• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከጅቡቲ ወደ ሞጆ የሚያመራውና ኮንቴነር የጫኑ ከባባድ መኪኖች የሚመለላሱበት መንገድ ይጠገናል ቢባልም እስካሁን ግን መፍትሄ አለገኘም ተባለ

ከጅቡቲ ወደ ሞጆ የሚያመራውና ኮንቴነር የጫኑ ከባባድ መኪኖች የሚመለላሱበት መንገድ ይጠገናል ቢባልም እስካሁን ግን መፍትሄ አለገኘም ተባለ፡፡ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በሾፌሮችና በመንገዱ ተጠቃሚዎች ቅሬታ የሚነሣበት ይኸው መንገድ ጥገና ይደረግለታል ተብሎ የነበረ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ችግሩ እንደቀጠለ ነው፡፡

ስለ ጉዳዩ መዘግየት አግኝተን የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና  ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ተፈራ ጥያቄው በተደጋጋሚ እንደሚቀርብ ተናግረው ችግሩ በኢትዮጵያ ክልል ብቻ እንዳልሆነና የጅቡቲ መንግሥትንም የሚመለከት ነው ብለውናል፡፡

የመንገዱ ችግር ቢኖርም ከኢትዮጵያ ጅቡቲ የሚዘልቀው የባቡር አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ሥራ ሲጀምር የመኪኖቹን ምልልስ ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር በቆሻሻ ናዳ አደጋ ለደረሰባቸው 400 አባዎራዎች ያሰናዳኋቸውን የተለያዩ ቁሣቁሶች ዛሬ ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት አደርሳለሁ አለ

የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር በቆሻሻ ናዳ አደጋ ለደረሰባቸው 400 አባዎራዎች ያሰናዳኋቸውን የተለያዩ ቁሣቁሶች ዛሬ ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት አደርሳለሁ አለ፡፡ማህበሩ አደጋው ከደረሰ ጀምሮ ከወረዳው መስተዳደር እና ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የተረጂዎች ቁጥር ይድረሰኝ ብሎ ሲጠባበቅ የነበረ ቢሆንም ብዛታቸውን እስካሁን ያሳቀው ስለሌለ ነው ዛሬ በራሱ ጊዜ ለ400 አባዎራዎች ድጋፍ የሚያደርገው ሲሉ ሥራ አስኪያጁ አቶ አበባው በቀለ ነግረውናል፡፡

በአደጋ ተጎጂዎች አፋጣኝ ምላሽም ይሻሉ የሚመለከታቸው የተጐጂ ቁጥር ያሳውቁኝ ብሎ መጠበቅ ነገሩን ሁሉ ምነው ከረፈደ አያደርገውም ወይ ያልናቸው ሥራ አስኪያጁ በአደጋ ጊዜ ተጣድፈን የዕርዳታ ቁሳቁስ ብንረዳ ተጐጂውን ካልተጐዳው ያለየ የጥድፊያ አሰራር ስለሚሆን ቅሬታ ያስነሳብናል በሚል ስጋት ነው የዘገየነው ብለዋል፡፡

ዛሬ ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ለ400 አባወራዎች የተሰናዱ ብርድ ልብሶችን፣ የመመገቢያና የማብሲያ ዕቃዎችን፣ ምንጣፎችን፣ የሸራ ላስቲኮችን፣ ጀሪካኖችንና የንፅህና እቃዎችን እናደርሳለን ያሉት የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ሥራ አስኪያጅ አቶ አበባው በቀለ ተጨማሪ ድጋፎችም ካስፈለጉ ለይተን እናቀርባለን ፤ የህፃናት አልሚ ምግቦችንም ለማቅረብ ከብሔራዊ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር እንነጋገራለን ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 5፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት እስከ አሁን 60 ሺህ የቤት እንስሣት ሞተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ለሰው፣ ለእንስሣትም እንዲሁም ለአካባቢም አደገኛ የሆኑ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የግብርና ኬሚካሎች በብዛት ተከማችተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማኅበር በቆሻሻ ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው 400 ቤተሰቦች የተሰናዳ የቁሳቁስ ድጋፍ ላደርግላቸው ነው አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ቅዳሜ ምሽት በደረሰው የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 65 መድረሱን ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተናገሩ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የዝናብ እጥረት ሰዎችን ለተረጂነት ዳርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር 1 ሚሊዮን ሊትር ውሃ በሞያሌ ኦሮሚያ እና በሞያሌ ሶማሌ አደለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • ከባድ የጭነት መኪኖች የሚመላለሱበት የጅቡቲ ሞጆ መንገድ ጥገና ይደረግለታል ቢባልም አሁንም ከነብልሽቱ እንደዘለቀ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት 233 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ 1 ሺ 25 ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት 233 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ 1 ሺ 25 ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል…የትራፊክ ደንብን የሚተላለፉ አሽከርካሪዎችን ደረጃ በደረጃ እስከ መንጃ ፈቃድ መንጠቅ ድረስ የሚቀጣው ህግ በቅርቡ ተግባራዊ መሆኑ አይቀርም ተባለ፡፡

ህጉ ከዚህ በፊት ተግባራዊ ሊሆን ነው በተባለበት ወቅት ከአሽከርካሪዎች ቅሬታ ቀርቦበት ሥራ ላይ ሣይውል መቆየቱ ይታወሣል፡፡አሁን ግን አሽከርካሪዎቹ ያነሷቸው ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በመፈታታቸው ህጉ ተግባራዊ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም ሲል የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገነቱ ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡

ደንቡ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አሽከርካሪዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች መቶ በመቶ መልስ ባያገኙም በትራፊክ አደጋ እየሞተ ያለውን ሰው ለመታደግ ሲባል መንግሥት ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ ከእንግዲህ በኋላ ወደኋላ እንደማይል ሰምተናል፡፡አዲስ አበባን ከትራፊክ አደጋ ይጠብቃታል የተባለ የ13 አመታት ስትራቴጂክ እቅድ በቅርቡ ይፋ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት 233 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ 1 ሺ 25 ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደገጠማቸው ተሰምቷል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሠረታዊ ሸቀጦችን ለማግኘት ከሚኖሩበት ወረዳ ኩፖን እንዲወስዱ ተጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሠረታዊ ሸቀጦችን ለማግኘት ከሚኖሩበት ወረዳ ኩፖን እንዲወስዱ ተጠየቀ፡፡መንግሥት ለድጐማ የሚያቀርባቸውን ስኳር፣ የስንዴ ዱቄትና ዘይት ሥርጭት ለመቆጣጠር አዲስ አሰራር መዘርጋቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ተናግሯል፡፡

አዲሱ የአሰራር ሥርዓትም እያንዳንዱ ነዋሪ በአካባቢው ካለው ቸርቻሪ ነጋዴ ምርቶቹን ለመግዛት የወረዳውና ክ/ከተማው ማህተብ ያረፈበት ኩፖን ማሳየት አለበት ተብሏል፡፡አንዳንድ ነጋዴዎች ለህብረተሰቡ እንዲሸጡ ከህብረት ሥራ ማህበራት የወሰዱትን ዘይትና ስኳር አየር በአየር እየሸጡ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል ያለው ንግድ ቢሮ ፤ ባለፉት 3 ወራትም ሰባት መቶ ኩንታል ስኳርና 64 ሺ ሊትር ዘይት ከከተማዋ ሊወጣ ሲል መያዙን አስታውሷል፡፡

ይህንን ለመቆጣጠርም አዲስ የሥርጭት ስርዓት መዘርጋት አስፈልጓል ተብሏል፡፡የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊው አቶ ዲላሞ ኦቶሬ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለቤት ባለቤቶችም ሆነ ተከራይተው ለሚኖሩ 950 ሺ ኩፓኖች እየታተሙ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ሣምንት መጨረሻ ጀምሮ ኩፖኖቹ ለህብረተሰቡ ይሰራጫሉ ፤ ከየወረዳው ኩፓኖቹን ለመውሰድ በአካባቢያችሁ ካሉ የችርቻሮ ሱቆች እንደቤተሰባችሁ ቁጥር ስኳር፣ ዘይትና የስንዴ ዱቄት መውሰድ ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡ኩፖን ላልያዘ ግለሰብ ሱቆቹ ሸቀጦቹን ለመሸጥ አይገደዱም ያሉት አቶ ዲላሞ ይህም የመሠረታዊ ሸቀጦችን የስርጭት መዛባት ለመቆጣጠር የተዘየደ ነው ብለዋል፡፡

በተያያዘም በአሁኑ ወቅት መንግሥት ለመንግሥት ሠራተኛው ያደረገውን የደመወዝ ማስተካከያ ተከትሎ በተወሰኑ የግብርና ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ንረት መሠረታዊ ምክንያት የለውም ያሉት ኃላፊው ከዛሬ ጀምሮ የዋጋ ንረት የታየባቸው የቲማቲም፣ የካሮት፣ ቀይ ጤፍና ሩዝ ምርቶችን ዋጋ ወደ ነበረበት እንዲመልሱ ከነጋዴው ህብረተሰብ ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ዘነበወርቅ አካባቢ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከትናንት በስቲያ ምሽት በአፈርና በቆሻሻ ናዳ ጉዳት ለጋጠማቸው ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ እያደረኩ ነው ሲል የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር ተናገረ

በአዲስ አበባ ዘነበወርቅ አካባቢ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከትናንት በስቲያ ምሽት በአፈርና በቆሻሻ ናዳ ጉዳት ለጋጠማቸው ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ እያደረኩ ነው ሲል የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር ተናገረ፡፡

የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበባው በቀለ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ አደጋው በደረሰበት በቅዳሜ ምሽት በ907 ነፃ የስልክ መስመራችን በደረሰን ጥሪ መሰረት በስፍራው ተገኝተን እስከ ሌሊቱ 9 ሰዓት ድረስ በናዳው የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን 24 ሰዎች ወደ አለርት ሆስፒታል አድርሰንል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር የአካል ጉዳት የገጠማቸውን ሰዎች በ5 አምቡላንሶች ወደ ሆስፒታል አደረስኩ ያለ ሲሆን 20 በጐ ፈቃደኞችና 9 ቋሚ ሰራተኞች በነፍስ አድን ስራው ተሳትፈዋል ሲል ተናግሯል፡፡

አሁን ከወረዳው ሥራ አስፈፃሚ እና ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጋር የተጐጂዎቹን ቁጥር አሳውቁን በማለት ጥያቄ አቅርበናል ይህ እንደተነገረን የብርድ ልብስ፣ የብረት ድስቶች፣ የመጠለያ የላስቲክ ድንኳኖች ለማቅረብ በብዛት አሰናድተናል ሲሉም ሥራ አስኪያጁ አቶ አበባው በቀለ ነግረውናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ትናንት ምሽት በአደጋው 46 ያህል ሰዎች በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን አጥተዋል ያሉ ሲሆን የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 4፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ከትላንት በስቲያ ከምሽቱ 2 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ዘነብወርቅ አካባቢ ቆሼ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በደረሰ የአፈርና የቁሻሻ ናዳ ከፍተኛ አደጋ መድረሱ ይታወሳለ፡፡ ትላንት ምሽት ላይ የአዲስ አከባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ሰዎች በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸው አልፏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሠረታዊ ሸቀጦችን ለማግኘት ከወረዳ ኩፓን እንዲወስዱ ተጠየቀ፡፡ የዋጋ ንረት የታየባቸው ምርቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ስምምነት ተደርሶበታል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚያደርሰው ሕግ ሊተገበር ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ መንግሥት ከጅቡቲ እጅ በድርድር ያስመለሳቸው የመጋዘን ንብረቶች ወደብ ላይ ተከማችተው እየተበላሹ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ለየት ያለ አፈጣጠር ያላት አንዲት ጥጃ ተወለደች፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ) 
 •  በጅቡቲ ወደብ የሚደርሰውን ጭንቅንቅና አላስፈላጊ ወጪ ይቀንሣል ተብሎ የተገነባው የሞጆ ደረቅ ወደብ በመጨናነቁ በእጥፍ ለማሳደግ ማስፋፊያ እየተገነባለት ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የናዳ አደጋ ለደረሰባቸው ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ተናገረ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያና የሩሲያ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 1፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው እያጡ ያሉት ወጣቶች ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ 439 ሰዎች በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ሲያጡ፤ ከነዚህ ውስጥ እድሜያቸው ከ25 እስከ 34 የሚሆኑት የ 25 % ድርሻ ይይዛሉ ተባለ፡፡(ንጋቱ ሙሉ) 
 • የዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በምስራቅ አፍሪካ ወቅትን እየጠበቀ የሚከሰተው ድርቅ በተለይ ሴቶች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍ ያለ ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • ብአዴን ጉባዔ ሊያካሂድ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • ለልማት ተነሺዎች የካሳ ዋጋን ለማሻሻል የተጀመረው ጥናት ተጠናቀቀ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ የሱፍ ዘይት የሚያመርት ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • አዲስ አበቤዎች እነቲማቲምና ቃርያ በጣሙን ተወድደው እየተቸገርን ነው እያሉ ነው፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 30፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የትራፊክ አደጋ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ብቻ 479 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሲሞቱ 1925 ሰዎች ደግሞ ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ (ተህቦ ንጉሴ) 
 • በአዲስ አበባ እና በካርቱም መካከል የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት የፊታችን እሁድ ይጀመራል ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • ትላንት ምሽት በየካ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 4 ቤቶች ተቃጠሉ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ሕገወጥና ሕገወጦች ችግር ሆነውብኛል ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአሰራር ረቂቅ ደንብ አላማዎች ዙሪያ ለ5ኛ ጊዜ ድርድራቸውን በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እያካሄዱ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም የካቲት 28፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ሕልውናዬ አደጋ ተጋርጦበታል እያለ ነው

ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ሕልውናዬ አደጋ ተጋርጦበታል እያለ ነው…በአሁኑ ወቅት 228 ረዳት የሌላቸውን የአእምሮ ሕሙማንን እየተንከባከበ የሚገኘው ማዕከሉ እስከ ፊታችን ግንቦት ወር ድረስ ያለበትን ቦታ እንዲገዛ አልያም ለቅቆ እንዲወጣ በቦታው ባለቤቶች መታዘዙን ሰምተናል፡፡

የማዕከሉ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ አየለ ለሸገር እንደተናገሩት ማዕከሉ ቦታ እንዲሰጠው መንግሥትን ጠይቆ ምላሽ እየተጠባበቀ ነው፡፡በተጨናነቀ ቦታ ሕሙማኑን የሚያስተናግደው ጌርጌሴኖን በየጊዜው ወደ ማዕከሉ የሚጎርፈውን ረዳት አልባ የአእምሮ ሕሙማን ተቀብሎ ማስተናገድ እየተሳነው መጥቷል…

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፣ አሁን ደግሞ ማዕከሉ እስከ ግንቦት ወር ድረስ ማዕከሉ ያለበትን ቦታ ይግዛ አልያም ቦታውን ይልቀቅ መባሉን ሰምተናል…እንጦጦ የሚገኘው ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ሰራተኞች 80 % ያህሉ በጎ ፍቃደኞች ናቸው፡፡

እንዲሁም ያለበት ቦታ አልበቃ ብሎት ችግር ላይ ያለው ጌርጌሴኖን ቦታውን ከ5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ዋጋ እንዲገዛ አልያም እስከ መጪው ግንቦት ድረስ ሌላ ቦታ እንዲፈልግ ተነግሮታል…ከልጅነቱ ጀምሮ ደጋፊ የሌላቸውን ሰዎች መርዳት የሚወደው የማዕከሉ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ አየለ ማዕከሉን የመሰረተው የዛሬ 10 ዓመት ነበር…

ጌርጌሴኖን ከለጋሾች በሚያገኘው ድጋፍ ነው ረዳት የሌላቸውን የአእምሮ ሕሙማን የሚረዳው…ጌርጌሴኖን ለመርዳት ለምትሹ አድራሻውን እነሆ…

የማዕከሉ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ አየለ ስልክ፥ 0912 18 88 76 ወይም 09 22 82 12 35

ፖ.ሳ ቁ፥ 31209 አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

http://www.gergesenon.org/whowe.php

አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ እንጦጦ፣ ቁስቋም ከ17 ቁጥር አውቶብስ ማዞሪያ አለፍ ብሉ ከውሃ ልማት ጎን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers