• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር ዞን ትናንት ውሣኔ ህዝብ ሲሰጥበት የዋለው የአማራና የቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ጉዳይ...

በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር ዞን ትናንት ውሣኔ ህዝብ ሲሰጥበት የዋለው የአማራና የቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ጉዳይ ጊዜያዊ ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎች ይፋ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም አባይ ለሸገር እንደተናገሩት የውሣኔ ህዝቡ ጊዜያዊ ውጤት በ24 የምርጫ ጣቢያዎች ይፋ እየተደረገ ነው፡፡

ከ20 ሺ በላይ ሰዎችም ድምፅ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡የህዝበ ውሣኔው አጠቃላይ ውጤት መስከረም 15 ቀን 2010 ዓ.ም የምርጫ ቦርድ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርቦ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል፡፡

ቀደም ሲል በአማራና በቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ጉዳይ ላይ ውሣኔ ህዝብ ይሰጥባቸዋል የተባሉት 12 ቀበሌዎች ሲሆኑ የ4ቱ ቀበሌዎች እንዲዘገይ መወሰኑ ይታወሣል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መስከረም 8፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በጫት የንግድ ሰንሰለት ውስጥ የተሰማሩ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው እየተስተጓጎሉና ባስ ሲልም ገና በለጋነታቸው ጫት ቃሚ እየሆኑ መጥተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ሴፍቲ ኔት ስርዓት መደገፊያ በቅርቡ የ600 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማፅደቁ ተሠማ፡፡ (የኔነህከበደ)
 • የየካ አባዶ ነዋሪዎች የጋራ መጠቀሚያ ወይም ኮምዩናል ዋጋ ከቤት ጋር ታስቦ እየከፈልን ቢሆንም የጋራ መጠቀሚያው ግን እስካሁን አልተሰጠንም አሉ፡፡ (በየነወልዴ)
 • በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር ዞን ትናንት ውሣኔ ህዝብ ሲሰጥበት የዋለው የአማራና የቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ጉዳይ ጊዜያዊ ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎች ይፋ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • ለ72ኛው የመንግሥታቱ የፀጥታው ምክር ቤት ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ኒውርክ ገብተዋል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ዛሬ የተጀመረው የትምህርት ባለሙያዎች ሥልጠና የግሎችንም ይመለከታል፤ የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት ጉዳይም ከአጀንዳዎቹ አንዱ ነው ተብሏል፡፡ (ትዕግሥትዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የሚጀምረው የተንቀሣቃሽ ስልክ ቀፎዎች ምዝገባ የተሰረቁ ቀፎዎች...

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የሚጀምረው የተንቀሣቃሽ ስልክ ቀፎዎች ምዝገባ የተሰረቁ ቀፎዎች ተበልተውም ቢሆን አገልግሎት የመስጠታቸውን እድል አነስተኛ እንደሚያደርገው ኢትዮ ቴሌኮም ተናገረ፡፡

የሞባልይ ቀፎዎች የመለያ ቁጥር ምዝገባው ሥርቆትን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል የተባለ ሲሆን አንድ ሞባይሉ የተሰረቀበት ሰው ስልኩ መሰረቁን ለኢትዮ ቴሌኮም ካሣወቀ የሰረቀው ሰው ሊጠቀምበት እንደማይችል ሲነገር ሰምተናል፡፡

የተሰረቀው ሞባይል ተበልቶ አገልግሎት መስጠት አይችልም ወይ ያልናቸው የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፕሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ እድሉ ጠባብ ነው ብለዋል፡፡ከውጭ ሀገር ከወዳጅ ዘመድ የሚላኩ የሞባይል ቀፎዎች እዚህ ሀገር ላይ ገብተው አገልግሎት ላይ አንዲውሉ ስልኮቹ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው ወደ ሀገር ቤት እንዴት ይገባሉ የሚለው ግን በነባሩ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሕግ ይወሰናል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል በውጭ ሀገር የሚኖሩና ይጠቀሙበት የነበረውን የተንቀሣቃሽ ስልክ ቀፎ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጠቀም በፊት በነበሩበት ሀገር ከፍለው የማያስለቅቁ ካልሆነ አይጠቀሙበትም ሲሉ አቶ አብዱራሂም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ 58 ሚሊዮን ቀፎዎች ተመዝግበዋል የተባለ ሲሆን ከተመዘገቡት ውስጥ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮኑ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ወይንም በተመሣሣይ መለያ ቁጥር የተሰሩ ቀፎዎች በመሆናቸው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚዎች ሊቀይሯቸው እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

ከእንግዲህ በኋላ የተንቀሣቃሽ ስልክ ቀፎዎችን ስትገዙ ትክክለኛ ወይንም ኦሪጅናል መሆናቸውን አረጋግጣችሁ ብቻ መግዛት እንዳለባችሁ አትርሱ የተባላችሁ ሲሆን ስልኩም ኦሪጅናል ስለመሆኑ ለማረጋገጥ በምትገዙት ቀፎ ውስጥ ሲም ካርዳችሁን በማስገባት ኮከብ 868 መሰላል በመደወል ማወቅ ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በነሐሴ ወር ብቻ ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸውን የግብርና ምርቶች...

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በነሐሴ ወር ብቻ ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸውን የግብርና ምርቶች አገበያየሁ አለ፡፡ምርት ገበያው ለሸገር እንዳለው በ23 ቀናት ያገበያየው ሰሊጥ፣ ቦሎቄና ቡና ነው፡፡

የግብርና ምርቶቹ በአጠቃላይ ከ33 ሺ 500 ቶን በላይ መጠን እንዳላቸው ሰምተናል፡፡ከተገበያየው ምርት ውስጥ ቡና በመጠን 63 በመቶ በዋጋ ደግሞ 82 በመቶውን በመሸፈን ቅድሚያውን መያዙ ተነግሯል፡፡

ምርት ገበያው እንዳለው በወሩ 1 ነጥብ 4  ቢሊየን ብር ዋጋ ያለው 21 ሺ 159 ቶን ቡና ተገበያይቷል፡፡የነሐሴ ወር የቡና ግብይት ከሐምሌ ጋር ሲነፃፀር በምርት መጠን 52 በመቶ በዋጋ ደግሞ 66 በመቶ ጨምሯል ተብሏል፡፡ወደ ውጭ የሚላክ ቡና ግብይት መጠንም ማደጉን ሰምተናል፡፡

ወደ ውጭ የሚላከው ቡና ግብይት በመጠን 66 በመቶ በዋጋ ደግሞ 80 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡የቡና መገኛንና ባለቤትነትን የተመረኮዘ የመኪና ላይ ግብይት ሥርዓት በምርት ገበያው መጀመር ለዕድገቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

በወሩ ግብይት ሰሊጥም ከቡና ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል ተብሏል፡፡ሰሊጥ ከአጠቃላይ ግብይቱ በመጠን 34 በመቶ በዋጋ ደግሞ 18 በመቶ ድርሻን ይዟል፡፡14 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው 890 ቶን ቦሎቄ ግብይት በነሐሴ ወር መፈፀሙንም ሰምተናል፡፡

የቦሎቄ ግብይት ከሐምሌ ጋር ሲነፃፀር በመጠን 49 በመቶ በምርት ደግሞ 52 በመቶ መቀነሱ ተነግሯል፡፡ይህም የምርቱ ወቅት ባለመሆኑ አቅርቦቱ ስለሚቀንስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 5፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ከመስከረም 8 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የተንቀሣቃሽ ስልክ ቀፎ ምዝገባ በአገልግሎት ላይ ያሉ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ቀፎዎችን በአመቱ መጨረሻ እንዳይሰሩ ያደርጋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የግሉ ዘርፍ ማህበራዊ ኃላፊነት ፈንድ የተወሰኑ ተቋማት በፍቃደኝነት በሚያዋጡት ገንዘብ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በኢትዮጵያ የተንቀሣቃሽ ስልክ ቀፎዎች ምዝገባ ሊከናወን ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ናንካይ የተባለው የቻይና ኩባንያ በጋምቤላ ክልል የደለል ወርቅ ለማልማት ትናንት ፈቃድ ተሰጠው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • እስካሁን ስለላብራቶሪያቸው በትክክል መስራት አስፈትሸው የእውቅና ሰርተፍኬት ያገኙ የህክምና ተቋማት 16 ብቻ ናቸው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በአዲስ አበባ የግዙፉ የስብሰባና የኢግዚቪሽን ማዕከል ግንባታ ተጀመረ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአዋሽ ወንዝ ሞልቶ መፍሰስ ምክንያት የሶደሬ ሪዞርት ሆቴል ሥራ ካቆመ ዛሬ ሳምንት ሆኖታል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በ2009 ዓ.ም ይጠናቀቃሉ ተብሎ ዕቅድ ከተያዘላቸው እና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣባቸው የመስኖ ውሃ ግድቦች ሁለቱ ወደ 2010 ተሻግረዋል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በነሐሴ ወር ብቻ ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው የግብርና ምርቶች አገበያየሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም ጠባ፣ ፀሀይዋ ብልጭ አለች ብላችሁ አዲስ አበቤዎችና ሌሎችም በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ ያላችሁ ከተሜዎች...

መስከረም ጠባ፣ ፀሀይዋ ብልጭ አለች ብላችሁ አዲስ አበቤዎችና ሌሎችም በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ ያላችሁ ከተሜዎች እንዳትዘናጉ ከጐርፍ አደጋ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡እንዲህ ያሉት የአዋሽ ተፋሰስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበራ ግዛው ናቸው፡፡

ሰሞኑን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ የቆቃ ግድብ እየተለቀቀ በመሆኑ ከግድቡ በታች ግድቡ የማይዛቸው ገባር ወንዞች ስላሉ በአንድ ላይ ሆነው የጐርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

አሁንም ቢሆን ከቆቃ የሚለቀቀው ውሃ ያልቆመ በመሆኑ ስጋቱ እንዳለ ነው ብለዋል፡፡ከዚህም በላይ ግን ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው የአዋሽ ተፋሰስ ለጐርፍ አደጋ የተጋለጠ ነውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡አዲስ አበባም ብትሆን ከፍተኛ የጐርፍ ስጋት ያለባት ናት ያሉት አቶ ጌታቸው አንድም የጐርፍ ማፋሰሻዎች የዲዛይን ችግር የሚያሳስብ በመሆኑ ዳግም መጠናት ያለበት ነው ብለዋል፡፡

በሌላም በኩል አዲስ አበቤ በተገኘው የውሃ መውረጃ ሁሉ የሚደፋው ቆሻሻ ቱቦዎቹን እየደፈነ የጐርፍ ችግር ያመጣልና ሊታሰብበት ይገባል ነው ያሉት፡፡ክረምቱ ከጐርፍ ጋር ይዞት የመጣው ደለል የውሃና የወንዝ መውረጃዎችን ውሃ የመያዝ አቅም ሊያጠበው ስለሚችል ዝናብ ጠብ ባለ ቁጥር የወንዝ ሙላትና የጐርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በተራራ ተከበው ያሉት እንደነ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ከምሴ፣ ሸዋ ሮቢት የመሳሰሉት ከተሞች በዝናብ ግፊት የተነሣ የመሬት መሰንጠቅና መንሸራተት ሊያጋጥማቸው ይችላልና በጥንቃቄ ሊታዩ ይገባል ሲሉም ነግረውናል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓትና ልማት ድርጅት /ኢኢግልድ/ የቆዳና የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች በዱቤ...

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓትና ልማት ድርጅት /ኢኢግልድ/ የቆዳና የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች በዱቤ የገዙኝን ቆዳና ጥጥ ዋጋ አለመክፈላቸው ችግር ፈጥሮብኛል አለ፡፡አንዳንድ ፋብሪካዎች በ6 ወር ጊዜ እዳችንን እንከፍላለን ብለው በቃላቸው ባለመገኘታቸው ክስ እየተመሠረተባቸው ነውም ተብሏል፡፡

የድርጅቱ የግብዓት ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ እንድሪስ ንጉስ ለሸገር ሲናገሩ በዱቤ ምርቱን የወሰዱ ፋብሪካዎች ካለመክፈላቸው በተጨማሪ አሁንም ያለውን ምርት እየወሰዱ አለመሆናቸው የሰበሰብነው የቆዳና የጥጥ ምርት ገንዘብ ይዞ እንዲቀመጥ አድርጓል ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ፋብሪካዎች የዱቤ እዳቸውን ባለመክፈላቸው የተከማቸውን ምርትም ባለማንሳታቸው ከቆዳና ጥጥ አቅራቢዎች ተጨማሪ ለመረከብ በመቸገሩ በተለይ የኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢ ጥጥ አምራቾች ያመረቱት ከ10 ሺ ቶን በላይ የተዳመጠ ጥጥ ገዢ አጥቷል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 4፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የጉምሩክ እቃ ፍተሻን በዘመናዊ መፈተሻ መሣሪያ የታገዘ ለማድረግ በጅግጅጋና ቶጎጫሌ ኬላዎች በዚህ ዓመት ስራው ይጀመራል ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አርብቶ አደር አካባቢዎች አምና ድርቅ ካሳደረባቸው ተፅዕኖ ገና ሙሉ ለሙሉ አልተላቀቁም ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሥራ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች በውስጥ ለውስጥ ሽምግልና ተድበስብሶ የሚቀርበትን አጋጣሚ ለማስቀረት እየሰራሁ ነው አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የክረምቱ መውጫ ቢቃረብም የጐርፍ ስጋቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው እና ጥንቃቄው መዘንጋት የለበትም ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ነጋዴው የማኅበራዊ ኃላፊነት ፈንድ ለማቋቋም ዛሬ የያዘውን ቀጠሮ ወደ ሌላ ቀን አስተላለፈው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢንዱስትሪ ግብዓትና ልማት ድርጅት የሰበሰብኳቸው የቆዳና ጥጥ ምርቶች ተረካቢ በማጣታቸው ተቸግሬያለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ትናንት በተከበረው የዘመን መለወጫ በዓል የእሳት አደጋ ባይከሰትም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የደረሰ የጎርፍ አደጋ...

ትናንት በተከበረው የዘመን መለወጫ በዓል የእሳት አደጋ ባይከሰትም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የደረሰ የጎርፍ አደጋ አንድ ትምህርት ቤትና በመቶዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡

በዋዜማው እለት ግን ሁለት የእሣት አደጋዎች ደርሰው እንደነበር በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ አስታውሰዋል፡፡በአራዳ ክፍለ ከተማ ፊንፊኔ አካባቢ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በሆነ መጠለያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የ10 አባዎራዎች መኖሪያ ቤት በዋዜማው ሌሊት ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን አቶ ንጋቱ ነግረውናል፡፡

በአደጋው 300 ሺ ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም 2 ሚሊዮን የተገመተ ደግሞ መትረፉን ሰምተናል፡፡ በዛው ሌሊት በልደታ ክፍለ ከተማ ሳንጋ ተራ አካባቢ በሚገኝ የገበያ ማዕከል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ ተቃጥሎ 30 ሺ ብር የተገመተ ንብረት መውደሙንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

ትናንት በተከበረው የዘመን መለወጫ እለት ግን ምንም አይነት የእሣት አደጋ አልደረሰም ያሉት አቶ ንጋቱ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ግን በአለም ባንክ፣ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10ና በአቃቂ ወረዳ 7 በመቶዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን ንብረት ማበላሸቱን ነግረውናል፡፡ በላዛሪስት ትምህርት ቤትም ጎርፍ ገብቶ የተማሪዎችን የመማሪያ ክፍል አጥለቅልቆ እንደበር ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ ቆየት ባለ ጊዜ የተቀበረ ነው የተባለ 2 በርሜል ወርቅ ተገኝቷል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ ቆየት ባለ ጊዜ የተቀበረ ነው የተባለ 2 በርሜል ወርቅ ተገኝቷል…በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ዞኖች በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ ከ100 በላይ ታራሚዎች አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በምህረት መለቀቃቸው ተሠማ፡፡

ሸገር ዛሬ ከክልሉ ማስታወቂያ ቢሮ አንደሰማው የክልሉ መንግሥት በአሶሳ፣ በመተከልና በካማሼ ዞኖች በማረሚያ ቤት የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ነው አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ የፈታቸው፡፡የክልሉ መንግሥት በየአመቱ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎች ምህረት ይሰጣል ተብሏል፡፡

በሌላ ወሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ ቆየት ባለ ጊዜ የተቀበረ ነው የተባለ 2 በርሜል ወርቅ ተገኝቷል ተብሏል፡፡መስከረም 1/2010 በባንባሲ ሾንጋ በተባለ ወንዝ ዳርቻ በአካባቢው ነዋሪዎች ተገኘ የተባለው ወርቅ በክልሉ ፖሊስ ጥበቃ እየተደረገለት ነው መባሉንም ከማስታወቂያ ቢሮው ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከፍተኛ የመጥለቅለቅ አደጋ ያደርሳል ተብሎ ተሰግቷል

የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከፍተኛ የመጥለቅለቅ አደጋ ያደርሳል ተብሎ ተሰግቷል፡፡የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመሙላቱና ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ እየተለቀቀ በመሆኑ ጉዳቱን ከፍ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል፡፡

ከግድብ የሚለቀቀውና ከገባር ወንዞች የሚፈሰው ውሃ በሚፈጥሩት ሙላት የሚጎዱት ከቆቃ ግድብ በታች ያሉትን ብቻ ሳይሆኑ ከግድቡ በላይ ያሉትንም አካባቢዎች ያሰጋቸዋል ተብሏል፡፡በአዋሽ ወንዝ አጠገብ የሚኖሩና የመስኖ ሥራ የሚያካሂዱ ተቋሞችም፣ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ኮሚሽን ሥራ አመራር አሳስቧል፡፡

የቆቃ ግድብ አካባቢ የሚኖሩትም ከግድቡ ራቁ ተብለዋል፡፡የክረምቱ ወቅት እያለፈ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ዝናብ መጣሉ ባለማቆሙ፣ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋም ይኖራል የሚል ትንበያ ተሰጥቷል፡፡ኮሚሽኑ ከዘጠኝ መሥሪያ ቤቶች በተወጣጡ ባለሙያዎች ግብረ ኃይል ማቋቋሙንና ምግብና ቁሣቁስ ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡ከዚያ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers