• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መስከረም 2፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ ጠጥቶ በማሽከርከር የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የተጀመረው ዘመቻ ውጤታማ ነው፡፡ ይህም በጥናት ተረጋግጧል ተባለ፡፡ (ምህረትስዩም)
 • የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ በድርቅ ምክንያት የግጦሽ እጥረት ላጋጠማቸው አርብቶ አደሮች የምሰጠው የካሣ ዋስትና ሽፋን አትራፊ ባይሆንም ማህበራዊ ኃላፊነቴን ለመወጣት ስል እገፋበታለሁ አለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • አዲስ አበባ የምሥራቅ አፍሪካ ካቶሊካዊያን ኅብረት ጉባዔን ልታስተናግድ ነው፡፡ (ዮሐንስየኋላወርቅ)
 • የሶደሬ ሪዞርት ሆቴል በአዋሽ ወንዝ ሙላት በመጥለቅለቁ ሥራ ለማቆም መገደዱ ተሠማ፡፡ (ትዕግሥትዘሪሁን)
 • በአዲስ አበባ ትናንት የተከሰተ የጐርፍ አደጋ በመቶዎች በሚቆጠሩ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከመቶ በላይ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰሞኑን በገበያው ላይ ጠፍተው የነበሩት ባለ 15፣ ባለ 25፣ ባለ 50 ብርና ባለ 100 ብር ካርዶች ከትናንት ጀምሮ...

ሰሞኑን በገበያው ላይ ጠፍተው የነበሩት ባለ 15፣ ባለ 25፣ ባለ 50 ብርና ባለ 100 ብር ካርዶች ከትናንት ጀምሮ በወኪል አከፋፋዮች መድረሱንና ከዚህ በኋላ ችግር እንደማይኖር ኢትዮ ቴሌኮም ተናግሯል፡፡የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ለሸገር እንደተናገሩት ካርዶቹ በገበያ ላይ ጠፍተው የነበሩት አስመጪዎች ከጉምሩክ ጋር ያልጨረሷቸው ነገሮች ስለነበሩ ነው ብለዋል፡፡

ከትናንት ጀምሮ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ህጋዊ ውክልና ያላቸው አከፋፋዮች እጅ ደርሷል ሲሉም ነግረውናል፡፡ፍላጎቱ ከፍተኛ ከሆነ ከአቅርቦቱ ጋር ለማጣጣም ለምን አልተቻለም በተደጋጋሚ ተመሣሣይ ጥያቄ ይነሣል ያልናቸው ዳይሬክተሩ አቶ አብዱራሂም ኢትዮ ቴሌኮም አቅርቦቱን በተገቢው መልኩ ከማድረግ ጐን ለጐን ሌሎች መፍትሄዎችንም እያፈላለገ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ህጋዊ የሆኑት ትላልቆቹ አከፋፋዮች ለቸርቻሪዎቹ እያደረሱ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ በገበያ ላይ ታገኟችኋላችሁ ሲሉ አቶ አብዱራሂም አህመድ የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ለሸገር ነግረዋል፡፡

አስፋው ስለሺ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፖሊስ ምርመራ ሲያካሂድባቸው የቆዩት ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌና አምስት ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል...

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፖሊስ ምርመራ ሲያካሂድባቸው የቆዩት ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌና አምስት ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል…ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ አባክነዋል ብሎ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ አቅርቧል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሙስና ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የቆዩትን  በእነ አቶ ፈለቀ ታደሰ መዝገብ የተካተቱት 7 ሰዎችም ላይ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ክስ መስርቷል፡፡ የመንገዶች ባለሥልጣን ዳይሬክተር በነበሩት አቶ ዚያድ ወልደገብርኤልና ሌሎች 13 በሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ተናግሯል፡፡

በዚሁ መዝገብ ሌላ ተጠርጣሪ ሆነው ዛሬ የቀረቡት አቶ እስክንድር ሰዒድ በ32 ሚሊዮን ብር ጉድለት በማድረስ የመዝገቡ አካል ሆኖ ቀርቧል፡፡ ፖሊስ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ኃላፊዎች ላይ ያደረገውን ምርመራ አጠናቆ ለዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ዛሬ ለተሰየመው ችሎት ተናግሯል፡፡

የከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው እነ ኢንጁነር ፈቃደ ለጥቅምት 9፣ እነ አቶ ፈለቀ ታደሰ ለጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም መቃወሚያቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ እነ አቶ ዚይድና በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ፕሮጀክት መዝገብ የተጠረጠሩት ለመስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም የዐቃቤ ሕግን ክስ ለማዳመጥ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 3፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ ያሉ ጥጥ አምራቾች ምርታቸውን የሚገዛቸው አጥተዋል ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የጤና ኮሌጅ ነፃ የጤና ምርመራ ላድርግላችሁ ብሎ ባቀረበው ጥሪ የተገኙት ተመርማሪዎች የታሰበውን ያህል ብዛት የሌላቸው ሆኑ ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ መልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ደረቅ ቆሻሻዎች እየተለዩ ቢሰበሰቡም ተረካቢ እያገኙ አይደለም ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስብርሃኑ)
 • የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢሕድን ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • እጥረት ሲስተዋልባቸው የሰነበቱ የተንቀሣቃሽ ስልክ መገልገያ ካርዶች በየዓይነቱ ለወኪል አከፋፋዮች በመድረሱ ችግሩ እንደሚቃለል ኢትዮ ቴሌኮም ዕወቁልኝ አለ፡፡ (አስፋውስለሺ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በመንገድ ላይ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ከጥፍነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው...

በአዲስ አበባ በመንገድ ላይ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ከጥፍነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው አደጋ 20 በመቶ የሞት መጠን የሚያስከትል ነው ተባለ፡፡ይህ የተባለው ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ልክ እንደ ጠጥቶ ማሽከርከር ሁሉ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከርን የሚቆጣጠር ዘመቻ በይፋ መጀመሩን በተናገረበት ጊዜ ነው፡፡በከተማዋ በዚህ ዓመት ብቻ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 477 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል፡፡

ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር በትራፊክ አደጋ ለሚደርሰው ጉዳት አንዱና 20 በመቶ የሞት መጠን የሚመዘገብበት ምክንያት በመሆኑ አደጋ በሚበዛባቸውና በተመረጡ የከተማዋ ቦታዎች ላይ የፍጥነት ወሰን ቁጥጥር ማድረጉ ይጀመራል ተብሏል፡፡በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሥራዎች ቢሰሩም የሚደርሰው የአደጋ መጠንና የተሰራው ሥራ ግን ሊመጣጠኑ እንዳልቻሉ ተነግሯል፡፡

በ2009 ዓ.ም ብቻ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች በደንብ መተላለፍ ቅጣት ያገኛቸው እንደሆኑና ለትራፊክ አደጋው ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር ህግን ያለማክበርና ደንብ መተላለፍ አስተዋፅኦ አላቸው ተብሏል፡፡የትራፊክ አደጋ በአሽከርካሪዎች ጥፋት ብቻ የሚደርስ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለአደጋው መቀነስና ለዘመቻው መሣተፍ እንደሚገባው ተነግሯል፡፡

የፍጥነት ወሰን ቁጥጥሩ ከጥቅምት 2010 ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል ፤ ለቁጥጥር የሚያስፈልገው የመሣሪያ ግዢም ተፈፅሟል ተብሏል፡፡በዘመቻ የተጀመረው የትራፊክ አደጋ መከላከል ሥራም አለም አቀፍ ድርጅት ከሆነው ብሉምበርግ ፒላንትሮፒስ ኢንሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮክ ሴፍቲ እና ቫይታል ስትራቴጂ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለትና ለ13 ዓመታት ሲሰራበት የሚቆየው ዘመቻ አንዱ አካል እንደሆነ ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጪው ዓመት የማስተማር ሥራ ለሚጀምሩ 11 አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች የተለያዩ ቁሣቁሶችን ለማሟላት መንግሥት የ272 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግዢ ሊፈፅም ነው

በመጪው ዓመት የማስተማር ሥራ ለሚጀምሩ 11 አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች የተለያዩ ቁሣቁሶችን ለማሟላት መንግሥት የ272 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግዢ ሊፈፅም ነው፡፡በመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ከተባሉና የመፅሐፍት፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የመመገቢያ እቃዎች ግዢ ከሚፈፀምላቸው መካከል የቦንጋ፣ ደባርቅ፣ ደምቢዶሎ፣ እንጅባራ፣ ጅንካና ሌሎችም ይገኙባቸዋል፡፡

በመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ምክትል የህዝብ ግንኙት ኃላፊው አቶ አሰፋ ሰለሞን እንደነገሩን ለተፈጥሮ ሣይንስ የማጣቀሻ መፅሐፍት 93 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን በወጣው አለም አቀፍ ጨረታ መሠረት አሸነፊ ለሆኑ 4 ድርጅቶች ግዢ እንዲፈፅሙ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ለዩኒቨርስቲዎቹ የቢሮና የመማሪያ ክፍሎች የሚሆኑ የተለያዩ ቁሣቁሶች ወይንም የቢሮ ዕቃዎች ግዢ አሸናፊ የሆኑ 7 ድርጅቶች በ138 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ግዢ ይፈፅማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እቃዎችን ለመግዛት 16 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግና ለመመገቢያና ማብሰያ እቃዎች ደግሞ 22 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተናግሯል፡፡

ዩኒቨርስቲዎቹ በ2010 ዓ፤ም ተማሪዎችን የሚቀበሉ ሲሆን የሚገዙትን እቃዎች የጨረታ አሸናፊዎቹ በ120 ቀን ውስጥ እንዲያቀርቡ መታዘዛቸውን ሰምተናል፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጷግሜ 2፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የሰሜን አዲስ አበባ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት በደል ደርሶብናል አሉ፡፡ በየነ ወልዴ
 • በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ቢጠናቀቅም በኃይል እጥረት የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻለም ተባለ፡፡ ምህረት ስዩም
 • በተለያዩ ክልሎች ለዓመታት የዘለቀ፣ የድንበር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠ፣ የማስማማት ተግባር እንደሚያከናውን በ2009 መግቢያ ላይ መንግሥት ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ውጤቱስ ምን ሆነ? ትዕግሥት ዘሪሁን
 • የአዲስ አበባ መንገዶች እንዴት ከረሙ? በመንገዱ ላይ ሲሰሩ የነበሩ ጥገናዎች እና ሌሎች ስራዎች ከምን ደረሱ? ንጋቱ ሙሉ
 • በስጋና ወተት ምርት የተሰማሩ ባለሀብቶች የመኖ አቅርቦትና የወተት ሽያጭ የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ ያለመኖር በምርታችን ላይ ችግር ፈጥሮብናል አሉ፡፡ መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ ከእናንተ ጋር በጋራ እንሰራለን ብሏል፡፡ አስፋው ስለሺ
 • የአንበሣ የከተማ አውቶብስ ነባሩን አርማ በአዲስ እለውጣለሁ አለ፡፡ በየነ ወልዴ
 • በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ ከሚከሰተው ሞት ከአምስቱ አንዱ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር የሚደርስ ነው ተባለ፡፡ ምህረት ስዩም
 • የአዲስ አበባ የTB ታካሚዎች የጐንዮሽ ጉዳት መከላከያ መድሐኒት ማግኘቱ አዳግቶናል አሉ፡፡ መንግሥታዊው የአቅርቦት መሥሪያ ቤት ችግሩ በቅርቡ ይቃለላል ብሏል፡፡ ማህሌት ታደለ፡፡
 • የኢንዱስትሪ ልማት ግብአቶች ድርጅት በዘመን መለወጫው እርድ ቆዳና ሌጦዎችን በብዛት ለመረከብ ተሰናድቻለሁ አለ፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ነሐሴ 30፣2009

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

አዲስ አበባ ለመጪዎቹ ሦስት አመታት የምትመራበት የመንገድ ደህንነት እስትራቴጂ የመተግበሪያ እቅድ ዛሬ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ ለመጪዎቹ ሦስት አመታት የምትመራበት የመንገድ ደህንነት እስትራቴጂ የመተግበሪያ እቅድ ዛሬ ይፋ ተደረገ፡፡ከተማዋ ለ13 ዓመታት የምትሰራበት የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ በዚህ አመት መጀመሪያ ወራት አካባቢ መፅደቁ ይታወሣል፡፡የ13 ዓመቱን እቅድ መሠረት አድርጐ የተዘጋጀውና ከ2010 እስከ 2012 የሚቆየውን የመተግበሪያ እቅድ ዛሬ በሸራተን ሆቴል ይፋ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ናቸው፡፡

በሦስት ዓመቱ የአዲስ አበባ የደህንነት ስትራቴጂ የመተግበሪያ እቅድ ላይ እንደተመለከትነው በከተማዋ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የተለያዩ ሥራዎች እንደሚሰሩ ይዘረዝራል፡፡በአሁኑ ሰዓት 70 በመቶ የሚሆነው አዲስ አበቤ ወዲህ ወዲያ የሚለው በእግሩ እንደሆነ የሚናገረው ሰነዱ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የትራፊክ አደጋ የሚደርስባቸው እግረኞች እንደሆኑም ያትታል፡፡

ስለዚህ ደህንነታቸው የተጠበቁ የእግረኛ መንገዶች ግንባታ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ተብሏል፡፡ዋና ዋና አደጋ የሚደርስባቸውን መንገዶች ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ የጠጥቶ ማሽከርከርን ቁጥር መቀነስ እንዲሁም የትራፊክ ደህንነት ትምህርትን ማጠናከር ሌሎች የሦስት ዓመቱ ዋና ዋና ትኩረቶች መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

እነዚህን ሥራዎች በመስራትም በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በአዲስ አበባ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ሞት በ30 በመቶ ለመቀነስ ታቅዷል፡፡ጠጥቶ ማሽከርከርና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከርን ደግሞ በ50 በመቶ ይቀንሣል ተብሎ ታስቧል፡፡

በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው 2009 በጀት ዓመት 463 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በዚህም መሠረት በአማካይ በቀን 1 ሰው ይሞታል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አሽከርካሪዎች ለትራፊክ አስተናባሪዎች እንደማይታዘዙ ተነገረ

አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አሽከርካሪዎች ለትራፊክ አስተናባሪዎች እንደማይታዘዙ ተነገረ፡፡ይህን የሰማነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የበጋ ወቅት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን የማበረታቻ የምስክር ወረቀትና ለቀጣይ ስራ ዝጅግት ስልጠና በሰጠበት መድረክ ነው፡፡

አሽከርካሪዎቹ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ትዕዛዝ ጥሰው በመሄድ የማስተናበሩን ስራ እንደሚያስተጓጉሉ ነው ወጣቶቹ የተናገሩት፡፡ከእነዚህም ውስጥ የተወሰኑ የመከላከያ ሚንስቴር እና ሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሾፌሮች እንደሚገኙበት ሰምተናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የግንባታ ተረፈ ምርቶች መንገድ ላይ መደፋት፣ የመንገድ መቆፋፈር እና በትላልቅ ህንፃዎች አካባቢ የመኪና ማቆሚያ እጥረት መኖሩ የትራፊክ አስተባባሪዎች ስራ የተቀላጠፈ እንዳይሆን ካደረጉት ውስጥ ይገኙበታል ተብሏል፡፡በእለቱ በቀረበ የጥናት ወረቀት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መኖር ሊደርስ ይችል የነበረውን አደጋ ለመቀነስ እገዛ እንዳደረገ ተጠቅሷል፡፡ከአስሩም ክፍለ ከተሞች ወጣት በጎ ፈቃደኞችን በስነ ምግባር፣ ኃላፊነትን በአግባቡ በመወጣትና የስራ ሰዓትን በማክበር ተመርጠው የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዛሬ ከ8 ሰዓት በኋላ የመሰናዶ መግቢያ ውጤትን ተፈታኞች መመልከት ይችላሉ ብሏል

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዛሬ ከ8 ሰዓት በኋላ የመሰናዶ መግቢያ ውጤትን ተፈታኞች መመልከት ይችላሉ ብሏል፡፡የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሣ እንደነገሩን ተፈታኞች RTN ብለው የመፈተኛ ቁጥራቸውን ወደ 8181 በመላክና በኤጀንሲው ድረ-ገፅ በwww.neaea.gov ማየት ይችላሉ ብለዋል፡፡

በርካታ ተፈታኞች በተመሣይ ሰዓት ሊሞክሩት ስለሚችሉ የኔትወርክ መጨናነቅ ሊፈጠር ይችላል ያሉት ዳይሬክተሩ ተፈታኞች በትግዕሥት ውጤታቸውን እንዲመለከቱ ጠይቀዋል፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers