• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የወጣት ኑሃሚ ጥላሁን ገዳይ ነው፣ ባለው ተጠርጣሪ ላይ ክስ መሠረተ

የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የወጣት ኑሃሚ ጥላሁን ገዳይ ነው፣ ባለው ተጠርጣሪ ላይ ክስ መሠረተ፡፡በዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ መሠረት፣ ተጠርጣሪው የ21 ዓመቱ ነብዩ ዮናስ፣ የ17 ዓመቷን ኑሃሚ ጥላሁንን ገድሏል፣ ተብሎ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ተከሣሽ ነብዩ ዮናስ፣ ከሌላ ሰው ጋር ፍቅር ጀምረሻል በሚል ኃሣብ በተፈጠረው ጭቅጭቅ፣ ኑሃሚ ጥላሁንን ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ፣ በስለት አንገቷንና ጀርባዋን ወግቶ ገድሏታል፣ ይላል የዐቃቤ ህግ ክስ፡፡ስለቱን የገዛው ከካዛንችስ ሸንኮራ ሻጮች ላይ መሆኑን ጭምር፣ በክሱ ላይ ያተተው ዐቃቤ ህግ፣ ከፍተኛ ቅጣት ሊያስጥል የሚችለውን የወንጀል አንቀፅ ጠቅሷል፡፡

ተከሳሹ አቅም የሌለው መሆኑን በማመልከቱ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምለት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ለመጋቢት 26 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ 

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 19፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ ለሚጓተቱና ለማይሳኩ ýሮጀክቶች መፈጠር የስታቲስቲክስ እውቀት አለማደግ አንዱ ምክንያት ነው ተባለ፡፡ ንጋቱ ሙሉ
 • ኔዘርላንድስ ኢትዮጵያ ውስጥ በአበባ ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶቼ እስካሁን ለ75 ሺ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥረዋል አለች፡፡ ንጋቱ ረጋሣ በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስን አምባሳደር አነጋግሮ የሚከተለውን አዘጋጅቷል፡፡    
 • የአዲስ አበባ አስተዳደር በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ያለ ሥራ ተቀምጠዋል የተባሉ ከ2 ሺ በላይ ወጣቶችን ሥራ አስይዛለሁ ባለው መሠረት 800 ያህሉን በውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ እንዲያገኙ ተወጥኗል ተብሏል፡፡ ትዕግሥት ዘሪሁን
 • ቦሌ አለም አቀፍ አውሮýላን ማረፊያ አፍሪካ ውስጥ ካሉ 288 ኤርፖርቶች ሰባተኛው ምርጡ ኤርፖርት ተብሎ ተመረጠ፡፡ ንጋቱ ረጋሣ     
 • በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ከ4 ሺ 500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳያቸው በህግ ተይዟል ተባለ፡፡ በማረሚያ ቤቶችም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩ ተነግሯል፡፡ ትዕግሥት ዘሪሁን   
 • በአዲስ አበባ በአሜሪካ ድጋፍ የተገነባ የኅብረተሰብ ጤና ማዕከል ተመረቀ፡፡ የኔነህ ሲሣይ
 • የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቁ፡፡ ምሥክር አወል
 • በአዲስ አበባ የአልኮል መጠጥ ጠጥተው የሚነዱትን አሽከርካሪዎች የሚቀጣው ደንብ ከነገ ጀምሮ ሥራ ላይ ሊውል ነው፡፡ ንጋቱ ሙሉ
 • በአዲስ አበባ ቦሌ ወረዳ 7 ጃክሮስ አደባባይ አለፍ ብሎ በሚገኘው ዳና የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ ላይ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ከ10 አካባቢ የተነሣ እሣት 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት አጠፋ፡፡ ወንድሙ ኃይሉ                                                                                                                                                                                                           
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፌዴራልና የጋንቤላ ክልል መንግሥት ባካሄደው ጥናት መሠረት መሬት ወስደው ለረጅም አመታት ሳያለሙ....

የፌዴራልና የጋንቤላ ክልል መንግሥት ባካሄደው ጥናት መሠረት መሬት ወስደው ለረጅም አመታት ሳያለሙ ያስቀመጡና ለሌላ ዓላማ ያዋሉ የ269 ባለሀብቶችን መሬት ሲቀማ ለ27ቱ ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተናገረ፡፡ከክልሉ መስተዳደር ሸገር ዛሬ እንደሰማው ከክልሉ መሬት ወስደው እናለማለን ያሉ ባለሃብቶች ያሉበት የሥራ እንቅስቃሴና ወቅታዊ ሁኔታ ለማወቅ በተደረገ ጥናት ባለ ሃብቶቹ ያሉበት የማልማት ደረጃ ይፋ መሆኑን ነው፡፡

በጥናቱ መሠረትም 269 ኢንቨስተሮች በጣም ደካማ ሆነው መሬቱን ተረክበው ለረጅም ዓመታት ቢይዙትም ምንም እንዳልሰሩበት ከክልሉ ሰምተናል፡፡በዚህም መሠረት የፌዴራልና የክልል መንግሥቱ በመተባበር መሬቱን እንደነጠቃቸው ሰምተናል፡፡

በጋምቤላ ክልል በርካታ መሬቶች በኢንቨስትመንት ስም ተይዘው ለረጅም አመታት ብድርም ተወስደውባቸውና የማልሚያ መሳሪያዎችም ከገቡ በኋላ ኢንቨስተሮቹ ገንዘቡንም ሳይመልሱ መሬቱንም ሳያለሙ ለብዙ አመታት የተቀመጡ ሲሆን የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በክልሉ ያለው የመሬት ይዞታና የልማት ሁኔታ እንዲጠና ባደረጉት መሠረት በርካታ ባለሃብቶች ንብረቶቻቸውን በየቦታው ጥለው ከክልሉ መሰወራቸውን ከዚህ ቀደም ሪፖርት መቅረቡን ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዝናብ ጥሎ ሳር ባበቀለበት ኩሬ ውሃ ባቆረበት ቦታ የከብቶቻቸውን ጭራ ተከትለው ከብት በማርባት ህይወታቸውን የሚገፉ የቦረና አካባቢ አርብቶ አደሮች...

ዝናብ ጥሎ ሳር ባበቀለበት ኩሬ ውሃ ባቆረበት ቦታ የከብቶቻቸውን ጭራ ተከትለው ከብት በማርባት ህይወታቸውን የሚገፉ የቦረና አካባቢ አርብቶ አደሮች ሁለት የዝናብ ወቅቶች በጊዜያቸው ባለመጣላቸው በድርቅ መጠቃታቸው ይታወሣል፡፡ሰሞኑን ቀዝቃዛና ደመናማ የሆነው አየርም ለቦረና አካባቢ ዝናብ መለገሱን ሰምተናል፡፡አቶ በዳሳ ድሪባ ከቦረና ዞን የያቤሎ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሲናገሩ ዝናቡ መጣል ከጀመረ ሦስት ቀኑ ነው እስካሁን እየዘነበ ነው የሚገኘው በሰላማዊ ሁኔታ እየዘነበ ነው፤ ትላንት ብቻ ትንሽ ከባድ ዝናብ ጥሎ ነበር ብለውናል፡፡

የጣለው ዝናብ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎችና ሁሉም ወረዳ ያካለለ እንደሆነ አቶ በዳሳ ነግረውናል፡፡ደረቅ የአየር ሁኔታ ቆይቶ በቀጥታ ዝናብ ሲጥል በከብቶቹ ላይ መጠነኛ አለመስማማትና ጉዳት እንዳደረሰም ሰምተናል፡፡አሁን የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ለከብቶች የሚሆን የግጦሽ ሣር በሣምንታቱ ውስጥ ሊበቅል እንደሚችል ከአቶ በዳሣ ሰምተናል፡፡

ተከስቶ የነበረውን ድርቅ አስከፊነት ሸገር በቦታው ተገኝቶ መዘገቡና 60 ሺ የሚሆኑ የዞኑ የቀንድ ከብቶች በውሃ ጥምና በግጦሽ ሣር እጦት መሞታቸውንና የዚህን ቁጥር ያክል እንስሣት ካለ ሰው ድጋፍ እንደማይንቀሣቀሱ መንገራችን ይታወሣል፡፡ስለ ዝናቡ ቀጣይነት ከብሔራዊ ሜትሬዮሎጂ ኤጀንሲ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሣካም፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዬቤል ልዩ በዓሉን ማክበር ጀመረ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዬቤል ልዩ በዓሉን ማክበር ጀመረ፡፡ዩኒቨርስቲ ፕሬሱ በእስካሁን ጊዜ ቆይታው 101 በሚሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ትምህርታዊ መዛግብትን ማሳተሙ ተነግሯል፡፡ከሀገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁሉ ቀድሞ በዘመናዊ መልክ እንደተደራጀ የሚነገርለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ በበጀትና አስተዳደር ባለ ሙሉ ሥልጣን ሆኖ ራሱን መምራት እንዳልቻለ ሲነገር ሰምተናል፡፡

ተቋሙ በታላላቅ አካዳሚያዊ እውቀት የተሞሉ አርታኢዎች፣ ገምጋሚዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሚቸግሩት ተነግሯል፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር በእግረ መንገድ የመፅሐፍ ዐውደ ርዕይ ያካሂዳል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 18፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ለ50 ዓመታት የተለያዩ የቤተሰብ ምጣኔ-አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር በገንዘብ ችግር ምክንያት የጀመርኳቸው ሥራዎቼ ሊስተጓጎሉብኝ ነው አለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • አነስተኛ የቆዳ ስፋትና ውስን የተፈጥሮ ሃብት ያላት እሥራኤል ራሷን በተሻለ የምጣኔ-ሐብት ይዞታ ላይ ለማድረስ ችላለች ይባላል፡፡ ቆሻሻ ውሃን እያጣራች ዳግም ጥቅም ላይ በማዋልም የነበረባትን ችግር እንደተወጣች ይነገራል፡፡ አሁን እነዚህን ልምዶቿን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ እንደሆነች ሰምተናል፡፡ በኢትዮጵያ የእሥራኤል አምባሳደር የሆኑት በላይነሽ ዛቫድያ ከሸገር ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህንኑ ተናግረዋል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከተለያዩ የገጠር አካባቢዎች ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መጥተው ህክምናቸውን እስኪጨርሱ መጠጊያ ያጡ ህሙማንን ጎጆ የህሙማን ማረፊያ ማህበር በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ይንከባከባቸዋል ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • እርጥበት ናፍቆት ለከረመው የቦረና አካባቢ ዝናብ መዝነቡ ተሰማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በጋምቤላ ባለሃብቶች መሬት ወስደው ባለማልማታቸው መንግሥት ተረከባቸው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ትልልቅ የውሃ ማስተላለፊያ ቦዮችን ለመገንባት የግል ውሃ ተቋራጮች አይሳተፉበትም ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዬቤል ልዩ በዓሉን ማክበር ጀመረ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬና ነገ በየኮሌጆቻቸውና ትምህርት ቤታቸው ዕርስ በርስ ይገመገማሉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬና ነገ በየኮሌጆቻቸውና ትምህርት ቤታቸው ዕርስ በርስ ይገመገማሉ፡፡ የግምገማ ውጤትም በደረጃ ይሰጣቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ የሚመዘኑትና ደረጃቸው የሚለካው፣ መንግሥት ተሰፈሩበት ብሎ ባወጣላቸው 3 መስፈርቶች ነው፡፡  ተማሪዎች የመወያያ ርዕስ ጉዳይም ተመርጦላቸዋል፡፡

ብቁና ውጤታማ የከፍተኛ ትምህርት ማህበራት በሚል ርዕስ ተመስርተው ውይይት ያደርጋሉ፡፡ተማሪዎች ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ለመሆን ያላቸው ባህሪና አመለካከት አንደኛው የግምገማ መስፈርት ሲሆን፣ የመቧደን ወይም በጋራ ማበር በትምህርት ጥራት በኩል ያለው አስተዋፅኦ የሚለው ሌላኛው መስፈርት ነው፡፡

ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ተማሪነታቸው ያመጡት ተከታታይ የባህሪና የአመለካከት ለውጥ እንዲሁም ተግባር የሚል የመገምገሚያ መለኪያ ቀርቦላቸዋል፡፡ተማሪዎቹ በእነዚህ መስፈርቶች ዕርስ በርስ ከተገማገሙ በኋላ በጣም ከፍተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ የሚል ውጤት ይሰጣቸዋል፡፡ ሸገር የመመዘኛ መስፈርቶቹን አመራረጥ በተመለከተ እንዲሁም የተማሪዎቹን ግምገማ አስፈላጊነት እንድያብራራለት የዩኒቨርስቲዎቹን ኃላፊዎች ለማነጋገር ያደረገው ጥረት ለጊዜ አልተሣካም፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የ‘አፍላቶክሲን…’ ነገር

በቅርቡ እንግሊዝ ሀገር ተልኮ የነበረ 2 ኮንቴነር ሙሉ በርበሬ የምግብ ደህንነት ማረጋገጫ ስላልተሰጠው እንዲሁም በአፍላ ቶክሲን ስለተጠረጠረ እንዲጣል ተፈርዶበታል…እነ በርበሬንና ለውዝን፣ በቆሎንና ቦሎቄን አኩሪ አተርና የቅባት እህሎችን በደንብ ጠርጥሯቸው…

ወደ ሆድ ገብተው ወዝና ውበት እንዲሁም ጉልበት በመስጠታቸው በሰው ልጆች የሚወደዱት እነዚህ ምርቶች የካንሰር አምጪ ኬሚካል ውህድ አይጠፋቸውምና ደህና አድርጋችሁ ጠርጥሯቸው የሚሉት የምግብ ደህንነት ፈታሾችና እህሎች ስለያዟቸው ንጥረ ነገሮች መመርመር ሥራቸው የሆኑ ሙያተኞች ናቸው፡፡በኢትዮጵያ አሁን አሁን ስሙ እየገነነ የመጣው አፍላ ቶክሲን የተባለ የኬሚካል ውህድ አያጣቸውም የተባሉት ለምግብነት የሚውሉ ሰብሎች አደገኛውን ኬሚካል ቀላቅለው በብዛት እየተገኙ ነው ይላሉ ሸገር ከሰሞኑ ያነጋገራቸው የብሌይስ አግሪ ፉድ ላብራቶሪ ማህበር ባለሙያዎች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 15፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአፍላ ቶክሲን መርዛማ ንጥረ ነገር ሳቢያ ወደ ውጭ አገራት እየተላኩ ተቀባይነት አጥተው የሚመለሱ የምግብ ምርቶችን መጠን ለመቀነስ እዚሁ በአገር ቤት የላቦራቶሪ ፍተሻው ሊጠናከር ይገባል ተባለ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የዘሉሲ ሜትር ታክሲ ማህበር በሊፋን ሞተርስ የምጠየቀው የጥገና ዋጋ የተጋነነ ነው፤ የማይቀንስ ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት እንደምሄድ በደብዳቤ አስጠንቅቄያለሁ ብሏል፡፡ የታሪፉ ጉዳይም በድጋሚ እንዲታይለት አቤት ለማለት መሰናዳቱን ተናግሯል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ፌር ፕላኔት የተሰኘው የእሥራኤል ድርጅት ኢትዮጵያ የግብርና ምርቷ እንዲበረታ እያገዘ መሆኑን ተናግሯል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ለወጪ ንግድ እክል መሰናክሎች መፍትሄ የሚሻ አገር አቀፍ ምክር ቤት ሊመሠረት ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የዓለም ባንክ ለተፈጥሮ ሚዛን ማስጠበቂያና ለደን ልማት ሥራ የሚያግዝ 18 ሚሊዮን ዶላር ለገሠ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የአዲስ አበባ ተማሪዎች እርስ በእርስ እየተገማገሙ ነው፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባህር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው በህገ-ወጥ መንገድ ሳውዲ አረቢያ ከገቡት መሀከል በአንድ አመት ብቻ ከ89 ሺ የሚበልጡት ኢትዮጵያዊያን ተይዘው ሀገር ቤት መመለሳቸው ተሠማ

ባህር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው በህገ-ወጥ መንገድ ሳውዲ አረቢያ ከገቡት መሀከል በአንድ አመት ብቻ ከ89 ሺ የሚበልጡት ኢትዮጵያዊያን ተይዘው ሀገር ቤት መመለሳቸው ተሠማ፡፡ከ2 ሺ 897 የሚልቁት ደግሞ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወርና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በሳውዲ አረቢያ እሥር ቤቶች እየማቀቁ ነው ተብሏል፡፡

ሸገር ወሬውን የሰማው የጀርመን ሬዲዮ ድምፅ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙትን የኢትዮጵያን ኤምባሲ የዲያስፖራ እና የቆንስላ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑትን አቶ ፋይሰል አልዩን ጠይቆ ካዘጋጀው ወሬ ነው፡፡ሳውዲ አረቢያ በባሕርና በየብስ በተለያዩ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ድንበሬን ተላልፈው ገብተዋል ብላ ከምታባርራቸው የዓለም ዜጎች መሀከል ኢትዮጵያዊያን ቀዳሚዎቹን ቁጥር መያዛቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ከጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም እስከ መስረም 2009 ዓ.ም ድረስ በነበረው አንድ ዓመት ብቻ ከሳውዲ አረቢያ የተባረሩና ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከ89 ሺ በላይ ነው ተብሏል፡፡በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች አማካይነት ባሕር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው ሳውዲ አረቢያ ከገቡ በኋላ ተይዘው የተመለሱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በአማካይ በየሣምንቱ 246 ነውም ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 14፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን ሞትና ጉዳትን ለመቀነስ የሐይማኖት ተቋማት ተከታዮቻቸውን ሊያስተምሩ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ሳውዲ አረቢያ በሕገ-ወጥ መንገድ ገብተውብኛል ብላ ካባረረቻቸው የውጭ ዘጐች ኢትዮጵያውያን ይበዛሉ ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ በ2009 ዓ.ም በተካሄደ አዲስ የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባ ከ60 ሺ በላይ ሥራ ፈላጊዎች ተገኝተዋል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የ40/60 መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኛ ተጠቃሚዎች የሚተላለፉበት ትክክለኛው ቀን አልተቆረጠም ተባለ፡፡ (ተኀቦ ንጉሴ)
 • የኢትዮጵየ አየር መንገድ በህንድ አምስተኛ የሆነውን የካርጐ አገልግሎት ሊጀምር ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በዞን ደረጃ በጐንደር የከተሞች ቀን ሊከበር ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የአልጄሪያው ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ አስቧል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ጦሳ ተራራ ሥር የውሃ ፕሮጀክት ተቋቋመ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የፕሪንተር ቀለም መያዣዎችን ብክለት አልባ በሆነ መንገድ የማስወግድበትን መላ ሥራ ላይ አውያለሁ አለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የቱርክ ባለሀብቶች ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት አድርገዋል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers