• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የመድኃኒት እጥረት ሳይኖር ዋጋ ለመጨመር መድኃኒቶችን እያከማቹ የገበያ እጥረት የሚፈጥሩ መድኃኒት ሻጮች ላይ ቁጥጥር...

የመድኃኒት እጥረት ሳይኖር ዋጋ ለመጨመር መድኃኒቶችን እያከማቹ የገበያ እጥረት የሚፈጥሩ መድኃኒት ሻጮች ላይ ቁጥጥር እያደረኩ ነው ሲል የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የዶላር መጨመርን ተከትሎ የስኳርና ሌሎች በተከታታይ መወሰድ ያለባቸው መድኃኒቶች ከገበያው ጠፍተው ተቸገርን ሲሉ ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ቆይተዋል፡፡

በመድኃኒቶች ላይ የተለየ የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም በመንግስት ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ መድኃኒቶች የሚከፈለው ዋጋ ለመድኃኒቶች ግዥ የወጣው እና የማጓጓዣው ብቻ እንጂ በመንግስት የጤና ተቋማት ላይ የዋጋ ጭማሪ የለም ሲሉ ወ/ሮ አድና በርሄ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የግል መድኃኒት መሸጫዎችም ከኤጀንሲው መድኃኒት ይገዛሉ ያሉት ወ/ሮ አድና ነገር ግን ከሚገባቸው ኮታ በላይ አከማችተው የመድኃኒት እጥረት እንዲፈጠር እንዳያደርጉ ኤጀንሲው ቁጥጥር ያደርጋል ብለዋል፡፡

መድኃኒቶች ጠፍተው ተጠቃሚው እንዳይቸገርም በቂ መድኃኒቶች ስለተከፋፈሉ መድሃኒቶችን በተቻለ መጠን ከከተማ መድኃኒት መሸጫዎች ብትገዙ ሲል የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡

በመደበኛነትና በተከታታይ የሚወሰዱ መድኃኒቶች በገበያው ላይ የለም ከተባላችሁ ዋጋም ከተጨመረባችሁ ለኤጀንሲው ቦታውንና የመድኃኒቱን ዓይነት አሳውቁ ተብላችኋል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ስለታላቁ ድምፃዊ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ሥራ እና ሕይወት...

ስለታላቁ ድምፃዊ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ሥራ እና ሕይወት የሚዳስሰውን በትላንትናው የ“ወይ አዲስ አበባ” ፕሮግራም የቀረበውን መሰናዶ ክፍል ፩(2) እንድታዳምጡ ጋበዘናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ መጋቢት 25፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አንድ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ተሸጠ…

በአዲስ አበባ አንድ ካሬ የ40/60 ቤቶች ፕሮግራም የንግድ ቤት በአንድ መቶ 71 ሺህ ብር በጨረታ ተሸጠ ፡፡በዚህም 156 ካሬ የ40/60 የጋራ መኖሪያ የንግድ ቤት በሰንጋተራ በ26 ሚሊዮን 676 ሺ 78 ብር መሸጡን የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ለሸገር ተናግሯል፡፡

የኢንተርፕራይዙ የጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ተስፋዬ ለሸገር እንደተናገሩት የ40/60 ንግድ ቤቶች ፕሮግራም ጨረታው የተከፈተው መጋቢት 18 ሲሆን በሰንጋ ተራ እና በክራውን ሳይቶች የተጠናቀቁ 230 የንግድ ሱቆች ጨረታ ወጥቶ ነበር ብሏል፡፡320 ሱቆች ከ70 እስከ 395 ካሬ ድረስ ስፋት ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

ጨረታው ክፍት ሆኖ በቆየባቸው ቀናት 4 ሺ 100 የጨረታ ሰነዶች ተሸጠዋል ያሉት አቶ አብርሃም 858ቱ ደግሞ ሰነድ ሞልተው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡በካሬ 19 ሺ 346 ከ30 ሳንቲም መነሻ ዋጋ ለሽያጭ የቀረቡት ቤቶቹ በሰንጋ ተራ ከአንድ ሱቅ 171 ሺ ብር ከ50 ሳንቲም በካሬ መሸጡን ነግረውናል፡፡

አጠቃላይ ዋጋውም ከ26 ሚሊዮን 676 ሺ 78 ብር ነው፡፡በጨረታ ለሽያጭ የቀረቡትን 320 ቆች ከአስር ሺ እስከ 15 ሺ የጨረታ ሰነዶች ለመሸጭ ታስቦ ነበር ያሉት አቶ አብርሃም የተሸጠው ግን ከታቀደው 1/3ኛውን ያህል መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ሱቆቹ ትልልቅ መሆናቸውና ክፍያውም በአንድ ጊዜ መሆኑ ምክንያቶች ሊሆን እንደሚችሉ መገመታቸውን ሰምተናል፡፡የ40/60 የጋራ መኖሪያ የንግድ ቤቶች ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ በብዛት ያሸነፉት እንደ ባንክ የመሳሰሉ የፋይናንስ ተቋማት ናቸው፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጤ የአሜሪካን ተምች በበቆሎ ምርት ላይ አሁንም ጉዳት ማስከተሉን ቀጥሏል ተባለ

መጤ የአሜሪካን ተምች በበቆሎ ምርት ላይ አሁንም ጉዳት ማስከተሉን ቀጥሏል ተባለ፡፡የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር እንደተናገረው በአሁኑ ጊዜ የመኸርና መስኖ አብቃይ በሆኑ 17 ሺ 555 ሄክታር መሬት ላይ ተምቹ ተከስቷል፡፡የሚያስከትለውንም ጉዳት ለመቀነስም የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ዶ/ር እያሱ አብርሃ፡፡

ከዚህ ቀደምም በ8 ክልል በ55 ዞኖች እና በ458 ወረዳዎች ተምቹ ተከስቶባቸው በነበሩ 6 መቶ 66 ሺ 8 መቶ 26 ሄክታር መሬት ላይ የመከላከል ስራ መሰራቱን ሚኒስትሩ አስታውሷል፡፡በየቀኑ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በማሳተፍም ተምቹን በባህላዊ መንገድ የመግደልና በኬሚካልም ጭምር በታገዘ ስራ 631 ሺ 239 ሄክታር መሬት ከተምቹ ነፃ ሆኗል ብለዋል፡፡

እስካሁኑ በምርት ላይ ያደረሰው ጉዳት ከ5 ነጥብ 7 በመቶ አይበልጥም ተብሏል፡፡ተምቹን በዘላቂነት ለማጥፋት የአሜሪካ ተምች የመከላከል ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል የግሪሳ ወፍ በየአመቱ በበልግና በመኸር በሚለሙ ሰብሎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ የመራቢያ አካባቢዎች ላይ ጥናት ተደርጓል ተብሏል፡፡

የተከሰተውን 37 ነጥብ 76 ሚሊዮን የሚገመት የወፍ መንጋም ተከላክለናል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡የስንዴ ዋግ በሽታም በ22 ዞኖችና በ117 ወረዳዎች ከ229 ሺ ሄክታር ላይ በሆነ መሬት ላይ ተከስቶ ሕዝቡን በማሳተፍም የመከላከል ስራ እንደተሰራም ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም በዋና ዋና የምግብ ሰብሎች በተያዘው የበጀት አመት 345 ሚሊዮን ኩንታል እህል ለመሰብሰብ ውጥን ተይዞ እንደነበርና ከእቅዱ ጋር ተቀራራቢ ምርት ሳይሰበሰብ እንዳልቀረም የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡ውጤቱም በቅርቡ በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአባባ ገብረሃና ደመቀ ነገር - የተጣለ ገንዘብ ፍለጋ በጎዳና…

የፒያሳው አባባ ገብረሃና ደመቀ ሁሌ መሬት መሬት እያዩ የሚሄዱት ያለ ነገር አይደለም ይለናል የሸገሩ ወንደሙ ኃይሉ፡፡ እንደስመ ሞክሼያቸው አለቃ ገብረሃና ቀልድ ሳይሆን የፒያሳው አባባ ገብረሃና የተጣለ ሳንቲም እና ብር ፍለጋ ነው ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ምሽት 11 ሰዓት የከተማዋን ጎዳናዎች የሚያስሱት፡፡

‘ድፍት ብለው ሲሄዱ ላያቸው ያዘኑ ይመስላሉ እሳቸው ግን ሥራ ላይ ናቸው’ ይሏቸዋል አባባ ገብረሃናን የሚያውቋቸው የሰፈራቸው ሰዎች…በጡረታ የማገኛት 700 ብር ለቀለቤ ነው፤ ከመሬት ፈልጌ በማገኘው ገንዘብ ደግሞ ወርሃዊ የእድር መዋጮዬ 20 ብሬን እከፍላለሁ የሚሉት የ85 ዓመቱ አባባ ገብረሃና የተጣለ ገንዘብ የሚገኝበት የተሻለ የሚባል ሰዓት የለም ይላሉ፡፡

የተጣለ ገንዘብ የሚገኝበት ምርጡ ቦታ ግን ሰዎች ከታክሲ የሚወርዱበት እና የሚወጡበት የመንገዱ ጠርዝ ነው ይላሉ…ደግሞ እንዲህ ሲሏችሁ ከታክሲ ወይም ከሌላ መኪና ስትሳፈሩ ወይም ስትወርዱ ገንዘብ ላለመለጣል ሞክሩ አሏችሁ !!! ታዲያ አባባ ገብረሃና በምን የእድራቸውን መዋጮ ይክፈሉ…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስለተፎካካሪ የፖለቲካ ማህበራት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስለተፎካካሪ የፖለቲካ ማህበራት እንዲሁም በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያስተላለፉትን መልዕክት አስመልክቶ የኔነህ ሲሳይ የሚከተለውን አዘጋጅቷል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት እና ሕብረት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ…

ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር አብይ አህመድ ግማሽ ሰዓት ያህል በወሰደው ንግግራቸው ከ30 ጊዜ በላይ ደጋግመው ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት እና ሕብረት የሚሉ ቃላትን አንስተዋል…

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥላቻን አውግዘዋል፡፡ ምንም ዓይነት የወቀሳ ቃል የሌለው ንግግር አድርገዋል፡፡የተሻለች ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባትም ዛሬ የተፈፀመውን የስልጣን ሽግግር በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡

ማንነታችን እንዳይለያይ ሆኖ የተሰናሰለ፣ እንዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደና የተዋደደ ነው ያሉት ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያውያን ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን ሲሉ ገልፀውታል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ መጋቢት 18፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers