• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በሀገር ውስጥ የተከሰተውን አረመረጋጋት ተከትሎ በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ላይ ትንኮሳ ፈፅመዋል ያላቸውን ዲያስፖራዎች በህግ ለመጠየቅ ሥራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ

በሀገር ውስጥ የተከሰተውን አረመረጋጋት ተከትሎ በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ላይ ትንኮሳ ፈፅመዋል ያላቸውን ዲያስፖራዎች በህግ ለመጠየቅ ሥራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየው ይህን ያሉት ዛሬ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የ8 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ነው፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ላይ ትንኮሳ ፈፅመውባቸዋል ያሏቸው ሀገራት በአውሮፓ ጄኔቫ፣ ስቶክሆልም፣ በርሊንና በአሜሪካ ዋሽንግተን ይገኙበታል፡፡ኢትዮጵያ በአራቱ የአለም ሀገራት ሚሲዮኖች ላይ ትንኮሳ ፈፅመዋል ያለቻቸውን ዲያስፖራዎች በህግ ለመጠየቅ ሥራ መጀመሯን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡በመጪው ጊዜም ሰላማዊ ባልሆነ መንገድ በሚሲዮኖች ላይ የሚደረግን ትንኮሳ በአለም አቀፍ ህግና ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ካላት ግንኙነት አንፃር ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በመኪና አደጋ ከ4 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ይሞታሉ፤ የመኪና ባለንብረቶች እባካችሁ የምትቀጥሯቸውን ሾፌሮች ባህሪ ለዩ ተባሉ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በመኪና አደጋ ከ4 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ይሞታሉ፤ የመኪና ባለንብረቶች እባካችሁ የምትቀጥሯቸውን ሾፌሮች ባህሪ ለዩ ተባሉ፡፡ዛሬ ረፋድ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ከ300 በላይ የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ባለንብረቶችን ሰብስቦ ነው እንዲህ ያላቸው፡፡

በፌዴራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ በሆኑት በአቶ አብዲሣ ያደታ ንግግር በተከፈተው በዛሬው የግማሽ ቀን ፕሮግራም ላይ እንደተባለው በኢትዮጵያ የሚያጋጥመውን የትራፊክ አደጋ መንግሥት ብቻውን ሊቀንሰው አይችልም የመኪና ባለሀብቶች የሾፌሮቻችሁን ሥነ-ምግባር እወቁና ቅጠሩ፤ ለሰው ህይወትና አካል እንዲሁም ለንብረታችሁ አስቡ ተብለዋል ሲሉ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ባለሙያው አቶ ድል አድርጋቸው ለማ ነግረውናል፡፡

በኢትዮጵያ የበዛው የትራፊክ አደጋ በአሽከርካሪ ሥነ-ምግባር ችግር ይደርሳል፤ 68 በመቶ የሚሆነው አደጋም በምቹ መንገዶች ላይ ያጋጠመ ነው ያሉት አቶ ድልአርጋቸው የትራንስፖርት ማህበራት፣ የቦርድ አመራሮችና ሥራ አስኪያጆችም ዛሬ ረፋድ በተከናወነው የምክክር ፕሮግራም ተሣታፊ ነበሩ ሲሉ ለሸገር ነግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የነበሩ ከ700 በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ባለፉት 8 ወራት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ

በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የነበሩ ከ700 በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ባለፉት 8 ወራት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡በስደት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ይኖሩ የነበሩ 510 ዜጎችና በማላዊ፣ ፕሪቶሪያና ዛምቢያ እሥር ቤቶች የነበሩ 240 ዜጎችም ይገኙባቸዋል ተብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያዊያኑን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ካደረገባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከልም ግብፅና ታንዛኒያ ይገኙባቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡ለስደት ምክንያት ናቸው የተባሉትን ድህነትና ሥራ አጥነትን ለመፍታት ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በመተባበር ከ500 እስከ 700 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጅ 2 የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዜጎችሽን ንፁህ ውሃ አጠጪበት ብሎ የ445 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀ…

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዜጎችሽን ንፁህ ውሃ አጠጪበት ብሎ የ445 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀ…445 ሚሊዮን ዶላሩ ከንፁህ ውሃ አቅርቦት በተጨማሪ ለፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት ማሳደጊያም እንደሚውል ከባንኩ የኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ቢሮ ሰምተናል፡፡አዲስ አበባን ጨምሮ ሌሎች 22 ከተሞች የውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓቱ ተጠቃሚዎች የሚሆኑ ከተሞች መሆናቸው ተነግሯል፡፡አጠቃላይም ብድሩ 3 ነጥብ 38 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡በኢትዮጵያ የፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓት ያላት አዲስ አበባ ብቻ ናት ያለው አለም ባንክ ይህም ቢሆን የነዋሪዎቿን 10 በመቶ ብቻ ተጠቃሚ ያደረገ ነው ብሏል፡፡

ቆሻሻ ውሃን ማከም፣ ያልተማከለ የቆሻሻ ሥርዓት መዘርጋት፣ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች መገንባት በብድሩ ሊከናወኑ ከሚችሉ ተግባራት መካከል መሆናቸውንም ባንኩ ተናግሯል፡፡በሌላ በኩል የዓለም ባንክ ሌላ የ50 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ ሊሰጣት ወስኗል፡፡50 ሚሊዮን ዶላሩ በሀገሪቱ የሚመረቱ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተቀባይነት እንዲኖራቸው በሚሰሩ ሥራዎች መደገፊያ ይሆናል ተብሏል፡፡ከሥራዎቹ መካከል የምርት ደረጃ ማውጣት፣ የአክሪዲቴሽን፣ የተስማሚነትና ምዘና ሥራዎች የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ብድሩን የሰጣት ባንኩ ከያዘው ድህነትን መቀነስና የጋራ ብልፅግናና መደገፍ ከሚሉት አላማዎች የመጣ መሆኑንም ባንኩ ተናግሯል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 26፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ወደ ውጪ ሃገር ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች ከአሰሪዎቻቸው ጋር እንዲግባቡ የሚያስችል ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሽንብራና ባቄላንም ለማገበያየት እያሰብኩ ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የመኪና ባለንብረቶች የአሽከርካሪዎቻችሁን ፀባይ በደንብ ለዩ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የዓለም ባንክ ለንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለኢትዮጵያ ብድር ሰጠ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የሰዎች ህገ-ወጥ ዝውውርን ለመቆጣጠር ያለመ ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኢትዮጵያ በተለያዩ አገራት በሚገኙ ሚሲዮኖቿ ላይ ትንኮሣ ፈፅመዋል ያለቻቸውን ዲያስፖራዎች በሕግ ልትጠይቅ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የነበሩ ከ700 በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ባለፉት 8 ወራት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ የለውዝ ምርቶችን ጥራት በተመለከተ ሁነኛ የደረጃ መስፈርት ፈጠን ብላ እንድታወጣ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎች እየጠየቁ ነው

ኢትዮጵያ የለውዝ ምርቶችን ጥራት በተመለከተ ሁነኛ የደረጃ መስፈርት ፈጠን ብላ እንድታወጣ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎች እየጠየቁ ነው፡፡ በሀገሪቱ እስካሁን ደረጃ ባለመውጣቱ ችግሩ እያሻቀበ መሆኑ ሥጋት ላይ ጥሏቸዋል፡፡ለውዝ በብዙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተመረተ ቢሆንም ከፍተኛ የአፍላ ቶክሲን ይዘት በውስጡ እንደሚገኙበት ሥራ ተብሎ የተደረጉ ጥናቶች በዳሰሣና በጥልቅ ምርምሮቻቸው እያሳዩ ነው፡፡የለውዝ ምርት ከዘሩ ጀምሮ በጥሬውም ሆኖ ታምሶ አልያም ተቆልቶና ተቀቅሎ ለምግብነት መዋሉ የታወቀ ነው፡፡

ይኸው ዘር እስከ ፋብሪካ ደርሶ አንዴ ቅቤ አልያም ዘይት ሲሆን በሌላ በኩል ለቁርስና ለመክሰስ የሚወሰዱ ሃልዋና ባቅላባን ለመሣሰሉት ጣፋጭ ምግቦች ማሰናጃ ሆኖም ያገለግላል፡፡የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያ የሚመረተው ለውዝ በከፍተኛ ደረጃ በአፍላ ቶክሲን የተጠቃ መሆኑን ተመራማሪዎች እየነገሩን ነው፡፡አፍላ ቶክሲን ለሻጋታ ዝሪያዎች አማካኝነት የሚመጣ ለጉበት ካንሰር የሚዳርግ መርዛማ ንጥረ ነገር የያዘ እንደሆነም ይታወቃል፡፡ከጉበት ሌላ ኩላሊትን የሚነካ በአፍላ ቶክሲን የተጠቃውን ለውዝ ደጋግሞ ከመብላት ብዛት ደግሞ የሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅም የሚዳከምበት የፅንስን እድገት የሚያጨናግፍ ከፍ ያለ አደጋም ለማድረስ የማይሳነው ኬሚካላዊ ውህድ መሆኑም ተረጋጧል፡፡

በሰመራ ዩኒቨርስቲ የአፕላይድ ማይክሮ ባዬሎጂ መምህር እንዲሁም በሀረማያ ዩኒቨርስቲ በለውዝ ላይ እስከ ዶክትሬት የደረሰ ምርምር ያካሄዱትን አቶ ኤፍሬም ጉቺን ሸገር በለውዝ ላይ ስለሚያይለው የአፍላ ቶክሲን ይዘት እንዲያብራሩለት ጠይቋቸዋል፡፡
አቶ ኤፍሬም የምርምር ውጤቶቻቸውን ለማጋራት ወደ ኋላ አላሉም፡፡ከኢትዮጵያ የለውዝ አምራች አካባቢዎች ሁሉ ብዙውን እጅ ምርት የሚያመርቱት የምሥራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች ለጥናት የተመረጡ ቦታዎች እንደነበሩ አቶ ኤፍሬም አስቀድመው ለሸገር ተናግረዋል፡፡ፈዲስ፣ ጉርሱምና የባቢሌ ወረዳዎች የለውዝ ምርት ከገበሬ ማሳ ላይ እንዳለ ተለቅሞ በአከፋፋዮች እጅ ከደረሰም በኋላ ከጅምላና ቸርቻሪዎች ላይ ተቆንጥሮ በባለሙያው ሲመረመር ቆይቷል፡፡

አቶ ኤፍሬም እንደሚሉት በነዚህ ለጥናት በተወሰዱ ናሙናዎች አስደንጋጭ የአፍላ ቶክሲን መጠን ነው የተገኘው፡፡ በተለይም በማከማቻ ቦታዎች ባለሙያው 85 በመቶ ያህሉ ምርት በአፍላቶክሲን የተበከለ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ቀድሞውኑ አለም ስለ አፍላ ቶክሲን መርዛማ ንጥረ ነገር ያወቀው ለዶሮዎች መኖነት ከ57 ዓመት በፊት በቀረበው ለውዝ አማካኝነት መሆኑን የምርምር ፅሁፎች ያትታሉ፡፡ለውዝ ደግሞ ከምሥራቅ ሀገርጌ ውጪ በቀሪዎቹ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በጋንቤላ፣ በሀዊ፣ በቻግኒ፣ ወሎ፣ ደዴሳ፣ አርባ ምንጭ በርከትከት ብሎ ይመረታል፡፡ለውዝ ከሀገር ቤት ገበያ ወጣ ብሎ ለውጭ ገበያ የመቅረብ እድል ግን በዚሁ በጥራት መጓደል ምክንያት ተነፍጐታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ልዩ ወሬ፣ “ለልመናማ እጄን አልሰጥም…”

በብየዳ ስራ ተሰማርቶ የአካል ጉዳተኛ ሚስቱን እና ሁለት ሴት ልጆቹን የሚያስተዳድረው አባወራ አእምሮው ታውኮ ማረፊያው ፀበል ሆነ የሚለን የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ከዚያ በኋላ እናትዬው ብርሃኔ አፈራ “ለልመና እጄን አልሰጥም…” በሚል የተሰማራችበትን ሥራ እና የኑሮ ትግል ያወጋናል…

በተሽከርካሪ ወንበር (Wheel chair) ብቻ የምትንቀሳቀሰው ብርሃኔ እስከ 11ኛ ክፍል ወዳስተማራት ተሐድሶ ወደተባለው ሕፃናት ማሳደጊያ አምርታ ችግሯን ተናግራ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የስፌት መኪና ለአንድ ዓመት በውሰት ተሰጣት…

ሕፃናት ማሳደጊያው የልብስ ስፌት ስልጠና ሰጥቷት ነበር፡፡

እነሆ አሁን ላይ መንገድ ዳር የላስቲክ መጠለያ አበጅታ … የሰፈሩን ሰው ልብስ እየሰፋች ልጆቿን ታሳድጋለች…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሰብዓዊና ቁሣዊ ሀብት ላይ ጉዳትና ብክነት አድርሰዋል ከተባሉ የሥራ ተቋራጮች መካከል 177 ያህሉ ይቅርታ እንደተደረገላቸው የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተናገረ

በሰብዓዊና ቁሣዊ ሀብት ላይ ጉዳትና ብክነት አድርሰዋል ከተባሉ የሥራ ተቋራጮች መካከል 177 ያህሉ ይቅርታ እንደተደረገላቸው የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ከአሁን በፊት ፈቃዳቸውን ሣያሣድሱ፣ የብቃት ማረጋገጫም ሳይኖራቸው የተጭበረበሩ ሰነዶችን ይጠቀሙ እንደነበር ማስረጃ የተገኘባቸው የሥራ ተቋራጮች ተለይተው መታወቃቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡

የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙሥና ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመሆን የለያቸውን ከደረጃ 1 እስከ 10 ያሉና በሰብዓዊና ቁሣዊ ሀብት ላይ ጉዳት ያደረሱ እንዲሁም አደጋ የደቀኑ የሥራ ተቋራጮች ናቸው ይቅርታ ያገኙት፡፡ዛሬ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ እንደተናገረው መንግሥት ጥናት አድርጎ በተሣሣተ ተግባር ላይ ነበሩ የተባሉ ከደረጃ 4 እስከ 10 ባሉ እርከኖች ውስጥ የሚገኙ 177 ሥራ ተቋራጮች መንግሥትን እንዲሁም ህዝብን ይቅርታ ጠይቀው ተገቢም ሥልጠና አግኝተው ወደ ሥራ እንዲመለሱ ውሣኔ ተላልፏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለአዲስ አበባ የልማት ተነሺዎች ለመስጠት በመጠባበቂያነት የተገነቡ ቤቶች ለቆሼ አደጋ ተጎጂዎች በኪራይ መሰጠታቸው ተነገረ

ለአዲስ አበባ የልማት ተነሺዎች ለመስጠት በመጠባበቂያነት የተገነቡ ቤቶች ለቆሼ አደጋ ተጎጂዎች በኪራይ መሰጠታቸው ተነገረ፡፡የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሸገር እንደተናገረው በኮልፌ ቀራንዬና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች ሲገነቡ ለነበሩ ቤቶች የከተማ አስተዳደሩ 24 ሚልዮን ብር አዋጥቶባቸዋል፡፡

የቆሼው አደጋ ከደረሰ በኋላም ቤቶቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ተደርጎ በቆሼ አካባቢ ህጋዊ ይዘት ሳይኖራቸው በላስቲክና በጭቃ ቤት ገንብተው ይኖሩ ለነበሩ 96 አባዎራዎች በኪራይ መሰጠታቸውን የቢሮው ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው ነግረውናል፡፡በአደጋው የጨረቃ ቤታቸው የፈረሰባቸው 102 አባዎራዎች ሲሆኑ 96ቱ መንግሥት በሰራው ቤት በኪራይ እዲገቡ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ቀሪዎቹ 6ቱ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው ስለሞቱባቸው የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤት ተገዝቶ እንደተሰጣቸው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡በአካባቢው ህጋዊ ይዞታ የነበራቸው 16 አባዎራዎችም በነበራቸው ይዞታ ልክ ምትክ ቦታና የቤት መሥሪያ ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር ተሰጥቷቸዋል ያሉት አቶ ኤፍሬም ለቤት እቃዎች መግዣም ለያንዳንዳቸው 144 ሺህ ብር እንደተሰጣቸውና ቤተሰብ ለሞተባቸውም በአንድ ሰው 40 ሺ ብር ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡

ለቆሼ አደጋ ተጎጂዎች እስካሁን 84 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ቃል መገባቱንና 60 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ደግሞ ገቢ መደረጉንም ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ 80 በመቶ ክፍል ውሃ አጣ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በቆሻሻ መደርመስ አደጋ ለደረሰባቸው የጨረቃ ቤት ነዋሪዎች በኪራይ የሚኖሩበት ቤት ተሰጣቸው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚታየውን ሙስና ግልፅ የሆነ አሰራር ሊታደገው ይችላል ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለ36 ሰዎች የተሳካ የኪላሊት ንቅለ ተከላ አከናወነ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ብሔራዊ ቤተ-መፀሐፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ በ300 ሚሊዮን ብር የመዛግብት ማከማቻ እየገነባ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ወደ ውጪ ሀገራት ቡና እየላኩ ገንዘብ የሚያመጡ ነጋዴዎች ችግሮች እየደረሱብን ነው አሉ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የለውዝ ምርቶችን በተመለከተ ኢትዮጵያ ፈጥና የጥራት መስፈርት ካላወጣች ችግር ላይ ትወድቃለች ተባለ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በኢትዮጵያ ያለው የሥራ አጥ ቁጥርን በተመለከተ የሚደረጉ ጥናቶች በየጊዜው የሚለዋወጡ ናቸው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በተሣሣተ ተግባር ላይ ለነበሩ ኮንትራክተሮች ምህረት መደረጉ ተሠማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች የኖርዌይ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • አንዲትን ሴት በድንጋይ የገደላት 9 ዓመት ተፈረደበት፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአፍላቶክሲን ነገር…

የአፍላቶክሲን ነገር…

ነጋዴዎች በርበሬ ሚዛን እንዲያነሣላቸው በርበሬው ላይ ውሃ አርከፍክፈው አጅለው የማስቀመጥ ልማድ አላቸው የሚሉት የምግብ ሣይንስና ኒውትሪሽን ባለሙያው ይህ ነገር ከሸጋታ አፍላ ቶክሲን በብዛት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል ይላሉ…

ለብዙዎቻችን አዲስ ይምሰል እንጂ በተመራማሪዎችና በአካዳሚክ ማህበረሰብ ዘንድ ጉዳዩ ሲነሣ እና ሲጣል 57 ዓመት ገደማ ሆኖታል - የአፍላ ቶክሲን ነገር !

የምንመገባቸውን ምግቦችና ጥፍጥና የሚሰጡልንን ቅመሞችና እህሎች በሙሉ ልብ እንዳናምናቸው ካስገደዱ የምርምር ውጤቶች መካከል የአፍላ ቶክሲን ገድል የናኘም ይመስላል፡፡

በአውሮፓውያኑ የዘመን ቆጠራ 1960 አካባቢ በእንግሊዝ ሀገር ተርኪሽ ተብለው ለሚታወቁ የአዕዋፋት ዝርያ ከብራዚል ተገዝቶ ለመኖነት የዋለ ለውዝ 100 ሺህ አዕዋፋትን በአንድ ቀን የመግደሉ ምክንያት ሲመረመር ነው የአፍላቶ ክሲን ነገር ብቅ ማለት የጀመረው፡፡

በለውዝ ውስጥ የነበረ ኬሚካል ውህድ መላ ሁኔታው ሲጠናም ከካንሰር ህመም ጋር ንክኪ እንዳለው ማረጋገጫዎች ተገኙበት፡፡

አፍላ ቶክሲን ተብሎ የሚጠራው ውህድ 4 ዓይነት መለያዎች ያሉት ሲሆን ከ4ቱ ምድቦች መካከል በተለይ B1 የተባለው ዓይነት ካንሰር አማጪ ንጥረ ነገር መያዙን አለም አቀፍ የምርምር ማዕከሎች ሣይቀሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተውበታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የኬሚካል ውህድ ለጉበት ካንሰር አይነተኛ ማጋለጫም እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከሰሞኑ ሸገር የአፍላ ቶክሲን ኬሚካል ውህድ ይገኝባቸዋልና ጠርጥሯቸው ብሎ ከባለሙያዎች ሃሣብ ጋር አነባብሮ የጥቂቶቹን ስም መንገሩን አትዘነጉትም፡፡ በርበሬ፣ ለውዝ፣ አኩሪ አተር፣ በቆሎ፣ ኑግና ሰሊጥ ዋና ዋናዎቹ ተጠርጣሪዎች እንደነበሩም ነግሯችኋል፡፡

በተለይ በተለይ የበርበሬ ምርት ከአፍላ ቶክሲን ጋር ያለው ቅርርቦሽ እንዴት ያለ ነው? ብላችሁ የተፍታት መልስ የጠየቃችሁንም ነበራችሁ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምግብ ሣይንስና ኒውትሪሽን ትምህርት ክፍል በርበሬ ውስጥ በብዛት ስለማይታጣው አፍላ ቶክሲን ጥናታዊ ምርምር ያካሄዱት አቶ ሀብታሙ ጋሻው ለጥያቄዎቻችን መልስ በመስጠት ተባብረውናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers