ አለ

የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ለዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል ጥንቃቄ ይደረግ አለ፡፡መስቀል የውጪ ሃገር ቱሪስቶች በተገኙበት በድምቀት የሚከበር በዓል ነው ይህንን በዓል ከእሣት አደጋ ተጠብቀን እንድናከብረው ኤሌክትሪክ መስመሮች በሚበዙበት ቦታ ዳመራ ባለመደመር፣ ችቦ በቤት ውስጥ በሚለኮስ ጊዜ ጥንቃቄ በማድረግ፣ በተጠጋጉ ቤቶች አካባቢ እሣት ባለማያያዝ ጥንቃቄ አድርጉ ብሏል፡፡

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሰለሞን መኮንን ለሸገር እንዳሉት በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በኩል አደጋን ለመከላከል የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችንና መኪኖችን በዛ አድርገን በዝግጅት ላይ ነን ብለዋል፡፡አይበለውና አደጋ ቢያጋጥም በ0111 55 53 00 ወይም በ0111 56 86 01 ደውላችሁ ጥሩን ሲሉም አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 15፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ የሚገኙ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ዋጋ ተገልጋዩ ሊመለከት በሚችልበት ሥፍራ ማስቀመጥ ይገባቸዋል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ግጭትን በተመለከተ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የፋሺስት ኢጣሊያ መሪ የነበረው ቤንቶ ሞሶሎኒ ከነሐስ የተሰራ ቅርፅ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት አለ ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በጋምቤላ በሚገኙ የመጠለያ ጣቢያዎች የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ብዛት እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ የስደተኞቹ መብዛት አዲስ መጠለያ እንዲዘጋጅ አስገድዷል ተብሏል፡፡ (የኔነህ ከበደ)
 • የኢትዮጵያ ጥቃቅን፣ አነስተኛ፣ ታዳጊና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አሰሪዎች ፌዴሬሽን የተቋማቱን የማምረቻ ቦታና የገበያ ችግሮች ለመቅረፍ ትልቅ ጉባዔ ላደርግ ነው አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ከ8 ሺ በላይ ታፔላ ለኮድ 3 ሚኒባሶች ሰጥቻለሁ አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ለዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል ጥንቃቄ ይደረግ አለ፡፡ (ወንድም ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 11፣ 2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኦሮሚያ ክልል 6 ሺ 700 የመንግሥት ሠራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መቀጠራቸውን በማመን ይቅርታ ጠይቀዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ሽንጠ ረጃጅምና ቅንጡ የተባሉ ሊሞዚንና ሀመር መኪኖች በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ያለ አገልግሎት ቆመው እየተበላሹ ነው ተብሏል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በጉለሌ ክፍለ ከተማ ምግብ ሰርቶ በማቅረብ የተደራጁ በውሃና በሌሎችም ችግሮች ሥራችን እየተስተጓጐለ ነው አሉ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)
 • ኢትዮጵያና ሱዳን በትናንትናው እለት የሁለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት አደረጉ ተባለ፡፡ (አንተነህ ሃብቴ)
 • ለአዲስ አበባ የመንገድ መጋጠሚያዎች ማሻሻያ ሊደረግላቸው ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን የሚያጠና ተቋም ይፋ ሆነ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በአገር ፍቅር ቲአትር ቤት ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት አቶ ከበደ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

እየተገባደደ ባለው ክረምት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከ900 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል

እየተገባደደ ባለው ክረምት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከ900 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ ንብረትም መውደሙን ሰምተናል፡፡የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሸገር እንደተናገረው የጎርፍ አደጋው የደረሰባቸው ክፍለ ከተሞች 6 ሲሆኑ ሦስቱ ክፍለ ከተሞች የከፋ አደጋ የደረሰባቸው ናቸው ብሏል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎች፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ሁለት ወረዳዎችና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አንድ ወረዳ የጐርፍ አደጋው የከፋባቸው ነበሩ ተብሏል፡፡በሦስቱ ክፍለ ከተሞች በጎርፉ ምክንያት ከቤታቸው ተፈናቅለው ድጋፍ እየተደረገላቸው ያሉ 324 አባወራና እማወራዎች ሲሆኑ ከነ ቤተሰቦቻቸው 991 እንደሚደርሱ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሣያል፡፡

ይህን የነገሩን በቢሮው የማኅበራዊ ችግር ተጎጂዎች መልሶ ማቋቋሚያ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማናዬ አባይ ናቸው፡፡በጐርፍ የተፈናቀሉት 991 አዲስ አበቤዎች በተለያዩ ወጣት ማዕከላት ተጠልለው ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡ከ940 በላይ ብርድ ልብስ፣ አንሶላና ፍራሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የውሃ ኮዳ፣ ፎጣ፣ ቲሸርትና ሣሙናም እንደታደላቸው ሰምተናል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአራዳ ክፍለ ከተማ በዚሁ ክረምት በደረሰ የእሣት አደጋ 32 ሰዎች ተፈናቅለው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አቶ ማናዬ ነግረውናል፡፡በተያያዘም የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን 2010 ዓ.ም ከመግባቱ በፊት በነበሩት የክረምት ወራት በጎርፍ አደጋው 28 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን ነግሮናል፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በጎርፍ የወደመው ንብረት 28 ሚሊዮን ብር እንደሚደርስ ያጠናሁት አገለግሎት በሰጠሁባቸውና የጐርፍ አደጋው በደረሰባቸው 32 ቦታዎች ብቻ ነው ብሏል፡፡በክረምቱ የጐርፍ አደጋ ደርሶባቸው እኔ አገልግሎት ያልሰጠሁባቸው የበዙ ቦታዎች ስለነበሩ በጐርፍ የወደመው ንብረት 28 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ማለትም አይቻልም ብሏል ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰበው ታክስ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ብሔራዊ ምርት የሚያበረክተው ድርሻ 13 በመቶ እንኳን አይሆንም ተባለ

በኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰበው ታክስ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ብሔራዊ ምርት የሚያበረክተው ድርሻ 13 በመቶ እንኳን አይሆንም ተባለ፡፡መንግሥት መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ እንዲያሟላ ከተፈለገ ታክስ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ብሔራዊ ምርት የሚያበረክተው ድርሻ ከ15 በመቶ ማነስ አንደሌለበት ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የታክስ ስርዓት ላይ የተደረጉ ጥናቶች እየቀረቡ ውይይት የሚካሄድበት የተመራማሪዎች ጥምረት /ኔትወርክ/ ዛሬ በካፒታል ሆቴል ተመስርቷል፡፡ኔትወርኩ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ታክስን አስመልክቶ የተካሄዱ ጥናቶች በውይይት ዳብረው ለመንግሥት ግብዓት የሚሆንበትን መንገድ ያፈላልጋል ተብሏል፡፡

የታክስ እውቀትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት የተመሠረተ ጥምረት እንደሆነም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የፊስካል ፖሊሲ ዳይሬክተር አቶ መዝገቡ አመሃ ተናግረዋል፡፡በየአመቱ በሚዘጋጀው ውይይት በዩኒቨርስቲዎች ያሉ ወጣት ተመራማሪዎች ጥናቶቻቸውን እንደሚያቀርቡበት ተናግረዋል፡፡

የተመራማሪዎቹን አቅም ለማሳደግ የተመሠረተ ጥምረት እንደሆነም ከአቶ መዝገቡ ሰምተናል፡፡የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ጥምረቱ እውን እንዲሆን ድጋፍ አድርጓልም ብለውናል፡፡

ICTD በተባለ የእንግሊዝ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሣቀስ ጥምረት እንደሆነም ተነግሯል፡፡በአስተዳደር ውስጥ ግን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና የምርምር ተቋማት የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይኖራሉ ተብሏል፡፡

እስከ ነገ በሚቆየው የጥምረቱ የመጀመሪያ መድረክ የኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት አስመልክቶ የተካሄዱ የተለያዩ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ሰምተናል፡፡ጥናቶቹ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ብሔራዊ ምርት 12 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ የሚያበረክተውና ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰበው የኢትዮጵያ ታክስ አስተዋፅኦው ከዚህ ከፍ የሚልበትን መላ የሚጠቁሙ እንደሚሆኑ ተገምቷል፡፡

ንጋቱ ረጋሣ

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 10፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ ውስጥ 8 ከመቶ የህክምና ዶክተሮች ብቻ ናቸው በገጠር ከተሞች የሚሰሩት ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስብርሃኑ)
 • በዚህ ክረምት በአዲስ አበባ ከተማ ከ900 በላይ ሰዎች በጐርፍ ተፈናቅለዋል፡፡ 28 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረትም ወድሟል፡፡ (ትዕግሥትዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰበው ታክስ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ብሔራዊ ምርት የሚያበረክተው ድርሻ 13 በመቶ እንኳ አይሆንም ተባለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • በስምንት ወራት ውሰጥ ከ72 ሺ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጋ ትሰራለች ሲል የንግድ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ (አስፋውስለሺ)

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የኃይል መጨናነቅ ያለባቸውን ዋና ዋና የክልል ከተሞች የኃይል ማከፋፈያ...

አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የኃይል መጨናነቅ ያለባቸውን ዋና ዋና የክልል ከተሞች የኃይል ማከፋፈያ ለማሻሻል ከ72 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መመደቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡

የአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን በማጥናት የኃይል ማከፋፈያ መስመሮችንና ትራንስፎርመሮችን የማሻሻል አንዲሁም የማስፋፋት ሥራዎች በማጠናቀቅ በተጨማሪም የስድስት የዞን ከተሞች በ72 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የመካከለኛና ዝቅተኛ የኃይል ማከፋፈያ መስመሮችና ትራንስፎርመራቸውን የማሻሻል እንዲሁም መልሶ ግንባታ ሥራዎች ይሰራሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ የኃይል ፍላጎትና ሥርጭት የተስተካከለ ለማድረግ ከቻይና መንግሥት በተገኘ 163 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር የማሻሻያ ሥራዎች የተጀመሩ ሲሆን በዚህ ዓመት መካከለኛና ዝቅተኛ መስመሮችን እንዲሁም ትራንስፎርመሮችን የማሻሻልና መልሶ ግንባታ ሥራዎች በማጠናቀቅ የሚያጋጥመውን የኃይል መቆራረጥ እንዲሁም ተቋርጦ የሚቆይበትን ጊዜም ለመቀነስ ይሰራል መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከ16 ዓመት በፊት ያወጣችውን የባህል ፖሊሲ አሻሽላ ይፋ አድርጋለች

ኢትዮጵያ ከ16 ዓመት በፊት ያወጣችውን የባህል ፖሊሲ አሻሽላ ይፋ አድርጋለች፡፡የቀደመው ፖሊሲ በርካታ የባህል ጉዳዮች የተካተቱበት የነበረ ቢሆንም አጠቃላይ ይዘቱ ግን የባህልን ምጣኔ-ሐብታዊ ፋይዳነት አጉልቶ ያሳየ አልነበረም ተብሏል፡፡

የባህል ሀብትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀትና የአሰራር ቅንጅቶችን በግልፅ ያላመለከተ እንደነበርም ተነግሯል፡፡በተለይም ባህል ከወቅቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር ሊኖረው በሚችለው ቁርኝት ትኩረት የሰጠ እንዳልነበር ሲነገር ሰምተናል፡፡

በባህል ልማትም፣ ጥፋትም መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ አቅም አላቸው ያሉት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተሩ አቶ ደስታ ካሣ ሀገሪቱ ባህሏን ጠብቃ ከአለም ሀገራት ጋር እኩል እንድትቆም ሁሉም ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይ ባህልን የመጠበቁን ሥራ ማኅበረሰቡ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ቤተሰብ ትኩረት ሰጥተው ሀገርን፣ ማንነነትን ከሚያሳጡ ከባህል ወረራ ለመታደግ መሥራት አለባቸው ተብሏል፡፡ሀገሪቱ በነበራት የቅኝ ግዛት ምከታ ባህሏንና ነፃነቷን አስጠብቃ በመቆየቷ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት እንደ ምሣሌ ትታይ ነበር ያሉት አቶ ደስታ አሁን ላይ ግን ያን ለማስጠበቅ ብዙ መሰራት እንደለበት የሚያሳዩ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ለመሰማራት የጠየቁ 17 የኔዘርላንድስ ባለሃብቶች ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ፡፡ ባለሃብቶቹ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከተያዘና ሦስት ሺ ሄክታር ከሚገመት መሬት የተወሰነውን ለመውሰድ የጠየቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያና የቼክ ሪፐብሊክን የቢዝነስ ልውውጥ ያሳድጋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የስኳር እጥረት ችግርን ለመፍታት ሦስት የመንግሥት ተቋማት በጋራ እየሰሩ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ለተለያዩ የኢትዮጵያ ወረዳዎች የኤች.አይቪ/ኤድስ መከላከያ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • አዲስ አበባ ዘንድሮ 4 ታላላቅ የንግድ ትርዒቶችን ታስተናግዳለች ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የተሻሻለውን የኢትዮጵያ የባህል ፖሊሲ እወቁት ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የኃይል መጨናነቅ ያለባቸውን ዋና ዋና የክልል ከተሞች የኃይል ማከፋፈያ ለማሻሻል ከ72 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መመደቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት እንዴት መሻሻል ይገባዋል የሚለው የትምህርት ባለሙያዎች ከዛሬ ጀምሮ...

የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት እንዴት መሻሻል ይገባዋል የሚለው የትምህርት ባለሙያዎች ከዛሬ ጀምሮ ከሚመክሩባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ተባለ፡፡የመንግሥትና የግል የሆኑ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉ የትምህርት ባለሙያዎች የ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ውጤታማ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ሥልጠና ገብተዋል፡፡

በሥልጠናው ይመከርባቸዋል ከተባሉት ጉዳዮች መካከል በተማሪዎች ማንነትና ሥነ-ምግባር ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ ማምጣት አልቻለም ተብሎ ሲወቀስና  ሲተች የቆየው የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት እንዴት ይሻሻል የሚለው አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሸገር እንደተናገረው ትምህርቱ አለበት የተባሉ ችግሮችም በምክክሩ ተነቅሰው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከትምህርት ጉባዔው የሚገኘው ኃሣብም በመጪው ጊዜ የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርትን መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ለመቅረፅ የሚያሽል አድርጎ ለማሻሻል ይረዳል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ እስከ መጪው መስከረም 12 በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ እስከ መስከረም 15 በሚዘልቀው የትምህርት ባለሙያዎች ሥልጠና ሌሎችም 4 አጀንዳዎች ይመከርባቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡

በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አበበ ቸርነት እንደነገሩን የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የመምህራን ሚና ምን መሆን አለበት የሚለውም አንዱ አጀንዳ ይሆናል፡፡በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘርፎች የነበራቸውን አፈፃፀም እንደሚገመግሙና የ2010 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይም እንደሚወያዩ አቶ አበበ ነግረውናል፡፡

የትምህርት ዘመኑን ውጤታማ ለማድረግ ይረዳል የተባለለትን ሥልጠና እንዲሰጡ በአዲስ አበባ 960 አሰልጣኞች የአሰልጣኞች ሥልጠና ወስደዋል የተባለ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮም ለመጪዎቹ 5 ቀናት ጉባዔውን እንደሚመሩ ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers