• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአደንዛዥ እፆች የሚያስከትሉት ጉዳት አገራዊ ቀውስ ከማስከተሉ በፊት መላ ሊባል ይገባል ተባለ

የአደንዛዥ እፆች የሚያስከትሉት ጉዳት አገራዊ ቀውስ ከማስከተሉ በፊት መላ ሊባል ይገባል ተባለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ትናንት ምሽት ሐምሌ 26፣2010 በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጃክሮስ አደባባይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙ ተነገረ

ትናንት ምሽት ሐምሌ 26፣2010 በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጃክሮስ አደባባይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙ ተነገረ፡፡በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ አመሻሽ 11 ሰዓት ከ30 በተነሳ የእሳት አደጋ 4 የንግድ ቤቶች እና 1 የመኪና መጠገኛ ጋራዥ ላይ ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡

ከአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን እንደሰማነው በአደጋው በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ሁለት መኪኖች የቃጠሎ ሰለባ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ተስፋዬ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አደጋውን ለመቆጣጠር 38 ባለሙያዎች 6 ከባድ የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች 64 ሺ ሊትር ውሃ እና 750 ሊትር ፎም በመጠቀም አደገው ወደ ሌላ እንዳይዛመት አድርጓል ተብሏል፡፡በዚህም ግምቱ 2 መቶ ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ሲቻል 1.7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ደግሞ በአደጋው መውደሙ ተነግሯል፡፡በክረምቱ ለእሳት አደጋ መባባስ ምክንያት ባይኖርም ህብረተሰቡ የሚጠቀምባቸውን የሀይል አማራጮች በጥንቃቄ በመጠቀም ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በገጠራማ አካባቢዎች የህክምና ቁሳቁሶችን በሰው አልባ በራሪ አካላት/ድሮን/ ማከፋፈል ሊጀመር ነው ተባለ

በገጠራማ አካባቢዎች የህክምና ቁሳቁሶችን በሰው አልባ በራሪ አካላት/ድሮን/ ማከፋፈል ሊጀመር ነው ተባለ፡፡ይህ ያለው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ነው፡፡ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉት በኢትዮጵያ ገጠራማ እና ጠረፍ አካባቢዎች የህክምና ቁሳቁሶችን በሰው አልባ በራሪ አካላት ወይንም ድሮኖች ለማከፋፈል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ህይወት አድን መድኃኒቶች ፣ ደም እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች በሰው አልባ በራሪ አካላት ወይንም ድሮን ለማከፋፈል የታሰቡ መሆናቸው የሚከፋፈሉ የህክምና ቁሳቁሶች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ስራውን የሚያቀላጥፉት የሰው አልባ በራሪ አካላት /ድሮን/ ሙከራ እና በቅርቡ እንደሚሆን ሚኒስትሩ መናገራቸውን ሰምተናል፡፡በአመት ጊዜ ውስጥም ስራው ይጀመራል ተብሏል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለአስራ አንዱ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ የተያዘው በጀት ማነስ የግንባታ ሂደታቸው እንዲጓተት አድርጓል ተባለ

ለአስራ አንዱ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ የተያዘው በጀት ማነስ የግንባታ ሂደታቸው እንዲጓተት አድርጓል ተባለ፡፡የውጪ ምንዛሪ እጥረትም ሌላው ችግር እንደነበር ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ማነስ እንደነበረም ተጠቅሷል፡፡የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች ፣ የዩንቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ፣ የግንባታ ስራ ተቋራጮችና መሐንዲሶች በተገኙበት ያለፈው አመት የተቋማቱ የግንባታ ሂደትና በመጪው አመት መከናውን ስለሚኖርባቸው ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎች ለመቀበል የተጀመሩ ግንባታዎችን ማጠናቀቅና ሌሎችንም ግንባታዎች ማካሄድ የዩንቨርሲቲዎች የቤት ስራ ነው ተብሏል፡፡የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና ዘላቂ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲሟላ ማድረግም ሌላው ስራቸው እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡የቦረና ዩኒቨርሲቲ ግንባታን ማስጀመርና የኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አጠናክሮ ማስቀጠል በ2011 ዓ.ም ለመስራት ከታቀዱት ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኤርትራና በጅቡቲ መካከል ያለው የተበላሸ ግንኙነት እንዲሻሻል ኢትዮጵያ ፍላጎት ያላት መሆኑ ተነገረ

በኤርትራና በጅቡቲ መካከል ያለው የተበላሸ ግንኙነት እንዲሻሻል ኢትዮጵያ ፍላጎት ያላት መሆኑ ተነገረ፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ከአንድ ሰዓት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኤርትራና ጅቡቲ በመካከላቸው ያለውን ችግር እንዲፈቱ ኢትዮጵያ አሸማጋይ ለመሆን እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያና ከሱማሊያ ጋር ዋና ወዳጅ ሆና መታየቷ ጅቡቲ የጣማት አትመስልም፡፡በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በኤርትራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጣለበት ማዕቀብ እንዲነሳ በይፋ እጠይቃለሁ ማለታቸው የጅቡቲውን ፕሬዝዳንት አናዷቸዋል፡፡ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ግሌ ለኤርትራ ማዕቀቡ እንዲነሳ የሚቀርበው ጥያቄ የማይገባና ጉንጭ አልፋ ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ማምኮ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ህልውናዬ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ

ማምኮ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ህልውናዬ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ፡፡ኩባንያው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለው ከምርቶቹ ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያለውን “የማምኮ የመፀዳጃ ቤት ሶፍት” በማስመሰል አምርተው ለገበያ የሚያቀርቡ ህገ-ወጦች በዝተዋል፡፡ህገ-ወጦቹ ለገበያ እያቀረቡ ያሉት ከኩባንያው አርማና ስም ጋር ተመሳሳይነት ያለውን የመፀዳጃ ቤት ሶፍት ነው ተብሏል፡፡ የኩባንያው ያልሆኑት እነዚህ ምርቶች ገበያውን እያጥለቀለቁና ህብረተሰቡንም እያደናገሩ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡
 
ህገ-ወጦቹ እንዲጠየቁና በኩባንያው ላይ ላደረሱት ኪሳራም ካሳ እንዲከፍሉ ለሚመለከታቸው የመንገስት አካላት በተደጋጋሚ ብናሳውቅም ከአንድ ወቅት ትክክል ያለፈ መፍትሄ አላገኘንም ሲሉ ሀላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ኩባንያው ከ100 ግራም በታች የሆኑ የመፀዳጃ ቤት ሶፍቶችን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አምርቶ እንደማያውቅም ተነግሯል፡፡ ህገወጦቹ ግለሰቦች ግን የማምኮ አርማና ስያሜ ማሸጊያ በማሳተም ባለ 70 ፣ 80 ግራም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ለገበያ እያቀረቡ ነው ተብሏል፡፡
 
ይህም ዘረፋው ዓይን ያወጣ መሆኑን ያሳያል ሲሉ የኩባንያው ሀላፊዎች በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡ በ1987 የተመሰረተው ማምኮ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከ200 በላይ ሰራተኞችን እንደሚያስተዳድር ሰምተናል፡፡ ከመፀዳጃ ቤት ሶፍት በተጨማሪም የፊት ማበሻ ሶፍት ፣ የገበያ ወይም የአፍ ማበሻ ሶፍት ፣ ለወጥ ቤት ንፅህና መጠበቂያ ሶፍትና ለተማሪዎች መማሪያ ደብተር በአገር ውስጥ በማምረት ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
 
ንጋቱ ረጋሳ
 
 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የስኳር ኮርፖሬሽን ፣ በጣና በለስ ፕሮጀክት በተቀሰቀሰ ግጭት ሶስት ሰዎች ሞተዋል የተባለው ወሬ ውሸት መሆኑን ዕወቁልኝ አለ

የስኳር ኮርፖሬሽን ፣ በጣና በለስ ፕሮጀክት በተቀሰቀሰ ግጭት ሶስት ሰዎች ሞተዋል ፣ የተባለው ወሬ ውሸት መሆኑን ዕወቁልኝ አለ፡፡የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ በነበሩት የአቶ ስመኘው በቀለ ፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተፈፀመበት ቀን መብራት በመጥፋቱ በፈንደቃ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር፡፡

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ ፈንደቃ ከተማ ፣ በቀብሩ እለት መብራት የጠፋው ሆን ተብሎ ነው በሚል መነሻ በተቀሰቀሰው ረብሻ 3 ሰዎች መሞታቸው የስኳር ኮርፖሬሽን ይናገራል፡፡ይሁንና ፣ግጭቱ የተነሳውና የሞቱትም ሰዎች የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ናቸው ተብሎ መነገሩ ሀሰት ነው ብሏል፡፡ግጭቱ የተነሳበት ፈንደቃ ከተማ ከፕሮጀክቱ በሶስት ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝና የሞቱትም የፕሮጀክቱ ሰራተኞች አለመሆናቸውን የተናገረው ስኳር ኮርፖሬሽን ሰራተኞቼ ፣ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጡና ተቻችለው ተዋደውና ተከባብረው የሚኖሩ ናቸው ብሏል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በህክምና ቁሶች እና የመድሃኒት እጥረት ላይ ይታያል በተባሉ ችግሮች ግብዓትን ለሌሎች ሆስፒታሎች በማካፈል ችግሩ እንዲፈታ ጥረት አድርጊያለሁ ሲል የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ተናገረ

በህክምና ቁሶች እና የመድሃኒት እጥረት ላይ ይታያል በተባሉ ችግሮች ግብዓትን ለሌሎች ሆስፒታሎች በማካፈል ችግሩ እንዲፈታ ጥረት አድርጊያለሁ ሲል የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ተናገረ፡፡  

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት የመከፈል ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ ትሰራለች አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት የመከፈል ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ ትሰራለች አሉ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተለያይተው የቆዩ ሲኖዶሶች ወደ አንድነት መምጣታቸው ለመላ አገሪቱም አርአያነት ያለው ነው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተለያይተው የቆዩ ሲኖዶሶች ወደ አንድነት መምጣታቸው ለመላ አገሪቱም አርአያነት ያለው ነው አሉ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምህረት ስዩም 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ልዑካቸው የአሜሪካ ተልዕኮ በእጅጉ የተሳካ እንደነበር ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ልዑካቸው የአሜሪካ ተልዕኮ በእጅጉ የተሳካ እንደነበር ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያውያን መካከል የጥላቻን ግንብ ያፈራረስንበትም ነበር ብለዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers