• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የካቲት 24፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት ለተማሪዎች ልዩ የመጓጓዣ አገልግሎት ለመሥጠት እየተዘጋጀ መሆኑ ተሠማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታሎች ጭምር መሰጠት ቢጀመርም ህመምተኞች ግን ሳይንሱ በሚፈቅደው መጠን አገልግሎት እያገኙ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የቦረና ኦሮሞ የገዳ ሥልጣን ርክክብ ተደርጓል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በነፃ የሕግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ያለመ ዐውደ ጥናት ሊካሄድ ነው፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በአዲስ አበባ የየካቲት 23 ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከአምናው ተምረው የዘንድሮውን የአድዋ ድል በዓል የትምህርት ቤታቸውን መጠሪያ የሚመጥን አድርገውት ሰንብተዋል፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በዚህ አመት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከተዘጉ 500 በላይ ትምህርት ቤቶች መካከል አብዛኞቹ ተመልሰው መከፈታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ገዢውና ተቃዋሚ የፖለቲካ ማኅበራት በረቂቅ የአሠራር ደንብ ሥያሜ ላይ ዛሬም አልተስማሙም፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በኦሮሚያ ልዩ ዞን መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ትላንት ማታ 4 ሰዓት ከ20 የተነሣ እሳት ሦስት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት አወደመ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም የካቲት 21፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ወትሮም ሀሜት አያጣውም የሚባለው የመንገድ ነገር አሁንም ተጨማሪ ገንዘብ እያሰወጣ የማጠናቀቂያ ጊዜውም እየተጓተተ መሆኑ ተነገረ

ወትሮም ሀሜት አያጣውም የሚባለው የመንገድ ነገር አሁንም ተጨማሪ ገንዘብ እያሰወጣ የማጠናቀቂያ ጊዜውም እየተጓተተ መሆኑ ተነገረ…በኮንስትራክሽን ዘራፍ ላይ ግልፅነት እንዲኖር ጥናት የሚያደርገው ኮስት ኢትዮጵያ የተባለው ተቋም ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥናቱ የመንገዶች ግንባታ ዘንድሮም መጓተትና ተጨማሪ ወጪ መጠየቁ አልቀረም፡፡

በጥናቱ ከተጠቀሱት የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የሀዩሰዋ አባላ አርቢቲ መንገድ ሲሆን ከ746 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ይገነባል ተብሎ የታቀደ ነበር፤ ይሁንና ከእጥፍ በላይ ዋጋው ንሮ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተሰምቷል፡፡

ይጠናቀቃል ተብሎ የተያዘለት የግዜ ገደብ 3 ዓመት ከ5 ወር ገደማ ቢሆንም ወደ ስድስት አመት ገደማ ተጓትቷል ተብሏል፡፡ ከ372 ሚሊዮን ብር ገደማ በጀት የተያዘለት የቶንጐ በጂ መጂ መንገድ ከ447 ሚሊዮን ብር በላይ ያሻቀበ ሲሆን በ3 ዓመት ገደማ ይጠናቀቃል ቢባልም ከ7 አመት ከመንፈቅ በላይ እንደተጓተተ በጥናቱ ተነግሯል፡፡

በአጠቃላይ በጥናቱ ከተካተቱ አምስት መንገዶች የግንባታ ወጪያቸው በአማካይ ከ42 በመቶ በላይ የጨመረ ሲሆን ከእጥፍ በላይም የማጠናቀቂያ ጊዜያቸው ዘግይቷል ተብሏል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከመተላለፋቸው በፊት ይዘቱን የሚቆጣጠር አካል ባለመኖሩ መተላለፍ የሌለባቸው ማስታወቂያዎች እንዲሰራጩ ምክንያት ሆኗል ተባለ

በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከመተላለፋቸው በፊት ይዘቱን የሚቆጣጠር አካል ባለመኖሩ መተላለፍ የሌለባቸው ማስታወቂያዎች እንዲሰራጩ ምክንያት ሆኗል ተባለ፡፡ይህን ያለው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ካለሥልጣን ነው፡፡ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አዳግ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው የምግብ ማስታወቂያ ውይይት ላይ በተወካዩ በኩል ሲናገር እንደሰማነው በተለይ የምግብ ማስታወቂያዎች የማስታወቂያ ሕጉን በሚፃረር መልኩ በየመገናኛ ብዙሃን ሲተላለፉ ይታያል፡፡

ሆኖም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ያለው ሥልጣን ማስታወቂያው ከተላለፈ በኋላ ችግር ካለው እንዲቆም ወይንም እንዲስተካከል ከማዘዝ ውጪ ቅድሚያ ምርመራ  ማድረግ እንደማይችል ሰምተናል፡፡ወደፊት ግን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከመተላለፋቸው በፊት ይዘታቸውን የሚመለከት አካል ለማቋቋም እየታሰበ ነው ተብሏል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 21፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የውሃና የመስኖ ግድብ ግንባታዎች ከጥናቱ አስቀድሞ ግንባታቸው ስለሚጀመር ከታቀደው ውጪ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ እያስወጡ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከመተላለፋቸው በፊት ይዘቱን የሚቆጣጠር አካል ባለመኖሩ መተላለፍ የሌለባቸው ማስታወቂያዎች እንዲሰራጩ ምክንያት ሆኗል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የቴክኒክ ብቃት ምርመራን የሚያልፉ ተሽከርካሪዎች ብዛት አነስተኛ ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የላይቤሪያዋ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሥራ ከተጀረ ወዲህ ከ73 ሺ በላይ ባለይዞታዎች አገልግሎቱን ማግኘታቸው ተነገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የመድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የሱማሌ ክልል አሽከርካሪዎች የሦስተኛ ወገን ሽፋን ካለመያዛቸውና ህጐችም ካለመተግበራቸው አኳያ ነገሩ ከአቅሜ በላይ ሆኗል አለ

የመድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የሱማሌ ክልል አሽከርካሪዎች የሦስተኛ ወገን ሽፋን ካለመያዛቸውና ህጐችም ካለመተግበራቸው አኳያ ነገሩ ከአቅሜ በላይ ሆኗል አለ…በተደጋጋሚ ከክልሉ ጋር ለመነጋገር መፍትሄም ለማበጀት ብሞክርም የሚሰማኝ አጥቻለሁ ብሏል ኤጀንሲው፡፡

ወሬውን የሰማነው ዛሬ የመድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የየክልሎችን አሰራር ሪፖርት ባቀረበ ጊዜ ተገኝተን ነው፡፡በአጠቃላይም በየክልሎቹ የሚገኙ የጤና ተቋማት የተሽከርካሪ አደጋ ላገኛቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እንደማይሰጡ ሰምተናል፡፡

ክልሎቹ ከሦስተኛ ወገን ጋር ተያይዞ እንዲገለገሉበት፣ ለሚደርሰው ጉዳትም ካሣ እንዲከፍሉበት የተቀመጠላቸውን ገንዘብ አይነኩትም ተብሏል፡፡በኦሮሚያ ክልል የጤና ተቋሞች የፖሊስ ሪፖርት ስላልደረሰን በሚል ህክምና ማግኘት ያለባቸውን ያጉላላሉ፣ በትግራይ ክልልም ገጭቶ ያመለጠ ተሽከርካሪ ተይዞ አያውቅም፤ የፖሊስ ቁጥጥር የተሟላ አይደለም፡፡ በክልሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች የድሮ ሰሌዳ ለጥፈው ይንቀሣቀሣሉ፣ ኢንሹራንሶችም ያጉላላሉ ብሏል ኤጀንሲው፡፡

በአማራ በክልሉ የሚገኙ የተሽከርካሪዎችን ቁጥር አለማወቅ፣ የግል የጤና ተቋማት የአስቸኳይ ህክምና አለመስጠት፣ አንበሣና አዋሽ ኢንሹራንስ ተጐጂዎችን ማንገላታት፣ ካሣ አለመክፈል ችግር ነው ሲል የመድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡በደቡብ ክልልም ሰሌዳ የሌላቸው ሞተሮች ይታያሉ፤ የህክምና ነገሩም አለመቀለጣጠፍ የክልሉ ጤና ቢሮም ትኩረት አለመስጠት እንደ ችግር ተነስተዋል፡፡

በአፋር ክልል ደግሞ በጤና ቢሮ በኩል የአስቸኳይ ጊዜ ህክምና አለመስጠት፣ ፖሊስም ለሚያገኛቸው ጥፋቶች ተገቢውን እርምጃ አለመውሰድ፤ አዋጁም እያለ ካሣ በጐሣ መሪዎች እንዲከፍሉ ማድረግ ታይቷል ተብሏል፡፡የአዲስ አበባ ከሞላ ጐደል የተሻለ ነው የተባለ ቢሆንም ጤና ቢሮ በግል ህክምና ተቋማት አገልግሎቱ ከተሰጠ በኋላ ካሣ ለመክፈል ያጉላላል ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ኦዲት ሪፖርት የማድረግ ችግር አለበት ሲል መድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው ጋር እየመከረ ነው፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 17፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ አዳዲስ ሆቴሎች የከተማዋን ቱሪስት የማስተናገድ አቅም እየጨመሩ መሆኑን ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተናገሩ፡፡ ትናንትም አንድ አለም አቀፍ ሆቴል በአዲስ አበባ ተመርቋል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ለመምህራን የተዘጋጁ 5 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በመጪው እሁድ በእጣ ለእድለኞች ይተላለፋሉ ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የመንግሥት ተቋሞች ከ170 ሚሊዮን ብር በላዩን አልተጠቀሙበትም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብም ያላግባብ ግዥ ተፈፅሟል ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በሶማሌ ክልል የተሽከርካሪዎች የ3ኛ ወገን የመድን ሽፋንን ሥራ ላይ ማዋሉ አዳጋች ሆኗል ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይን ለመሣብ ይበልጥ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይኖርባታል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀና ለአንድ ሣምንት የሚዘልቅ የቦንድ ሽያጭ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ

በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀና ለአንድ ሣምንት የሚዘልቅ የቦንድ ሽያጭ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ፡፡ግንባታው ከተጀመረ 6 አመታት ላስቆጠረው የህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ አንዲሆን ታስቦ ለአንድ ሣምንት ያህል ይቆያል የተባለው የቦንድ ሽያጭ ሳምንቱ ከህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከሌሎችም መሥሪያ ቤቶች ጋር በጋራ የሚከናወን ነው  ተብሏል፡፡

የቦንድ ሽያጭ ሣምንቱ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ እንደሆነም ሰምተናል፡፡ለህዳሴ ግድቡ እስካሁን በቦንድ ደረጃ 12 ቢሊየን ብር ቃል የተገባ ሲሆን ከ9 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ደግሞ እንደተሰበሰበ ተነግሯል፡፡የቦንድ ሽያጭ ሣምንቱ በከተማዋ በተመረጡ የተለያዩ ቦታዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 29 ድረስ በሽያጭ ላይ እንደሚቆይና ከ50 ብር ጀምሮ መግዛት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“ሙሽራውና ሙሽሪትም ከነ ሚዜዎቻቸው በአሰቃቂው የመኪና አደጋ ከሞቱት መካከል ናቸው…”

“ሙሽራውና ሙሽሪትም ከነ ሚዜዎቻቸው በአሰቃቂው የመኪና አደጋ ከሞቱት መካከል ናቸው…”አርብ ቀን ከቡራዩ ከታ የተነሱት ሙሽሮች ቅዳሜ የሠርግ ሥነ-ሥርዓታቸውን ምሥራቅ ጐጃም ላይ አድርገው ሲመለሱ ነው አደጋው የደረሰባቸው፡፡

በአደጋው የስድስት ወንዶችና የሁለት ሴቶች ህይወት ተቀጥፏል፡፡

ይህን የነገሩን በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ ናቸው፡፡አስቸጋሪውን የአባይን በረሃና የፍልቅልቅ መንገድን በሠላም ያለፉት ሙሽሮቹና አጃቢዎቻቸው በሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ልዩ ስሙ አናጅሩ በተባለ ቦታ ላይ ሲደርሱ አደጋው አጋጥሟቸዋል፡፡የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ ኮድ 3/41261 የሆነው ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ጐጃም  ሲያቀና ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 4/9685 ከሆነ ታርጋ ካለው ሚትስቡሺ ገልባጭ መኪና ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

በአደጋውም ከተሳፈሩት 15 መንገደኞች ሹፌሩን ጨምሮ ስምንቱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በአደጋውም ሙሽራውና ሙሽሪትም ከነ ሚዜዎቻቸው ከሞቱት መካከል ናቸው ተብሏል፡፡ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ አምስቱ ከባድ ሁለቱ ደግሞ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ተጎጂዎቹም በቅዱስ ጳውሎስ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ ነግረውናል፡፡

እንደ ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ ገለፃ ከሆነ አደጋው ተሽከርካሪዎቹ ደርበው ለማለፍ ሲሞክሩ እንደደረሰ ተገምቷል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 20፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደገም ወረዳ አናጅሩ በተባለ ቦታ በደረሰ የመኪና አደጋ 8 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ድርቅና የተፈጥሮ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ይከላከላል የተባለ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በ10ኛው ዙር በቱሉ ዲምቱ ሳይት የኮንዶሙኒየም ቤቶች የገቡ ነዋሪዎች መሰረተ ልማቶች አልተሟሉልንም፤ ግንባታቸው ባልተጠናቀቁ ቤቶች እየኖርን ነው የሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የመንግሥት ሀብትና ንብረት እንዲባክን አድርጓል ተባለ፡፡ ሀብትና ንብረቱንም እንዲሰበስብ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የራሳቸው የመኖሪያ ቤት የሌላቸው ዕድለኛ የአዲስ አበባ መምህራን ትላንት በአነስተኛ ኪራይ የጋራ የመኖሪያ ቤት አግኝተዋል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የህዳሴ ግድብ የቦንድ ሣምንት ዛሬ ተጀመረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የጂ 24 የቴክኒካል ግሩፕ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀመረ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • አንድ የአልጄሪያ ኩባንያ በሀገራችን ፋብሪካዎች የሚመረተውን ጥሬ ስኳር አጣርቶ ለገበያ  ሊያቅርብ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከመመሪያ ውጪ 137 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያለ አገልግሎት ያከማቿቸውን ንብረቶች በሽያጭ እንዲያስወግዱ ታዘዙ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

አፍሪካ ከእንስሣት ሀብቷ የምታገኘውን ጥቅም ያሣድግላታል የተባለ አህጉራዊ ፕሮጀክት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል

አፍሪካ ከእንስሣት ሀብቷ የምታገኘውን ጥቅም ያሣድግላታል የተባለ አህጉራዊ ፕሮጀክት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል፡፡ለ33 ዓመት የተነደፈው ፕሮጀክቱ በተባበሩት መንግሥታት በአለም የእርሻና የምግብ ድርጅት ፋኦ እንዲሁም በአሜሪካ አለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ልማት ድጋፍ አለው የተባለ ሲሆን ዘላቂ ልማት ለእንስሣት ሴክተር ይሰኛል ተብሏል፡፡

ቡርኪናፋሶ ፣ ኢትዮጵያ ፣  ግብፅ ፣ ኬኒያ ፣ ናይጄሪያና ኡጋንዳ ፕሮጀክቱ እንዲሰራባቸው የተመረጡ ሀገሮች ናቸው፡፡የየሀገራቱ ከፍተኛ የዘርፉ ባለሥልጣናትም ተገኝተዋል፡፡የኢትዮጵያ የእንስሣትና አሣ ሀብት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ በታዳጊ ሀገሮች ያለው የእንስሣት ሀብትና እርባታ ዘመናዊ አይደለም በቁጥር ላይ እንጂ ጥራት ላይ ያተኮረ ባለመሆኑ ፕሮጀክቱ የእንስሣት ልማቱን ጥራት እንዲኖረው እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ሀገራትን ያቀናጀ በመሆኑ ልምድ በመለዋወጥና በጋራ በመስራት እንደ ድንበር ዘለል ተላላፊ የእንስሣትና ከእንስሣት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡ጤናማ የሆነ የእንስሣት ሀብት መፈጠር አሁን ላይ በአህጉሪቱ በእጥፍ የጨመረውንና በጥቂት አሥርት አመታት ውስጥ በሦስትና አራት እጥፍ ይጨምራል ለተባለው የሥጋ፣ የእንቁላልና ወተት ፍላጐት ጥራት አጋዥ ነው ሲባል ሰምተናል፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers