• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ባሳለፍነው ሳምንት አዘዋዋሪው ያልታወቀ የዝሆን ጥርስ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኘ

ባሳለፍነው ሳምንት አዘዋዋሪው ያልታወቀ የዝሆን ጥርስ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኘ፡፡ንብረትነቱ የሳውዲ አረቢያ የሆነ አውሮፕላን ካርጐ ውስጥ ተቀምጦ የተገኘው 62 የዝሆን ጥርስ ሲሆን ክብደቱም 307 ኪ.ግ ይመዝናል ተብሏል፡፡

ከዱር እንስሣት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን የዱር እንስሣትና ውጤቶቻቸው የዝውውር ቁጥጥር ባለሙያው አቶ ዳንኤል ጳውሎስ ለሸገር ሲናገሩ ሳዑዲ አረቢያ ዝሆኖች እንደሌሏት ይታወቃል፤ በአውሮፕላኗ ካርጐ ውስጥ የተገኙት የዝሆን ጥርሶች ከአፍሪካ የተነሳ ሳይሆኑ አይቀሩም ብለዋል፡፡

በጥቂት የዝሆን ጥርሶቹ ላይ ሌጐስ የሚል ፅሁፍ ተገኝቷል ይህም ከናይጄሪያ የተነሱ ሣይሆኑ እንዳልቀሩ አስጠርጥሯል ተብሏል፡፡ከአቶ ዳንኤል እንደሰማነው የዝሆን ጥርሶቹ ማን በአውሮፕላኑ እንደጫናቸው እንዲያጣራ በአዲስ አበባ ላለው የኢንተርፖል ጽ/ቤት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የሚሰሙና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ቀኑ ከሚከበርበት ቀን ባለፈ ተከታታይነት ያለውና ለውጥ የሚያመጣ ሥራ መሰራት አለበት ተባለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የሚሰሙና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ቀኑ ከሚከበርበት ቀን ባለፈ ተከታታይነት ያለውና ለውጥ የሚያመጣ ሥራ መሰራት አለበት ተባለ፡፡ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ሴቶች በየዘርፋቸው ያስመዘገቧቸውን ስኬቶች መዘከሪያ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሚደርስባቸው ጥቃት የሚወገዝበትና ለማስቆምም የሚሰራበት መሆን አለበት ሲሉ ወ/ሮ የምወድሽ በቀለ የሴቶች ይችላሉ የበጐ አድራጐት ማህበር ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

ሴቶች በሥራ ቦታ ላይ ከቅጥር እድገት ከማግኘትና የሙያ ደህንነት አንፃር በርካታ ችግሮች እንደሚደርስባቸውም ተነግሯል፡፡በሥራ ቦታቸው ላይ ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠርና የወላድ እናቶች ልጆቻቸውን የሚያቆዩበት ቦታ ለማዘጋጀት ሥራውን የጀመሩ ድርጅቶችም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ማህበርም ተናግሯል፡፡

የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ እስካሁን የተሰሩ ሥራዎች ቢኖሩም ገና የሚቀሩና ብዙ መሠራት ያለባቸው ሥራዎች እንዳሉ መታሰብ አለበት ተብሏል፡፡በሀገሪቱ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃትም ይሆን ሌሎች ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሄ ለማበጀት የሚተባበሩኝን እፈልጋለሁ ያለው የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ነው፡፡

 “ተግባራዊ ለውጥ ለሴቶች እኩልነት መረጋገጥ” በሚል የሚከበረው የዘንድሮ የሴቶች ቀን በቃል ከሚነገረው በላይ ተግባራዊ ለውጥ ለማምጣት ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል የሚል ዓላማን ይዟል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ይህ ወሬ እጅግ አሳዛኝ ነው…

አስከፊው የመኪና አደጋ እነሆ አሁን ደግሞ የአራት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ደናግላንን ሕይወት ቀጥፏል…ለበርካታ ዓመታት በደናግልነት ሲያገለግሉ የነበሩ አራት ኢትዮጵያዊያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እህቶች ትላንትና በተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሠማ፡፡

ሸገር አሳዛኙን ወሬ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠቅላይ ፀኃፊ ከሆኑት ከአባ ሀጐስ ሀይሽ ሰምቷል፡፡በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ አደጋ ከደረሰባቸውና ህይወታቸውን ወዲያውኑ ካጡ እህቶች በተጨማሪ ሌላኛዋ ደናግል በከፍተኛ ጉዳት ህክምና ላይ እንደሚገኙም አባ ሀጐስ ተናግረዋል፡፡

የማህበራቸው አባል ለሆኑ በአንድ ድንግል እህት ዘመድ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት በጉዞ ላይ ሳሉ አደጋ የደረሰባቸው የኢትዮጵያዊያን ደናግል የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ በልደታ ካቴድራል የፍትሀት ፀሎት ከተደረገ በኋላ በቀኑ በ8፡00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈፀምም አባ ሀጐስ ነግረውናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 29፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

{audio}/news/Wednesday_Morning_News_Yekatit_29_2009.mp3{audio}

 • በሲኖ ትራክ መኪና አደጋ አራት የካቶሊክ መነኮሳት ሕይወታቸውን አጡ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በሳውዲ አውሮፕላን የተገኙ የዝሆን ጥርሶች የማን እንደሆኑ አልታወቁም ባለቤቱንም ለማወቅ በኢንተርፖል እየተፈለገ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠ የገዳ ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ ያደረጉት ጥረት ተሞገሰላቸው፡፡ ለሽልማትም አብቆቷቸዋል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከየክልሉና ከአስተዳደሮች ተወክለው አዲስ አበባ የሚገኙት ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊናገሩ ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ የሲሚንቶ የማምረት አቅም በዓመት 12 ሚሊዮን ቶን ደርሷል መባሉ ተሠማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • ውሃ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ጥልቅ ጉድጓዶችን ለመቆፈር የሶላር ኢነርጂ ተመራጭ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • መቆሚያ ያላገኘው የሴቶች ጥቃት ለመከላከል የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሰጥተውበት ሊሰሩበት ይገባል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የሴቶችን ጥቃት ለመከላከልና የሚደርስባቸውን ችግሮች ለማስቆም ተከታታይ ጥረት ያስፈልጋል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 27፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የምትገኘው ያቤሎ ከተማ የገበሬዎቿን ብዛት ከፍ ለማድረግ አስባለች፡፡ መሠረታዊ ችግሮቿ በሆኑት የውሃ እጥረትና የመብራት መቆራረጥ ላይም እየሰራች መሆኑን ሰምተናል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የጨፌ ኦሮሚያ አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ጉባዔውን በማድረግና የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት በአዳማ ተጠናቀቀ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳትን ወደ ውጭ ሀገር ልካ ያሰበችውን ያህል ገቢ ማግኘት አልቻለችም ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ ቅርሶች ያጋጠማቸውንና የሚያጋጥማቸውን ችግር ይፈታል የተባለ ምክክር ዛሬ ተጀመረ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በጉራጌ ዞን ቤት ለመሥራት በማኅበር የተደራጁ ቦታ አልተሰጠንም አሉ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የጋምቤላ ክልል አስተዳደር ጉባዔ አካሄደ፣ አዳዲስ ሹመቶችንም ሰጠ፣ በአካባቢው ፀጥታ ጉዳይ ላይም መከረ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ነፃ የህግ ምክርና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቢኖሩም የተለያዩ ችግሮች እንዳለባቸው ተነገረ

በኢትዮጵያ ነፃ የህግ ምክርና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቢኖሩም የተለያዩ ችግሮች እንዳለባቸው ተነገረ፡፡ወሬውን የሰማነው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር በነፃ የህግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ባለሙያዎችን ያሣተፈ ዐውደ ጥናት ሲያካሂድ ተገኝተን ነው፡፡በዐውደ ጥናቱ በኢትዮጵያ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ያሉበት ደረጃና ምን ዓይነት ችግሮችስ አለበት ? የሚሉ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡

ነፃ የህግ አገልግሎት በተለያየ መንገድ ከፍለው አገልግሎቱን ማግኘት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሰጣል፡፡ይህም ከማማከር ጀምሮ የህግ አገልግሎቱን እስከመስጠትና ጠበቃ እስከማቆም እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነፃ የህግ አገልግሎት እንዲሰጡ የታሰቡ ማህበራት ቢኖሩም በከተሞች ላይ ብቻ ተወስነው ቀርተዋል ተብሏል፡፡

ወደ እነዚህ ነፃ የህግ አገልግሎት ቦታዎች ከመሄድ ይልቅ ወደ ሌሎች ተቋማት ማምራት በተገልጋዬች ዘንድ የሚታይ ክፍተት እንደሆነ ተነግሯል፡፡በተሰበሰቡ መረጃዎችና በቀረበ ጥናት እንደተነገረው ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አገልግሎቱ እንዳይሰጥና ተደራሽ እንዳይሆን ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ማህበራቱ የበጐ ፈቃድ ድርጅት በመሆናቸውም ከለጋሾች የሚገኝ ገንዘብ ሲቋረጥ እንዲዘጉ እያደረጋቸው ነው ተብሏል፡፡አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊትም የዳሰሳ ጥናት ስለማይካሄድ ትክክለኛ አገልግሎት ፈላጊዎችን እያዳረሰ እንደማይገኝ ተነግሯል፡፡የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር የነፃ አገልግሎቱን ማግኘት የሚሹና ፍትህን የተጠሙ ዜጐች ስላሉ አገልግሎቱን ለብዙሃኑ ለማዳረስ የሚደግፈኝ እፈልጋለሁ ብሏል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 24፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት ለተማሪዎች ልዩ የመጓጓዣ አገልግሎት ለመሥጠት እየተዘጋጀ መሆኑ ተሠማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታሎች ጭምር መሰጠት ቢጀመርም ህመምተኞች ግን ሳይንሱ በሚፈቅደው መጠን አገልግሎት እያገኙ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የቦረና ኦሮሞ የገዳ ሥልጣን ርክክብ ተደርጓል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በነፃ የሕግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ያለመ ዐውደ ጥናት ሊካሄድ ነው፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በአዲስ አበባ የየካቲት 23 ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከአምናው ተምረው የዘንድሮውን የአድዋ ድል በዓል የትምህርት ቤታቸውን መጠሪያ የሚመጥን አድርገውት ሰንብተዋል፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በዚህ አመት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከተዘጉ 500 በላይ ትምህርት ቤቶች መካከል አብዛኞቹ ተመልሰው መከፈታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ገዢውና ተቃዋሚ የፖለቲካ ማኅበራት በረቂቅ የአሠራር ደንብ ሥያሜ ላይ ዛሬም አልተስማሙም፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በኦሮሚያ ልዩ ዞን መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ትላንት ማታ 4 ሰዓት ከ20 የተነሣ እሳት ሦስት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት አወደመ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተግባራዊ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ፣ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተከስቶ የነበረውን ብጥብጥና ሁከት በማባባስ...

ተግባራዊ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ፣ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተከስቶ የነበረውን ብጥብጥና ሁከት በማባባስ፣ ለኦፌኮ አባላት የሥራ ክፍፍል በማድረግ በህዝብና በመንግሥት ተቋማት ላይ ውድመት እንዲከናወን በማድረግ፣ የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸዋል፡፡

ዶክተር መረራ ጉዲና በጠበቃቸው በኩል ለክሱ፣ የቅድሚያ ክስ መቃወሚያ ለማቅረብ ቀጠሮ እንዲሰጣቸውና የዋስ መብታቸውም እንዲከበር ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ዶክተር መረራ እድሜ ልካቸውን በሰላማዊ ትግል የሚታወቁ በመሆናቸው፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ሀገር ያለ እንደማይመስላቸው እና ይህም የሚታወቅላቸው በመሆኑ፣ በሽብር ህጉም ያልተከሰሱ በመሆኑ የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠበቃቸው አመልክተዋል፡፡

ክሳቸውም ከሌሎች ተከሣሾች እንዲነጠል አመልክተዋል፡፡በተጨማሪም የሰኳር ህመምተኛ በመሆናቸው፣ አሁን ካሉበት የማዕከላዊ እሥር ቤት ወደ ማረሚያ ቤት እንዲተላለፉ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡የፌዴራሉ ፍርድ ቤት 19ነኛው ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ፣ በዋስ መብቱ ጉዳይ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 30/2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሲሰጥ ሌሎቹን ማመልከቻዎችም በዚያው እለት የሚመልሳቸው መሆኑን አሳውቋል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ የትምህርት ቤት አውቶብሶችን ለማሰማራት አቅጃለሁ አለ

ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ የትምህርት ቤት አውቶብሶችን ለማሰማራት አቅጃለሁ አለ፡፡ድርጅቱ ጋዜጠኞችን ጠርቶ መግለጫ ሲሰጥ ተገኝተን እንደሰማነው አውቶበሶቹ ብዛታቸው አንድ መቶ ሲሆን ስልሣዎቹ አስር ሜትር የሚረዝሙና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፤ ቀሪዎቹ አርባዎቹ ለመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጁ ናቸው፡፡

ሸገር ባስ ወደ አገልግሎቱ በገባ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተቀባይነት እንዳገኘና ለዚህም በሰዓቱ ተነስቶ በሰዓቱ መድረሱ፣ ምቾቱና የአውቶብስ ንፅህና የጠበቀ መሆን አግዞታል ተብሏል፡፡ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ግንቦት 19 ከሜክሲኮ ሽሮ ሜዳ በ10 አውቶብሶች አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን በመቶ ስምንት አውቶብሶች በ23 መስመሮች አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ማለቱን ሰምተናል፡፡

32 ተጨማሪ አውቶብሶች ህዝብ በሚበዛባቸውና የአገልግሎት ፍላጐት በበረታባቸው ቦታዎች በቅርቡ አሰማራለሁ ብሏል፡፡እስካሁንም ወደ ሥራ ከተሰማራበት ጊዜ ጀምሮ 19 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረጉን ተናግሯል፡፡አዳዲስ በተገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ አገልግሎታችን ተፈላጊነቱ እየጨመረ ነው፤ ከህብረተሰቡም ጥሩ ምላሽ እያገኘን ነው ሲሉ የሥራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ለነፍሰ ጡሮች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለህፃናት እንዲሁም ለአረጋዊያን የተመቸ በመሆኑ ተመራጭነቴን ጨምሮልኛል ብሏል፡፡የተማሪዎች መጓጓዣ አውቶብሶቹን በተመለከተም አሁን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነና በመጪው አመት የተወሰኑት በ2011 ደግሞ ሙሉ በመሉ ለመጀመር ማቀዱን ተናግሯል፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ነፃ የህግ ምክርና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቢኖሩም የተለያዩ ችግሮች እንዳለባቸው ተነገረ

በኢትዮጵያ ነፃ የህግ ምክርና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቢኖሩም የተለያዩ ችግሮች እንዳለባቸው ተነገረ፡፡ወሬውን የሰማነው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር በነፃ የህግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ባለሙያዎችን ያሣተፈ ዐውደ ጥናት ሲያካሂድ ተገኝተን ነው፡፡በዐውደ ጥናቱ በኢትዮጵያ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ያሉበት ደረጃና ምን ዓይነት ችግሮችስ አለበት ? የሚሉ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡ነፃ የህግ አገልግሎት በተለያየ መንገድ ከፍለው አገልግሎቱን ማግኘት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሰጣል፡፡

ይህም ከማማከር ጀምሮ የህግ አገልግሎቱን እስከመስጠትና ጠበቃ እስከማቆም እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነፃ የህግ አገልግሎት እንዲሰጡ የታሰቡ ማህበራት ቢኖሩም በከተሞች ላይ ብቻ ተወስነው ቀርተዋል ተብሏል፡፡ወደ እነዚህ ነፃ የህግ አገልግሎት ቦታዎች ከመሄድ ይልቅ ወደ ሌሎች ተቋማት ማምራት በተገልጋዬች ዘንድ የሚታይ ክፍተት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በተሰበሰቡ መረጃዎችና በቀረበ ጥናት እንደተነገረው ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አገልግሎቱ እንዳይሰጥና ተደራሽ እንዳይሆን ምክንያት ነው ተብሏል፡፡ማህበራቱ የበጐ ፈቃድ ድርጅት በመሆናቸውም ከለጋሾች የሚገኝ ገንዘብ ሲቋረጥ እንዲዘጉ እያደረጋቸው ነው ተብሏል፡፡

አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊትም የዳሰሳ ጥናት ስለማይካሄድ ትክክለኛ አገልግሎት ፈላጊዎችን እያዳረሰ እንደማይገኝ ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር የነፃ አገልግሎቱን ማግኘት የሚሹና ፍትህን የተጠሙ ዜጐች ስላሉ አገልግሎቱን ለብዙሃኑ ለማዳረስ የሚደግፈኝ እፈልጋለሁ ብሏል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን 1 ቢሊየን 111 ሚሊየን 777 ሺ 942 ብር ከማን እንደሚሰበስበው ማስረጃ የሌለው ብር

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን 1 ቢሊየን 111 ሚሊየን 777 ሺ 942 ብር ከማን እንደሚሰበስበው ማስረጃ የሌለው ብር እንዳለው የሰማነው…የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለከተማዋ አስተዳደር ምክር ቤት የ2009 ዓ.ም ግምሽ ዓመት ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነበር፡፡ 

ሪፖርቱን የተከታተለው የሸገሩ ዮሐንስ የኋላወርቅ እንደሚለው መሰል ችግር ያለባቸውና በኦዲት ክትትል ወቅት ሒሳቡን አጥርተው መናገር ያልቻሉ ድርጅቶች 6 ናቸው…፡፡ ከነዚሁ 6 ድርጅቶች ዋንኛው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ሲሆን የሌሎቹ 5 ድርጅቶች በጥምረት 2 ሚሊየን ብር ገደማ ይሆናል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers