ሕዳር 26፣ 2012/ በኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉና ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን የሚደግፍ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
“ኢዱኬሽን ካን ኖት ዌይት” የተሰኘው ተቋም በመደበው 27 ሚሊዮን ዶላር ከ750 000 በላይ ህፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ መታሰቡን ሰምተናል፡፡ዩኒሴፍ፣ የህፃናት አድን ድርጅት እና የትምህርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ያስፈፅሙታል የተባለው ፕሮጀክት በግጭት እና በረሀብ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ህፃናትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ተነግሯል፡፡በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ህፃናት ጭምር በዚሁ ፕሮጀክት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ይደረጋል መባሉን ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ሰምተናል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት አደጋ ውስጥ ያሉ ህፃናትን ታሳቢ ያደረገ የትምህርት መርሃ ግብር ባለመኖሩ ፕሮጀክቱ በዚህ በኩል ያለውን ክፍተት ለመሙላት ያግዛል ተብሏል፡፡በመላው ዓለም ከ75 ሚሊዮን በላይ ህፃናት በተለያዩ ችግሮች የተነሳ ትምህርታቸውን ማቋረጣቸው ይነገራል፡፡“ኢዱኬሽን ካን ኖት ዌይት” የተባለው ተቋም በ30 ሃገራት በተመሳሳይ ሁኔታ ከትምህርት የተገለሉ ህፃናትን ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)