• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ጥር 8፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 8፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ያለ አሳማኝ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ዋጋ ጨምረዋል በተባሉ የአርማታና ቱቦላሬ ብረት አስመጪዎችና አምራቾች ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ የመድሃኒት ግዢ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታየውን ብልሹ አሰራር ለማስተካከል እገዛ ያስፈልገኛል አለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የአየር ፀባይ መለዋወጥ የአየር ንብረቱን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ እያደረገው ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • መንግስት 13 የልማት ድርጅቶቼን ሙሉ በሙሉ እና ድርሻዬን እሸጣለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የመንግስት ኮሙኒኬንሽን ጉዳዮች ሀላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጡ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • አዲሱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን በኦፌሴል ይጎበኛሉ፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
 • ቅሬታ ከቀረበባቸው ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ጠበቆች መካከል ዘጠና ሁለቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው፡፡ ሌሎች አራት ጠበቆች ከስራ ታግደዋል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚሰጠውን ነፃ የህግ ድጋፍና ሌሎች አገልግሎቶች ለማሻሻል የሚያስችል ረቂቅ ሰነድ ማዘጋጀቱን ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ጃፓንና ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስምምነት ጉዳዮች እየመከሩ ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠያቂም ተጠያቂም የለም…

በምስሉ ላይ የሚታየው ሚሊየን ብሮች ፈስሰውበት ለዘመናት ያገለግላል ተብሎ የተገነባው ህንፃ አመት ሳይሞላው መፈራረስ ጀምሯል፡፡ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሆነው ይሄው ንብረት ለኮሌጁ አስተዳዳሪዎች ቢሮነት የተገነባ ነበር፡፡ አስተዳዳሪዎቹ እየፈራረሰ ያለው ህንፃ ለደህንነታቸው ስጋት ቢሆንባቸው ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት ወደተገነባውና አሁንም ከነውበት እና ጥንካሬው ጋር ወዳለው ሕንፃ ተዛውረዋል...

ለዚህ አሳዛኝ ኪሳራ ጠያቂም ተጠያቂም አልተገኘም ይለናል የትዕግስት ዘሪሁን ዘገባ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋታና የትራንስፖርት አገልግሎት ያስፈልገኛል ካላቸውና ውጭ ሄደው...

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋታና የትራንስፖርት አገልግሎት ያስፈልገኛል ካላቸውና ውጭ ሄደው ከሰለጠኑ 440 በላይ ኢትዮጵያውያን መካከል እስካሁን ስራ ያላገኙ አሉ ተባለ፡፡ተማሪዎች የሰለጠኑት ከ5 ሺህ ኪ.ሜትር በላይ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ ይኖራል ተብሎ በተያዘው ውጥን መሰረት ነበር፡፡ይሁንና በአቅም ችግር ምክንያት የታሰበውን ያህል የባቡር መስመር ዝርጋታውን መከወን ስላልተቻለ በተለያዩ የአለም ሀገራት የሰለጠኑ ኢትዮጵያውያንን ሁሉንም መቅጠር እንዳልተቻለ ኮርፖሬሽኑ ለሸገር ተናግሯል፡፡

በምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሚዮኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ደረጀ ተፈራ ለሸገር እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር 441 ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ውጭ ሀገር ሄደው እንዲሰለጥኑ አድርጓል፡፡ከመካከላቸው 254ቱ በቻይና ፣ 12ቱ በራሽያ የሰለጠኑ ሲሆን በሌሎች ሀገራትም ትምህርቱን ወስደው የተመለሱም መኖራቸውን ሰምተናል፡፡

በተያያዘ በመጪው ጊዜ ለባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትና ለባቡር መስመር ዝርጋታው የሚያስፈልጉ ባለሙያዎችን በሀገር ውስጥ ለማሰልጠን ኮርፖሬሽኑ የባቡር አካዳሚ ሊገነባ ነው ተብሏል፡፡የማሰልጠኛ ተቋሙ በመጪው 2011 ዓ/ም በቢሾፍቱ ከተማ ግንባታው ይጀመራል ብለዋል አቶ ደረጀ፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለአካዳሚው ግንባታ ከቻይና መንግስት ከ373 ሚሊዮን ዩዋን በላይ እርዳታ ለማግኘት ስምምነት ተፈርሟል፡፡ግንባታው በሁለት አመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በመጀመሪያ ዙር እስከ 1000 የሚደርሱ ሰልጣኞች በቴክኒክና ሙያ በተለያዩ 7 ልዩ ልዩ የስልጠና መስኮች ይሰለጥናሉ የተባለ ሲሆን ለዚህም 250 መምህራን ያስፈልጉኛል ብሏል ኮርፖሬሽኑ፡፡በተጨማሪም የባቡር ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋሙ በሙያው እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ሊያሰለጥን እንደሚችልና በአመት እስከ 3 ሺህ የቅበላ አቅም ይኖረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ተናግሯል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

የዛሬ ጥር 7፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ለባቡር መስመር ዝርጋታና የትራንስፖርት አገልግሎቱ ያስፈልጋሉ ተብለው በውጭ ሀገር ስልጠና ካገኙ ከ440 በላይ ኢትዮጵያውያን መካከል ያለ ስራ የተቀመጡ አሉ ተባለ፡፡ በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በአገር ውስጥ የባቡር ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋም ሊገነባ መሰናዳቱ ተነግሯል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተወሰኑ እስረኞችን ክስ ማቋረጡን ዛሬ ተናግሯል፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • ዘንድሮ እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ሊተላለፉ ይችላሉ ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ እና በፊት ገፃችሁ ላይ ጉዳት የደረሰባችሁ በነፃ ታከሙ ተብላችኋል፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ቀዬ ለመመለስ ባለመቻሉ ለጊዜው በየክልላቸው መልሶ ለማቋቋም ተወስኗል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የ1970ዎቹንና የአሁኑ የኑሮ ሁኔታ በንፅፅር የሚያሰቃኝ “ዘመን” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሙዚየም ተከፈተ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን መጪውን የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ አድርጌ ለማስመዝገብ የሚረዱትን ስራዎች ማከናወኑን ተናገረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • በአቃቂ 9 ሰዎችን በዕቃ መጫኛ ላይ አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተገልብጦ የሰው ሕይወት አለፈ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 4፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ በየአመቱ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የአፍሪካን እድገት ለማበርታት የኤሌክትሪክ ሀይል ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ መጤን አለበት ተብሏል፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • በአክሱም ጥንታዊ ነው የተባለ መቃብር በቁፋሮ መገኘቱ ተነገረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የሰብአዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብሩን ተፈፃሚ የማያደርጉ ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተነገረ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያደረጉት ጉብኝት የኤርትራ ፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂን የግብጽ ጉብኝት ተከትሎ የተደረገ ነው መባሉን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሀሰት ነው አለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ዐቃቤ ህግ ክስ በመሰረተባቸው ተከሳሾች ላይ ይመሰክሩልኛል ብሎ የቆጠራቸውን ቀሪዎቹን ምስክሮች እንዳይመሰክሩ ብይን ተሰጠ፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
 • የራስ ቴአትር ስራ አስኪያጅ አርቲስት ቢንያም ሀይለ ስላሴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • አዲስ አበባ ከተማ ቆሻሻን ከቤት ለቤት ለማሰባሰብ የገቡ ተሽከርካሪዎች ስራ ያልጀመሩት አስመጪ ድርጅቱ ማጠናቀቅ ያለበትን ቅድመ ሁኔታው ባለመጨረሱ ነው ተባለ፡፡ (በየነ ወልዴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 3፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የኮሪያ ሆስፒታል 1500 ለሚሆኑ ህሙማን ነፃ የሕክምና አገልግሎት ሰጠሁ አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የብሔራዊ ፀጥታ ም/ቤት ባለፉት ሁለት ወራት በሰራሁት ስራ የተሻለ ሰላም በሀገሪቱ አካባቢዎች እንዲመጣ ማድረግ ችያለሁ አለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በዘንድሮ የጤናማ እናትነት ወር በአፍላ ወጣትነት በማርገዝ የሚፈጠር የጤና ችግር እና የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ለመቀነስ ትኩረት አደርጋለሁ ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በኢትዮጵያ በአፋጣኝ ክትባት ያስፈልጋቸዋል የተባሉ የእንስሳት በሽታዎች ተለይተው ክትባቱም እየተሰራጨ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • ባለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የመገናኛ ብዙሃን ድርሻ ብዙ ነበር ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በቀላሉ ለሚበላሹት አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የውጭ ገበያቸው የሰመረ እንዳይሆን የሀይል አቅርቦት እና ውጣ ውረድ የበዛበት አሰራር ፈተና ሆኗል፡፡ (ምስክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አገኘ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኦሮሚያና በሱማሌ ክልል የተነሳውን ግጭት ለማስቆም የፌዴራል መከላከያ ሀይል ጣልቃ የገባው በክልሎች ጥያቄ መሰረት...

በኦሮሚያና በሱማሌ ክልል የተነሳውን ግጭት ለማስቆም የፌዴራል መከላከያ ሀይል ጣልቃ የገባው በክልሎች ጥያቄ መሰረት ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትርና የብሔራዊ የፀጥታ ደህንነት ምክር ቤት ሰብሳቢው አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ተናገሩ፡፡

ግጭቱ በተፈጠረ ሰሞን ቁጥጥሩን ለማድረግ ከአቅማችን በላይ ሆኗል ብለን የጠራነው አንድም የመከላከያም ሆነ የፀጥታ ሀይል የለም ይህም ጉዳይ የፈፀሙ መከላከያ ሀይሉንም የላኩ ወገኖች በህግ ይጠየቁ ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለረጅም ጊዜ ኢህአዴግና ተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሲያወዛግብ የቆየው የፖለቲካ እስረኛ የለም የሚለው ጉዳይ...

ለረጅም ጊዜ ኢህአዴግና ተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሲያወዛግብ የቆየው የፖለቲካ እስረኛ የለም የሚለው ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ እስረኛ ይፈታል ካሉ በኋላም ማወዘጋቡ ቀጥሏል፡፡የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እንዲሁም ጉዳያቸው በዐቃቤ ሕግ ተይዘው በስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ክስ በማቋረጥ በምህረት ወይም በይቅርታ ለመልቀቅ ገዢው ፓርቲ መወሰኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢናገሩም ከቀናት በኋላ ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ የፖለቲካ እስረኛ የሚባል ነገር ኢትዮጵያ የላትም ሲሉ ተደምጧል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የመንግስት የልማት ድርጅቶች የተለያዩ ፕሮጀክቶችና ግንባታዎች በተከታታይ ስለሚከወኑ ከፍተኛ የብረት ቁርጥራጭ ክምችት እንዳላቸው ይገመታል

የመንግስት የልማት ድርጅቶች የተለያዩ ፕሮጀክቶችና ግንባታዎች በተከታታይ ስለሚከወኑ ከፍተኛ የብረት ቁርጥራጭ ክምችት እንዳላቸው ይገመታል፡፡በየቦታው ያላግባብ የወደቁ ቁርጥራጭ ብረቶች በሽያጭ ተወግደው መልሰው ለመንግስት ሀብት እንዲሆኑ በማድረግ ኢትዮ ቴሌኮምና መብራት ሀይል የተሻሉ እንደሆኑ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለሸገር ተናግሯል፡፡

በግማሽ የበጀት አመቱ ብቻ የማይገለገሉበትን ቁርጥራጭ ብረት ለብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች በማስረከብ ከኢትዮ ቴሌኮም 9.9 ሚሊየን ከመብራት ሀይል ደግሞ 20.4 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ሰምተናል፡፡በአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰለሞን አይንማር እንደነገሩን በመብራት ሀይል በኩል የማይጠቀሙባቸውን ብረቶችን ለማስወገድ ፕሮጀክቱ እስከሚያልቅ የመጠበቅ ችግር አለ በሌላ በኩልም የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት አያያዝ የተሻለ መልክ እየያዘ ነው ብለዋል፡፡

በተያያዘ ስኳር ፍብሪካዎች በሽያጭ ተወግዶ ለመንግስት መልሶ ሀብት መሆን ያለበት ከ1 ሺህ 300 ቶን በላይ የብረት ክምችት እንዳላቸው በጥናት ቢረጋገጥም ለማስወገድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ፋብሪካዎች መኖራቸውን ሰምተናል፡፡አቶ ሰለሞን እንደነገሩን ባለፈው አመት በአምስት የስኳር ፋብካዎች ጥናት ተደርጓል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 2፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከዓሣና ከዶሮ ቆዳ የተለያዩ ምርቶችን ሰርቷል የተባለው የደብረ ብርሃን ቆዳ ፋብሪካ የዓሣ ቆዳ እየባከነ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • በገንዘብ እጥረት የተነሳ የአዋሽ ወንዝን ከስጋት መታደግ አልተቻለም ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በባህል ዕቃ መሸጫ ሱቆች ውስጥ የሚሸጡ የሰዕሊያን ኮፒ ስራዎች ባለሙያው ተገቢውን ጥቅም እንዳያገኝ እያደረጉ ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • የፍትህ አካላት ማሰልጠኛ ማዕከልና የፍትህ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ተዋሃዱ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ የሚያስችል የተፋሰስ ስራ ተጀመረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • ለ41 የውሃ መስመሮች አዲስ የኤሌክትሪክ ግንባታ ሊከናወን ነው፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • በኢትዮጵያ አስቸኳይ ክትባት የሚያስፈልጋቸው የእንስሳት በሽታዎች ተለይተዋል፡፡ አንድ መቶ አስራ ሰባት ሚሊዮን ክትባቶች ተሰራጭተዋል፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የብሔራዊ ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫ የሰጡት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ናቸው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በተለያዩ ፕሮጀክቶቻቸው የተራረፉና የማይጠቀሙባቸውን ቁርጥራጭ ብረቶች በሽያጭ በማስወገድና መልሰው ለመንግስት ሀብት በማድረግ ኢትዮ ቴሌኮምና መብራት ሀይል የተሻለ አፈፃፀም አላቸው ተባለ፡፡ የስኳር ፋብሪካዎች ላይ ግን እስካሁን ችግር መኖሩን ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers