• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መስከረም 30 ወደ ቤተ መንግስት ሄደው ጥያቄ እናቀርባለን ስላሉ ወታደሮች የተናገሩት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መስከረም 30 ወደ ቤተ መንግስት ሄደው ጥያቄ እናቀርባለን ስላሉ ወታደሮች የተናገሩትን እሸቴ አሰፋ ተመልክቶታል፡፡ እንዲያዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመጪው ሳምንት ወደ አውሮፓ እንደሚሄዱ ተነገረ

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመጪው ሳምንት ወደ አውሮፓ እንደሚሄዱ ተነገረ፡፡ የየኔነህ ሲሳይን የስልክ ሪፖርት ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመስከረም ወር መጀመሪያ በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተለቀቁ

በመስከረም ወር መጀመሪያ በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተለቀቁ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ በፊት ሰጥቶት በነበረው መግለጫ ወጣቶቹ ወደ ጦላር ተልከው ነበር፡፡ በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ወጣቶች ዛሬ ከእስር መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ ታገሰ ጫፎ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ

አቶ ታገሰ ጫፎ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ፡፡ አቶ ታገሰ በደቡብ ክልል በተለያዩ ስራ ሀላፊነቶች ላይ ሲያገለግሉ የቆዩና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ስብሰባ ባለፈው ማክሰኞ ከምክር ቤቱ አፈ ጉባኤነት ተነስተው የሰላም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙትን ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ተክተው እንዲሰሩ ተመርጠዋል፡፡ አቶ ታደሰ ቃለ መሐላ ፈፅመው ከወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር የስልጣን ርክክብ በማድረግ በይፋ ስራቸውን ተረክበዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከኮልፌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሱቆችን ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ከአግባብ ውጪ ከሥራችን ተፈናቅለናል ይላሉ

ከኮልፌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሱቆችን ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ከአግባብ ውጪ ከሥራችን ተፈናቅለናል ይላሉ፡፡ ትምህርት ቤቱ በበኩሉ ተገቢነት የሌለው ቅሬታ ነው ብሏል፡፡ የበየነ ወልዴን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከአራቱም መዓዘን የአፍሪካ ሐገራት ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚፈልጉ እንግዶች እዚህ ከደረሱ በኋላ ቪዛ የሚያገኙበት አሰራር ከአንድ ወር በኋላ ይጀመራል ተባለ

ከአራቱም መዓዘን የአፍሪካ ሐገራት ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚፈልጉ እንግዶች እዚህ ከደረሱ በኋላ ቪዛ የሚያገኙበት አሰራር ከአንድ ወር በኋላ ይጀመራል ተባለ፡፡ የትዕግስት ዘሪሁንን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መምህራን በአካባቢያቸው በቀላሉ የሚያገኟቸውን ቁሳቁሶች በመጠቀም የተማሪዎቻቸውን የሳይንስ እውቀት ማሻሻል እንደሚችሉ ተነገረ

መምህራን በአካባቢያቸው በቀላሉ የሚያገኟቸውን ቁሳቁሶች በመጠቀም የተማሪዎቻቸውን የሳይንስ እውቀት ማሻሻል እንደሚችሉ ተነገረ፡፡ የቴዎድሮስ ብርሃኑን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡ የአማራ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ያገለገሉት፣ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፤ ባለፈው ሚያዚያ ወር የመረጃ መረብና ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው በዶ/ር ዐቢይ የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትና፣ ከሐዋሳው ግጭት በኋላ በሌላ የተተኩት አቶ ደሴ ዳልኬ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርና እና የመስኖ አማካሪ እና አቶ መለስ አለሙ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ዋና ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ ሆነው ተሾመዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ከአካባቢው ሃገሮች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ለመምከር ሞቃዲሾ ደርሰዋል

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ከአካባቢው ሃገሮች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ለመምከር ሞቃዲሾ ደርሰዋል፡፡ ከዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳልህ አብረው ሄደዋል፡፡ ሁለቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ኢላ አዋድ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ ዶ/ር ወርቅነህና ሌሎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የቀጠናውን ሃገሮች ትብብር የሚጠናከርበትን መላ ይመክራሉ ከማለት ውጭ ዝርዝሩ አልተገለፀም፡፡ በዚህ ስብሰባ ጅቡቲ አልተካተተችም፡፡

ኤርትራና ጅቡቲ ያላቸውን ፀብና ልዩነት አጥብበው መልካም ግንኙነት እንዲመሰርቱ ባለፈው ወር ኢትዮጵያና ሶማሊያ አሸማጋይ ሆነው ማነጋገራቸው ይታወሳል፡፡ በጊዜው ስምምነት ላይ መድረሳቸው ቢነገርም በአሁኑ የአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለምን ተካፋይ እንዳልሆነች አልተነገረም፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባን የፀጥታ ችግር የሚያቃልልና ሰላሙንና ፀጥታውን አስተማማኝ የሚያደርግ ተቋም እንዲቋቋም ሃሳብ ቀርቧል

የአዲስ አበባን የፀጥታ ችግር የሚያቃልልና ሰላሙንና ፀጥታውን አስተማማኝ የሚያደርግ ተቋም እንዲቋቋም ሃሳብ ቀርቧል፡፡ ምክትል ከንቲባው ተቀብለውታል፡፡ የአዲስ አበባን ፀጥታና ሰላም ያስተማምናል የተባለው ተቋም የፍትህ ተቋማትን፣ የፖሊስ ኮሚሽን የደንብ ማስከበር አገልግሎቶችን አቀናጅቶ የሚመራው ተቋም ይሆናል ተብሏል፡፡ ተቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ተብሎ ይዋቀራል ተብሏል፡፡

ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ አዳማ ላይ ለአዳዲስ ተሿሚዎች በተሰጠ የስልጠና መድረክ ላይ፣ በከተማዋ በጠራራ ፀሀይ የወንጀል ድርጊቶች እየተፈፀሙ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት የፀጥታ ተቋማትን በአንድ ላይ የሚመራ ተቋም የማደራጀትን አስፈላጊነት ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማን አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር የሚያጠናው ፕሮጀክት የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የመዋቀሩን አስፈላጊነት ያቀረበውን ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ እንደሚሆንም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ አውታር ላይ የተንጠለጠለ ግለሰብ የኤሌክትሪክና የትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል ምክንያት ሆኖ ማርፈዱ ተሰማ

በአዲስ አበባ በከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ አውታር ላይ የተንጠለጠለ ግለሰብ የኤሌክትሪክና የትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል ምክንያት ሆኖ ማርፈዱ ተሰማ፡፡ የወንድሙ ሀይሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers