የፌድራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀድቆ በስራ ላይ እንዲውል የተፈቀደው የምህረት አዋጅ አፈፃፀምን በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን አውጥቷል
የፌድራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀድቆ በስራ ላይ እንዲውል የተፈቀደው የምህረት አዋጅ አፈፃፀምን በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን አውጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው የወንጀል ዓይነቶችና የሚካተቱን ዘርዝሯል፡፡
በህገ መንግስትና በህገ መንግስት ሥርዓቱ ላይ የሚደረግ ወንጀልን በተመለከተ ፣ የህገ መንግስታዊ ስልጣንን ተግባራዊነት ማሰናከል ፣ የጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት በማነሳሳት በመንግስት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት የሚደረግ ወንጀል ፣ የሀገር መከላከያ ሀይልን መጉዳት ፣ የሀገር መክዳት ወንጀል ፣ በስለላ ወንጀል ፣ በኩብለላ ወንጀል ፣ የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝብን ማነሳሳት እንዲሁም በፀረ ሽብርተኝነት የወጣን አዋጅ የተመለከተ የወንጀል ድንጋጌዎችን መተላለፍ እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከቱ የወንጀል ድንጋጌዎችን የፈፀሙ ግለሰቦም የይቅርታ አዋጁ የሚመለከታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡
ነገር ግን በተፈፀሙት የወንጀል ዓይነቶች ተሳትፈው የሰው ሕይወት በእጃቸው የጠፋባቸው ተከሳሾች በልዩ ሁኔታ ከምህረቱ ተጠቃሚ እንደማይሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡ከተዘረዘሩት የወንጀል ድርጊቶች ውጪ ያሉ በተለያዩ ወንጀሎች የከተሰሱትንም የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል የተባለ ሲሆን ነገር ግን አሁንም በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች በሰው መግደል ወንጀልና አስገድዶ መድፈር እስር ላይ የሚገኙ ታራሚዎች የምህረት አዋጅ ይመለከተናል በሚል የሚያነሱት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ፡፡
በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ የሚሆነው ግለሰብም በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በክልል በሚገኙ የፍትህ ቢሮዎች በአካል ወይም በወኪል ቀርቦ ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል፡፡ በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ የሚሆን ግለሰብም በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና በክልል በሚገኙ የፍትህ ቢሮዎች በተሰጠው የጊዜ ገደብ በአካል ወይም በወኪል ቀርበው ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል ነገር ግን ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጪ የሚመጣ አይስተናገድም ተብሏል፡፡ በዝርዝሩ መሰረት በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ባላችሁበት ቦታ በድረ ገፅ www.fag.gov.et ገብታችሁ ማመልከት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡
Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.